Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Meleket
Member
Posts: 3057
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

ልደተ ክርስቶስ (ገና) - በኤርትራዊና ኢትዮጵያዊ ዳንኤሎች እይታ! (ሁለት ቁምነገራዊ መጣጥፎች)

Post by Meleket » 06 Jan 2021, 04:36

ብርቂን መሳጢን ህያብ ዘለዎም ክልተ ጸሓፍቲ፡ እቱይ ሓደ ኤርትራዊ ዳንኤል ተስፋይ ሰመረ እቱይ ካልኣይ ድማ ኢትዮጵያዊ ዲያቆን ዳንኤል ክብረት፡ ብዛዕባ ልደተ ክርስቶስ ዘስተንተንዎ ጽሑፋት ክንርኢ። ዳንኤል ተስፋይ ብትግርኛ (21.12.2017)፡ ዲያቆን ዳንኤል ክብረት ድማ በምሓርኛ (January 16, 2014) ዝቐረቡልና አስተንትኖታት ንቋደሰን’ዶ! ብ“ቅየዐ” ናይ ዳንኤል ወዲ’ያ ተስፋይ ሰመረ ጀሚርና፡ ናይ ዲያቆን ዳንኤል ክብረት “ገና በጎዳና” ክንቅጽል ኢና። ሰናይ ንባብ፡ ቡሩኽ ልደት! :mrgreen:

ቅየዐ
እቶም ሰለስተ ለባማት ልደት ናይ’ዚ ዓመት’ዚ
ክርስቶስ ነፍሲ ወከፍ ዓመት ይውለድ። ነፍሲ ወከፍ ዓመት ድማ ይስቀል። ነፍሲ ወከፍ ዓመት ድማ ካብ ሓጢኣትና
የድሕነና። እቶም ሰለስተ ለባማት ድማ ነፍሲ ወከፍ ዓመት ንምላደ ክርስቶስ ከብዕሉ ሓደ ኮኾብ መሪሑዎም ናብ ቤት
ልሔም ይመጹ። ነፍሲ ወከፍ ዓመት ድማ ሄሮዶቶስ ህጻናት ይሓርድ። ነፍሲ ወከፍ ዓመት ድማ ዮሴፍ ንማርያምን ወዳን
ሒዙ ይሃድም። እዚ ፍጻሜ’ዚ ንልዕሊ 2000 ዓመታት ነፍሲ ወከፍ ዓመት ተደጋጊሙ እቶም ወድሰብ ዝፍጽሞም
ሓጢኣታት እምብዛ በዚሖምን ከፊኦምን ብሓንቲ ቅትለተ መድሕን ጥራሕ ዘይነጽሁ ኴይኖም። እንተኾነ ናይ ሎሚ ዓመት
ምላድ ክርስቶስ ካብ’ቶም ናይ ዝቐደሙ ዓመታት ቍሩብ ይፍለ።

እቶም ለባማት ንገለ 1500 ዓመታት ካብ ምብራቕ እዮም ዝመጹ ነቢሮም። ካብ 1500ድ.ል.ክ. ግን እስልምና ኣብ
ኵሉ ማእከላይ ምብራቕ ነጊሱ እቶም ለባማት ናይ’ዚ ዞና’ዚ ናብ መካነ ምላድ ክርስቶስ ናይ ምጋሽ ተመሳጥነቶም
እንዳማህመነ ከይዱ ንመጠረስትኡ ከኣ ናብ መካ- መካነ ምላድ መሓመድ - ጥራሕ ሓጀዙ። በብቍሩብ ከኣ ናይ ዝኾነት
ክርስትያን ሃገር ለባማት ኣብ ዕለተ ልደት ክርስቶስ ናብ ቤተ ልሔም እንዳገሹ ንማርያም እንኳዕ ማርያም መሓረትኪ
ናይ ምባል ባህሊ ተፈጥረ። እቶም ሎሚ ዓመት ገጸ በረከቶም ሒዞም ናብ ቤተ ልሔም ዝተበገሱ ለባማት ፕሮፈሶር
ሻይንሃይሊገ ካብ ሃገር ጀርመን፣ ሊቀ መኳስ ገብረመንፈስቅዱስ ካብ ዓዲ ሓበሻ፣ ኣቶ ቺን ቹላይ ካብ ርሑቕ ሃገረ
ቺና እዮም። ሰለስቲኦም ከኣ በብመገዶም ናብ ቤተ ልሔም ተበገሱ።

እቲ ከም ቀዳማይ ናብ እስራኤል ዝኣተወ፡ፍሉጥ፡ ፕሮፌሶር ሻይንሃይሊገ እዩ። ንሱ ብBMW ቱጉቱግ ብዘማናዊ GPS
እንዳተመርሐ እዩ ነቲ ነዊሕ መገዲ ካብ በርሊን ክሳብ ተል ኣቪቭ ኣሰላሲልዎ። ብቈጸራ ኣኽባርነት ጀርመናውያን
ተሓቢኑ ነቶም ክልተ ካልኦት ለባማት ብቈጽራ ዘይኣኽባርነቶም እንዳተጻረፈ ንበይኑ ናብ ቤተ ልሔም ደለየ። እቲ
መራሒ ኮኾብ ግን ኣብ ልዕሊ ተልኣቪቭ ተሸኺሉ ምንቅስቓስ ኣበየ። ፕሮፈሶር እቲ ዘይምቅስቓስ ናይ’ቲ ኮኾብ
ገሪምዎ ምኽንያቱ ንምፍላጥ ንእሽቶይ ጥራዝ ኣውጺኡ ክሓናጥጥን ክድምርን ከጉድልን ጀመረ።

ሓሙሽተ ሰዓታት ይደንጕ ድኣ’ምበር ንመጨረስትኡስ ኣቶ ቺን ቹላይ እውን ንተል ኣቪቭ ኣተወ። “ኣብ ፍራንክፎርት
ብርቱዕ በረደጡጥ ወሪዱ ነፈርቲ ኣብ ሰዓተን ክበራ ኣይከኣላን። ምድንጓየይ ጉድለተይ ኣይኮነን” በለ። ሕዚ
ቺናውያን ብብልሓትን ሃብትን ማዕረ ጸዓዱ ኴይኖም እቲ ንጸዓዱ ንንእሽቶይ ጉድለት ዓቢዪ እቅሬታ ምሕታት ሓዲጎሞ
እዮም። ሕዚ እቲ ሓበሻ ተሪፉና ኣሎ ከኣ ተበሃሃሉ። ፕሮፈሶር ብዛዕባ’ቲ ኣብ ልዕሊ ተል ኣቪቭ ዝደረቐ ኮኾብ
ንኣቶ ቺን ነጊሩዎ ነቲ ምኽንያት ንምቅላዕ ክልቲኦም ፈተኑ። ኣይከኣሉን። ኣቶ ቺን፡ “ምናልባት ኣምላኽ ንጸትታዊ
ምኽንያት ነቲ ልሙድ መካነ ምላድ ክርስቶስ ቀዪሩዎ ይኸውን። ኣብ’ዚ እዋን’ዚ፡ ክርስቶስ ዳዕሽ ዝተባህሉ ካብ
ሄሮዶቱስ ዝኸፍኡ ጸላእቲ ኣጥርዩ ኣሎ” ቢሉ ተፈላሰፈ።

