Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum

MINILIK SALSAWI
Member+
Posts: 8892
Joined: 24 Aug 2012, 12:02

Re: የመከላከያ ሠራዊታችን ትእዛዝ ተሰጥቶታል ቀዩ መሥመር የመጨረሻው ነጥብ ታልፏል። ሀገርና ሕዝብ ለማዳን ሲባል ኃይል የመጨረሻው አማራጭ ሆኗል። ጠ/ ሚ አብይ

Post by MINILIK SALSAWI » 23 Nov 2020, 13:49

የእስር ማዘዣ በወጣባቸው 167 ባለስልጣናትና ከሕወሃት ጋር ግንኙነት ያላቸው ግለሰቦች በሀገር ክህደት፣ በትጥቅ የታገዘ አመጻ፣ በሮኬት ተኩስ ሽብርና በጉረቤት ሀገር ላይ ጥቃት በመፈጸም ይከሰሳሉ - ጠ/ዐቃቤ ሕግ ጌዲዮን ጢሞቲዮስ


MINILIK SALSAWI
Member+
Posts: 8892
Joined: 24 Aug 2012, 12:02

Re: የመከላከያ ሠራዊታችን ትእዛዝ ተሰጥቶታል ቀዩ መሥመር የመጨረሻው ነጥብ ታልፏል። ሀገርና ሕዝብ ለማዳን ሲባል ኃይል የመጨረሻው አማራጭ ሆኗል። ጠ/ ሚ አብይ

Post by MINILIK SALSAWI » 24 Nov 2020, 11:11

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮምሽን የማይካድራው ጭፍጨፋ በትህነግ የፀጥታ መዋቅር የተፈፀመ መሆኑን ይፋ አድርጓል። በጭፍጨፋው በትንሹ 600 ያህል ንፁሃን ተገድለዋል ብሏል። የሟቾች ቁጥር ከዚህም ከፍ ሊል ይችላል ብሏል።

ኢሰመኮ መግለጫ
ኅዳር 15 ቀን 2013 ዓ.ም.
ትግራይ፡ የማይካድራ ሲቪል ሰዎች ጭፍጨፋ የግፍና ጭካኔ ወንጀል ነው
የተጎዱትን ማቋቋም እና የአጥፊዎችን ተጠያቂነት ማረጋገጥ ይገባል

