Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
eden
Member+
Posts: 9268
Joined: 15 Jan 2009, 14:09

Your opinion is needed here please

Post by eden » 31 Oct 2020, 09:27

Hey guys

Need your input for my new research.

Here's a question for you to reflect on and answer.

If TPLF changes its long standing position and rejects nation & nationalities based organization in Ethiopia, will this change your heart and mind on whether you oppose or support and how intensely you oppose or support it?

Would and should Abiy and Isayas work with TPLF if TPLF renounces nation & nationalities based organization?



.
Last edited by eden on 31 Oct 2020, 09:36, edited 2 times in total.

Halafi Mengedi
Senior Member+
Posts: 45809
Joined: 30 May 2010, 23:04

Re: Your opinion is needed here please

Post by Halafi Mengedi » 31 Oct 2020, 09:32

It is like changing your God given sex.

Abere
Senior Member
Posts: 11120
Joined: 18 Jul 2019, 20:52

Re: Your opinion is needed here please

Post by Abere » 31 Oct 2020, 10:41

Eden,

Actually this is a very good question.

a) If TPLF rejects nation & nationalities based organization in Ethiopia, it will certainly change my heart and most informed Ethiopians as well. This is the only and only reason why the country has been in such a mess now. Admission to mistakes and asking for forgiveness are human in nature. But, let's not for get also putting them in power back will also be undemocratic. Ethiopia has to be for all Ethiopians, whether a person goes to Bale or Wellega or Gojjam or Tigray, he/she should feel as Ethiopian and belong to wherever that person. That is what we need as a country. Ethnic/tribal federation will not serve doing it forever, it is discriminatory inherently.

b) Would Abiy and Isayas work with TPLF if TPLF renounces nation & nationalities based organization? If TPLF does and Abiy/Isaias don't, then the blame is entirely on them. In my opinion, Abiy Ahmed himself is also as ethnocentric thug as TPLF. He may struggle in quitting his motto of Oromuma, which an antithesis of Ethiopianism. Don't forget Abiy will also follow the direction of the wind. Regarding Isaias, he too has been referred as the man that assigned a 100 years challenging homework to Ethiopia, he may or may not see this in his favor. However, he will be forced too cancel that 100 years homework. Again, the point is do these same people stay in power. No. They all have to repair the decades damage they caused to the impoverished illtreated, ill-informed citizen and give way to the new generation that will create a conducive political environment.
They have squandered their time.

This is just my opinion. What else does Ethiopia want? War? whining and complaining indefinitely? The country has to have an articulated need. Lack of articulated need has opened green pasture for so-called activists feeding the fire of violence and shattering the inviolable sovereignty of Ethiopia built on the sweat and blood of our sacred ancestor for thousands of years.

Tog Wajale E.R.
Member+
Posts: 9947
Joined: 31 Oct 2019, 15:07

Re: Your opinion is needed here please

Post by Tog Wajale E.R. » 31 Oct 2020, 12:21

Bissbiss Shettattam Agga*me A.K.A. Sister Eden :--- No Matter What, We Will Never Ever Sleep Until We Buried All Former Dedebit Woorgach Woyane T.P.L.F. Aggames Six Feet Underground For Good, Short Of That, There Will Be No Communications With Tigrayian Leaders Or Peace.
The Bottom Line Is Woyane T.P.L.F. Criminals Leaders Must Be Apprehended Or Buried Six Feet Underground.

AbebeB
Member+
Posts: 7694
Joined: 15 Oct 2016, 10:31

Re: Your opinion is needed here please

Post by AbebeB » 31 Oct 2020, 14:14

eden wrote:
31 Oct 2020, 09:27
Hey guys

Need your input for my new research.

Here's a question for you to reflect on and answer.

If TPLF changes its long standing position and rejects nation & nationalities based organization in Ethiopia, will this change your heart and mind on whether you oppose or support and how intensely you oppose or support it?

Would and should Abiy and Isayas work with TPLF if TPLF renounces nation & nationalities based organization?
.
The only way out is and only if it appears as below.



Cigar
Senior Member
Posts: 11640
Joined: 19 Apr 2010, 00:03

Re: Your opinion is needed here please

Post by Cigar » 31 Oct 2020, 14:27

Eden the agame hoe, as an Eritreans spokesperson we will take that deal when your sherm*uta mom grows a di*ck and two balls and you start calling her daddy.
Why ask such stupid question when you know your woyane shiftas are waving white flag at our border and begging us to forgive and forget their sins like 188 times, just to be rejected?
Woyane needs to be buried 100 feet down and we will wait for 2 to 3 generations to see if your yet unborn snotty agame childrenget born with human, decent, untwisted hearts, which is still doubtful.
Hopefully the miseries of two to three generations will fixt that.

eden
Member+
Posts: 9268
Joined: 15 Jan 2009, 14:09

Re: Your opinion is needed here please

Post by eden » 31 Oct 2020, 23:12

So far, 4 but 1 of you implied policy change by TPLF away from nation & nationalities based organization would not change your attitude towards TPLF.

If this sample reflects the sentiment of people on the ground, TPLF does not have the incentive to change its philosophy.

This is fascinating!

YAY
Member
Posts: 943
Joined: 21 Aug 2013, 11:51

Re: Your opinion is needed here please

Post by YAY » 31 Oct 2020, 23:23

Dear Eden: You may consider this as background knowledge for your research

Any improvement displayed by the MLLT/TPLF (Tigraiy People's Liberation Front) might appear to be better than never, but the issues that cause problems to Etiyopiya and Eritrea are more than just the case of a federal State structure based on nations and nationalities. The fundamental problem with MLLT/TPLF leaders is the fact that they are not true to themselves and others. Do you know how one could tell when they are lying? When they open their mouths to talk. Deception seems to be their over-arching modus operandi (i.e. their established way of doing things). Read the following interview carefully as well as patiently.


አዲስ ዘመን እሁድ ግንቦት 16 ቀን 2012 ዓ.ም ገጽ 12
ወቅታዊ ጉዳይ
«የኢትዮጵያ ብሔር፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች መገንዘብ የሚኖርባቸው ፤
የትግራይ ህዝብ ትክክለኛ ኢትዮጵያዊና ትክክለኛ አካሄድ የሚሄድ ህዝብ መሆኑን ነው»

ወንድወሰን ሽመልስ

የህዝቦች ብሶት የወለደው ትግል የሆነውን አገራዊ ለውጥ ተከትሎ በርካቶች በጋራ ተከባብረው የሚኖሩባት ለሁሉም የምትመች ህብረ ብሔራዊት አገር ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ በተባበረ አቅም ሲተጉ ይስተዋላል:: በአንጻሩ ላለፉት 27 ዓመታት በነበረው አገዛዝ ወቅት ህዝብ ይልቅ ለራሳቸው ጥቅምና ስልጣን ቅድሚያ ሰጥተው የሚኖሩ ኃይሎች ከለውጡ አጋዥነትና አባልነት ራሳቸውን ለማግለል ሲማስኑ መታዘብ ተችሏል:: ዛሬም ህዝብና አገር አንድም በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ እየተጨነቁ ባሉበት፤ ሁለተኛም ከህዳሴ ግድቡ ጋር በተያያዘ በአገር ሉዓላዊነት ላይ የተቃጣ አደጋ እያንዣበበ ባለበት ሁኔታ ላይ ከአገርና ህዝብ ይልቅ የራስን ጥቅምና ስልጣን ለማስቀደም አጥብቀው ሲጥሩ እየታየ ነው፡፡

ለዚህ ደግሞ ህወሓት አብይ ማሳያ ሲሆን፤ በዚህ ወቅት ከህዝብ ይልቅ ለራስ ጥቅምና ስልጣን ሲል የህዝብን ጤና አደጋ ላይ ጥሎ ምርጫ ላካሂድ ማለቱ የዚህ እማኝ ምግባሩ ማሳያ ነው:: አሁን ላይ ይህ ተግባሩ ጎልቶ ይውጣ እንጂ ላለፉት ሁለት ዓመታት በነበረው የለውጥ ጉዞ ውስጥ ከአጋዥነት ይልቅ የአደናቃፊነት ሚና እንደነበረው የሚታወቅ የአደባባይ ተግባሩ ነበር:: ለዚህ ተግባሩም ያግዙኛል ካልሆነም ልጠቀምባቸው እችላለሁ ብሎ ያሰባቸውን ኃይሎች መልምሎ በስልጣን ዘመኑ ከአገርና ህዝብ ጉሮሮ ነጥቆ ባካበተው ሀብት ለማጥመድ ሲሰራም ተስተውሏል:: ለዚህ ማሳያው ደግሞ የፌዴራሊስት ኃይሎች ጥምረት በሚል እንዲመሰረት በፋይናንስ ሲደግፈው የነበረው ስብስብ ነው፤ ይህ ስብስብ ግን የህወሓትን የሴራ ጉዞ በተረዳበት ወቅት የሀሳብ ልዩነት መፈጠሩ ተሰምቷል፡፡

እኛም በዛሬው እትማችን የዚህ ጥምረት ዓላማ ምን ነበር፤ የጥምረቱ ስብስብና የህወሃት የአጋርነት ጉዞ ምን ይመስላል፤ ዛሬ ላይ የጥምረቱና የህወሓት ትስስር በምን መልኩ ሊሻክር ቻለ፤ ጥምረቱ ዛሬ ላይ ያለውን የኢትዮጵያ ፖለቲካ እና መሆን ስላለባቸው ጉዳዮች እንዲሁም ተያያዥ ወቅታዊና አገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ የኢትዮጵያ ፌዴራሊስት ኃይሎች ጥምረት ሊቀመንበር፤ እንዲሁም የኦሮሞ ነጻነት ንቅናቄ ሊቀመንበር ከሆኑት አቶ ደረጀ በቀለ ጉደታ ጋር ያደረግነውን ሙሉ ቃለ ምልልስ ይዘን ቀርበናል፡፡

አዲስ ዘመን፡- የፌዴራሊስት ኃይሎች ማን ነው? የስብስቡ ዓላማስ ምንድን ነው?
አቶ ደረጀ፡- የፌዴራሊስት ኃይሎች ማለት በመጀመሪያ ከሁሉም የአገሪቱ አካባቢዎች የተሰባሰቡ 35 የፖለቲካ ፓርቲዎች ስብስብ ነው፤ አዲስ አበባን ጨምሮም ሶማሌን፣ አፋርን፣ ሐረሪን፣ ትግራይን፣ አማራን፣ ኦሮሞንና ሌሎችንም ብሄር ብሄረሰቦችን ያቀፈ እና ሁሉንም ኢትዮጵያውያን የዳሰሰ ነው:: በመጨረሻም ከእነዚህ 35 ፓርቲዎች ውስጥ ፍቃድ ለማግኘት ለምርጫ ቦርድ ያመለከትነው 25 ፓርቲዎች ናቸው:: ስለዚህ የፌዴራሊስት ኃይሎች ጥምረት ማለት የእነዚህ 25 ፓርቲዎች ስብስብ ነው፡፡ የመሰባሰባችን ዋና ዓላማ በሁሉም ክልሎች የሚገኙ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች በኢትዮጵያ አንድ አማራጭ የፖለቲካ ፓርቲ ለመሆን፤ ለዚህም በጋራ ለመንቀሳቀስና በጋራ ለመስራት ብሎም በጋራ ለመታገል እና ለአንድ የምርጫ ክልል ተጋግዞ ለመወዳደር ነው:: ከዚህ ባለፈም አንዱ የሚያውቀውን ለማያውቀው እንዲያስረዳ የተሰባሰበ ስብስብ ነው፡፡

አዲስ ዘመን፡- ጥምረት ምን መሰረታዊ አገራዊ አጀንዳዎችን ይዞ ነው የተሰባሰበው?
አቶ ደረጀ፡- ከአገራዊ አጀንዳዎቻችን መካከል የመጀመሪያው በአገራችን ኢትዮጵያ ሰላም፣ ፍትህ፣ ዴሞክራሲ እንዲሰፍን መስራት ነው:: ከዚህ ባለፈም በብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ከጭቆና ተላቅቀው ራሳቸውን በራሳቸው እንዲያስተዳድሩ ብሎም እንዲያለሙ ማስቻልን መሰረት ያደረገ ነው። ይህ ደግሞ እንደዚህ ቀደሙ አመራር ተልኮላቸው ወይም ተሰይሞላቸው ሳይሆን በራሳቸው እንዲሾሙ፤ በልማቱም ቢሆን በራሳቸው ሃብትና አቅም የሚለሙበትን እድል እንዲያገኙ ለማድረግ ነው::ለዚህ ደግሞ ሁሉም በራሱ ብሔርና ክልል የራሱን ፖለቲካዊ አጀንዳ መጫወት እንዲችል፤ ያንን ደግሞ በጋራ አምጥተን በአንድ ማዕከል በኢትዮጵያ ፌዴራሊስት ኃይሎች ጥምረት ስር ለማስተባበርና ለመምራት እንዲቻል ያለመም ነው፡፡

አዲስ ዘመን፡- ጥምረቱ አገራዊ ወይስ ክልላዊ ገጽታን የተላበሰ ነው? ምናልባት እንደ ዓላማውና አጀንዳዎቹ አገራዊ ከሆነ የፌዴራሉን መንግስት መቀመጫ አዲስ አበባን ትቶ መቐሌ ላይ ምስረታና ጉባኤውን ማካሄዱ ለምን አስፈለገ?

አቶ ደረጀ፡- ስብስቡ አገራዊውንም ክልላዊውንም ገጽታ የተላበሰ ነው:: ለምሳሌ፣ ሕወሃትን ጨምሮ የእኛም ፓርቲ የኦሮሞ ነጻነት ንቅናቄ ክልላዊ ፓርቲ ነው:: ሌሎች አዲስ አበባ ላይ መሰረታቸውን ያደረጉ አገራዊ ፓርቲዎችም አሉ:: ይህ የ25 ፓርቲዎች ተናጥላዊ ገጽታ ሲገለጽ ነው:: ነገርግን የእነዚህ ስብስብ የፈጠረው ጥምረት ግን አገራዊ ገጽታን ተላብሶ የሚንቀሳቀስ ነው:: ጥምረቱ ለምስረታውም ሆነ ለጉባኤው መቐሌን የመረጠበት ምክንያት ነበረው፡፡
ምክንያቱም እነዚህ ፓርቲዎች ራሱ ህወሓት ያጫቸው ናቸው:: የራሳቸው የሆነ ፋይናንስም የላቸውም:: ማናኛውም የፓርቲው አባል ራሱን ከማንቀሳቀስ በተረፈ ሌሎችንም ሆነ ህዝቦችን አንቀሳቅሶና አዳራሽም ተከራይቶ የአበልና ትራንስፖርትም ከፍሎ ማንቀሳቀስ የማይችሉበት ሁኔታ አለ:: ለዚህ የገንዘብ ፋይናንስ አቅም ያለው ህወሓት ነው:: ህወሓት ለትራንስፖርት፣ ለሆቴል፣ ለምግብ ሆነ ለሌሎች ሎጅስቲክ አገልግሎቶች የሚሆን አቅም ስላለውና እሱው ስለጠራን ነው እዛው ጀምረን፣ ሁለት ስብሰባዎችን መቐሌ ያካሄድነው:: መቐሌ መሰባሰብ ያስፈለገንና እዛው እንድናዘልቅም አስገዳጅ የሆነብን የፋይናንስ ምንጫችን ህወሓት ስለሆነ ነው፡፡
ይህ ደግሞ የአባላቱ የፋይናንስ አቅም ማጣት ውጤት ሲሆን፤ እኛ ወደመቐሌ ስንሄድ የአውሮፕላን ትኬት ተልኮልን፣ ሆቴል ተይዞልን፣ ሌሎችም አስፈላጊ ወጪዎች ተሸፍነውልን ነው:: በዚህም ጅግጅጋም፣ አዲስ አበባም፣ አፋርም፣ ድሬዳዋም፣ ሐዋሳም፣ ወላይታም፣ ጅማም ሆነ ሌሎች ቦታዎች ላሉ ሁሉ የአውሮፕላን ትኬት ባሉበት እየተላከ፤ ሁሉንም ወደ መቐሌ በመውሰድና ወጪያቸውን በመሸፈን ነው ስብሰባው የሚካሄደው:: በዚህ መልኩ የሁሉንም ፓርቲዎች አበል፣ ትራንስፖርት፣ ሆቴል፣ ምግብና ሌሎችን ወጪዎች የሚሸፍነው ህወሓት ነው፤ እርሱ ሁሉም ነገር መቐሌ እንዲካሄድ ስለሚፈልግ ነው መቐሌ ላይየሆነው፡፡

አዲስ ዘመን፡- በዚህ መልኩ ተሰባስባችሁ ጥምረት ፈጥራችሁ ስትሰሩ የጋራ የሆነ መተዳደሪያ ደንብና ሌሎች የፓርቲ ሰነዶች ነበሯችሁ? በዛ መሰረትስ በምን መልኩ ትሰሩ ነበር?
አቶ ደረጀ፡- የጋራ የሆነ መመሪያ፣ ደንብና ማኒፌስቶ አለን:: ፍቃድ እንዲሰጠን ለብሔራዊ ምርጫ ቦርድም ያቀረብነው ሁሉንም ነገር አሟልተን ነው:: ይሄንንም በስብስቡ ስም አደራጅተንና በዛ ላይም ተወያይተን አጽድቀንም ነው:: እያንዳንዱ ፓርቲ በራሱ ማህተምና በራሱ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አጽድቆም ነው ያቀረብነው:: ምርጫ ቦርድም ጥያቄያችንን ተቀብሎና የሚመረምረውን መርምሮኖ በ25ቱ ፓርቲዎች አማካኝነት መመስረት እንደሚቻል ባቀረበው ግብረ መልስ መሰረት እኛም መልስ ሰጥተን ፈቃዱን እየተጠባበቅን ባለንበት ወቅት ነው የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ መጥቶ ሂደቱን ተጓተተብን:: ወደ ጉዳዩ ስመለስ ግን እንደ ስብስብ የምንሰራውም ሆነ የምንመራው በእነዚህ ሰነዶች መሰረት ነው፡፡

አዲስ ዘመን፡- በዚህ መልኩ በሰነዶች ታግዛችሁ የምትሰሩ ከሆነ መቐሌ ካለው የህወሓት ስብስብ ጋር ያላችሁ አጋርነት በምን መልኩ የሚገለጽ ነው? በዚህ ትብብርስ ምን ያክል ተጉዛችኋል?
አቶ ደረጀ፡- መቐሌ ካለው የህወሓት ስብስብ ጋር ያለን አጋርነት በፋይናንስ ነው:: ሌላ ነገር የለም:: ህወሓት አዳራሽ ይከራይልናል፤ የምግብ፣ ትራንስፖርትና አበል ይችለናል:: ከዚህ ውጪ ሚስጢራቸውን ለእኛ በተለይም ከመሀል አገር፣ ከወደ ምስራቅ እና ከምዕራብም ለሄዱት በግልጽ አያስቀምጡም:: እናም የእነርሱ አጋርነት በፋይናንስ ረገድ ነው:: እስካሁንም የቆየነው በፋይናንስ አጋርነታቸው ነው፡፡

አዲስ ዘመን፡- ከፋይናንሱ ባለፈ ወደ መቀሌ ስትሄዱ ዓላማና አጀንዳ አድርጋችሁ በሄዳችሁባቸው ጉዳዮች ላይ ያላችሁ አጋርነትስ እስከምን ድረስ ነው?
አቶ ደረጀ፡- ለጋራ ግብ ብለን የሄድነው፣ እኛ እንግዲህ መጀመሪያ እንደጠቀስኩት በአገራችን ሰላም፣ ልማትና ዴሞክራሲን ለማምጣት፤ ህዝቦች ራሳቸውን በራሳቸው እንዲያስተዳድሩ ማስቻልን እቅድ በማድረግ ነበር:: ይሁን እንጂ የህወሓት ፍላጎት የጋራ ዓላማችንን ሳይሆን የራሱን ዓላማ በእኛ ላይ ለመጫን ነው የሚፈልገው:: ብዙውን ጊዜ እኛ የምንቀርጸውን አጀንዳ አይቀበልም ነበረ:: የራሱን አጀንዳ ያቀርባል፤ የእኛን አጀንዳ ደግሞ በሚቀጥለው እንወያይበታለን ይላል:: በዚህ መልኩ የራሱን እያስቀደመ የእኛን እያሳደረ ከመሄድ በዘለለ፤ የእኛን ለመቀበል አይፈልግም:: የራሱን አጀንዳ ግን እኛ ላይ ለመጫን ይጣጣራል፡፡

አዲስ ዘመን፡- ይህ ማለት በአብሮነት ጉዟችሁ እናንተ እንደ ግለሰብም ሆነ እንደ ፓርቲ ሀሳብን በነጻነት አቅርቦና አንሸራሽሮ የጋራ የማድረግ መብትና ነጻነት የላችሁም፤ በአንጻሩ የህወሓት የበላይነትና ፈላጭ ቆራጭነት ነግሶ የራሱን ዓላማ እንዲፈጸምለት የመስራት አካሄድ የነበረበት ነው እያሉኝ ነው?
አቶ ደረጀ፡- እንደዛ ነው:: ምክንያቱም አንደኛ፣በፋይናንስም እስከረዳን፤ ሆቴልም እስከተከራየልን እና ትራንስፖርትም እስከቻለን ድረስ እርሱ በሁለት በሶስትና አራት አባላት ድረስ እየተሳተፈ እኛን አንዳንድ (በሊቀመንበር ወይም በምክትል ሊቀመንበር ወይም በዋና ፀሐፊ) እንድንሳተፍ በማድረግ ብዙውን ነገር የሚያንቀሳቅሰው በራሱ ነው:: በስራ አስፈጻሚ ደረጃ መድቦ ነው የሚያንቀሳቅሰው፤ የህወሓት ሊቀመንበርም ራሳቸው ሰብስበው እንዲህ ነው፣ እንዲህ ነው የሚሉበት ወቅትም ነበረ:: እናም ብዙውን ጊዜ የእነርሱን አመለካከትና ሀሳብ እኛ ላይ ለመጫን ነው የሚንቀሳቀሱት:: አጋርነቱንም የሚፈልጉት ለዚሁ ነበር፡፡