እቲ ለባም ሓበሻ ገና ኣይኣተወን። ምናልባት ናይ ቪዛ ሽግር ኣጋጢምዎ ከይከውን ናብ ኢሚግረሽን እስራኤል ከይዶም
ሓተቱ። ኢሚግረሽን ድሕሪ ብዙሕ ገድሊ ቪዛ ከምዝተዋህቦ ገለጸሎም። ብተወሳኺ ድማ ንሱ ኣብ ክንዲ ብነፋሪት
ዝመጽእ ከምቲ ባህሊ መጽሓፍ ቅዱስ ኣባቕልን ኣእዱግን ሒዙ ከም ዝተበገሰን፣ ኣብ ሲናይ ድማ ብበደው ራሻይዳ
ከምዝተጨውየን፣ $30,000 እንተዘይከፊሉ ድማ ብህይወቱ ተጠቢሑ እቲ ውሽጣዊ ኣቝሕቱ ክሽየጥ ምዃኑን ሓበሮም።
ፕሮፌሶር፡ “እሞ ስለምንታይ ዘይከፍል? እቲ ምሉእ ዓዲ ሓበሻ ሰላሳ ሽሕ ከዋጽእ ኣይክእልን ድዩ?” በለ ሕቶን
ምግራምን ኣጠቓሊሉ።

“ንዓኻ ሰላሳ ሽሕ ዶላር ሰላሳ ሽሕ ሳንቲም ኴይነን ይስምዓኻ ይኾና። ንዓዲ ሓበሻ ግን ሰላሳ ሚልዮን ዶላር
እየን። ኣብ ልዕሊ’ዚ ባጠራኦም ዶላር ኪዕድግ ኣይክእልን እዩ” በለ ኣቶ ቺን።

“እምም! እሞ ንሕና መገድና ንቐጽል” በለ ፕሮፈሶር። ‘ንዕኡ ድማ ክርስቶስ ይሓግዞ”

“ሎሚ ዝተወልደ ቈልዓ በየናይ ዓቕሙ ኪሕግዞ! ድሓር ከኣ እቲ መራሒና ኮኾብ እንሆ ገና ካብ ተል ኣቪቭ ፈልከት
ምባል ኣብዩ። እሞ ናበይ ኢልና ኢና ክንብገስ?” ኣመልከተ ኣቶ ቺን።

“እምም! እሞ ናብ’ታ እቲ ኮኾብ ኣብ ልዕሌኣ ደው ኢሉላ ዘሎ ቦታ ከድና ነቲ ምኽንያት ንምፍላጥ ንፈትን” ኣመተ
ፕሮፈሶር። ጽቡቕ ሓሳባት ተበሃሂሎም ከኣ ተበገሱ። ነቲ ኮኾብ ድማ ልክዕ ኣብ’ቲ ሓበሻ ‘እንዳ ሳዕሪ’ ኢሎም
ዝሰመዪዎ መዘናግዒ ቦታ ብርሃኑ ኮሊዑ ረኸብዎ።

“እዚ ኮኾብ’ዚ ከምቲ ዓለምና ተጸሊላቶ ዘላ ተጸሊሉ ኣሎ። ኣነ ኣብ’ዚ ዝኾነ ሰብ፡ ዝኾነ ጓሳ እርኢ የለኹን” በለ።

“እቶም ኣብ ትሕቲ’ታ ገረብ ተቐሚጦም ዘለዉ ጸለምቲ’ኸ ሰብ ኣይኮኑን!” ተዋቕዐ ኣቶ ቺን። እቲ ጸዓዱ ኣብ
ልዕሊ ቺናውያን ዘርእይዎ ዝነበሩ ንዕቐት ገና ጸላዕላዕ የብሎ እዩ።

“እዚኣቶም ጸለምቲ ኣፍሪቃውያን እዮም … ማለት፡ እስራኤላውያን ኣይኮኑን … “ ተኻትዐ ፕሮፈሶር።

“ፈላሻ ዝተባህሉ ጸለምቲ ኣይሁድ ካብ ዓዲ ሓበሻ መጺኦም ኣብ’ዚ ኣብ እስራኤል ዝቕመጡ ከም ዘሎዉ ኣይትፈልጥን።
ካብኣቶም እንተኾን’ኸ?” ወጠረ ኣቶ ቺን ነታ ፕሮፈሶርነት ፕሮፈሶር ኪጠራጠራ ጀሚሩ። እሞ ንቕረቦም ንሕተቶም
ተበሃሂሎም ከኣ ቀረብዎም። ኣብ ሓደ “JAVA ORANGES” ዝተጻሕፎ ገዚፍ ባኮ ዕንጨይቲ ከኣ ሓደ ሽዑ
ዝተወልደ ህጻን ርኣዩ። ሓንቲ ጽብቕቲ ከደረይቲ መንእሰይ ሰበይቲ ኣብ ጥቃ’ቲ ቈልዓ ተቐሚጣ ነበረት። በቲ ካልእ
ሸነኽ ድማ ኣብ ገጹ ሓደ ዓቢዪ ጭንቀት ዝተሳእሎ ደልዳላ ከደራይ መንእሰይ ተቐሚጡ ነበረ። ከምኡ’ውን ገለ ካብ
ኣዕርዅቲ ኣብ’ኡ ነበሩ። እቶም ክልተ ለባማት ከመዓልኩም ኢሎም ሓቢሮሞም ተቐመጡ። ፕሮፈሶር ምስ’ቲ ኣቦ’ቲ
ቈልዓ ኴይኑ ዝተሰምዖ ዕላል ጀመረ።

“እዚ ቈልዓ ወድኻ ድዩ?”

“እወ”

“ይቕረታ። መን ትበሃል?”

“ዮሴፍ”

በቲ መልሲ ክልቲኦም ለባማት ሰንቢዶም ተጠማመቱ።

“ሰበይትኻ’ኸ መን ትበሃል?”

“(ወ)ለተማርያም”

በቲ መልሲ ክልቲኦም ለባማት ደጊሞም ሰንቢዶም ተጠማመቱ።

“እቲ ቈልዓ’ኸ እንታይ’ዩ ስሙ?”

