Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Ejersa
Member
Posts: 3976
Joined: 05 Nov 2019, 10:39

በአማራ ህዝብ ላይ የዘር ማጥፋት መፈፀሙ ተረጋግጧል!

Post by Ejersa » 25 Nov 2020, 17:04

ጥቅምት 30/2013 ዓ.ም ከቀኑ 9:00 ሰዓት ጀምሮ እስከ ንጋት ድረስ የተፈፀመውን አሰቃቂ ድርጊት የሚገልፀው ብቸኛ ቃል ዘር ማጥፋት (Genocide) የሚለው ነው። በተጠቀሰው ቦታና ሰዓት የተፈፀመው ድርጊት፤ በሰብዓዊነት ላይ የተፈፀመ ወንጀል፣ ጅምላ ጭፍጨፋም ወይም የጦር ወንጀል አይደለም። እነዚህን ሦስቱን ከባድ ወንጀሎች አንድ ላይ አጠቃልሎ የያዘው፤ የተባበሩት መንግስታት በ1948 ዓ.ም ባፀደቀው ድንጋጌ ሆነ የፖለቲካና የታሪክ ምሁራን ባስቀመጧቸው መስፈርቶች መሰረት በአማራ ህዝብ ላይ የዘር ማጥፋት ወንጀል (Genocide) ተፈፅሟል። በምክንያታዊነት እና የሃሳብ የበላይነት የምታምኑ ሰዎች፤ በአንድ በኩል የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ያቀረበውን ሪፖርት ከአምንስቲ ኢንተርናሽናል እና ሌሎች ተቋማት ዘገባና ሪፖርት ጋር አንድ ላይ አጣምራችሁ፣ በሌላ በኩል ደግሞ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የዘር ማጥፋትን አስመልክቶ ያስቀመጣቸው መስፈርቶች የዘርፉ ምሁራን ካስቀመጧቸው ተጨማሪ መስፈርቶች ጋር በማጣምር፣ ስለ እውነት፣ ስለ ፍትህ፣ ስለ ወደፊቱ ግዜ ብለን በግልፅ እንነጋገር፦ በማይካንድራ የተፈፀመው የዘር ማጥፋት ነው። ይሄ ደግሞ የተፈፀመው በማንም ላይ ሳይሆን በአማራ ላይ ነው።