አዲስ ዘመን፡- አሁን ባለው ሂደት በመካከላችሁ ልዩነት መፈጠሩ አደባባይ የወጣ ጉዳይ ነው:: ልዩነቱ እንዲፈጠር ያደረገው መሰረታዊ ምክንያት ምንድን ነው?
አቶ ደረጀ፡- የልዩነታችን ምንጭ ህወሓቶች የሚፈልጉት የፌዴራሊስት ኃይሎች ሁል ጊዜ መቐሌ ላይ እንዲሰባሰቡ ነው:: እኛ ደግሞ በሁለተኛው የመቐሌ ስብሰባችን ላይ የወሰንነው በሚቀጥለው ጽህፈት ቤትም አዲስ አበባ ወይም ማዕከል ላይ ለመክፈት፤ መደበኛ ስብሰባችንንም ማዕከል ላይ ለማካሄድ ነው:: አሁን እኛ ሶስተኛ መደበኛ ስብሰባውን እዚህ ፋይናንስ ስጡንና እንቀሳቀስ ስንል ፋይናንሱንም ዝም አሉን:: ቢሮ መክፈትም ከተማውን ሙሉ በሙሉ ዞረናል፤ ሆኖም በተለያየ ምክንያት በዛ አነሰ በሚል ሰበብ እስካሁን ቢሮውንም አልከፈትንም፡፡
በዚህ ምክንያት ብዙ መራራቆች እየተፈጠሩ መጡ:: ይሄን ተከትሎም በህወሓት በኩል ሰዎችንና ፓርቲዎችን መለያየት መጣ:: ፓርቲዎችን በመለያየት ሂደትም መጀመሪያ አቅፈው የያዙትና ገንዘብም ሊሰጡ የፈለጉት ከትግራይ የተወከሉትን የፓርቲ አባላት ነው:: ቀጥሎ ደግሞ ከአዲስ አበባ የተወከሉ አንዳንድ ፓርቲዎችን አቅፈው ለመያዝ ሞከሩ:: ከኦሮሞ ያሉት በፊቱንም እየተንጠባጠበ ወደ ስድስት የማንሞላ ብቻ ቀርተን ስለነበረ እነዚህንም ለመበታተን በእኔ ላይ ጫና ለመፍጠር ሞከሩ:: ይህ ደግሞ እኔ ሰብሳቢ ስለሆንኩ ሲሆን፤ ስብሰባው መቐሌ ካልሆነ በስተቀር አዲስ አበባ ላይ ጽህፈት ቤትም ሆነ ስብሰባም አይቻልም በሚል ነበር፡፡
ይህ ደግሞ የማይሆን ነበር:: ምክንያቱም ለምሳሌ፣ እኔ መኖሪያዬ አዲስ አበባ ነው፤ የወከልኩትም የኦሮሞን ህዝብ ነው:: ስለዚህ መቐሌ መኖርም ሆነ በመቐሌ ስብሰባ ማካሄድ አልችልም:: ሌሎቹም በተመሳሳይ የየክልላቸውን ህዝብ ወክለው ያሉ እንደመሆኑ መቀመጫቸውን መቐሌ ሳይሆን አዲስ አበባ ማድረግ የሚፈልጉ በመሆኑ ማዕከሉ አዲስ አበባ እንዲሆን ነው የሚፈልጉት:: በመሆኑም የነበረው አቋም ማዕከሉ አዲስ አበባ ሆኖ ስብሰባውም አዲስ አበባ ይሁን፤ ስብሰባውን በዙር ክልል ላይ የሚደረግ ከሆነም መቐሌ ብቻ ሳይሆን፡ ሀዋሳም፣ ሰመራም፣ ጅግጅጋም፣ በህር ዳር እና ሐረርም እያልን ማካሄድ አለብን የሚል ነው፡፡
ለዚህ ደግሞ እንደ ፌዴራሊስት ኃይሎች ጥምረት እናንተ (ህወሓቶችን) አንድ ፓርቲ ናችሁ፤ ሆኖም ለምሳሌ፣ ከሶማሌ ሶስት ፓርቲ አለ፣ አፋር ወደ ሁለት አሉ፣ ከኦሮሚያ ወደ ስድስት አሉ፣ እናም ማዕከላችንን አዲስ አበባ ካላደረግን እኔ ወደዛ አልመጣም በሚል የሀሳብ ልዩነት ተፈጠረ:: እኛም ይሄን መሰረት አድርገን ከባለሃብቶች ገንዘብ አግኝተን ስብሰባ አዲስ አበባ ስንጠራ ነው የበለጠ ልዩነቱ ሊፈጠር የቻለው፡፡

አዲስ ዘመን፡- ህወሓቶች ከመቐሌ ውጪ በአዲስ አበባ ጽህፈት ቤት እንዳይከፈትም ሆነ ስብሰባ እንዳይካሄድ ያልፈለጉበትን ምክንያት ጠይቃችኋቸዋል? ምክንያታቸው ምንድን ነበር?
አቶ ደረጀ፡- በምክንያትነት የሚያቀርቡት ነገር የለም:: ከእነርሱ አኳያ እንዲሁ እንደተረዳሁት ከሆነ ግን ፍርሀት ነው:: ለምሳሌ፣ እኛ ይሄ ጥምረት በፓርቲ ሊቀመናብርት መመራት አለበት ነው የምንለው:: ስብሰባ ሲኖር ደግሞ ከሊቀመናብርት ባለፈ ከአባላትም እስከ ስራ አስፈጻሚ ድረስ የሚሰበሰቡበት ጊዜ አለ:: በስራ አስፈጻሚ ሲሰበሰቡ ደግሞ ዶክተር ደብረጽዮንን ጨምሮ እዛ ያሉት ሁሉም ናቸው መሰብሰብ ያለባቸው:: ጽሕፈት ቤቱ እዚህ ከሆነም ሊቀመንበሩ ናቸው እዚህ መሳተፍ ያለባቸው::

አዲስ ዘመን፡- ከፋይናንሱ ባለፈ ወደ መቀሌ ስትሄዱ ዓላማና አጀንዳ አድርጋችሁ በሄዳችሁባቸው ጉዳዮች ላይ ያላችሁ አጋርነትስ እስከምን ድረስ ነው?
አቶ ደረጀ፡- ለጋራ ግብ ብለን የሄድነው፣ እኛ እንግዲህ መጀመሪያ እንደጠቀስኩት በአገራችን ሰላም፣ ልማትና ዴሞክራሲን ለማምጣት፤ ህዝቦች ራሳቸውን በራሳቸው እንዲያስተዳድሩ ማስቻልን እቅድ በማድረግ ነበር:: ይሁን እንጂ የህወሓት ፍላጎት የጋራ ዓላማችንን ሳይሆን የራሱን ዓላማ በእኛ ላይ ለመጫን ነው የሚፈልገው:: ብዙውን ጊዜ እኛ የምንቀርጸውን አጀንዳ አይቀበልም ነበረ:: የራሱን አጀንዳ ያቀርባል፤ የእኛን አጀንዳ ደግሞ በሚቀጥለው እንወያይበታለን ይላል:: በዚህ መልኩ የራሱን እያስቀደመ የእኛን እያሳደረ ከመሄድ በዘለለ፤ የእኛን ለመቀበል አይፈልግም:: የራሱን አጀንዳ ግን እኛ ላይ ለመጫን ይጣጣራል፡፡

አዲስ ዘመን፡- ይህ ማለት በአብሮነት ጉዟችሁ እናንተ እንደ ግለሰብም ሆነ እንደ ፓርቲ ሀሳብን በነጻነት አቅርቦና አንሸራሽሮ የጋራ የማድረግ መብትና ነጻነት የላችሁም፤ በአንጻሩ የህወሓት የበላይነትና ፈላጭ ቆራጭነት ነግሶ የራሱን ዓላማ እንዲፈጸምለት የመስራት አካሄድ የነበረበት ነው እያሉኝ ነው?
አቶ ደረጀ፡- እንደዛ ነው:: ምክንያቱም አንደኛ፣ በፋይናንስም እስከረዳን፤ ሆቴልም እስከተከራየልን እና ትራንስፖርትም እስከቻለን ድረስ እርሱ በሁለት በሶስትና አራት አባላት ድረስ እየተሳተፈ እኛን አንዳንድ (በሊቀመንበር ወይም በምክትል ሊቀመንበር ወይም በዋና ፀሐፊ) እንድንሳተፍ በማድረግ ብዙውን ነገር የሚያንቀሳቅሰው በራሱ ነው:: በስራ አስፈጻሚ ደረጃ መድቦ ነው የሚያንቀሳቅሰው፤ የህወሓት ሊቀመንበርም ራሳቸው ሰብስበው እንዲህ ነው፣ እንዲህ ነው የሚሉበት ወቅትም ነበረ:: እናም ብዙውን ጊዜ የእነርሱን አመለካከትና ሀሳብ እኛ ላይ ለመጫን ነው የሚንቀሳቀሱት:: አጋርነቱንም የሚፈልጉት ለዚሁ ነበር፡፡

አዲስ ዘመን፡- አሁን ባለው ሂደት በመካከላችሁ ልዩነት መፈጠሩ አደባባይ የወጣ ጉዳይ ነው:: ልዩነቱ እንዲፈጠር ያደረገው መሰረታዊ ምክንያት ምንድን ነው?
አቶ ደረጀ፡- የልዩነታችን ምንጭ ህወሓቶች የሚፈልጉት የፌዴራሊስት ኃይሎች ሁል ጊዜ መቐሌ ላይ እንዲሰባሰቡ ነው:: እኛደግሞ በሁለተኛው የመቐሌ ስብሰባችን ላይ የወሰንነው በሚቀጥለው ጽህፈት ቤትም አዲስ አበባ ወይም ማዕከል ላይ ለመክፈት፤ መደበኛ ስብሰባችንንም ማዕከል ላይ ለማካሄድ ነው:: አሁን እኛ ሶስተኛ መደበኛ ስብሰባውን እዚህ ፋይናንስ ስጡን [ አዲስ ዘመን እሁድ ግንቦት 16 ቀን 2012 ዓ.ም ገጽ 13] እንዳልፈለጉ እኛ አናውቅም:: ነገር ግን ስብሰባም ሆነ ዋና ጽህፈት ቤት አዲስ አበባ መሆን የለበትም፤ መቐሌ መሆን አለበት የሚል አቋም አላቸው፡፡

https://vdocuments.mx/-oe-oe-f-oe-aa.html
eden wrote:
31 Oct 2020, 09:27
Hey guys

Need your input for my new research.

Here's a question for you to reflect on and answer.

If TPLF changes its long standing position and rejects nation & nationalities based organization in Ethiopia, will this change your heart and mind on whether you oppose or support and how intensely you oppose or support it?

Would and should Abiy and Isayas work with TPLF if TPLF renounces nation & nationalities based organization?



.
Last edited by YAY on 01 Nov 2020, 00:37, edited 2 times in total.

YAY
Member
Posts: 943
Joined: 21 Aug 2013, 11:51

Re: Your opinion is needed here please

Post by YAY » 31 Oct 2020, 23:49

Dear Eden: You may consider this as background knowledge for your research

Any improvement displayed by the MLLT/TPLF (Tigraiy People's Liberation Front) might appear to be better than never, but the issues that cause problems to Etiyopiya and Eritrea are more than just the case of a federal State structure based on nations and nationalities. The fundamental problem with MLLT/TPLF leaders is the fact that they are not true to themselves and others. Do you know how one could tell when they are lying? When they open their mouths to talk. Deception seems to be their over-arching modus operandi (i.e. their established way of doing things). Read the following interview (part 2) carefully as well as patiently.

አዲስ ዘመን፡- በ35 የጀመረው ስብስብ በ25 ጸንቶ ጥምረቱን መፍጠሩ ይታወቃል:: ሆኖም በተፈጠረው የሀሳብ ልዩነት አሁን ላይ እናንተ ወደ አዲስ አበባ ስትመጡ የተወሰኑት ከህወሓት ጋር መሆናቸው ታውቋል:: ይሄን በቁጥር ቢገልጹልን? በጥምረቱ አባላት መካከል ይሄን መሰል መከፋፈል የተፈጠረበትን ምክንያትም ቢያስረዱ?
አቶ ደረጀ፡- የጥምረቱ 25 አባል ፓርቲዎች ያቀረብነውን ጥያቄ ተከትሎ ምርጫ ቦርድ ህጋዊ መሆናቸውን አረጋግጦ በደብዳቤ ያሳወቃቸው ናቸው:: ከእነዚህ 25 ውስጥ ደግሞ አዲስ አበባ የተሰባሰብነው 18 ፓርቲዎች ነን:: ህወሓትን ጨምሮ ሰባቱ መቐሌ የቀሩ ናቸው:: በመሆኑም 18ቱ ፓርቲዎች ከፌዴራሊስት ኃይሉ ጋር እየተንቀሳቀሱ ያሉ ናቸው:: ለዚህ መከፋፈል ያበቃው ደግሞ ሌላ ምንም የሚጠቀስ መሰረታዊ ጉዳይ የለም:: ዋናው ጉዳይ መቐሌ ካልሆነ የሚለው የህወሓት ምክንያት አልባ ሴራ ነው:: እኛ ደግሞ ማዕከሉ አዲስ አበባ ይሁን የምንል ሃይሎች ነን፡፡
ስብሰባው አዲስ አበባ እንዳይካሄድና መቐሌ እንዲካሄድ ደግሞ ህወሓት ለእኔም ጭምር እዚህ ድረስ የአውሮፕላን ትኬት ልኳል:: አልጋ የት እንደተያዘልኝም ተነግሮኛል:: ሆኖም ልዩነቱ የተፈጠረው በዋናነት መቐሌ በመሄድና አዲስ አበባ በመሄድ ነው:: በዚህም 18ታችን እዛ ላለመሄድ በመወሰን አዲስ አበባ ቀርተናል:: እንደሰማሁት ከሆነ ህወሓት የተቀሩትን የራሱ አጋር እንዳደረጋቸው ሲሆን፤ እኛ ወደ አዲስ አበባ አንመጣም የሚል አቅጣጫ ይዘዋል፡፡
እነዚህ ፓርቲዎች ደግሞ በፊትም የሚንቀሳቀሱት በትግራይ አካባቢ ሲሆን፤ የተወሰኑት ደግሞ በአዲስ አበባ ነበር:: በመሆኑም እዛ የቀሩት የትግራይ እና የአዲስ አበባ ፓርቲዎች ሲሆኑ፤ ከእነዚህ ውስጥ ከህወሓት ጋር ሶስቱ የትግራይ እና በልጅ መስፍን የሚመራውን ፓርቲ ጨምሮ ከአዲስ አበባ ያሉ ናቸው:: ከእነዚህ ውጪ ሌሎች የሶማሌ፣ የአፋር፣ የሐረሪ፣ የኦሮሚያ፣ የደቡብና ሌሎችም ክልሎችን የወከሉ ፓርቲዎች በሙሉ እዚሁ አዲስ አበባ ላይ ነው ያሉት፡፡