“ገ(ብ)ረኢየሱስ”

በቲ መልሲ ክልቲኦም ለባማት ሰሊሶም ሰንቢዶም ተጠማመቱ። እሞ እቲ ኮኾብ ኣይተጋገየን በለ ኣቶ ቺን።
“ጽናሕ ድኣ ጽናሕ!” በለ ፕሮፈሶር ፒፓኡ እንዳኮልዐ። “ወለተ፡ ገብረ እንታይ ማለት’ዮም?” ተወከሰ።
“ወለተ ማለት ኣገልጋሊት፣ ገብረ ማለት ከኣ ዓሽከር ማለት እዩ” ገለጸ ዮሴፍ። ፕሮፈሶር ሓሰበ። ንቺን ተመልኪቱ
ከኣ፡ “እሞ ሎሚ ዓመት’ስ መንፈስ ቅዱስ ምስ ኣገልጋሊት ማርያም እዩ ተጋቢኡ። እቲ ህጻን ድማ ዓሽከር ክርስቶስ
ድኣ’ምበር እቲ ኣስሊ ክርስቶስ ንባዕሉ ኣይኮነን። ሎሚ ዓመት ስላሴ ካብ ወካሊት ማርያም ወካሊ ክርስቶስ እዮም
ሰዲዶሙልና” በለ።

“እንታይ ፍልልይ ኣሎዎ’ሞ … ? ሎሚ ኣብ ቺና ጎይታን ኣገልጋልን ሓደ ኴይኖም እዮም” መለሰ ቺን ኣብ ወረድኡ
ናይ ፖለቲካን ፕሮፓጋንዳን ሓላፊ እዩ። ነዚ ኣቕጣጫ ክትዕ’ዚ ኪቕጽሎ ኣይፈተወን ፕሮፈሶር ሕሉፍ ታሪኽ ህዝቡ
ኴርኵሑዎ። ናብ’ቶም ከቢቦሞም ዝነበሩ መንእሰያት ተመልኪቱ ድማ እንታይ ከምዝሰርሑ ሓተቶም። ብሓባር “ጓሶት”
በልዎ። ጤለ በጊዖም ኣበይ ከምዘሎዋ ኪፈልጥ ደልየ ፕሮፈሶር። ጠለ በጊዕና ድኣ ኣብ ጎቦታተን ሓዲግናየን መጺና።
ኣሓና ድማ ኣብ መረብ ኣሎዋ በልዎ። ፕሮፈሶር ርእሱ ነቕነቐ። መገድን ጥበብን ኣምላኽ ፍሉጥ ኣይኮነን ቢሉ
ሓሰበ። ምናልባት ናይ ሎሚ ዓመት ክርስቶስ እዚ ከደራይ ቈልዓ እዩ ቢሉ ከኣ ደምደመ። እሞ ንሕና ነቲ ህጻን
ክንበጽሕ ገለ ገጸ በረከት ሒዝና ኢና መጺእና በለ። (ወ)ለተማርያም- ቀረብታኣ ለቲና እዮም ዝብልዋ- ንፈለማ
ጊዜ ኣብ’ቲ ዕላል ተገደሰት።

“ዕጣንን ከርበን ሊቀ መኳስ ገብረመንፈስቅዱስ ካብ ኣፍሪቃ ክማልኡ ኢና ተሰማሚዕና ኔርና። እንተኾነ ሊቀ መኳስ
ኣብ ሲና ተጨውዮም ኪመጹ ኣይከኣሉን። ኣነ ግን ሽቶታት ካብ ቻነል 5ን፡ ሚኒሮክ ካብ ጆርጅ ኣርማኒን ስእኒ
ጉቺን ሒዘ መጺአ ኣሎኹ” ቢሉ ንለቲና ሃባ።

“ኣነ’ውን ካብ ቺና ዝተፈላለዩ መጻውቲ ቈልዑትን ባንቡላታትን ኣምጺኤ ኣሎኹ” ኢሉ ብዓቢዪ ቺናዊ ትሕትና
ተንበርኪኹ ኣብ እግሪ’ቲ ባኮ ኣቐመጦ።

ለቲና ብዛዕባ’ቲ ገጸ በረከት እኳ ቅጭጭ ኣይበላን ኣዕይንታ ኣፍጢጣ ጥራሕ ጠመተቶም። ንሕና ብርክና ንዓጽፈላ
ንእሽቶይ ኣጕዶ ስኢን’ና ብጥምዬት ተኾርሚና እንዳሓደርና ንስኻትኩም ድማ ጨና ወዲ ጨናን ጨርቃ መርቅን
ተራእዪኩም። ጨናስ ናይ ትሽቱሽና ምኣኸለና። እዚ ነተንያሁ ሄሮዶቱስ ለይትን መዓልትን የሳድደና ኣሎ። ናብ ገለ
ጫካ ኣፍሪቃ ክሰደና’ውን ይምድብ ኣሎ። ጨና ወዲ ጨና ኣይኮነን ዘድልየና ንሕና ፓስፖርት ምስ ቪሳኡን ዶላራትን
እዩ ዘድልየና ዘሎ” ኢላ ነቲ ገጸ በረከታት ናብ ገጾም ደርበየትሎም። አረ እንቋዕ ኣዕይንቶም ኣየንቈሮትም
ኣራእሶም ኣይሰበረቶም እቲ ኣብ ቀረብኦም ዝነበረ ህጻን ክርስቶስ ግዲ ተኸላኺልሎም። ቺን ኣዕይንቱ ኣፍጢጡ
ንፕሮፈሶር ተመልከተ’ሞ፡ “ እዚ’ኣ እታ ንፈልጣ ማርያም ኣይኮነትን!” በለ። ብዳርጋ ብጕያ ድማ ካብ’ቲ መካነ
ምላድ ክርስቶስ ኣልገሱ።

ነዚ ጸብጻብ’ዚ ዝኣከበን ዝጸሓፈን ጋዜጠኛ ዳንኤል ሰ. ተስፋይ ወኪል ጋዜጣ “ንሓቂ ድፈራ” ኣብ ምብራቕ ኣፍሪቃ እዩ።

21.12.2017
A Satire from the series “Dare the Truth”
ስሓቕ ዝመልኦ ፍሱሕ በዓል ልደትን ሓዲስ ዓመትን ይግበረልና

Meleket
Member
Posts: 3057
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

Re: ልደተ ክርስቶስ (ገና) - በኤርትራዊና ኢትዮጵያዊ ዳንኤሎች እይታ! (ሁለት ቁምነገራዊ መጣጥፎች)

Post by Meleket » 06 Jan 2021, 04:56

የዲያቆን ዳንኤል ክብረትን “ገና በጎዳና” ደግሞ እነሆ። የእምዬ ማርያም ልጅ አንድዬ ገናን ለመቅበር ሳይሆን በአግባቡ ለማክበር ልቦናውን ይስጠን!

