Page 2 of 2

Re: Another confession!

Posted: 23 Feb 2021, 11:22
by Meleket
ግሩም ብለሃል ወንድማችን Zmeselo. “ኣገናዕ!” አካፋ አካፋ መባል ኣለበት። ዶክተር በረኸት ሃብተሥላሴንስ ቢሆን የኤርትራን ሕገመንግሥት አርቃቂ ኮሚሽንን እንዲመሩ ራሳቸው ብረዚደንት ኢሳይያስ አይደሉም እንዴ ታሜሪካ ድረስ ተጣጥፈው ያመጧቸው!

እነ በኣሉ ግርማ ከነ ፊያሜታ ጋር እየተሻሹ “ኦሮማይን” ይጽፉ በነበሩበት በዚያ ቀውጢ በቀይ ኮከብ ዘመቻ ወቅት፡ እልፍ አእላፍ የደርግ ሠራዊትን የመከቱ ኤርትራዉያን የነጻነት ታጋዮች መካከል፡ በህግ ትምህርት የላቀ ክብር የነበራቸው የነጻነት ታጋዮች እነ በራኺ ገብረሥላሴ፡ እነ አድኃኖም ገብረማርያም፣ እነ ጠዓመ በየነ፡ እነ አለምሰገድ ተስፋይ ወዘተን የመሳሰሉ ደርግን በመደምሰሱ ሂደት በአካል የተሳተፉ ጀግኖች በኣካል ከጎናቸው እያሉ፡ ዶክተር በረኸትን ታሜሪካ ድረስ ጠርተው የመረጧቸው ራሳቸው ብረዚደንታችን ናቸው። ታድያ ከዶክተር በረኸትና ሕገ መንግሥት እንተግብር ካሉ ታጋዮች ጋር ስለተኾራረፉ ብቻ የኤርትራን ህዝብ ሕገመንግሥት የሞተ ሕገመንግሥት ለማለት እንዴት ይደፍራሉ? ይህ ትልቅ ስሕተትና ከዚያም ወረድ ሲል ነውርም ነው!

በጣም የሚገርመው ደግሞ “አዲስ ሕገ መንግሥት አርቃቂ ኮሚሽን አዋቅሪያለው” ብለው ለህዝብ ባደባባይ ይፋ አድርገው ሲያበቁ፡ እርሳቸው ስለሚያስረቅቁት አዲሱ ሕገመንግሥት ለዓመታት ትንፍሽ አለማለታቸው ነው። የኤርትራ ህዝብ በሙሉ በዚህ አካሄዳቸው ታዝቧቸዋል። “ንመለስ ከምዚ ኢለዮ ‘እዚ ሕገመንግሥቲ ንህዝቢ ኢትዮጵያ ኣየርብሕን ኢዩ ኢለዮ” ምስበሉ። ሕዝቢ ኤርትራ ብሓፈሻ “ሃየ!” ከምዝበሎም ኣይፈለጡን ማለት ዲዩ፧

የኤርትራ ህዝብ እንደታዘባቸው ሁሉ፡ ኢጦብያዉያን ቦለቲከኞች እነ ጠቅላዪ ኣብዪ ኣሕመድ፣ እነ ልደቱ አያሌው፡ እነ ኢንጅነር ይልቃል፡ እነ ታዬ ደንደኣ፣ እነ አንዳርጋቸው ጥጌ፣ እነ ብርሃኑ ነጋ፣ እነ እስክንድር ነጋ፡ እነ ዲያቆን ዳንኤል ክብረት እነ ወዘተ . . . ጋዜጠኞቹም እነ ኤልያስ ክፍሌ፡ እነ ሲሳይ ኣጌና፡ እነ ፋሲል የኔዓለም፣ እነ መሳይ መኮነን፡ እነ ኤርምያስ ለገሰ፣ እነ ግዛው ለገሰ፣ እነ ሃብታሙ ኣያሌው እነ ወዘተ . . . የኦሮሞ ቦለቲከኞች እነ መራራ ጉዲና፣ እነ ጃዋር መሓመድ እነ ለማ መገርሳ እነ አባ ዱላ ገመዳ ወዘተ ሳይቀር እንደሚታዘቧቸው ረስተውታል እንዴ።

መች ይህ ብቻ እዚህ መረጃ ውስጥም እነ Selam/, Hawzen, Sabur, መረጃ ላይ ስለ ሕግ ብዙ የሚጽፈው YAY, Deki-Arawit, Fed-up, Kerenite, Cigar, Cartman, Sesame, justo, Minilik Salsawi, pushkin, Horus, Fiyameta, Digital Weyane ‘ከይቀረዩ’፡ ኧረ ኣናሎጎቹም ጭምር ካሉ ይታዘቧቸዋል፡ እድሜ ለቴክኖሎጂ!

አካፋማ አካፋ መባል ኣለበት፡ ዶማም ዶማ፣ ለምን ይዋሻል!

ሓቂ ምስ ገለጽና ንሓሶት ነሸቝርራ፣
ፍለጡና በሉ ንሕና ኢና ኤርትራ። :mrgreen:

Re: Another confession!