አዲስ ዘመን፡- ከሰሞኑ አዲስ አበባ ላይ ያካሄዳችሁት ስብሰባ ዓላማው ምንድን ነው? ምንን መሰረት ያደረገስ ነው?
አቶ ደረጀ፡- ስብሰባው ግልጽ ነው:: ለእነሱም ነግረናል:: ይሄ የተለየ ፖለቲካዊ አጀንዳ የያዘ አይደለም:: የስብሰባው ዓላማም ሆነ መሰረት አንድምጥምረቱ ጽህፈት ቤቱንም ሆነ ስብሰባውን አዲስ አበባ ላይ ለማድረግ መወሰኑን ለመግለጽ ነው። ከዚህ ባለፈ ደግሞ አገራዊ ጉዳዮች እንዲሁም ምርጫውን ተከትሎ ህወሓት የያዘው የብቻ ውሳኔ ላይ ያለንን አቋም ማሳወቅ ነው:: ከአገራዊ ጉዳዮች መካከል አንዱ ስለ ኮቪድ 19 ወረርሺኝ ጉዳይ ሲሆን፤ በዚህም ህዝባችን ከዚህ ወረርሽኝ መጠንቀቅ እንዳለበት እና እኛም እንደ ፓርቲም ሆነ እንደ ጥምረት ጉዳዩ ስለሚመለከተን ህዝባችን ከዚህ እንዴት መጠንቀቅ እንዳለበት የራሳችንን መግለጫ መስጠት/ለማውጣት ነው፡፡

ሁለተኛው ጉዳይ፣ የ2012ቱን አገራዊ ምርጫ የተመለከተ ሲሆን፤ በዚህን ጊዜ ሰው ተራርቆ በሚንቀሳቀስበት፣ ተራርቆ በሚበላበት፣ ከቤት በማይወጣበትና ፍርሃት ባለበት ሰዓት ምርጫ ማካሄዱ አግባብ አይደለም የሚለውን አቋማችንን ያሰማንበትን ዓላማ መሰረት ያደረገ ነው:: ሶስተኛም፣ እኛ ከገዢው ፓርቲ ጋር መደጋገፍም ሆነ ተቃውሞ ቢኖረንም በአገር ጉዳይ አንድ መሆናችን ለመግለጽ ነው። በዚህም የህዳሴ ግድቡ የሁላችንም ጉዳይና ፕሮጀክት እንደመሆኑ ይሄንን የሚመለከቱ ማናቸውንም ጉዳዮች ብሎም ከውጪ የሚመጡ ተቃውሞዎችን ከመንግስት ጎን ሆነን ለመከላከል ያለንን አቋም ለመግለጽ ነው፡፡ በግድቡ ላይ የሚቃጡ ማናቸውንም ነገሮች ከመንግስት ጎን ሆነን አብረን መከላከል አለብን እንጂ መቃወም የለብንም፤ ግንባታውም ለአንዲት ደቂቃም ቢሆን መቋረጥ የለበትም:: ለምን ቢባል፣ ግድቡ የእናቶች፣ የወጣቶች፣ የአዛውንቶች በጥቅሉ የሁሉም ኢትዮጵያውያን ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች አሻራ እና ላብ እስከሆነ ድረስ ጉዳዩ የፖለቲካ ፓርቲ ጉዳይ ሳይሆን የአገርና ህዝብ ህልውና ጉዳይ በመሆኑ ነው:: እኛም ይሄንን አቋም ነው ያራመድነው፡፡

ከዚህ ውስጥ ግን ህወሓት ምርጫውን አካሂዳለሁ አለ:: ያንን ምርጫ ለማካሄድ ግን እንደ ስብስብ ኃይሉ የጋራ ስምምነት እኛን ማሳወቅ አለበት:: ምክንያቱም እኛ ልናውቅ እና ወይ ልንቃወም ወይም ልንደግፍ ይገባል:: የጋራ ጥምረት እንደመሆኑ በጋራ ነው ወስነን መሄድ የነበረብን፤ በጋር የተመሰረተ ጥምረት እንደመሆኑም መግለጫውን መስጠት የነበረብን በጋራ ነው:: ሆኖም ወደ 20 የሚሆኑት የጥምረቱ አባላት ምርጫውን አናካሂድም እያሉ ባለበት ሁኔታ ህወሓት ለብቻው ይሄን ውሳኔ ማሳለፉ ተገቢም ትክክልም አይደለም፡፡

ምክንያቱም ሰው ሊመርጠን የሚችለው ሰላምና ጤነኛ ሆኖ ሲኖር ነው:: አገርም ተማምኖ መሄድ ሲችል ነው::ካልሆነ በጀብደኝነት ተነስቼ ምርጫ ላካሂድ ብል አያዋጣም:: እኛም ይሄን ስለምንገነዘብ ለምን እኛን ሳታማክሩ መግለጫ ሰጣችሁ ብለንም ጠይቀናል:: ሆኖም ይህ የግሌ ነው፣ በዚህ ጉዳይ ላይ አይመለከታችሁም የሚል ሀሳብ ይዞ ነው የመጣው:: እኛም በበኩላችን የስብስቡ አባል እስከሆናችሁና የጋራ ስምምነት እስካለ ድረስ መፈጸም ያለበት በጋራ እንጂ በአንድ ፓርቲ የግል ፍላጎት አይደለም፤ አካሄዱም
አንድነት አያመጣም፤ ምክንያቱም፣ ሶማሌው ለብቻ አንድ ሲል፣ አፋሩም ሌላ ሲል፣ ኦሮሞውም ለብቻው ሌላ ሲል ነገሮች ልክ አይመጡምና ምርጫውን ማካሄድ አትችሉም በማለታችን በመካከል ጭቅጭቅ ነበር:: የአዲስ አበባውስብሰባ መሰረትና አንዱ ዓላማ በዚህ መልኩ ከጥምረቱ አቋም ውጪ ህወሓት ምርጫ አካሂዳለሁ ብሎ የወሰነው ግላዊ ውሳኔ ተገቢም ትክክልም አለመሆኑን ለመግለጽ ነው::ን

