Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Horus
Senior Member+
Posts: 30915
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

ካልቸር ፤ የጉርጌኛ እርገጣ (ጭፈራ) እና እስፖርት

Post by Horus » 21 Jan 2021, 05:16

ትክክለኛ የጉራጌ ዳንስ ለመቻል ወጣትነት፣ ሰልካካነት ፣ጠንካራነት ይጠይቃል ። ድሮ የሴትቹ ለስላሳና ዝላይ የማይጠይቅ ነበር ። አሁን ወጣት ሴቶች ልክ እንደ ወንድ ልጆችና ጎረምሶች ይሰሩታል ። ጥቂት ምሳሌዎች እነሆ ተዝናኑ !! ጭፈራ ማለት በጉራጌ ወርግጥ (መርገጥ) ይባላል። ዘፈን ደሞ ደርስ (ድርሰት) ይባላል። ግጥም ማውረድ ደርስ ወይም ድርሰት ነው!!!




ነጆ አራጆ እኔ ራሴ የተጫወትኩት የመስከረምና ጥቅምት ወራት የጎረምሶች ጨዋታ ነው ። እኛ ኩስ (ኳስ) ዝላለ (ዝላይ) እንለዋለን። የቆመውን ልጅ ጭንቅላት ሳይነኩ መዝለል ነው። ያ ካልሆነ ዘላዩ በተራው ይቆምና ይሸከማል፣ በትከሻው፣ ትከሻ አጋት ይባላል።

Last edited by Horus on 21 Jan 2021, 05:38, edited 1 time in total.



Post Reply