Posted: 24 Feb 2021, 13:52
by Fiyameta
:lol: :lol: :lol: :lol: :lol:

Re: Another confession!

Posted: 25 Feb 2021, 04:50
by Meleket
አንዷ ታዛቢ ፈገግ ብለዋል! :mrgreen:

Re: Another confession!

Posted: 25 Feb 2021, 06:34
by Sabur

Meleket:

It has been close to two years now since the dictator openly declared the Ratified Eritrean Constitution is dead and that a new committee has been formed to draft a new constitution.

There is NO Committee formed and NO new drafted constitution two years after.

Basically the president lied to the Eritrean People on a National TV.


Meleket wrote:
23 Feb 2021, 11:22


በጣም የሚገርመው ደግሞ “አዲስ ሕገ መንግሥት አርቃቂ ኮሚሽን አዋቅሪያለው” ብለው ለህዝብ ባደባባይ ይፋ አድርገው ሲያበቁ፡ እርሳቸው ስለሚያስረቅቁት አዲሱ ሕገመንግሥት ለዓመታት ትንፍሽ አለማለታቸው ነው። የኤርትራ ህዝብ በሙሉ በዚህ አካሄዳቸው ታዝቧቸዋል። “ንመለስ ከምዚ ኢለዮ ‘እዚ ሕገመንግሥቲ ንህዝቢ ኢትዮጵያ ኣየርብሕን ኢዩ ኢለዮ” ምስበሉ። ሕዝቢ ኤርትራ ብሓፈሻ “ሃየ!” ከምዝበሎም ኣይፈለጡን ማለት ዲዩ፧

አካፋማ አካፋ መባል ኣለበት፡ ዶማም ዶማ፣ ለምን ይዋሻል!

ሓቂ ምስ ገለጽና ንሓሶት ነሸቝርራ፣
ፍለጡና በሉ ንሕና ኢና ኤርትራ። :mrgreen:

Re: Another confession!

Posted: 27 Feb 2021, 04:47
by Meleket
ክቡር Sabur እርግጥ ነው፡ የኤርትራ ህዝብ መክሮና ዘክሮ ከዘረኝነት በጠዳ መልኩ ያዘጋጀውን ህገ መንግሥቱን፡ ብረዚደንታችን “ሳይታወጅ የሞተ ህገ መንግሥት ነው” በማለት በድፍረት የአፍ ወለምታ ካጋጠማቸው 7 ዓመታት ተቆጥረዋል። አዲስ ህገ መንግሥት እያስረቀቅኩ ነው ብለው በይፋ ለህዝብ ከደሰኮሩም ዓመታት አልፈዋል። ሁለት ዓመታት’ማ ምን አላት? “ሥልጣኔን በሙሉ ለኣብዪ ኣሕመድ ሰጥቸዋለው፡ እርሱ ይመራናል:mrgreen: ብለው ከተናገሩም እኮ ሁለት ዓመታት አካባቢ ሆኗል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ፡ ታላላቆቻችን “ናታ ገዲፋስ ናይ ሓማታ” እንዲሉ፡ ብረዚደንታችን ለኤርትራ ህዝብ ስለ ኤርትራ ህገ መንግሥት ከማብራራት ይልቅ ስለ ኢትዮጵያ ህዝብ ህገ መንግሥት ለመደስኮር መሞከራቸው በጭራሽ አያምርባቸውም ለማለት ነው። የኢጦብያን ቦለቲካ ለመቃኘትና ለመፍተል የተደረገ ንግግር ከሆነም፡ ዛሬ ሳይሆን ያኔ፡ ተመለስ ጋር በተነጋገሩበት ሰዓት ይህን ኣቋማቸውን በቃለመጠይቆቻቸው ባንዱ ቢገልጡትና ለጦቢያ ህዝብ የሳቸውን አቋም በወቅቱ ቢያብራሩ አይሻልም ነበር? እነ ኣብዪም ሆኑ እነ አንዳርጋቸው ወይም እነ ብርሃኑ ነጋ ሌሎቹም የወያኔ ተቃዋሚዎች ከ27 ዓመታት በኋላ ሳይሆን፡ ያኔውኑ ሞራል አግኝተው፡ በፍጥነት ተንሰራፍተው ወያኖቹን በገረሰሷቸው ነበር። :lol:

ነገሩ ነው እንጂ የጦቢያን ጕዳይ በሚመለከት የጦቢያ ልጆች ይበቁታል። የኤርትራን ጕዳይ ወጥመድ ውስጥ አስገብተው ሲንፈላሰሱ የነበሩት የወያኔ አመራሮች እንደሆኑ ላይመለሱ ተሸኝተዋል። ታሁን በኋላ ወለም ዘለም በሌለበት አኳኋን፡ የናቴ መቀነት አደናቅፎኝ ነው በማይባልበት ሁኔታ፡ የኤርትራንና የጦብያን ደንበር መሬቱ ላይ ቁልጭ አድርጎ ማመላከት። ተዚያም ወደማይቀረው የኤርትራ ህገ መንግሥት ትግባሬ ማቅናት ነው። “ዘይተርፈካ ጋሻ አጥቢቕኻ ሰዓሞ!” ነው ነገሩ።
:mrgreen: