Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
sarcasm
Senior Member
Posts: 10186
Joined: 23 Feb 2013, 20:08

በዓለም ላይ አገሩን በባዕድ አገር አስወርሮ ፣ ህዝብ ሲሰቃይ ፣ በድል አድራጊነት የሚጨፍር ፣ አገርስ ይኖር ይሆን?

Post by sarcasm » 26 Jan 2021, 07:22

ይህን ሁሉ ጭካኔ በህዝብ ላይ ለምን?

እውነት ትግራይ የኢትዮጵያ አካል ነች?

በየቀኑ ንፁሃን ሰዎች እየተገደሉና የማህበረሰቡ ስነልቦና እንዲላሽቅ ሆን ተብሎ ሴቶች በቤተሰቦቻቸው ፊት ጭምር መድፈር ከእንስሳ ካልሆነ ከሰው ይጠበቃል?
ሃብትና ንብረቱን ዘርፎና አውድሞ 4.5 ሚልዮን ህዝብ ተርቦ ወደ እልቂት እያመራ አለምን አስተባብሮ በከፍተኛ ደረጃ ከመረባረብ ይልቅ የተጋነነ ረሃብ የለም የሚል የፖለቲካ ጨዋታስ ከዘር ማጥፋት በምን ይለያል?

በዓለም ላይ አገሩን በባዕድ አገር አስወርሮ ህዝብ ሲሰቃይ በድል አድራጊነት የሚጨፍር አገርስ ይኖር ይሆን? መልሱን ለናንተ ትቻለሁ። ይሁን እንጂ አሁንም ህዝቡ ከማለቁ በፊት በፍጥነት እንደርስለት ዘንድ ግን የአማራና የኤርትራ ሃይሎች የትግራይን ምድር ለቀው እንዲወጡ በግፍ እየፈሰሰ ያለው የትግራይ ህዝብ ደም ይጣራል።

ትንሳኤ ዘ ትግራይ
Please wait, video is loading...