Tirhas Tarekegn - Kobeley
ዛሬ በመከራ የመቐለ ስልክ ሰራልኝ
እፎይ ብያለሁ ቤተሰብ ሁሉ ሰላም ነው: : እንዳሰብነው የተፈጠረ ብዙ ችግር የለም: : የትግራይ ህዝብ ጦርነት ሰልችቶታል እዚህ አሜሪካ ሆናችሁ ስለ ጦርነት የምታወሩ ሰወች ለህዝባችን እረፍት ብትሰጡት ጥሩ ነው: : ኢትዮጲያውይ አይደለንም ከአማራ ጋር የተጋባችሁ ተፋቱ ወደ ሌላ ቤተክርስትያን አትህዱ አትገበያዩ እየተባለ የሚደረገው ቅስቀሳ ጥሩ አይደለም አይጠቅመነም ለተጋሩም አይጠቅምም :: ህወሃት የእጁን ነው ያገኘው ለራሳቸው ቤተሰቦቻቸው እንኳን አያዝኑም ቤተሰቦቻቸውን አብረው ይዘው ነው ያስጨረሷቸው :: እኛ ኢትዮጵያውያን ነን ከኢትዮጵያ የሚለየን ነገር የለም: : አዲሱን የትግራይ ጊዜያዊ መንግስት ልንደግፍ ይገባል: : ስህተት ሲሰሩ ማውገዙ የተሻለ ነው ::