ገና በጎዳና

ሁለት የጎዳና ልጆች የገና ዋዜማ አመሻሽ ላይ፣ ጎዳና ዳር ቁጭ ብለው አላፊ አግዳሚው ለዓመት በዓሉ ሲራወጥ ያያሉ፡፡ ዶሮ ያንጠለጠለ፣ በግ የሚጎትት፣ ቄጤማ የቋጠረ፣ በሬ የሚነዳ፣ እህል ያሸከመ፣ ‹የገና ዛፍ› የተሸከመ፣ አብረቅራቂ መብራት የጠቀለለ፣ ዋዜማ ሊቆም ወደ ቤተ ክርስቲያን ነጭ ለብሶ የሚጓዝ፣ ምሽቱን በዳንስ ሊያሳልፍ ሽክ ብሎ ወደ ጭፈራ ቤት የሚጣደፍ፣ ብቻ ምኑ ቅጡ፣ ከተማዋ ቀውጢ ሆናለች፡፡

እነርሱ ደግሞ የተበጫጨቀች ልብስ ለብሰው፣ የደረቀ ዳቦ ይዘው፣ በቢል ቦርድ ላይ የተለጠፈውን የጥሬ ሥጋ ሥዕል እያዩ፣ መጣሁ መጣሁ የሚለው የገና ብርድ እያቆራመዳቸው፣ የቆሸሸ ሰውነታቸውን እየፎከቱ፣ የቀመለ ፀጉራቸውን እያከኩ፣ በታኅሣሥ 15ና በታኅሥ 29 መካከል ያለው ልዩነት ጠፍቷቸው፣ የበግ ድምጽ እንጂ ሥጋው ርቋቸው፣ የበሬው ፎቶ እንጂ ሥጋው ጠፍቶባቸው፣ ያገኙትን ወረቀት እያነደዱ ጎዳናው ዳር ተቀምጠዋል፡፡

‹‹ቆይ ግን ገና ምንድን ነው?›› አለ አንደኛው ሰውነቱን እየፎከተ፡፡

‹‹የክርስቶስ ልደት ነዋ፤ በማይክራፎን ሲሰብኩ የሰማሁት እንደዚያ ነው››

‹‹የት፣ መቼ፣ ለምን ተወለደ?››

‹‹እነርሱ የሚሉት ቤተልሔም በምትባል ከተማ፣ በእኩለ ሌሊት፣ በብርድ ወቅት፣ ራቁቱን፣ እናቱ በከተማዋ ማደሪያ የሚሰጣት አጥታ፣ በተናቀው ቦታ በከብቶች በረት ውስጥ ተወለደ፡፡ በጣም ስለበረደውና ራቁቱን ስለነበር ከብቶቹ በትንፋሻቸው አሞቁት፤ ሌላ ሰው ስላልነበረ እረኞቹ መጥተው ዘመሩለት፡፡ እንዲህ ነው የሰማሁት፡፡››

‹‹እኛምኮ እንደርሱ የሚያስጠጋን አጥተን ነው ጎዳና የወደቅነው፡፡ እንደርሱ ራቁታችንን ነን፤ እንደርሱ የሚበላ የለንም፤ እንደርሱ እኛንም የሚያሞቁን እነዚህ ውሾች ናቸው፤ እንደርሱ እንደርሱ እኛም በተናቀው ቦታ ላይ ነን›› አለ ሁለተኛው ልጅ ውሻውን እየደባበሰ፡፡

‹‹የሚገርምህ ነገር ጌታ የተወለደው በከብቶች በረት ዋሻ ውስጥ ነው፡፡ ያኔ ጥድ የለም፤ በረት እንጂ፡፡ ጌታኮ ጫካ ውስጥ አልተወለደም፡፡ ያኔ ከረሜላ የለም፤ ያኔ ጥጥ የለም፣ ያኔ ፖስት ካርድ የለም፣ የሰብአ ሰገል ወርቅ፣ ዕጣንና ከርቤ እንጂ፡፡ አሁን ይኼን ሁሉ ከየት እንዳመጡት እንጃ፡፡ ይልቅስ ራቁታችንን ሆነን፣ የሚበላ ናፍቆን፣ በእንግዶች ማረፊያ ሥፍራ የሚሰጠን አጥተን፣ ከእንስሳት ጋር ተኝተን እኛ አለንላቸው፡፡ ገናኮ መከበር የሚገባው ከእኛ ጋር ነበር፡፡ ገና የሀብታሞች ሳይሆን የድኾች፣ የተከበሩ ሳይሆን የተዋረዱ፣ ቤት ላላቸው ሳይሆን ማደርያ ያጡ፣ ዘመድ ያላቸው ሳይሆን ወገን ያጡ ሰዎች በዓል ነው፡፡ ገና የሚወርዱበት እንጂ የሚወጡበት በዓል አልነበረም፡፡››

‹‹እኔም እሱን እያሰብኩ ነበር፡፡ ተመልከት ያኔ የዘመሩትን እረኞች አሁን ማንም አያስታውሳቸውም፡፡ ያኔ የቤተልሔም ሰዎች በጥጋብና በዕንቅልፍ ተወስደው አላስጠጋው ሲሉ በረታቸውን የሰጡት ከብቶች ነበሩ፡፡ አሁን የእነርሱ ዋጋ መታረድ ሆነ፡፡ በዓሉኮ የከብቶች በዓል ነበረ፡፡ እኔ ከብቶች ውለታ በዋሉበት፣ ከሰው የሚበልጥ ሥራ በሠሩበት በገና ቀን መታረዳቸው ይገርመኛል፡፡››

‹‹አይግረምህ፤ በሰው ልጅ ታሪክ ሁሉ እንደዚህ ነው፡፡ ታሪክ የሠሩትና መሥዋዕትነት የከፈሉት ምንጊዜም መሥዋዕት እንደሆኑ ናቸው፡፡ በኋላ የሚጠቀመው ታሪክ ሠሪው አይደለም፤ ታሪክ ተራኪው ነው፡፡ ‹የበሬን ምስጋና ወሰደው ፈረሱ› የተባለው ዝም ብሎ እንዳይመስልህ፡፡ አንተ በሠራኽው ታሪክ አንተን አርደው ያንተን በዓል የሚያከብሩ ሞልተዋል፡፡››

‹‹እርሱማ አታይም እንዴ፤ በኛ በድኾች ስም ይለመናል፤ ብር ይሰበሰባል፤ እኛ በፊልም እየተቀረጽን ታሪኩን እንሠራዋለን፤ በኋላ ግን እኛው ራሳችን በድህነት ቢላዋ እንታረድና የኛን በዓል ሌሎች ያከብሩልናል፡፡ ታሪኩን የሚሠሩት እረኞች፣ አበሉንና ደመወዙን የሚበሉት ግን የቤተልሔም ሰዎች፡፡ አንተ ፖስት ካርድ ብቻ ሆነህ ትቀራለህ፡፡ እስኪ የገናን በዓል ተመልከት፡፡ እረኞቹ የታሉ፤ በረቱ የታለ፤ ከብቶቹ የታሉ፤ ከሩቅ ሀገር የመጡት የጥበብ ሰዎች የታሉ፤ ጌታ የተኛበት የእንጨት ርብራብ የታለ፡፡ ሁሉም የሉምኮ፡፡ የእረኞቹን ቦታ ተኝተው የነበሩት የቤተልሔም ሰዎች ወስደውታል፤ የበረቱን ቦታ የገና ዛፍ ወስዶታል፤ የጥበብ ሰዎችን ቦታ የገና አባት ተረክቦታል፤ የከብቶቹን ታሪክ ሰባኪዎቹና ዘማሪዎቹ፣ ፓስተሮቹና ቄሶቹ ወስደውታል፤ የመላእክቱ ዝማሬ በጭፈራ ቤቶቹ ዘፈን ተተክቷል፡፡ ከብቶቹንም፣ እረኞቹንም፣ ሰብአ ሰገልንም፣ በረቱንም፣ መላእክቱንም፣ የምታገኛቸው ፖስት ካርድ ላይ ብቻ ነው፡፡››

‹‹የሚገርመኝ ምን እንደሆነ ታውቃለህ፤ በዚህ መንገድ ዳር በተሰቀለ ትልቅ ቴሌቭዥን ላይ ሳይ፣ የሃይማኖት አባቶች ‹በዓሉን ከተቸገሩት ጋር በማክበር አሳልፉት› ሲሉ እሰማለሁ፡፡ አንዳቸውም ግን ከመናገር ባለፈ ከተከበረ መንበራቸው ወርደው ከእኛ ጋር ሲያሳልፉ አይታዩም፡፡ ‹ክርስቶስ ከሰማያት ወረደ› ማለት እንጂ መውረድ ለካስ ከባድ ነው፡፡››

‹ካመጣኸውማ ገናኮ የመውረድ በዓል ነበር፡፡ ክርስቶስ ከሰማየ ሰማያት ወረደ የሚባልበት በዓል ነበር፡፡ አሁን ግን የሚወጣ እንጂ የሚወርድ የለም፡፡ ወደ እኛ የሚወርድ የለም፡፡ ሰው አምላክ መሆን ቢያቅተው አምላክ ሰው ሆነ ይላሉ፡፡ እኛ እንደነርሱ መሆን አቅቶናል፤ ታድያ ምናለ እነርሱ እንደኛ ቢሆኑ፡፡ በጣም የሚገርመው ሰብአ ሰገል ስጦታ የሰጡት ራቁቱን ለነበረው፣ ቤት ላጣው፣ የቤተልሔም ሰዎች አላስጠጋ ላሉት፣ ከሰው ወገን ጠያቂ ላልነበረው ለክርስቶስ ነበረ እንጂ ሁሉ በእጃቸው፣ ሁሉ በደጃቸው ለሆኑት ለቤተልሔም ሰዎች አልነበረም፡፡ ዛሬ ግን ስጦታው ለቤተ ልሔም ሰዎች ሆነ፡፡››

‹አንድ ቀን አንድ ሰው ሲያስተምር ምን ሰማሁ መሰለህ፡፡ ክርስቶስ ‹ተርቤ አላበላችሁኝም፣ ተጠምቼ አላጠጣችሁኝም› ይላል፡፡ የሰሙት ሰዎች ‹የት አግኝተን እናብላህ እናጠጣህ› ቢሉት ‹ለታናናሾቹ ካላደረጋችሁ ለእኔ አላደረጋችሁትም፣ ለታናናሾቹ ካደረጋችሁ ለእኔ አድርጋችሁታል› አላቸው አሉ፡፡ ታድያ ከኛ የባሰ ታናሽ ማን አለ? ያኔምኮ ክርስቶስ ተራ፣ ድኻ፣ እዚህ ግባ የማይባልና የተናቀ መስሎ ስለመጣ ነው የቤተልሔም ሰዎች ያላስጠጉት፡፡ ዛሬስ ድንገት ከእኛ መካከል ቢኖርስ፣ እዚህ ጎዳና ዳር ከውሾቹ ጋር ተኝቶ ቢሆንስ፤ በገዛ የልደቱ ቀን ሰዎች እርሱን ንቀው እያለፉ፣ ተጸይፈው እያለፉ፣ በጽድና በከረሜላ፣ በበግና በዶሮ፣ በጠላና በጠጅ፣ በፖስት ካርድና በስጦታ የራሱን በዓል እያከበሩለት ቢሆንስ፤ ››

‹ማን ያውቃል ወዳጄ፤ ሰው እንደሆነ በዓሉን እንጂ ራሱን ክርስቶስን የሚፈልገው አልመሰለኝም፡፡ ቢፈልጉት ኖሮማ አንድ ጥድ የሚገዙበት እኛን አልብሶ ‹ታርዤ አላለበሳችሁኝም› ከሚለው ያወጣቸው ነበር፤ የአንድ ፖስት ካርድ ዋጋ ለኛ የወር የቤት ኪራያችን ነበር፤ በጉን በልተው እንኳን ቆዳውን ቢሰጡን ለኛ የዓመት ቀለብ ነበር፤ ለከረሜላው የሚወጣው ገንዘብ የኛን የዓመት ጤና ይጠብቅ ነበር፡፡ አሁንማ የበዓሉ ምክንያት ተረስቶ በዓሉ ብቻ ቀርቷል፡፡››

‹‹እና አሁን ገና እየተከበረ ይመስልሃል››

‹‹ምን እየተከበረ ነው፤ እየተቀበረ ነው እንጂ››

© ይህ ጽሑፍ በአዲስ ጉዳይ መጽሔት የወጣ ነው

Meleket
Member
Posts: 3057
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

Re: ልደተ ክርስቶስ (ገና) - በኤርትራዊና ኢትዮጵያዊ ዳንኤሎች እይታ! (ሁለት ቁምነገራዊ መጣጥፎች)

Post by Meleket » 12 Jan 2021, 10:31

ቅየዐ” በሚል ርእስ በትግርኛ ዳንኤል ሰመረ ተስፋይ ያቀረበውን ልደትን የተመለከተ አዝናኝና አስተማሪ ጥሑፍ፡ በግርድፉ ወደ አፍሪካ ቀንድ ቋንቋ እንዲህ አቅርበንላችኋል። ኮምኩሙ። ምርጡንና ድንቁን ኤርትራዊ ጠሓፊ ዳንኤል ሰመረንም ብዕርህን ይባርክ፡ ሳትታክት ሌሎች ጡሑፎህንም አቅርብልን ቢለናል!!! :mrgreen:

የዘንድሮው ልደት ሶስቱ የጥበብ ሰዎች

ክርስቶስ በየዓመቱ ይወለዳል። በየ ዓመቱም ይሰቀላል። በየ ዓመቱም ከሓጢኣታችን ያድነናል። ሶስቱ የጥበብ ሰዎችም በየዓመቱ የክርስቶስን መወለድ ለማክበር አንድ ኮከብ እየመራቸው ወደ ቤትልሔም ይመጣሉ። በየዓመቱም ሄሮዶቶስ ህጻናትን ያርዳል። በየዓመቱም ዮሴፍ ማርያምንና ልጇን ይዞ ይሸሻል። ይህ ፍጻሜ ከ2000 ዓመታት በላይ በየዓመቱ ተደጋግሟል፡ የሰው ልጅ የሚፈጽማቸው ሓጢያቶች እጅግ ስለበዙና ስለከፉ፡ በአንዲት ቅትለተ መድሕን ብቻ ሊነጹ የማይችሉ ሆነዋል። ቢሆንም ግን ቅሉ፡ የዘንድሮው ምላድ ክርስቶስ (የክርስቶስ መወለድ) ካለፉት ዓመታት ትንሽ ለየት ያለ ሆኗል።

ብልሆቹ የጥበብ ሰዎች ላለፉት 1500 ዓመታት ይመጡ የነበሩት ከምስራቅ ነበር። ከ1500ዓ.ም. ወዲህ ግን እስልምና በመላው መካከለኛው ምስራቅ ስለተንሰራፋና ስለነገሠ፡ የዚሁ ቀጠና ብልሆችና የጥበብ ሰዎች፡ ክርስቶስ ወደ ተወለደባት ስፍራ የሚያደርጉት ጉብኝትና መመሰጥ እየተመናመነ ሂዶ፡ አመሻሹ ላይ መሓመድ ወደ ተወለደበት ስፍራ ወደ መካ ብቻ ሓጂያቸውን ማካሄድ ጀመሩ። ቀስ በቀስም የማንኛውም የክርስትያን ሃገር ብልሆች ወይም ጥበበኞች፡ ክርስቶስ በተወለደበት ዕለት ወደ ቤተ ልሔም በመሄድ ማርያምን እንኳን ማርያም ማረችሽ የሚሉበት ባህል ተፈጠረ። በዘንድሮው ዓመት ገጸ በረከት ማለትም ስጦታዎቻቸውን ይዘው የተነሱት ጠቢቦች ወይም ብልሆች ከጀርመን ሃገር ፕሮፌሶር ሻይንሃይሊገ፡ ከሓበሾች ምድር ሊቀ መኳስ ገብረመንፈስቅዱስ፡ ከሩቅ ምስራቅ ማለትም ከሃገረ ቻይና ደግሞ አቶ ቺን ቹላይ ናቸው። ሶስቱም ጠቢቦች በየመንገዳቸው ወደ ቤተ ልሔም ጉዟቸውን ጀመሩ።

አስቀድመው ወደ እስራኤል የገቡት፡ ታዋቂው ፕሮፌሰር ሻይንሃይሊገ ናቸው። ፕሮፌሰሩ በ BMW ሞተርሳይክላቸው ላይ በተገጠመው ዘመናዊ አቅጣጫ መጠቆሚያ GPS እየተመሩ፡ ረጂሙን ከበርሊን እስከ ቴል ኣቪቭ የተዘረጋውን ጎዳና አገባደዱ። በጀርመኖች ቀጠሮ አክባሪነት በመመካት፡ ሌሎቹ የጥበብ ሰዎች ቀጠሮ አክባሪ ባለመሆናቸው እየተሳለቁ፡ ፕሮፌሰሩ ብቻቸውን ወደ ቤተ ልሔም ሊያቀኑ ፈለጉ። ይመራቸው የነበረው ኮከብ ግን ተልኣቪቭ ላይ ተቸክሎ ከተልኣቪቭ አልንቀሳቀስም አለ። ፕሮፌሰሩ የኮከቡ አለመንቀሳቀስ ገርሟቸው ምክንያቱን ለማወቅ ትንሽ ደብተራቸውን አውጥተው መሞነጫጨር እንዲሁም በመደመርና በመቀነስ ሂሳብ ማስላት ጀመሩ።

ምንም እንኳን አምስት ሰዓቶች ቢዘገዩም አቶ ቺን ቹላይም ቢሆኑ ተል አቪቭ ገቡ። “ፍራንክፈርት ላይ ከባድ የበረዶ ጥጥ ዘንቦ አውሮፕላኖች በተወሰነላቸው ሰዓትና በፕሮግራማቸው መሰረት ሊበሩ አልቻሉም። መዘግየቴ የኔ ጥፋትና ድክመት አይደለም።” አሉ። አሁን አሁን ቻይናውያን በብልሐትና በሃብት ከነጮች ጋር መሳለመሳ ስለሆኑ፡ እንደነጮቹ ለትንንሽ ጉድለቶች ሳይቀር ይቅርታ መጠየቅን ትተውታል። “አሁን እንግዲህ ሓበሻው ቀርቶናል፡ ምነው’ሳ ዘገየ”ም ተባባሉ። ፕሮፌሰሩም ለአቶ ቺን ቹላይ ተል አቪቭ ላይ ተተክሎ አንቀሳቀስም ስላለው ኮከብ ጉዳይ ነገሯቸው፡ ያልተንቀሳቀሰበትን ምክንያት ለማወቅም በጋራ መመራመር ጀመሩ፤ ምክንያቱን ማወቅ ግን አልቻሉም።

አቶ ቺንም “ምናልባት አምላክ በጸጥታ ጉዳይ ምክንያት የዘንድሮውን የክርስቶስ መወለጃ ስፍራ ቀይሮት ይሆናል። ግዜው እንደሆነ፡ ለክርስቶስ ዳዕሽ የተባሉ ከሄሮዶቱስ የከፉ ጠላቶች የበቀሉበት ዘመን ሆኗል” በማለት ተፈላሰፉ።

የሐበሻው ብልኃተኛ ጠቢብ ሰው ገና እስራኤል ሃገር አልገባም። ማን ያውቃል፡ ምናልባት የቪዛ ችግር አጋጥሞት እንዳይሆን በማለት ወደ እስራኤል የኢሚግረሽን መስሪያቤት በመሄድ ጠየቁ። ከብዙ ድካም በኋላ፡ የኢሚግረሽን ባለስልጣኖችም ለሐበሻው ጠቢብሰው ቪዛ እንደተሰጠው ገለጹላቸው። በተጨማሪም የሃበሻው ብልኃተኛ ጠቢቡ ሰው፡ በአውሮፕላን ከመምጣት ይልቅ እንደ የመጽሓፍ ቅዱስ ባህል መሰረት በቅሎዎችና አህዮችን ይዞ በእግር ጉዞውን እንደጀመረ፣ ሲናይ በረሃ ላይም በበደዊን ወይ በራሻይዶች እንደታገተ፡ $30,000 ካልከፈለ ደግሞ ከነህይወቱ ተዘልዝሎ ሆድቃው ውስጥ ያሉ ብልቶቹ ሁሉ እንደሚሸጥ ተገለጸላቸው። ፕሮፌሰሩም “ታድያ ለምን አይከፍልም? ዝም ብሎ ከሚሞት ቢከፍል አይሻለውም? ሃበሻ ሙሉ ተባብሮ ሰላሳ ሺሕ ማዋጣት እንዴት ያቅተዋል?” አሉ በጥያቄና በአግርሞት።

“ለርስዎ መቸም ሰላሳ ሽሕ ዶላር ሰላሳ ሽሕ ሳንቲም ሆኖ ይሰማዎ ይሆናል። ለሃበሾች ግን ሰላሳ ሚልየን ዶላር ማለት ነው። ከዚ በተጨማሪም የሃበሾች ገንዘብ ከዶላር አንጻር ሲተያይ እዚህ ግባ የሚባል አይደለም” አሉ አቶ ቺን።

ፕሮፌሰሩም “እንዲያ ከሆነማ ይህ ሃበሻ ጉዱ ገና ነው! ታድያ እኛ ጉዟችንን ለምን አንቀጥልም” በማለት አያይዘውም ‘እሱንም ክርስቶስ ይርዳው’ አሉ ፕሮፌሰር።

“እንዴ! ዛሬ የተወለደ ህጻን በምን ዓቅሙ ነው ይህን የሃበሻ ጠቢብ የሚረዳው! በዚህ ላይ ደግሞ መሪያችን የሆነው ኮከብ እስከአሁን ድረስ ገና ከተል አቪቭ ንቅንቅ አላለም። ለመሆኑስ ወዴት አቅጣጫ ብለን ነው ጉዟችንን የምቀጥል?” በማለት ጥያቄያቸውን አቀረቡ አቶ ቺን።

“ኣሃ! ታድያ ኮከቡ የቆመበት ስፍራ ላይ ሄደን ጉዳዩን ለምን ለመመርመር አንሞክርም” አሉ ፕሮፌሰሩ። መልካም ሃሳብ ነው ተባብለውም ጉዟቸውን ጀመሩ። ኮከቡንም፡ ሃበሾች “ሳር ቤት” ብለው በሚጠሩት የመዝናኛ ቦታ ብርሃኑን አብርቶና አድምቆ አገኙት።

“አለማችን እንዳበደችው ሁሉ፡ ይህ ኮከብም አብዷል ማለት ነው። ለኔ እዚህ ስፍራ ላይ አንድም ሰው ሆነ እረኛ አይታየኝም” አሉ ፕሮፌሰር አካባቢውን ቃኝተው።

“እንዴ! ዛፉ ስር ተቀምጠው ያሉት ጥቁሮች፡ ሰው አይደሉም ማለትዎ ነው እንዴ!” በሃሳብ ሞገቱ አቶ ቺን። ነጮች በቻይናውያን ላይ ያሳዩት የነበረው ንቀት ገና ከአቶ ቺን ኣእምሮ አልተፋቀም።

“እነዚህማ ጥቁር አፍሪካውያን ናቸው . . . ይህም ማለት፡ እስራኤላዉያን አይደሉም” ሞገቱ የጀርመኑ ፕሮፌሰር።

“ፈላሻ የተባሉ ጥቁር አይሁዶች ከሃበሻ ምድር መጥተው እዚህ እስራኤል ውስጥ የሚኖሩ እንዳሉ አታውቁምን? የዘንድሮው ክርስቶስ የሚወለደው ከነዚህ ከፈላሾች መካከል እንደሆነስ ማን ያውቃል?” በማለት አቶ ቺን የፕሮፌሰሩን ፕሮፌሰርነት መጠራጠር ጀመሩ። ከዚያም፡ ታድያ ቀርበን ለምን አንጠይቃቸውም ተባብለውም ሃበሾቹን ቀረቧቸው። አንድ “JAVA ORANGES” የሚል ጽሑፍ በሰፈረበት ትልቅ የእንጨት ባኮ ውስጥ፡ አንድ ያኔውኑ የተወለደ ህጻንን አዩ። አንዲት መልከመልካም ወጣት ጠይም ቆንጆ ሴትዮም ከህጻኑ ጎን ተቀምጣ ነበር። በሌላ በኩል ደግሞ ፊቱ ላይ ጭንቀት የሚታይበት ደልዳላ ጠይም ወጣት ተቀምጦ ነበር። በተጨማሪም አንዳንድ ጓደኞቻቸውም እዚያው በአካባቢው ከበው ያወጉ ነበር። ሁለቱ የጥበብ ሰዎች ቻይናዊው ኣቶ ቺንና ጀርመናዊው ፕሮፌሰር ሻይንሃይሊገም “እንዴት ዋላችሁ” በማለት ሰላምታቸውን አቅርበው ተቀላቀሏቸው። ፕሮፌሰሩም የልጁ አባት ሆኖ ከተሰማቸው ሰውየ ጋር ወግ ጀመሩ።

“ይህ ልጅ፡ ልጅህ ነውን?”

“አዎን”

“ይቅርታ፡ ለመሆኑ ስምህ ማን ነው?”

“ዮሴፍ”

በመልሱ ሁለቱም የጥበብ ሰዎች ደንገጥ ብለውና ተገርመው እርስ በርስ ተያዩ።

“መልካም ነው፡ ባለቤትህስ ማን ትባላለች?”

“(ወ)ለተማርያም”

በመልሱ አሁንም ጠቢባኖቹ ዳግመኛ ተገርመውና ደንግጠው እርስበርስ ተያዩ።

“ያ ህጻኑስ ማን ይሆን ስሙ? ማን አላችሁት?”