-
በትግራይ ክልል ምዕራባዊ ዞን በምትገኘው የማይካድራ ከተማ ጥቅምት 30 ቀን 2013 ዓ.ም. በወቅቱ በስልጣን ላይ በነበረው የአካባቢው መስተዳድር የጸጥታ መዋቅርና ሳምሪ በተባለ ኢ-መደበኛ የወጣቶች ቡድን የተፈጸመው ጥቃት፤ ግድያ፣ ጉዳትና ውድመት፤ ጠቅላላ ድርጊቱና ውጤቱ ግፍና ጭካኔ የተሞላበት በሲቪል ሰዎች ላይ የተፈጸመ የጭፍጨፋ ወንጀል (atrocious crime of massacre against civilians) መሆኑን የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ገለጸ፡፡
-
ይህ የተገለጸው ኮሚሽኑ ከሕዳር 5 እስከ ሕዳር 9 ቀን 2013 ዓ.ም. ድረስ በማይካድራ ከተማ እንዲሁም በአብርሀጅራ፣ በሳንጃ፣ በዳንሻ፣ በሁመራ እና በጐንደር ከተማ ተዘዋውሮ ባደረገው ምርመራ የደረሰበትን ግኝቶች ይፋ ባደረገበት የመጀመሪያ ደረጃ ቀዳሚ ሪፖርት ነው፡፡ ይህ ከፍተኛ የሰብአዊ መብቶች ጥሰት በሰብአዊነት ላይ የተፈጸመ ወንጀል (crimes against humanity) እና የጦር ወንጀል (war crime) ሊሆን እንደሚችል የሚያመለክት ስለሆነ ኮሚሽኑ ዝርዝር ማስረጃዎቹን እና ወንጀሉን የሚያቋቁሙትን የሕግና የፍሬ ነገር ትንተና በሙሉ ሪፖርቱ ላይ በዝርዝር አጣርቶ የሚያቀርብ መሆኑን አሳውቋል፡፡
-
በቀዳሚ ሪፖርቱ እንደተመለከተው በአካባቢው የነበረው የሚሊሽያና የፖሊስ ጸጥታ መዋቅር በፌዴራሉ አገር መከላከያ ሰራዊት እርምጃ ሸሽቶ አካባቢውን ለቅቆ ከመውጣቱ በፊት ሳምሪ ከተባለ መደበኛ ያልሆነ የትግራይ ወጣቶች ቡድን ጋር በማበርና በመተባበር በተለይ ‹‹አማሮችና ወልቃይቴዎች›› ያሏቸውን የአካባቢው ነዋሪ ሲቪል ሰዎች ከቤት ቤት እየዞሩና በየጐዳናው ላይ በገመድ በማነቅ፣ በስለት በመጥረቢያ በዱላ በመደብደብ ገድለዋል፣ የአካል ጉዳት አድርሰዋል፣ እንዲሁም ንብረት አውድመዋል፡፡ ኢሰመኮ ከአካባቢው ምንጮች እስከ አሁን በአገኘው መረጃ በአነስተኛ ግምት እስከ 600 ሰዎች የተገደሉ ሲሆን ትክክለኛው ቁጥር ከዚህ ሊበልጥም እንደሚችል በሪፖርቱ ተመልክቷል፡፡
-
ሳምሪ የሚባለው የትግራይ ወጣቶች ቡድን በዚህ ከባድ ወንጀል ላይ ቢሰማራም፤ በአንጻሩ የትግራይ ብሔረሰብ ተወላጅች የሆኑ ሌሎች የአካባቢው ነዋሪዎች አጥቂው ቡድን ሲያሳድዳቸው የነበሩ ሲቪል ሰዎችን በቤታቸው፣ በቤተክርስቲያን እና በእርሻ ቦታ ደብቀው በመሸሸግ ሕይወታቸውን እንዳተረፉላቸው ኢሰመኮ ያነጋገራቸው ምስክሮች አረጋግጠዋል፡፡
-
የኢሰመኮ ዋና ኮሚሽነር ዳንኤል በቀለ (ዶ/ር) ‹‹በማይካድራ ከተማ በአነስተኛ ጽንፈኛ ቡድን የተፈጸመው በብሔር ማንነት ላይ የተመሰረተ እጅግ ዘግናኝ ኢሰብዓዊ ወንጀል ልብ ሰባሪ ቢሆንም፤ በአንጻሩ ኢትዮጵያውያን በብሔር ሳይለያዩ አንዱ የሌላው ጠባቂ ሆነው መታየታቸው ልብ ይጠግናል፤ ስለ ወደፊት በሰላም አብሮ መኖርም ተስፋ ይሰጣል›› ብለዋል፡፡ አክለውም ‹‹የተጐዱ ሰዎችን እና አካባቢዎችን መልሶ ከማቋቋምና ከመጠገን በተጨማሪ፤ በዚህ ከባድ የሰብዓዊ መብቶች ወንጀል በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ የተሳተፉ በየደረጃው ያሉ ጥፋተኞችን በሕግ ፊት ተጠያቂነት ማረጋገጥ ያስፈልጋል›› ብለዋል፡፡
-
የኮሚሽኑን የመጀመሪያ ደረጃ ቀዳሚ ሪፖርት - https://docs.google.com/document/d/1Gje ... GW3HM/edit
-

MINILIK SALSAWI
Member+
Posts: 8892
Joined: 24 Aug 2012, 12:02

Re: የመከላከያ ሠራዊታችን ትእዛዝ ተሰጥቶታል ቀዩ መሥመር የመጨረሻው ነጥብ ታልፏል። ሀገርና ሕዝብ ለማዳን ሲባል ኃይል የመጨረሻው አማራጭ ሆኗል። ጠ/ ሚ አብይ

