Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
temari
Member
Posts: 3743
Joined: 28 Dec 2014, 21:18

Ethiopian private banks should merge ASAP to be competitive against the coming foreign banks

Post by temari » 14 Jan 2021, 18:38

There is no way 17 and more banks can survive in the future. This is not sustainable.


temari
Member
Posts: 3743
Joined: 28 Dec 2014, 21:18

Re: Ethiopian private banks should merge ASAP to be competitive against the coming foreign banks

Post by temari » 15 Jan 2021, 12:28

Even though the banks are preforming well now, making profit after profit every year, this still will not be enough to compete against international banks. They have to become big, very big in the shortest time possible otherwise most of them will be out of the market. Relying on the government's policy of not opening up for foreign banks is not a good strategy. The government can't block foreign banks for too long and will soon be forced to open up to attract FDI etc.


Ethoash
Senior Member+
Posts: 26144
Joined: 20 Apr 2013, 20:24

Re: Ethiopian private banks should merge ASAP to be competitive against the coming foreign banks

Post by Ethoash » 30 Jan 2021, 08:32

ብዙዎቹን ብሎግህን ሳይ የአብይ ተላላኪ ትመስላለህ ግን የመልስን ዝናን ነው የምታቀነቅነው። በጣም የሚገርም ነው እኮ የግልን ባንክን መስራች መለስ ነው። የባቡር ሹፈሩዋን የፈጠረው መለስ ነው። አክሲዎንን መስረት የጣለው መለስ ነው። ብቻ ምንም እድገት ነገር ስታወራ መለስ ይታውስኛል ። ለሱም ምስጋና ሳናቀርብ እሱ በስራው መዝናናት ት ዝብት ነው።

አንድ ግዜ እነለማኝ ከአሜሪካ መጥተው አይተው የማያውቁትን አዳራሽ አዲሳባ ሲያዩ ይህ ኬት መጣ አሜሪካ የሌለ ነገር ብለው ይሆናል። የሚሊየሙን አዳራሽ ነው የምልህ።

ስለ ባንኩ ስመለስ ። ብዙ ባልኩኝ ነበር ግን ኢትዬዽያኖች ቡዳዎች ነን ። ለባንክ የምንመች ፍጥረቶች አይደለንም ። ለባንክ ሁለት ነገር ያስፈልጋል እምነት ። ባንኩ አምኖህ ብድር ማበደር አለበት ። አንተ ደግሞ ታማኝ ሆነህ ብድሩን መመለስ አለብህ ። ሶስተኛው ነገር ደግሞ አይናችን ቀይ መሆኑን ማቆም አለብን ከኛ በላይ ገንዘብ ያለው ስው ስናገኝ ይህ አስተሳስብ ለባንክ ምቹ ያረገናል።

ለምሳሌ የሽሪያ ባንክ ብንከፍት ምድረ አረብ በሙሉ ገንዘቡን እኛ ጋ ያስቀምጣል። ግን ቡዳ ስለሆንን አረቦች አይማኖት ሊያስቀይሩን ነው። ለምን እኛ ጋ መጥተው አብታም ይሆናሉ ።እያልን የቅናት ድራችንን እንስፋለን ታድያ ቤት በኩል ነው ባንክ ቤቶች የሚያድጉት።

የውጭ ሀገር ባንኮች ቢገቡ መጀመሪያ ፓርትነር ሁኑ ብንላቸው ። መክፈቻው ግዜ ከመድረሱ በፊት ከአፍሪካኖች ባንኮች ወይ ከውጮቹ ባንኮች ጋራ ብንስራ ትንሽ ልምድ እናገኛለን ግን ብቻችንን ባለህበት ብንረግጥ ምንም ውጤት አናመጣም። ባንኮች ልብ ያስፈልጋቸዋል ለማበደር። አስር ብር አበድረው መቶ ብር ተያዝ አምጣ የሚሉ ከሆነ የውጭ ባንክ ሲገባ አንድ ቀን አያድሩም።

ከዚህ ባላይ ድግሞ ባንኮቻችን እንዲያድጉ ከፈለግን የባንኩን ጠቅላይ አስተዳድሩን ደሞዝ በሚሊዬን ማሳደግ አለብን ። አይ እንደድሮ ሶስት ሺህ ብር እየከፈልኩ ከውጮቹ ጋር እወዳደራለሁ ማለት ዘበት ነው።

ሽሪያ ባንክ ካለን ከአረቦች ባንኮች ጋራ ለመስራት ከማሌዥያ ባንኮች ለመስራት ብዙ እድሎች አሉን ። ሌላው ቢቀር አማራውን ለውጭ ባንኮች ብናጣቸው ትንሽ ክፍ ያለ ወለድ ለማግኘት ብሎ ። እስላሙ ግን በተሀምር ከሽሪያ ባንክ የሚለቅበት ምክን ያት የለውምና የውጭ ባንኮች መቶ በመቶ አያከስሩንም።

ሁለተኛው ነገር ደግሞ የውጭ ባንኮችን በገጠር ባንኮቻቸውን እንዲከፍቱ መደራደር ነው። ገበሬውን ብድር እንዲስጡ። የገጠሩን ገበያ እንዲይዙ። የግል ባንኮቻችን ያልደረሱበትን ቦታ የውጭ ባንኮች እንዲስሩት ። በአጠቃለይ። አበሻ ለውጭ ባንኮች ዝግጁ ይመስሉኛል።

ብዙ አገሮችን ዲመኒካ ሪፕብሊክ የመሳስሉትን መጎብኘት አለብን። ሌላው ቢቀር አንድ ጋዘጠኛ የታክስ ገነት የተባሉትን ቦታዎች ተዘዋውሮ እንዴት የውጭ ባንኮች አገሪቱን እንዳሳደጉት ወይ እንደጎዱት ጥናታዊ ዘገባ ማቅረብ አለብት እዚው አረቦች አገር ሄዶ መጠየቅ ይችላል። ሌላ ደግሞ እንዴት የውጭ ባንኮች አገሪቱን ሀደህይተው እንደሄዱም መዘገብ አለብት ። ይህ ከሆን እኛ ለኛ የሚስማማ መንገድ እንወጣለን ማለት ነው።

በዚህ ጉዳይ ዘመዴነህ ቢጠየቅ ቡዙ የደቡብ አሜሪካ ልምድ ስላለው ሊነግረን ሊያስተምረን ይችላል። አንድ ስዓት የፈጅ ውይይት ከሱ ጋራ ማረግ በቢሊዬን ዶላር ኪሳራ ያድነናልን አንድ ጋዜጠኛ ቢያስብበት ይሻላል። አዋቂዎቻችንን ልክ እንድ አባይ ውሃ ልክ እንደውርቃችን ማየት አለብን ጥቂት ናቸው ያለን። እዚህ ላይ ዶክተር ብርሀኑን አይመለከትም ምንም የስራ ልምድ ስሌሌለው።

Post Reply