“ገ(ብ)ረኢየሱስ”

አሁንም በመልሱ ጠቢቦቹ ለሶስተኛ ግዜ ደንግጠው ተያዩ። “እንዲህማ ከሆነ ኮከቡ አልተሳሳተም ማለት ነው” አሉ አቶ ቺን።

“ቆይ ቆይ ቆይማ!” በማለት ፕሮፌሰሩ ፒፓቸውን ለኩሰው ማጉ። “ለመሆኑ ‘ወለተ’ና፡ ‘ገብረ’ ማለት ትርጉማቸው ምንድን ነው?” ጠየቁ።

“ወለተ ማለት አገልጋይ፣ ገብረ ማለት ደግሞ አሽከር ማለት ነው” በማለት ዬሴፍ ገለጸላቸው።

ፕሮፌሰሩም ላፍታ አሰብ አደረጉና። አቶ ቺንን እየተመለከቱ “እንዲህ ከሆነማ ታድያ፡ መንፈስ ቅዱስ ዘንድሮ በማርያም አገልጋይ ላይ ነው የሰፈረው። ህጻኑም የክርስቶስ አሽከር እንጂ ኦሪጅናሉ ክርስቶስ አይደለም። ስለሆነም ዘንድሮ፡ ስላሶች በማርያም ወኪል አማካኝነት ክርስቶስን የሚወክለውን ነው የላኩልን” አሉ ፕሮፌሰሩ።

“ታድያ ይህ ምን ልዩነት አለው . . .? በአሁኑ ግዜ ቻይና ውስጥ ጌታና (መስፍንና) አገልጋይ አንድ ሆነዋል” በማለት መለሰ አቶ ቺን፡ መቸም እንደሚታወቀው አቶ ቺን በወረዳው የፖለቲካና ፕሮፓጋንዳ ክፍል ሃላፊ ነው። በመሆኑም፡ ጀርመናዊው ጠቢብ ፕሮፌሰር፡ ያለፈው የህዝባቸው ታሪክ ስላሳፈራቸው፡ ይህን በመሰለው ክርክር ውስጥ ዘው ብለው መግባትንና መቀጠልን አልመረጡም።
ስለሆነም በተወልደው ህጻን ዙሪያ ከበው ወደነበሩት ወጣቶች በመሄድ ጥያቄያቸውን አዥጎደጎዱ፡

“እናንት ወጣቶች ስራችሁ ምንድን ነው”

“እረኞች ነን” ወጣቶቹ በጋራ መለሱ።

“ታዲያ በጎቻችሁና ፍየሎቻችሁ የታሉ” ጠየቁ ፕሮፌሰር።

“በጎቻችንና ፍየሎቻችንንማ በተራራዎቻቸው አሰማርተናቸው ነው የመጣን። ከብቶቻችን ደግሞ መረብ ነው ያሉት” መለሱ እረኞች።

ፕሮፌሰር በሁኔታው ተገርመው ራሳቸውን እየነቀነቁ “የአምላክ መንገድና ጥበቡ መቸም በቀላሉም አይታወቅም” በማለት አሰላሰሉ። ቀጠሉናውም “ምናልባት የዘንድሮው ዓመት ክርስቶስ ይህ ጠይም ህጻን ሳይሆን አይቀርም” በማለትም ደመደሙ። አያይዘውም ፕሮፌሰሩ “እኛ ይህን ህጻን ለመጎብኘትና ለህጻኑ ገጸ በረከትን ለማቅረብ ነው የመጣነው” አሉ። በቅርብ የሚያውቋት ሰዎች ለቲና ብለው የሚጠሯት (ወ)ለተማርያም - ለመጀመርያ ግዜ በሰዎቹ ንግግር ቀልቧ የተሳበ መሰለ።

“ዕጣንና ከርቤ ሊቀ መኳስ ገብረመንፈስ ቅዱስ ከአፍሪካ ይዘው እንዲመጡ ነበር የተስማማነው። ነገር ግን ሊቀ መኳስ በሲና በረሃ ስለተጠለፉ ሊመጡ አልቻሉም። እኔ በበኩሌ ከ ቻነል 5 ሽቶዎችን፡ ሚኒሮክ ከጆርጅ አርማኒን ወዘተን ይዜ መጥቻለሁ” በማለት ጀርመናዊው ጠቢብ ገጸ በረከታቸውን ለለቲና ሰጧት።

“እኔም ከቻይና የተለያዩ የህጻናት መጫወቻ አሻንጉሊቶችን አምጥቻለሁ” በማለት በታላቅ ቻይናዊ ትህትና ተንበርክከው አቶ ቺን ገጸበረከታቸውን ከትልቁ ባኮ ስር አስቀመጡ።

ይህ ሁሉ ሲሆን ለቲና በገጸበረከቱ ምንም አልተመሰጠችም፡ ዓይኖቿን አፍጥጣ ብቻ ተመለከተቻቸው። “እኛ ተጠቅልለን የምተኛባት አንዲት ደሳሳ ጎጆ እንኳን አጥተን በረሃብ አለንጋ እየተገረፍን ተጣጥፈንና ተኮረማምተን እያደርን፡ እናንተ ደግሞ ሽቶና አሻንጉሊት ምናምን ነው የሚታያችሁ? ሽቶ እንደሆነ የብብታችን ሽቶ ይበቃናል። ይህ ናተንያሁ የተባለ ሄሮዶቱስ ሌተቀን እያሳደደን ነው። ወደ አንዳች የአፍሪካ ጫካም ሊልከን አስቧል። የሚያስፈልገን ሽቶና አሻንጉሊት አይደለም፡ ለኛ የሚያስፈልገን ፓስፖርት ከነቪዛውና ዶላር ነው።” በማለት ስጦታዎቻቸውን በፊታቸው ላይ በተነችላቸው። ብቻ እንኳን አይኖቻቸውን አላጠፋችው፡ እንኳንም ራሳቸውን አልሰበረቻቸው። መቸም እዚያ አጠገባቸው የነበረው ክርስቶስ ህጻን ባይከላከልላቸው ኖሮ አልቆላቸው ነበር። አቶ ቺን ዓይኖቻቸውን አፍጥተው ፕሮፌሰሩን እያዩ “ይህቺ ያቺ የምናውቃት ማርያም አይደለችም!” አሉ። ባጋጠማቸው ክስተት ተገርመውም ከመካነ ምላድ ክርስቶስ እየተጣደፉ ወጡ።

ይህን ዘገባ ያቀናበረና የጣፈው “እውነትን ድፈር” ለተሰኘችው ጋዜጣ፡ የምስራቅ አፍሪካ ወኪል የሆነው፡ ጋዜጠኛ ዳንኤል ሰ. ተስፋይ ነው።

21.12.2017
A Satire from the series “Dare the Truth”
ሳቅና ደስታ የሞላበት የልደት በዓልና አዲስ አመት ያድርግልን።

Post Reply