አዲስ ዘመን፡- በዚህ ሁሉ ሂደት ውስት ከህወሓት ጋር በጥምረት በቆያችሁባቸው ጊዜያት ቀደም ሲል ከውጭ ስትሰሙትና ስትገምቱት ከነበረው አንጻር ስለ ህወሃት ባህሪና እውነተኛ ማንነት ምን የተለየ ነገር ተገነዘባችሁ?
አቶ ደረጀ፡- እውነት ለመናገር፣ ከህወሓት የተረዳነው ባህሪ አንዱ፣ ህወሓት ማለት የተወሰኑ ቡድኖች ናቸው::የተወሰኑ ቡድኖች ብዬ ስል የትግራይ ህዝብ ወይም በትግራይ ክልል የሚገኙ ወጣቶች፣ አዛውንቶች፣ ተማሪውም ሆነ ሌላው የህብረተሰብ ክፍልን ስታይ ህወሓት በከተማ ውስጥ እንጂ በገጠር የለም:: ይሄንንም ከመቐሌ እስከ ደደቢት እና ዛላንበሳን ጨምሮ ሌሎችም የትግራይ ክልል ክፍሎችን ባስጎበኙኝ ወቅት ተመልክቼ ተገንዝቤያለሁ:: በእነዚህ የክልሉ ዞኖችና ወረዳዎች በነበረኝ ጉብኝት ተመለከትኩት
እና አንዳንዴም አማርኛ የሚናገሩ/የሚችሉ ሰዎችን አነጋግሬ እንደተረዳሁት፤ ህወሓት ከህዝቡ ጋር የለም:: ምናልባት የተወሰነ ህዝብ ነው ከህወሓት ጋር ያለው፡፡

ይሄ የተወሰነ ህዝብ ደግሞ በመቐሌ ከተማ እና ዙሪያዋ ያሉ ጥቂት ሰዎችን የሚመለከት ሲሆን፤ ሌላው ቀርቶ ወደ አድዋና አክሱም ስንሄድ እውነት ለመናገር ህዝቡ የሚያሳዝን ህዝብ ነው:: ምክንያቱም ሰፊው የትግራይ ህዝብ አንደኛ፣ በአሁን ጊዜ በዚህ ዘመን ለእግሩ እንኳን ጫማ የሌለው ህዝብ ነው:: ልብስ በረከሰበት በዚህ ወቅት ልብስ እንኳን መልበስ ያልቻለ ህዝብ ነው:: ይህ ደግሞ ጥቂት የህወሓት አመራሮችና አባላት ገንዘቡንም ለራሳቸው፤ አገሩንም የራሳቸው አድርገው እንደያዙት የሚያሳይ ነው፡፡

እንዳየሁት ከሆነ ህዝቡ መፈናፈኛ ስላጣ ነው ዝም ያለው:: ለዚህ ደግሞ ወደ ዛላንበሳ በሄድኩበት ወቅት ያነጋገርኳቸው አንድ አዛውንት ያጫወቱኝ ትልቅ አብነት ነው:: እኚህ አዛውንት እንዳጫወቱኝ፣ እዚሁ ተወልጄ የኖርኩ ነኝ፤ ነገር ግን ስርኣቱ ወይም የህወሓት አስተዳደር ለእኔም ሆነ ለአካባቢው ምንም ያደረገው ነገር ስለሌለ አብዛኛው በችግር ውስጥ ያለ፤ በእድሜ መግፋት ምክንያት ከቤት የማትወጣው ባለቤቴም ሆነች እኔም በቤተ ክርስቲያን እርዳታ ኑሮዬን እየገፋሁ የምንኖር ህዝቦች ነን ነበር ያሉኝ:: በህወሓት አገዛዝ ምክንያትም በርካታ ወጣቶች ከአገር ለመውጣትና ለመሰደድ ስለመብቃታቸውም ነው ያጫወቱኝ፡፡

ይሄን ከመስማቴና ክልሉን በተለይ ገጠራማውን አካባቢ ከመመልከቴ በፊት፤ እኔም የነበረኝ ግንዛቤ የትግራይ ህዝብ ከሌሎች ህዝቦች በተለየ መልኩ እንደተጠቀመ፤ የትግራይ ህዝብ ከህወሓት ብዙ ነገር እንዳገኘ ነበር:: እንደኔ ሁሉ ሌሎችም እንዲሁ ሊያስቡ ይችላሉ:: እውነቱ ግን ይሄ አይደለም፤ የትግራይ ህዝብ ጭቆና ውስጥ ነው ያለው:: የትግራይ ህዝብ በኢኮኖሚው አሁንም ወደኋላ የቀረ ነው:: የኢኮኖሚው ችግር ደግሞ ከምግብ እስከ አልባሳት በሚፈልገው ልክ እንዳያገኝ ያገደው ህዝብ ነው:: መቐሌን ጨምሮም በየከተማው ያለ ወጣትም መስራት በሚችልበት እድሜውና ሰዓቱ ያለስራ ከጠዋት እስከ ማታ በየበረንዳውና በየመንገዱ ላይ ባሉ የጀበና ቡናዎች ወንበር ላይ ተቀምጦ ዳማ እና ካርታ ሲጫወት የሚውልበትን እውነት ተመልክቻለሁ:: ከዚህ በተቃራኒው ግን ጥቂት የህወሓት አባላትና ወደ ህወሓት የሚጠጉ ሰዎች ግን የናጠጠ ኑሮ ይኖራሉ፡፡

ስለዚህ ህወሓት አንድ ነን እንደሚለው፤ ህወሓትንና የትግራይ ህዝብን በአንድ ላይ ማየት የተሳሳተ መሆኑን ተገንዝቤያለሁ:: ምክንያቱም፣ ከዚህ በፊት ከአመራሮቹ ስንሰማ እና እኔም ትግራይ ስሄድ የመጀመሪያዬ እንደመሆኑ፤ የትግራይ ህዝብና ህወሓት አንድ ናቸው ብዬ ነበር የምወስደው:: አሁን ውስጡ ገብቼ ባየሁት መሰረት ግን በጣም የተራራቁ ናቸው:: ህዝቡ ከእጅ ወደ አፍ በሆኑ ኑሮ ውስጥ ነው ያለው:: ጥቂት የህወሓት አመራሮችና እነርሱን ተጠግተው ያሉት ግን በጣሙን ከህዝቡ የራቀና ሊነጻጸርም በማይችል የናጠጠ ኖሮ ውስጥ ነው ያሉት:: በትላልቅ ሆቴሎች ነው የሚዝናኑት:: ህዝቡ ግን አሁንም ጭንቀት ውስጥ ነው ያለው:: በመሆኑም የህወሓት ጥቂት ቡድኖች እንደሚሉት ህዝቡን እና ህወሓትን አንድ ላይ ጨፍልቆ ማየቱ ተገቢ አለመሆኑን፤ እነዚህ ጥቂት የህወሓት አመራሮች የሚሉትም በጣሙን የተሳሳተ መሆኑን ተገንዝቤያለሁ:: እኔም ትግሬ ሁሉ የተጠቀመ፤ ትግሬ ሁሉ የህወሃት አባል የሆነ አድርጌ ሳይ የነበረበት ሁነት የተሳሳተ መሆኑን አይቼ በመገንዘብ፤ ይሄን ምስል ያስያዘኝ የህወሓት አሳሳች የሴራ ምስል መሆኑን በተግባር አረጋግጫለሁ፡፡

