Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Horus
Senior Member+
Posts: 30915
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

አንድ ስንኝ ለምስለ ስዩም ዘወያኔ

Post by Horus » 22 Jan 2021, 03:28


በሰራው ግፍ ኮርቶ ሲፎክር ሰንብቶ፣
በመንፈስ በስጋ መታየቱ ሞቶ፣
ባነጣጥሮ ተኳሽ ግምባሩ ተመቶ
በትምክት ለሞተ በዕብሪቱ ተነፍቶ፣
ለመጸየፍ አይቶ ትራማ ተፈርቶ፣
እውነት አየን እንጂ ባሰቃቂ ፎቶ፣
ምስል ነዋሪ ነው መች ይሞታል ከቶ፣
ፎቶ አይዋሽም መች ይዋሻል ፎቶ።


ለሙታነ ዎያኔ
ሆረስ አይነ ኩሉ
ጥር 12 2013
Last edited by Horus on 25 Jan 2021, 04:40, edited 1 time in total.

Horus
Senior Member+
Posts: 30915
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: አንድ ስንኝ ለምስለ ስዩም ዘወያኔ

Post by Horus » 23 Jan 2021, 00:16

The Genius of Bob Dylan (1965)

Horus
Senior Member+
Posts: 30915
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: አንድ ስንኝ ለምስለ ስዩም ዘወያኔ

Post by Horus » 23 Jan 2021, 22:29

እግዚአብሄር ኢትዮጵያና መሪዋን ይጠብቅ ! አሚን !!!

Horus
Senior Member+
Posts: 30915
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: አንድ ስንኝ ለምስለ ስዩም ዘወያኔ

Post by Horus » 25 Jan 2021, 04:32

ጠ/ሚ አቢይ በደህነት ላይ ከሆነ ባንድ ቃል ማድረግ የሚችለው በፎቶ ብቅ ማለት ነው ። ይህን ማድረግ አልቻለም ። ለሚቀጥለው አምላክ ይጠብቀው ! የሱን እውነተኛ ደህንነት ማወቅ የሚሹት ደጋፍዎቹ ናቸው። ይህን ማክበር አለበት ። በቃ!!!

Horus
Senior Member+
Posts: 30915
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: አንድ ስንኝ ለምስለ ስዩም ዘወያኔ

Post by Horus » 29 Jan 2021, 04:33

ለጌታቸው ረዳ መሰናበቻ እስከምለው ችኩያለሁ !!

Meleket
Member
Posts: 3057
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

Re: አንድ ስንኝ ለምስለ ስዩም ዘወያኔ

Post by Meleket » 29 Jan 2021, 10:05

ለምስሉ ከተገጠመለት ዘንዳ፡ የኤርትራ ቀንደኛ ጠላቶች ፍጻሜ መጻፍ ስላለበት፡ በበኩላችን የሰውየውን ታሪክ ለማቆየት፣ የኤርትራ ጠላቶች ፍጻሜያቸው እንደማያምር ለማሳየት ይረዳ ዘንድ፡ ኤርትራዊ እይታችንን በግርድፍ ግጥም እናስቀምጣ! :mrgreen:

እናቱ ስትወልደው፡ ምላጯን አግላ፣
ጋድምና ትኩል መስመር አመሳቅላ፣
ተኩሳው ነበረ ቅንድቡን ተልትላ፣
ምስክር እንዲሆን እንዲለይ ከሌላ።

እሱም አልሰነፈ እጂጉን ተለዬ፣
በውሸት ለመታወቅ ምንም አልዘገዬ፣
የጦቢያው ውጭ ጉዳይ፡ ‘ሥዩሙ’ አምባዬ።


“የኤርትራ ጄቶች ቀድመው ደብድበዋል፣
የዓዲ ግራትን፡ ፋብሪካ አውድመዋል”፣
ብሎ ሓሰት ዘርቶ ኢትዮጵያን አታሏል።

ይግባኝ የሌለውን፡ ብይን ለማስቀየር፣
“ባድመ የኛ ሆናለች”፡ ብሎ በመፎከር፣
“የጠየቅነውና ያልጠየቅነው ጭምር፣
ተሰጥቶናል” ብሎ፡ እስጦቢያን ሲያስጨፍር፣
እኛ እናውቅ ነበር፡ ኋላ እንደሚያፍር . . . እንዲህ እንደሚከሥር።


ይህ ቀውስ እንዳይመጣ በጣም ስለሰጉ፣
የሃይማኖት አባቶች ሃገር ሊያረጋጉ፣
መልሱ አሳዝኗቸው እስኪበረግጉ፣
ለምነውት ነበር ሥዩምን በወጉ፣
ለምነውት ነበር እምባዬን በወጉ።

እናማ እግዚአብሔር፡ የፍርዱ ቀን ደርሶ፣
ጁንቶችን አዋርዶ ከሥልጣን ገርስሶ፣
አጋድሞ አሳይቶናል ድንጋይ አስተርሶ።


የጦብያው የውጭ ጉዳይ፡ 'ያ ጋሜው ሰላቶ'፣
በአልሞ ተዃሾች ግንባሩን ተበስቶ፣
ሥዩምን አየንው መሬት ላይ ተሰጥቶ።

ትዕቢት የወጠረው ይህ የትግራይ ፈገር፣
መስማት ስላልቻለ ቢመከር ቢዘከር፣
ህዝብ ላያደናግር ህዝብ ላያጭበረብር፣
ወደዚያኛው ዓለም ወደዚያኛው ሀገር፣
ተሸኝቷል አሉ ከሁለቱ አባዮች ጋር።

