Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Za-Ilmaknun
Member
Posts: 4080
Joined: 15 Jun 2018, 17:40

የተወካዮች ምክር ቤት በአማራ ሕዝብ ላይ የዘር ማጥፋት ወንጀል መፈፀሙን አምኗል

Post by Za-Ilmaknun » 03 Nov 2020, 14:34

መንግስት በጥፋት ኃይሎች አማካይነት በአማራ ብሔር ላይ የሚደርሰው ግድያ፣ ጭፍጨፋ እና የዘር ማጥፋት ወንጀል፤ በመንግስት በኩል የማያዳግም ርምጃ እንዲወሰድበት ጠየቀ፡፡
(ዜና ፓርላማ)፤ ጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ.ም.፤ 5ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በ6ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 2ኛ መደበኛ ስብሰባው፤ በጥፋት ኃይሎች አማካይነት በአማራ ብሔር ላይ የሚደርሰው ግድያ፣ ጭፍጨፋ እና የዘር ማጥፋት ወንጀል፤ በመንግስት በኩል የማያዳግም ርምጃ እንዲወሰድበት ጠየቀ፡፡

ምክር ቤቱ ይህንን ጥያቄ ያነሳው፤ ከትናንት በስቲያ በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ወለጋ ዞን፣ ጉሊሶ ወረዳ፣ ጋዋ ቃንቃ ቀበሌ የአማራ ብሔርን ለይቶ የተፈጸመውን ጅምላ ጭፍጨፋ እና አሰቃቂ ግድያ አስመልክቶ ባደረገው ውይይት ነው፡፡ ይህም “በመግለጫ ጋጋታ የሚታለፍ ጉዳይ መሆን የለበትም፣ በሰፊው ልንወያይበት እና እንደ መንግስት ሀገሪቷን ከመበታተን አደጋ ልንታደግ ይገባል” ሲሉ የምክር ቤቱ አባላት አስገንዝበዋል፡፡

ሀገሪቷ አንድነቷን አስጠብቃ እንድትቀጥል ከተፈለገ፤ መንግስት የጥፋት ኃይሎችን በአሸባሪነት ፈርጆ የማያዳግም ርምጃ መውሰድ እንዳለበት የጠቆሙት የምክር ቤቱ አባላት፤ በምዕራብ ወለጋ የተከሰተው ጅምላ ግድያ፣ መከላከያ ሠራዊቱ ስፍራውን ለቅቆ በወጣ በጥቂት ሰዓታት ልዩነት የተፈጠረ በመሆኑ፤ የሀገር መከላከያ ሠራዊቱ የአሠራር ሂደት መፈተሸ እንዳለበትም አሳስበዋል፡፡ በመንግስት መዋቅር ሥር ሆነው ከጥፋት ኃይሎች ጋር ተባብረው የሚሠሩ ግለሰቦችም ስለሚኖሩ፤ በትኩረት መጣራት እንደሚገባውም የምክር ቤቱ አባላት አመላክተዋል፡፡

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ-ጉባዔ የተከበሩ አቶ ታገሰ ጫፎ በበኩላቸው፤ የውስጥም ሆነ የውጭ ፀረ-ሰላም ኃይሎች ዓላማቸው ሀገሪቷን ማፍረስ እንደሆነ ገልጸው፤ ይህን ዕኩይ ተግባራቸውን ተገንዝበን ሀገሪቷን ከጥፋት ለመታደግ በአንድነት ልንቆም ይገባል እንጂ፣ ዕድል ልንሰጣቸው አይገባም ብለዋል፡፡

የምክር ቤቱ ምክትል አፈ-ጉባዔ የተከበሩ ወ/ሮ ሽታዬ ምናለ በበኩላቸው፤ አማራን እየለዩ ማጥቃት አሁን የተጀመረ ሳይሆን፣ ከ1983 ዓ.ም. ጀምሮ ተጠናክሮ የቀጠለ ነው ብለዋል፡፡ ከአማራ ክልል ውጭ በሚኖሩ አማራዎች ላይ ተመሳሳይ ግድያ እና የጅምላ ጭፍጨፋ ሲካሄድ መቆየቱን ያስታወሱት ምክትል አፈጉባዔዋ፣ ችግሩ ከሕገ-መንግስቱ የመነጨ እንደሆነም አስታውሰዋል፡፡

የሰላም ሚኒስቴር ባለበት ሀገር የሰው ልጅ እንደቅጠል እየረገፈ ማየት እጅግ ያማል ያሉት ምክትል አፈ-ጉባዔዋ፤ የሕዝብን ደኀንነት ማስጠበቅ የማንችል ከሆነ የእኛ መኖር ትርጉም አልባ ስለሚሆን የዜጎች መፈናቀል እና ግድያ መቆም እንዳለበትም አሳስበዋል፡፡

https://mereja.com/amharic/v2/385985