Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Thomas H
Senior Member
Posts: 12608
Joined: 27 Jan 2007, 16:30
Location: Kaliti
Contact:

በተሳካ Twitter ዘመቻ ዓብይ አህመድን $500 ሚሊዮን ዶላር አሳጣነው

Post by Thomas H » 13 Feb 2021, 18:35

ኢትዮጵያ በዓመት ከአበባ ኤክስፖርት $500 ሚሊዮን ዶላር ታገኝ ነበር ነገር ግን ባደረግነው የ Twitter ዘመቻ ከኢትዮጵያ አበባ import የሚያደርጉት ትልልቅ ድርጅቶች ከኢትዮጵያ አበባ ላለመግዛት ወሰኑ

ከድርጅቶቹ በጥቂቱ
1.Marks & Spencer
2.Aldi UK
3.Morrisons
4.Tesco
5.Sainsbury's








Hamza Oromuma
2h ·
በቁሟ የተሸጠች ሀገር
============
በአብይ አሕመድ የምትመራው ኢትዮጵያ ላለፉት ተከታታይ 3 ዓመታት የውጭ ምንዛሪ ዶላር እጥረት ድርቅ መመታቷ ይታወቃል። ይህንን ችግር የተረዱት የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ ገዢ በአንድ ወቅት በሰጡት መግለጫ "አገራችን ያጋጠማት የውጭ ምንዛሪ እጥረት ጠቅላያችን ከወዳጅ አገሮች (በውስጠ ታዋቂነት የዓረብ አገሮች) ባላቸው መልካም ግንኙነት ይፈቱልናል" ብለው መናገራቸው ይታወቃል።
ይህ የልመና መክሊት አልቀናህ ያለው አብይ አሕመድ አሊ አገሪትዋ ያጋጠማትን የውጭ ምንዛሪ እጥረት ለመቅረፍ ትልቁና ትርፋማውን መንግስታዊ ተቋም የኢትዮጵያ ቴሌኮሚኒኬሽን ለአንድ ተቀማጭነቱ ፈረንሳይ አገር ለሆነ ኦሬንጅ የሚባል ድርጅት እና ለግዜው የድርጅቱ ስም በውል ያልታወቀው ተቀማጭነቱ መካከለኛ ምስራቅ አረብ ሀገር ለሚገኝ በጥምር በእያንዳንዳቸው $2 ቢልዮን የአመሪካን ዶላር በድምር በ $4 ቢልዮን የአመሪካን ዶላር መሸጡ ምንጮች አስታውቀዋል።
ከሁለት ሳምንት በፊት እንደነገርኩዋቹ በብርጋዴር ጀነራል አብርሃ ካሳ የተመራው የኤርትራ ልኡክ በትግራይ ክልል ለተጨማሪ ሶስት ወር የሚቆይበትን ሁለተኛ ዙር $500 ሚልዮን የአሜሪካን ዶላር እንዲከፈላቸው በመጠየቃቸው በሁለቱ መንግስታት ተደራዳሪዎች በኩል አለመስማማት ተከስቶ የኤርትራ ወታደሮች ንብረትነታቸው የኢትዮጵያ መከላከያ የሆኑ የውግያ ታንኮች ከዓዲ ግራት እና መቐለ ከተማ ለመውሰድ ባደረጉት ጥረት በሁለቱም ወገን በተፈጠረው እንካሰላንትያ ወደ ግጭት በማምራት በተኩስ ልውውጥ የወታደሮች ህይወት ማለፉ አይዘነጋም።
ከላይ በተጠቀሰው የረብጣ ዶላር የኢትዮ ቴሌኮም ሽያጭ መሰረት በማድረግ የአብይ አሕመድ አሊ መንግስት ለኤርትራ መንግስት ወታደሮች ለቀጣይ 3ወር በትግራይ ክልልን ለሚኖራቸው ቆይታ የ$500ሚልዮን ሁለትኛው ዙር ክፍያ መክፈላቸው እና አንድ ንብረትነቱ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሆነው የጭነት ማመላለሻ አውሮፕላን የኤርትራ መንግስት መረከቡን ለማወቅ ተችሏል።