Kuasmeda
Member+
Posts: 6387
Joined: 26 Mar 2015, 08:47

Re: አንድ ስንኝ ለምስለ ስዩም ዘወያኔ

Post by Kuasmeda » 29 Jan 2021, 10:50

:lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol:
Meleket wrote:
29 Jan 2021, 10:05
ለምስሉ ከተገጠመለት ዘንዳ፡ የኤርትራ ቀንደኛ ጠላቶች ፍጻሜ መጻፍ ስላለበት፡ በበኩላችን የሰውየውን ታሪክ ለማቆየት፣ የኤርትራ ጠላቶች ፍጻሜያቸው እንደማያምር ለማሳየት ይረዳ ዘንድ፡ ኤርትራዊ እይታችንን በግርድፍ ግጥም እናስቀምጣ! :mrgreen:

እናቱ ስትወልደው፡ ምላጯን አግላ፣
ጋድምና ትኩል መስመር አመሳቅላ፣
ተኩሳው ነበረ ቅንድቡን ተልትላ፣
ምስክር እንዲሆን እንዲለይ ከሌላ።

እሱም አልሰነፈ እጂጉን ተለዬ፣
በውሸት ለመታወቅ ምንም አልዘገዬ፣
የጦቢያው ውጭ ጉዳይ፡ ‘ሥዩሙ’ አምባዬ።


“የኤርትራ ጄቶች ቀድመው ደብድበዋል፣
የዓዲ ግራትን፡ ፋብሪካ አውድመዋል”፣
ብሎ ሓሰት ዘርቶ ኢትዮጵያን አታሏል።

ይግባኝ የሌለውን፡ ብይን ለማስቀየር፣
“ባድመ የኛ ሆናለች”፡ ብሎ በመፎከር፣
“የጠየቅነውና ያልጠየቅነው ጭምር፣
ተሰጥቶናል” ብሎ፡ እስጦቢያን ሲያስጨፍር፣
እኛ እናውቅ ነበር፡ ኋላ እንደሚያፍር . . . እንዲህ እንደሚከሥር።


ይህ ቀውስ እንዳይመጣ በጣም ስለሰጉ፣
የሃይማኖት አባቶች ሃገር ሊያረጋጉ፣
መልሱ አሳዝኗቸው እስኪበረግጉ፣
ለምነውት ነበር ሥዩምን በወጉ፣
ለምነውት ነበር እምባዬን በወጉ።

እናማ እግዚአብሔር፡ የፍርዱ ቀን ደርሶ፣
ጁንቶችን አዋርዶ ከሥልጣን ገርስሶ፣
አጋድሞ አሳይቶናል ድንጋይ አስተርሶ።


የጦብያው የውጭ ጉዳይ፡ 'ያ ጋሜው ሰላቶ'፣
በአልሞ ተዃሾች ግንባሩን ተበስቶ፣
ሥዩምን አየንው መሬት ላይ ተሰጥቶ።

ትዕቢት የወጠረው ይህ የትግራይ ፈገር፣
መስማት ስላልቻለ ቢመከር ቢዘከር፣
ህዝብ ላያደናግር ህዝብ ላያጭበረብር፣
ወደዚያኛው ዓለም ወደዚያኛው ሀገር፣
ተሸኝቷል አሉ ከሁለቱ አባዮች ጋር።

Weyni
Member
Posts: 309
Joined: 14 Sep 2007, 18:47

Re: አንድ ስንኝ ለምስለ ስዩም ዘወያኔ

Post by Weyni » 29 Jan 2021, 12:20

:D :D :D :) :) :) :lol: :lol: :lol:

Horus
Senior Member+
Posts: 30915
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: አንድ ስንኝ ለምስለ ስዩም ዘወያኔ

Post by Horus » 30 Jan 2021, 02:44

የግማሽ ምዕተ አመት ቅብጠት
ግፍ ቅሚያ ወንጀል ትዕቢት
ግራት ጥጋብ ውጥረት ዕብሪት
ጉልበት ንቀት ዉሸት ክህደት
በሰካራም ድንፊያ በድቁርና ኩራት፤
ለምን ብሎ መጫር ክብሪት
ለመጋ'የት በራስ እሳት
አልቦ አንጎል ባዶ ስድስት
የድሮን ምሳ የጅብ እራት
ለመፈ'ጸም ለማሸለብ በደደቢት፤
በተከዜ ምድረ በዳ ጭርታ
በነደደው ሃሩር ፍላታ
ከማይናገሩት ቋጥኝ ተርታ
በተምቤን በረሃ ጸጥታ።

ሆረስ አይነ ብርሃን
January 29, 2021

Horus
Senior Member+
Posts: 30915
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: አንድ ስንኝ ለምስለ ስዩም ዘወያኔ

Post by Horus » 04 Feb 2021, 03:18

አሁን የዎያኔ ትግሬን የዉሸት ባቡር የሚነዳው የድሮ ቅዠት (አሁን ስለሞተ) የተሸናፊ ንዴት እና ትራማ፣ ፖስት ትራማ ሳልይ (ሰፈሪንግ) ነው። ይህ ደሞ ኮምፕሊኬትድ ግሪቪንግ የተባለው ያይምሮ ህመም ያስከትላል ። የወዎያኔ አጎኒና ሳጋ ይቀጥላል !!

Post Reply