Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Wedi
Member+
Posts: 7993
Joined: 29 Jan 2020, 21:44

ባለቤት አልበዋ የአዲስ አበባ ከተማ!! በአዲስ አበባ በህገ-ወጥ ወረራ የተያዘው መሬት በገንዘብ ሲተመን ከ14 ቢሊየን ብር በላይ ይገመታል፡፡

Post by Wedi » 26 Jan 2021, 14:55

ባለቤት አልበዋ የአዲስ አበባ ከተማ!! በአዲስ አበባ በህገ-ወጥ ወረራ የተያዘው መሬት በገንዘብ ሲተመን ከ14 ቢሊየን ብር በላይ ይገመታል፡፡

ባለቤት አልባዋ የአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ የተካሄደው የመሬት እና የኮንደሚኔም ዘረፋ ሪፖርት

ባለፉት 3 አመታት በአዲስ አበባ የተካሂደው የመኖርያ ቤቶች፣ የኮንደሚኔም እና የመንግስት ቤቶች፣ የመሬት ወረራ እና ዘረፋ "ሪፖርት"

በአዲስ አበባ ከተማ 332 ባለቤት የሌላቸው ሕንፃዎች ሲገኙ 58 ግንባታቸው የተጠናቀቀና አገልግሎት የሚሠጡ ሲሆን የቀሩት ግንባታው ያልተጠበቀና የቆሙ ናቸው። በህገወጥ መንገድ የተያዙ የጋራ መኖርያ ቤቶች በጠቅላላው 21,695 ሲሆኑ 15,891 የጋራ መኖሪያ ቤቶች መረጃ ያልቀረበባቸው፣ 4530 ባዶ የሆኑ፣ 850 ዝግ የሆኑ እና 424 በህገወጥ መልክ በግለሰቦች ተይዘው ሲሆን፤ በዕጣ ሳይሆን በተለያዪ አግባቦች ወደ ተጠቃሚው ግለሰቦች የተላለፉ ደግሞ 51,064 ቤቶች ሆነው ተገኝተዋል፡፡

በአጠቃላይ በወ/ሮ አዳነች አቤቤ "ሪፖርት" መሰረት

• 13 ሚሊዮን 389 ሺሕ 955 ካሬ ሜትር ሜትር በህገ ወጥ የተወረረ መሬት
• 64 መንደሮች ወይም 79 ሺህ ቤቶች በህገወጥ የተገነቡ
• ከ121 ወረዳዎች በ88ቱ ወረራ ተፍፅሙማል
• 322 ህንፃዎች (የመሬት ስፋታቸው ከ500 ካሬ መትር በላይ የሆኑ) ባለቤት አልባ ናቸው
• 21 ሺህ 695 በህገወጥ የተያዙ የኮንደሚኔም ቤቶች ተገኝተዋል
• 14,641 መኖሪያና ለንግድ የተከራዩ የቀበሌ ቤቶችን ያለ አግባብና በህገ-ወጥ ይዞታነት ይገኛሉ፡፡
• 4 ሺህ 530 ባዶ ቤቶች ተገኝተዋል
• 850 ዝግ የሆኑ ቤቶች ተገኝተዋል
• 424 በህገወጥ የተያዙ ቤቶች ተገኝተዋል
• 51 ሺህ 064 ያለ እጣ የተላለፉ የኦንደሚኒዬም ቤቶች
• 132 ሺህ 678 እጣ በወጣላቸው እና በመስክ የተገኙ ቤቶች ልዮነት
• 132 ሺህ 423 የቤት ባለቤትነት ስም የሌላቸው
• 28 ብሎክ (ብሎክ 782 842) ያልተገነቡ
• 83 የጋራ መጠቀሚያ /ኮሚናል/ ያልተገነቡ
• 10 ሺህ 565 የቀብሌ መኖርያ ቦእቶች ቁልፍ የተሸጠ
• 7 ሺህ 723 የቀብሌ መኖርያ ቤቶች በህገወጥ ወደ ግል ንብረት የዞሩ
• 265 ቤቶች በሶስተኛ ወገ የተያዙ
• 164 መኖርያ ቤቶች ኮንደሚኔም በደረሳቸው የተያዙ
• 137 በሽያጭ ወደ ግል የዞሩ
• 1 ሺህ 243 ታሽገው/ተዘግተው የተቀመጡ
• 5 ሺህ 043 በህውገወጥ መንገድ የፈረሱ ቤቶች
• 180 የጠፉና እና አድራሻቸው የማይታወቅ ቤቶች
• 1 ሺህ 070 የቀብሌ የንግድ ቤቶች ውል የሌላቸው
• 10 ሺህ 565 የቀበሌ መኖሪያ ቤቶች በህገወጥ መንገድ የተያዙ ናቸው፡፡

• 75% ኮንዶሚኒየሞች የተያዙት ባልተመዘገቡና ባልቆጠቡ ሰዎች ነው፡፡
• በህገ-ወጥ ወረራ የተያዘው መሬት በገንዘብ ሲተመን ከ14 ቢሊየን ብር በላይ ይገመታል፡፡
• በሪል ስቴት አልሚዎች፣ በግለሰቦች፣ በሀይማኖት ተቋማትና በቡድን በመደራጀትና መንደር በመመስረት ጭምር በሚገለፅ መልኩ የመሬት ወረራ ተፈፅሟል፡፡

Please wait, video is loading...