Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Wedi
Member+
Posts: 7993
Joined: 29 Jan 2020, 21:44

የ780 ቢሊዮን ብር እዳ!! የመንግስት ኢንተርፕራይዞች የ780 ቢሊዮን ብር እዳ እንዳለባቸው!! የገንዘብ ሚ/ር አቶ አህመድ ሽዴ ገለፀ። ግዜው የብል*ግና ነው!!

Post by Wedi » 15 Feb 2021, 14:19



የ780 ቢሊዮን ብር እዳ!!

የመንግስት ኢንተርፕራይዞች የ780 ቢሊዮን ብር እዳ እንዳለባቸው!! የገንዘብ ሚ/ር አቶ አህመድ ሽዴ ገለፀ።

ግዜው የብል*ግና ነው!!
*********************



Ethiopian Broadcasting Corporation
https://www.facebook.com/EBCzena/posts/4136508179714360

በመንግስት የሚተዳደሩ ኢንተርፕራይዞች የ780 ቢሊዮን ብር እዳ እንዳለባቸው ተገለጸ
*********************
በመንግስት የሚተዳደሩ ኢንተርፕራይዞች የ780 ቢሊዮን ብር እዳ እንዳለባቸው የገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሽዴ ገልጸዋል።

ሚኒስትሩ ይህን የገለጹት፣ በጠቅላይ ሚኒስቴር ጽ/ቤት አዘጋጅነት ትኩረቱን በፖሊሲ ጉዳዮች ላይ አድርጎ በተከታታይ በሚቀርበው ውይይት ላይ ነው፡፡

በውይይቱ ላይ የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሺዴ በመንግስት የሚተዳደሩ ኢንተርፕራይዞችን በተመለከተ ጋር ሰፋ ያለ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

በዚህም በመንግስት የሚተዳደሩ ኢንተርፕራይዞች ሪፎርም መንግስት በዋናነት ከያዛቸው ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ሪፎርም እቅዶች አንዱ ነው ብለዋል።

በእዳ በመዘፈቃቸው ለውጥ ያስፈልጋቸዋል ብሎ መንግሥት ከለያቸው ኢንተርፕራይዞች መካከል የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል፣ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት፣ የኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን፣ ኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ (ሜቴክ)፣ የኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን፣ የኮንስትራክሽን ስራዎች ኮርፖሬሽን እንዲሁም የስኳር ኮርፖሬሽን ዋነኞቹ ናቸው።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ እና ኢትዮ-ቴሌኮም በጥሩ አፈፃፀም ላይ ስላሉ በዚህ ሪፎርም አልተካተቱም ብለዋል።
ኢንተርፕራይዞቹ አሁን ያሉበትን የፋይናንስ ሁናቴ፣ እዳቸውን እና የካፒታል አስተዳደር ሁኔታቸውን የዳሰሰ ጥናት ተዘጋጅቷል ብለዋል ሚኒስትሩ።

በዚህም የእዳቸው ሁኔታ ከፍተኛ የሆነ እና ለውጥ የሚያስፈልጋቸው ተቋማት ከላይ የተጠቀሱት እንደሆኑ ገልጸዋል።
የእዳ አስተዳደር መዋቅራዊ ለውጥ አንዱ የሀገር በቀል ኢኮኖሚ ማሻሻያ አጀንዳ ነው።

በመንግስት የሚተዳደሩ ኢንተርፕራይዞች ላይ ለውጦችን ማካሄድ ያስፈለገው በማይክሮ ኢኮኖሚ የሚታየውን አለመመጣጠን ለማስተካከል ነው ብለዋል።

እነዚህ ኢንተርፕራይዞች ላለፉት አስር ዓመታት ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የብድር አቅርቦት ሲያገኙ የነበረ ሲሆን፣ የእነዚህ ኢንተርፕራይዞች ውድቀት በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ በፋይናንስ ተቋማት ላይ ጫና ሲፈጥር ቆይቷል ብለዋል።
በሪፎርሙ የፋይናንስ ሴክተሩን ማረጋጋት አንዱ ቁልፍ ተግባር ሲሆን፣ መንግስት ይህንኑ በበጀት ሳይሆን በተለያዩ የፈጠራ ስራዎች እና አግባቦች እዳን ለመቀነስ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል ብለዋል።

የሀብት እና እዳ አስተዳደር ኮርፖሬሽን የተሰኘው የቢዝነስ ተቋም የተቋቋመው የፋይናንስ ተቋማት ይህን እዳ ማስተዳደር እንዲችሉ እና መዋቅራዊ ለውጥ በማድረግ ድርጅታቸውን በአግባቡ መምራት እንዲችሉ ለማድረግ ነው ብለዋል።
ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት ሁሉን አቀፍ ፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ ለውጦችን እያካሄደች ነው።

ባለፉት 15 ዓመታት በሀገሪቱ ትልልቅ ኢንቨስትመንቶች ሲከናወኑ የነበሩ ሲሆን፣ አብዛኛዎቹ ኢንቨስትመንቶች የሚከናወኑት ደግሞ በመንግስት በጀት ነበር ብለዋል።

ይህም በዋናነት ከሀገር ውስጥ የገቢ ምንጭ እና በውጭ ብድር በስፋት ሲከናወን እንደነበርም ገልጸዋል።
በዚህ ምክንያት በተለይ ባለፉት አስር ዓመታት የመንግስት ኢንተርፕራይዞች እዳ እያሻቀበ መጥቷል ብለዋል።
ስለሆነም ኢንተርፕራይዞች በእዳ ምክንያት እንደ ድርጅት በራሳቸው ለመስራት እና ለሌላ ፕሮጀክት መዋዕለ ንዋይ ለማፍሰስ መቸገራቸውን ገልጸዋል።

የዚህ ሪፎርም ዋና ዓላማም የኢንተርፕራይዞቹን እዳ ማስተዳደር መቻል እና ከዚህ ችግር ወጥተው እንደ ኢንተርፕራይዝ እንዲቀጥሉ ማስቻል ነው ብለዋል የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ።