Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Bwendimu
Senior Member
Posts: 10101
Joined: 07 Apr 2007, 08:24

ጌቾ ራያ በመሆኑ ታሰረ

Post by Bwendimu » 20 Nov 2020, 11:28

ሰበር ሹክሹክታ

ጌታቸው ረዳ ታስሯል

ፀቡ ከሁለት ቀን በፊት ነበረ የተጀመረው።
በስብሰባ ላይ፣

ምክንያቱ ይህ ነው።
ጌታቸው መግለጫ ሰጪነት ቦታውን በሌላ ሰው ተተካ። ለምን አለ ጌታቸው፣

ጌታቸው አገልግሎትህ አልቋል፣ አማርኛ ተናጋሪን ማሳመን አንፈልግም። አንተን ሰምቶ የሚያምነን የለም። አሁን ተጋሩን ማሳመን ነው የምንፈልገው ሲባል በንዴት

"ደደቦች ናችሁ፣ የአለማቀፍ ህብረተሰብ ለማሳመን በየትኛው እንግሊዘኛችሁ ነው የምትናገሩት፣ የምትፅፉት፣ ሰውን ተጠቅማችሁ መወርወራችሁ ያናዳል" እያለ በንዴት እየተሳደበ ሲናገር አይነስውሩ አስመላሽ በጥፊ ሊመታው ሲሰነዝር ጌታቸው ዝቅ ብሎ ጥፊውን ሲያመልጥ የአስመላሽ ጥፊ ጌታቸው አጠገብ የነበሩት አቦይ ስብሃት ላይ ያርፋል።

አቦይ በጣም ተናደው በጥፊ የመቱት አስመላሽን ሳይሆን ጌታቸውን ነው። ዝቅ ባትል ኖሮ አልመታም ነበረ ነው የጥፊው ምክንያት።

ከፍተኛ የግጭት ድራማ ተከስቶ ሽጉጥ መማዘዝ ሁሉ ነበረ ነው የተባለው።

ጌታቸው ወደ የተለየ ቦታ ተወስዷል። መታሰሩን ነው የተገኘው መረጃ የሚያሳየው።

ጌታቸው በመታሰሩ የትህነግ ካድሬ ዲያስፖራዎች የሚዲያ ካምፔን ስትራቴጂ ጠፍቶባቸዋል። በመረጃ እጦት ተወዛግበዋል።

ከዚህም በተጨማሪ አሁን የተናበበ የፕሮፓጋንዳ ስራቸው መሪ አጥቶ የሚሉት ጠፍተዋቸው ሲታይ ይህንን የሚመራ የነበረ ጌታቸው አሁን ማድረግ አለመቻሉ ግኃድ እየሆነ ነው።

ነገሮች የተካረሩት የመቀሌ የአየር ድብደባ ኦፕሬሺን ከፍተኛ ኪሳራ በማድረሱ ነው።

በመሆኑም ኦፕረሽኑ መገናኛ ስርዓቱን ከመበጣጠሱና የመሳርያ ክምችቱ ከመምታቱ ባለፈ ኮማንድ ፓስት አመራሩ ላይም አደጋ ማድረሱ እየተገለጠ የመጣ እውነት ይመስላል።

ጌታቸው ፀቡ ቆመው ከቀሩት የትህነግ ሽማግሌዎች ጋር ነው። ጦርነቱን መጀመር ኪሳራ ያደርስብናል ብዬ ነበረ እያለ ሲናገር፣

"የትግራዋይን ጀግንነት እናንተ አታቁም፣ እናሸንፋለን!"
ብሎ አስመላሽ ሲናገር፣ ጌታቸው በበኩሉ፣ "አሃ እኔ ትግራዋይ አይደለሁም?" ብሎ ጠይቆት ነበረ። ጌታቸው ራያ ነው። ራያ ሳይዋጋ ሸሸ እያሉ እንደ ከሃዲ እየተብሰለሰሉ ሲያወሩ ጌታቸው ሲታገሳቸው ከርሟል።

ጅግንነታችን ሲሉ ራያን ቀንሰው መሆኑ አናዶታል።

በነገራችን ላይ የጌታቸው የጫት ሱስ መቋረጡ ቶሎ ቁጡ እንዲሆን እያደረገው መሆኑ ተነግሯል።

በእስር ላይ ቢሆንም አንዳንዶች እየመጡ የሚጠይቁት አሉ ተብሏል።

(መረጃ ነው፣ አታድንቅ፣ ደግሞም አትናቅ! "

አረጋግጠህ ፃፍ የምትሉ ደግሞ በጦርነት ወቅት መረጃን ማረጋገጫ መንገድን አብራችሁ ንገሩኝ። የተፃፈው ውሸትም እውነትም ሊሆን ይችላል። እውነት የመሆን እድሉን መመዘን ነው።

Dawi
Member
Posts: 4311
Joined: 30 Aug 2016, 03:47

Re: ጌቾ ራያ በመሆኑ ታሰረ

Post by Dawi » 20 Nov 2020, 11:44

Bwendimu wrote:
20 Nov 2020, 11:28
"የትግራዋይን ጀግንነት እናንተ አታቁም፣ እናሸንፋለን!"
ብሎ አስመላሽ ሲናገር፣ ጌታቸው በበኩሉ፣ "አሃ እኔ ትግራዋይ አይደለሁም?" ብሎ ጠይቆት ነበረ። ጌታቸው ራያ ነው። ራያ ሳይዋጋ ሸሸ እያሉ እንደ ከሃዲ እየተብሰለሰሉ ሲያወሩ ጌታቸው ሲታገሳቸው ከርሟል።
ሌላው ራያ ስለ ከሃዲው ቡድን ቅጥፈትና ተለዋዋጭ አመል ያጫውተናል፤ :P



Abaymado
Member
Posts: 4216
Joined: 27 Sep 2017, 21:56

Re: ጌቾ ራያ በመሆኑ ታሰረ

Post by Abaymado » 20 Nov 2020, 12:16

በሂወቴ እንዲህ ያለ ቀልድ ስናፍቅ ነበር:: የፈጠራ ተረት ነው የሚመስለው::


""ደደቦች ናችሁ፣ የአለማቀፍ ህብረተሰብ ለማሳመን በየትኛው እንግሊዘኛችሁ ነው የምትናገሩት፣ የምትፅፉት፣ ሰውን ተጠቅማችሁ መወርወራችሁ ያናዳል" እያለ በንዴት እየተሳደበ ሲናገር አይነስውሩ አስመላሽ በጥፊ ሊመታው ሲሰነዝር ጌታቸው ዝቅ ብሎ ጥፊውን ሲያመልጥ የአስመላሽ ጥፊ ጌታቸው አጠገብ የነበሩት አቦይ ስብሃት ላይ ያርፋል።

አቦይ በጣም ተናደው በጥፊ የመቱት አስመላሽን ሳይሆን ጌታቸውን ነው። ዝቅ ባትል ኖሮ አልመታም ነበረ ነው የጥፊው ምክንያት።
"


:lol: :lol:

Post Reply