Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Ejersa
Member
Posts: 3976
Joined: 05 Nov 2019, 10:39

ሰበር ዜና፣ የትግራይ ልዩ ሃይል በኤፍ ኤስ አር (FSR) መኪኖች ተጭነው ከወደ ትግራይ እየመጡ ነው!

Post by Ejersa » 03 Nov 2020, 10:06

በዚህ ሰዓት ብዙ ቁጥር ያለው የትግራይ ልዩ ሃይል በኤፍ ኤስ አር (FSR) መኪኖች ተጭነው ከወደ ትግራይ እየመጡ ነው:: ራያ ኮረምን አቆራርጠው ወደ ራያ አላማጣ ወደ ራያ ዋጃ ጥሙጋ እና ሰሌን ውሃ እየከነፉ ነው። የራያ ሚሊሻዎች ቤተሰቦቻቸውን እንዲሰናበቱ ታዘዋል:: ለግዳጅ የሚወጣ ሰው መቸ እንደሚመለስ አይታወቅም የሚል መልእክት እያስተላለፉ ነው። በሰሌን ውሃ አድርገው ራያ ቆቦ አካባቢ እንደሚገቡ እና ጥቃት እንደሚሰነዝሩ ተነግሯቸዋል::

"ሰራዊት አዘጋጅተናል:: ሚልሻ አዘጋጅተናል:: ልዩ ሃይል አዘጋጅተናል:: ለሰላም ነበር የተዘጋጀነው:: ጦርነቱ የሚጀምር ከሆነ ግን እናሸንፋለን::" ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል

ይሄው ባሉት መሰረትም ልዩ ሃይሉን ወደ ራያ አላማጣ ራያ ዋጃ ጥሙጋ : ራያ ጨርጨር እና ራያ አዘቦ ድንበሮች ላይ እያስጠጉ ይገኛል:: ህዝቡን ለጦርነት እየቀሰቀሱ ነው:: ሚሊሻውን እያዋከቡት ሲሆን አሁን በዚህ ሰዓት ሚሊሻው ወደ ግንባር እንዲዘምት እየሰበሰቡት ይገኛሉ:: በቅርብ ቀናት ውስጥ የትህነግ ልዩ ሃይል የአማራ ክልልን ይወጋል:: ጦርነቱን ስለፈለጉት አይቀሬ ነው:: ትንኮሳ ፈፅመው ቶሎ ያስጀምሩታል:: አንድ ክልል የፌደራል መንግስትን ወጋ ተብሎ በታሪክ ይፃፋል!!!

Hameddibewoyane
Member
Posts: 3890
Joined: 25 Sep 2019, 02:42

Re: ሰበር ዜና፣ የትግራይ ልዩ ሃይል በኤፍ ኤስ አር (FSR) መኪኖች ተጭነው ከወደ ትግራይ እየመጡ ነው!

Post by Hameddibewoyane » 03 Nov 2020, 10:11

"ከግብፅ ጋር ጨርሰናል:: በቅርብ ሁሉን ነገር ታዩታላችሁ::" አቶ ሃፍቱ ኪሮስ (የትህነግ ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል እና የደቡባዊ ዞን ምክትል አስተዳዳሪ)

ነገሩ እንዲህ ነው:: በራያ አላማጣ ከተማ ታዋቂ እና ባላባት የሚባሉ ከ 50 በላይ የራያ አላማጣ ተወላጆች ያለፈው እሁድ ለሰኞ አጥቢያ በለሊት ከየቤታቸው ተለቅመው እንዲታፈኑ ተደረገ:: ከዚያም ይህ የምትመለከቱት የትህነግ ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል አቶ ሃፍቱ ኪሮስ ለታፈኑት የራያ ተወላጆች በአደባባይ ይህን ንግግር አደረገ:-

ከዚህ በኃላ እናንተን አንለማመጥም:: ከኮሚቴው እና ከራዴፓ ጋር ያላችሁን ግንኙነት ካላቆማችሁ ግንባራችሁን በጥይት እንመታዋለን:: እኛ ከግብፅ ጋር ጨርሰናል:: በቅርቡ ሁሉን ነገር ታዩታላችሁ:: የምታርፉ ከሆነ አርፋችሁ ከእኛ ጋር ወግኑ:: ካልሆነ ግን መጀመሪያ እናንተን ነው የምንገድለው:: >> በማለት በእስር በነበሩት የራያ አባቶች : ባለሃብቶች እና ወጣቶች ላይ በእብሪት ደነፋባቸው:: የራያ አባቶች እና ባለሃብቶችም እጅግ አዘኑ:: በቀያቸው መኖር እንዳልቻሉም ፊት ለፊት ተናገሩ:: ሰርተን መብላት እንኳን አልቻልንም እያሉ ምሬታቸውን ገለፁ:: ጦርነቱ ከተጀመረ እንዲገደሉ ስም ዝርዝራቸው የተላለፈ ተጨማሪ የራያ ተወላጆችም አሉ:: በየስብስባው እያስተላለፉት ያሉት ዛቻ አስገራሚ ነው:: አፈናው አሁንም ቀጥሏል:: ይህ የራዮች ብሶትና ምሬት እንደተጠበቀ ሆኖ ሃፍቱ ኪሮስ እንዳለው ግን ሰኞ ቀን ብዙ ሃዘን ከወለጋ ተሰማ:: በታሪክ ይመዝገብ!!! ገዳያችንም አስገዳያችንም ማን እንደሆነ እናውቃለን!! በራያ ለሚከሰተው ግድያ ደግሞ ሃፍቱ ኪሮስ : ጣሰው ቦጋለ እና እቁባይ ገ/መድህን (ሚግ) ዋና ናቸው ተብሏል::

አሁንም የጦርነት ነጋሪቱ እየተደለቀ ነው:: እነሆ በዛሬው ዕለት ደግሞ ትህነግ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ልዩ ሃይሉን ወደ አማራ አዋሳኝ ድንበሮች እያስጠጋ ይገኛል::
በዚህ ሰዓት በሁሉም የራያ ወረዳዎች ላይ የወረዳ ፀጥታ ሃላፊዎች ከልዩ ሃይሉ ጋር በመሆን በፓትሮል መኪና እየዞሩ የጦርነት ቅስቀሳ እያደረጉ ሲሆን በከተማ እና በገጠር ያለውን ሚሊሻ አስገድደው ወደ ማዕከል እየሰበሰቡት ይገኛል:: የሚገርመው በእርሻ አውድማ ላይ የሚገኙ ሚሊሻዎችን ጭምር በግዳጅ እያስመጧቸው ነው:: ዛሬ ከሰዓት ወደተመደቡበት የጦርነት ቀጠና ያሰማሯቸዋል ተብሏል:: ከፍተኛ ውጥረት አለ:: ትህነግ የአማራ ክልልን እንደሚያጠቃ ግልፅ ነው:: ራያ ቆቦ ጥንቃቄ ይደረግ:: ዛሬ ወይም ነገ የራያ ቆቦን ወረዳ ትህነግ መውረሩ አይቀሬ ነው:: ደግሜ እናገራለሁ በቅርብ ቀናት ትህነግ የአማራ ክልልን ያጠቃል!!!! የተሰጣቸው አቅጣጫ ይሄው ነው!!!!

Post Reply