Post by MINILIK SALSAWI » 24 Nov 2020, 13:29

Ethiopia’s Government and the TPLF Leadership Are Not Morally Equivalent
የኢትዮጵያ መንግስት እና ህወሃት በተመሳሳይ ሚዛንና በእኩል ስነ ምግባር የሚቀመጡ አይደሉም


The leaders of the Tigray People’s Liberation Front are seeking to manipulate the international community into backing a power-sharing deal that grants it impunity for past crimes and gives it far more future influence over the country than it deserves. …………… The key problem in the international community’s approach to Ethiopia is the assumption of moral equivalence, which leads foreign governments to adopt an attitude of false balance and bothsidesism.

By Hailemariam Desalegn

Read Here : https://mereja.com/amharic/v2/404528


MINILIK SALSAWI
Member+
Posts: 8892
Joined: 24 Aug 2012, 12:02

Re: የመከላከያ ሠራዊታችን ትእዛዝ ተሰጥቶታል ቀዩ መሥመር የመጨረሻው ነጥብ ታልፏል። ሀገርና ሕዝብ ለማዳን ሲባል ኃይል የመጨረሻው አማራጭ ሆኗል። ጠ/ ሚ አብይ

Post by MINILIK SALSAWI » 25 Nov 2020, 09:05

የተባበሩት መንግሥታት የፀጥታዉ ጥበቃ ምክር ቤት ትግራይ ዉስጥ ሥለሚደረገዉ ዉጊያ ትናንት ሌሊት በመንግስታቱ ድርጅት ዋና መቀመጫ ኒዮርክ ተሰብስቦ ነበር።

ምክር ቤቱ በጉዳዩ ላይ ለመነጋገር ቀደም ሲል ይዞት ለነበረዉ ቀጠሮ የአፍሪቃ ሐገራት ድጋፍ ባለመስጠታቸው ምክንያት ሰርዞት ነበር።

ይሁንና በምክር ቤቱ ድምፅን በድምፅ የመሻር ሥልጣን ያላቸዉን ፈረንሳይና ብሪታንያን፣ ጨምሮ የአዉሮጳ ሐገራት ዉይይቱ እንዲደረረግ ግፊት በማድረጋቸዉ የጸጥታው ምክር ቤት አባላት በጉዳዩ ዙሪያ መሰብሰባቸው ዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።

አዣንስ ፍራንስ ፕሬስ እንደዘገበዉ ሶስተኛ ሳምንቱን የያዘዉ ጦርነት በርዕስነት እንዲቀርብ ከፈረንሳይና ከብሪታንያ በተጨማሪ ግፊት ያደረጉት ቤልጂየም፣ ጀርመንና የወቅቱ የጸጥታው ምክርቤት ተለዋጭ አባል የሆነችው ኢስቶኒያ ናቸዉ።

አፍሪካን ወክለው የጸጥታው ምክር ቤት ተለዋጭ አባል የሆኑት ደቡብ አፍሪካ፣ኑጀር እና ቱኒዝያ የኢትዮጵያ ፌደራዊ መንግስት ጦርና የሕዝባዊ ወያኔ ሐርነት ትግራይ ታጣቂዎች ሥለገጠሙት ጦርነት መረጃ የሚያሰባስብ የመልዕክተኞች ጓድ ወደ ኢትዮጵያ መሔድ አለበት በሚል ምክንያት ጉዳዩ ለዉይይት መቅረቡን ተቃውመው ነበር።

ይሁንና በመጨረሻም ስብሰባው ያለ ስምምነት መጠናቀቁ የተገለጸ ሲሆን ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ ጦርነቱ የኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ መሆኑን ገልጸው የትኛውም አገር በውስጥ ጉዳያችን ጣልቃ ከመግባት እንዲቆጠብ አሳስበዋል።

ኢትዮ ኤፍ ኤም

MINILIK SALSAWI
Member+
Posts: 8892
Joined: 24 Aug 2012, 12:02

Re: የመከላከያ ሠራዊታችን ትእዛዝ ተሰጥቶታል ቀዩ መሥመር የመጨረሻው ነጥብ ታልፏል። ሀገርና ሕዝብ ለማዳን ሲባል ኃይል የመጨረሻው አማራጭ ሆኗል። ጠ/ ሚ አብይ

Post by MINILIK SALSAWI » 25 Nov 2020, 10:03

በማይካድራ ከተማ አብነትና ሴንትራል መውጫ በተባሉ ገጠራማ ቦታዎች 74 ንጹሃን የተቀበሩበት ሥፍራ ተገኝቷል፡፡ 56 ዜጎች በአንድ ጉድጓድ ተቀብረው ነው የተገኙት፡፡ የውሃ ጉድጓድ ውስጥም የሰለባዎቹ አስክሬን መኖሩም ተረጋግጧል፡፡

https://mereja.com/amharic/v2/405416
MINILIK SALSAWI
Member+
Posts: 8892
Joined: 24 Aug 2012, 12:02

Re: የመከላከያ ሠራዊታችን ትእዛዝ ተሰጥቶታል ቀዩ መሥመር የመጨረሻው ነጥብ ታልፏል። ሀገርና ሕዝብ ለማዳን ሲባል ኃይል የመጨረሻው አማራጭ ሆኗል። ጠ/ ሚ አብይ

Post by MINILIK SALSAWI » 27 Nov 2020, 09:57

ጀግናው የሀገር መከላከያ ሰራዊት የተቆጣጠራቸው ምሽጎች፣ የማረካቸው መሳሪያዎች፣ ያወደማቸው የጁንታው መሳሪያዎች በፎቶግራፍ (ኢ.ፕ.ድ)

SEE MORE PICTURES : https://mereja.com/amharic/v2/406842MINILIK SALSAWI
Member+
Posts: 8892
Joined: 24 Aug 2012, 12:02

Re: የመከላከያ ሠራዊታችን ትእዛዝ ተሰጥቶታል ቀዩ መሥመር የመጨረሻው ነጥብ ታልፏል። ሀገርና ሕዝብ ለማዳን ሲባል ኃይል የመጨረሻው አማራጭ ሆኗል። ጠ/ ሚ አብይ

Post by MINILIK SALSAWI » 27 Nov 2020, 10:53

በማይካድራ ተጨማሪ የጅምላ መቃብሮች ተገኙ።

(አብመድ) ጥቅምት 30/2013 ዓ.ም በንጹኃን የአማራ ብሔር ተወላጆች ላይ ዘርን መሠረት ያደረገ ጥቃት በማይካድራ ከተማ መፈፀሙ ይታወቃል። ይህን አስነዋሪ ተግባር የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን በቦታው በመገኘት ባደረገው ጥናት እና ይፋ ባደረገው መረጃ የሟቾች ቁጥር በትንሹ 600 እንደሆነ ገልጾ ነበር።

ግድያውም ዘርን መሠረት ያደረገና በተለይም የአማራ ተወላጆች ላይ ያነጣጠረ ጅምላ ጭፍጨፋ መሆኑን ገልጿል። ይሁን እንጂ የሟቾች ቁጥር በትንሹ 600 ነው ተብሎ የተገለጸው በማይካድራ ከተማ በየቤቱ ህይወታቸው አልፎ የተገኙ እና በቤተክርስቲያን ውስጥ የተቀበሩትን ብቻ መሠረት ያደረገ ነው።
የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ጥናት አድርጎ ከተመለሠ በኃላ ከማይካድራ ከተማ ወጣ ባሉ የገጠር አካባቢዎች በርካታ የጅምላ መቃብሮች መገኘታቸውን የአማራ ብዙኃን መገናኛ ድርጅት ጋዜጠኞች በቦታው በመገኘት አረጋግጠዋል።

በአንድ ቦታ 18 ሰው በጉድጓድ ውስጥ በጅምላ የተጣሉ ሲሆን በሌላ የገጠር አካባቢ ደግሞ 57 ሰዎች በጎርፍ ማፋሰሻ ቦይ ውስጥ በጅምላ ተገድለው እና ተጥለው ተገኝተዋል።

በዛሬው ዕለትም በማይካድራ ሌላ የገጠር ቀበሌ ውስጥ 17 ሰዎች በጅምላ ተገድለው በጉድጓድ ውስጥ ተጥለው ተገኝተዋል። አሁንም ሴንትራል፣ ደሮ እርባታ፣ በረኸት በሚባሉ አካባቢዎች ላይ አሠሳ እየተደረገ እንደሚገኝ እና ቁጥሩ እንደሚጨምር የማይካድራ ነዋሪዎች ገልጸውልናል።
በዚህ የዘር ማጥፋት ወንጀል ተሳታፊ ናቸው የሚባሉት ተጠርጣሪዎች በብዛት ሱዳን ሐሻባ በሚባል የስደተኞች መጠለያ ውስጥ እንደሚገኙ ይነገራል።
ከዚህ በተጨማሪ በማይካድራ የዘር ማጥፋት ወንጀል ላይ ተሳታፊ ናቸው በሚል ተጠርጥረው ከተያዙት 60 ግለሠቦች ውስጥ 17ቱ በቀጥታ የወንጀሉ ተሳታፊ መሆናቸውን የማይካድራ ከተማ ጊዜያዊ አስተዳደር ገልጾልናል።

ትህነግ በወልቃይትና አካባቢው ተወላጆች ላይ በአስር ሽህ የሚቆጠሩ ዜጎችን ገድሏል፤ ከግማሽ ሚሊየን በላይ ሰዎችን ደግሞ ከአካባቢያቸው እንዲፈናቀሉ አድርጓል፡፡


MINILIK SALSAWI
Member+
Posts: 8892
Joined: 24 Aug 2012, 12:02

Re: የመከላከያ ሠራዊታችን ትእዛዝ ተሰጥቶታል ቀዩ መሥመር የመጨረሻው ነጥብ ታልፏል። ሀገርና ሕዝብ ለማዳን ሲባል ኃይል የመጨረሻው አማራጭ ሆኗል። ጠ/ ሚ አብይ

Post by MINILIK SALSAWI » 27 Nov 2020, 11:06

No dialogue with Tigray leaders, Ethiopia PM tells AU envoys

Abiy rules out dialogue with TPLF during meeting with three AU envoys, a day after he announced ‘final phase’ of three-week conflict.

Please wait, video is loading...

MINILIK SALSAWI
Member+
Posts: 8892
Joined: 24 Aug 2012, 12:02

Re: የመከላከያ ሠራዊታችን ትእዛዝ ተሰጥቶታል ቀዩ መሥመር የመጨረሻው ነጥብ ታልፏል። ሀገርና ሕዝብ ለማዳን ሲባል ኃይል የመጨረሻው አማራጭ ሆኗል። ጠ/ ሚ አብይ

Post by MINILIK SALSAWI » 27 Nov 2020, 13:22

ከጥቂት ቀናት በሁዋላ መቀሌ በቁጥጥር ስር ትገባለች - ሌ/ጀ ሀሰን ኢብራሂም ................. ከአድዋ የተነሳው ሀይላችን ሀውዜንን ፣ አብርሀ ወአፅብሀ ፣ ውቅሮን ፣ እና እጉላዕን ተቆጣጥሮ መሶቦ በሚባለ እና ከፍተኛ ወታደራዊ ጠቀሜታ ያለው ቦታ ደርሷል ። ዕዳጋ ሀሙስ የነበረው ሀይላችንም ሰንቃጣን ፣ እና እል ነጃሺን ተቆጣጥሮ ውቅሮ በመግባት ከአድዋ ከመጣው ሠራዊታችን ጋር በጣምራ ግዳጃቸውን በአኩሪ ሁኔታ እየተወጡ ይገኛሉ ።

https://mereja.com/amharic/v2/407170


MINILIK SALSAWI
Member+
Posts: 8892
Joined: 24 Aug 2012, 12:02

Re: የመከላከያ ሠራዊታችን ትእዛዝ ተሰጥቶታል ቀዩ መሥመር የመጨረሻው ነጥብ ታልፏል። ሀገርና ሕዝብ ለማዳን ሲባል ኃይል የመጨረሻው አማራጭ ሆኗል። ጠ/ ሚ አብይ

Post by MINILIK SALSAWI » 28 Nov 2020, 09:20

የኢትዮጵያ የመከላከያ ሰራዊት የትግራይ ክልል ዋና ከተማ የሆነችውን መቀሌ ከተማን ለመቆጣጠር ወታደራዊ ዘመቻ መጀመሩን አልጀዚራ ተናገረ። .... ዶ/ር ደብረፂዮን ለሮይተርስ የዜና ወኪል በጽሑፍ ባስተላለፉት መልዕክት መቀሌ የከባድ መሳሪያ ድብደባ ውስጥ ናት ሲሉ ዶ/ር ደብረፂዮን አማረሩ ሲል አልጀዚራ በድረ ገጹ ጽፏል።

https://mereja.com/amharic/v2/407846

MINILIK SALSAWI
Member+
Posts: 8892
Joined: 24 Aug 2012, 12:02

ነቀርሳው ተነቅሏል !!!!! የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት የመቀሌ ከተማን ሙሉ ለሙሉ ተቆጣጥሯል። የሰሜን ዕዝን የማዘዣ ጣቢያን ተቆጣጥሯል

Post by MINILIK SALSAWI » 28 Nov 2020, 13:12

ነቀርሳው ተነቅሏል !!!!!

የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት የመቀሌ ከተማን ሙሉ ለሙሉ ተቆጣጥሯል። የሰሜን ዕዝን የማዘዣ ጣቢያን ተቆጣጥሯል

ንጹሐን ዜጎች ዒላማ ሳይሆኑ፣ ከተሞቻችንና ቅርሶቻችን ሳይጎዱ መቀሌ ለመግባት ተችሏል" ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ

https://mereja.com/amharic/v2/408095

MINILIK SALSAWI
Member+
Posts: 8892
Joined: 24 Aug 2012, 12:02

Re: የመከላከያ ሠራዊታችን ትእዛዝ ተሰጥቶታል ቀዩ መሥመር የመጨረሻው ነጥብ ታልፏል። ሀገርና ሕዝብ ለማዳን ሲባል ኃይል የመጨረሻው አማራጭ ሆኗል። ጠ/ ሚ አብይ

Post by MINILIK SALSAWI » 29 Nov 2020, 03:23

"ሸረሪቷ ተጨፍልቃለች፡፡ አሁን የሸረሪት ድሩን መጥረግ የማይናቅ ግን እጅግ የቀለለ ተግባር ይቀረናል" የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት ዋና ዳይሬክተር አቶ ተመሥገን ጥሩነህ

https://mereja.com/amharic/v2/408369

MINILIK SALSAWI
Member+
Posts: 8892
Joined: 24 Aug 2012, 12:02

Re: የመከላከያ ሠራዊታችን ትእዛዝ ተሰጥቶታል ቀዩ መሥመር የመጨረሻው ነጥብ ታልፏል። ሀገርና ሕዝብ ለማዳን ሲባል ኃይል የመጨረሻው አማራጭ ሆኗል። ጠ/ ሚ አብይ

Post by MINILIK SALSAWI » 29 Nov 2020, 13:24

Please wait, video is loading...


MINILIK SALSAWI
Member+
Posts: 8892
Joined: 24 Aug 2012, 12:02

Re: የመከላከያ ሠራዊታችን ትእዛዝ ተሰጥቶታል ቀዩ መሥመር የመጨረሻው ነጥብ ታልፏል። ሀገርና ሕዝብ ለማዳን ሲባል ኃይል የመጨረሻው አማራጭ ሆኗል። ጠ/ ሚ አብይ

Post by MINILIK SALSAWI » 01 Dec 2020, 14:52

Please wait, video is loading...

Post Reply