አዲስ ዘመን፡- ከፌዴራሊዝም አንጻር እርሶ ስለ ፌዴራሊዝም ካለዎት ግንዛቤ በመነሳት እንዲሁም ህወሓት በቃል ከሚናገርለት ፌዴራሊዝምና የፌዴራሊዝም ጠበቃነት አኳያ፤ በጥምረት አብረው በቆዩበት ጊዜ በህወሓት ቤት ፌዴራሊዝም በቃል እና በተግባር እንዴት የሚገለጹ ሆነው አገኟቸው?
አቶ ደረጀ፡- ፌዴራሊዝም እኮ የእኩል አስተዳደር ነው:: ፌዴራሊዝም ስንልም የጋራ አስተዳደር ማለታችንም ነው:: ህወሓት ግን የእኩል አስተዳደር ብሎ ነገር የለውም::ህወሓት የበላይነቱን ለማንጸባረቅ ብቻ የሚንቀሳቀስ ቡድን ነው:: የህወሓት አመራሮች ቦረና ያለውን ከብት አርቢ ነው፤ ሶማሌ ያለውን እንዲህ ነው እያሉ ከመናገር ውጪ፤ ቦረና ያለውም ራሱን ለማስተዳደር ይችላል፤ ሶማሌ ያለውም ራሱን ለማስተዳደር ይችላል፤ እንዲሁም የአካባቢውን ልማት መምራት ይችላል ብሎ የሚያስብ ቡድን አይደለም:: የራሱን የበላይነት ብቻ ለማንጸባረቅ የሚንቀሳቀስ ቡድን ነው:: ይሄን የበላይነቱን ለማረጋገጥም በየቦታው የራሱን የስለላ መረብ በመዘርጋት የሚሰራ ቡድን ነው፡፡
ፌዴራሊዝም ማለትኮ የመጀመሪያው ጉዳይ ራስን ማስተዳደር ነው:: በራስ መዳኘት ነው:: በራስ ቋንቋ መማር ነው:: ህወሓት ግን ያንን ለይምሰል ይናገር እንጂ ውስጥ ገብተን ስናየው የራስን በራስ የማስተዳደር መብትን የሚጨፈልቅ ቡድን ነው:: ይሄንን መብት ጨፍልቆም እሱ እንዴት መግዛት እንደሚችል የሚያስችለውን የወጥመድ መረብ የሚዘረጋ ነው:: ለዚህ ደግሞ በስለላ መረብ በጣሙን የተሳሰረ ነው:: በሆቴልም ሆነ በየትም ያለ ሰራተኛን በዚህ መረብ ውስጥ በማስገባት የስለላ መረቡ አባል አድርጎታል:: ከዚህ አንጻር ለምሳሌ እኔ በጅማ ወይም ኢሉባቦር አካባቢ ሄጄ አንድ ነገር ስፈጽም የህወሓት ሰላዮች እዛው ስላሉ ወዲያው መረጃው ይደርሰዋል:: ስለዚህ እኔ በጥምረቱ ውስጥ ካለሁት ሰው ይልቅ እነርሱን ይቀበላል:: ይህ ደግሞ የፌዴራሊዝሙን ራስን በራስ ማስተዳደር የሚለውን የሚያፋልስ ነው፡፡
የዚህ ጨፍላቂነቱ ማረጋገጫ የሚሆነው ደግሞ፤ እነዚህ ሁሉ ፓርቲዎችና ምርጫ አናካሂድም በሚሉበት ወቅት እርሱ አካሂዳለሁ ማለቱ የራሱን የበላይነት ለማንጸባረቅ የሚያደርገው ድርጊት ነው:: ከዚህ ባለፈ ስለ ህዳሴው ግድብ ያገባናል ብለን ሁላችንም ፓርቲዎች ስንናገር፤ ስለሱ ጉዳይ መንግስትን እንጂ እኛን አይመለከትም ማለቱ ነው:: ይሄን የሚል ድርጅት ደግሞ የፌዴራሊዝም ጠበቃ ሊሆን አይችልም:: ምክንያቱም ይህ ፕሮጀክት ከዳር እስከዳር ያሉ የፌዴራል መንግስቱ አባል ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች ውስጥ ያሉ ህዝቦች ፕሮጀክት ሆኖ ሳለ፤ ይሄን የኢትዮጵያ ህዝብ አንጡራ ሀብት ስለሆነው ግድብ አያገባንም ብሎ መናገር አግባብነት የሌለው፣ ስለፌዴራሊዝም የማያስብና የራሱን ኑሮ ብቻ ለማንቀሳቀስ የሚጥር ድርጅት መሆኑን ነው የተረዳሁት፡፡

አዲስ ዘመን፡- እርሱ ከውጪ ሆነው ሲያዩት እና በውስጡ ሆነው ሲያዩት ስለ ህወሓት ከተገነዘቡት አንጻር፤ የትግራይ ህዝብም ሆነ የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች ስለ ህወሓት ሊያውቁት ይገባል ብለው የሚነግሩትና የሚያስተላልፉት መልዕክት ምንድን ነው?
አቶ ደረጀ፡- አንደኛ ለትግራይ ህዝብ ነው መልዕክት የማስተላልፈው:: ይሄውም ህወሓት ላለፉት 40ም ይሁን 50 ዓመት ታግሏል:: አንድ ትግል ደግሞ ወደ ህዝቡ ሰርፆ ይገባና ያድጋል፤ ያለበለዚያ ደግሞ ይከስማል:: አሁን በህወሓት ላይ የምናየው ይሄንኑ ነው:: ምክንያቱም ላለፉት 45 ዓመታት የዘለቀው የህወሃት ትግል የጉዞ ምዕራፉ ወደ መጠቃለሉ እንደመሆኑ መጠን፤ አሁን ላይ የትግራይ ወጣት የህወሓትን ወቅታዊ አካሄድ አይቀበለውም:: ህዝቡም አሁንም በድህነቱ ያለ እንደመሆኑ ከድህነት መውጣትን ይፈልጋል:: ምክንያቱም ህወሓት የዘረፈውን ወደ አውሮፓና መሰል አገሮች ከማሸሽ የዘለለ ለህዝቡ የሰራለት ነገር የለም::
ስለዚህ በተለይ በትግራይ ያለው የገጠር ህዝብ ስለ ህወሓት መሰሪነትና ተንኮል በደንብ ተረድቷል:: የትግራይን ህዝብ ከሌላው የኢትዮጵያ ህዝብ ለመነጠል የሚያደርገውንም አካሄድ ተገንዝቧል:: ይሄን የተገነዘበ ህዝብ ደግሞ ህወሓትን በቃህ ሊለው ይገባል:: የትግራይ ተወላጆችና የትግራይ ህዝብ ደግሞ በዚህ ረገድ ትልቅ ድርሻቸውን መወጣት ይኖርባቸዋል:: የትግራይ ወጣቶች፣ የትግራይ ምሑራን፣ በትግራይ ውስጥ የሚንቀሳቀሱ ፓርቲዎች ህወሓትን በቃህ ሊሉት ይገባል:: ለዚህ ደግሞ አንድም፣ ላለፉት 45 ዓመታት ያደረጋቸውን በማሰብ፤ ሁለተኛም አንድ ነገር የተወሰነ ደረጃ ላይ ሲደርስ የሚያቆም መሆኑን መገንዘብ ይኖርባቸዋል:: በመሆኑም የትግራይ ህዝብ የህወሓትን አመራሮች እዚህ ጋር በቃችሁ ሊሏቸው ይገባል፡፡
ለምን ቢባል፣ እነዚህ አመራሮች የራሳቸውን ሀብት አካብተዋል:: ይህ ሀብት ደግሞ በመቐሌ ብቻ ሳይሆን በአዲስ አበባና በሌሎች ክልሎች ጭምር ከህንጻ እስከ ተሽከርካሪ የሚገለጽ ሀብት ነው:: በክልሉ ደግሞ ለእለት ጉርሱም ሆነ ለእግሩ ጫማ እና ለሰውነቱ ልብስ መለወጥ ቀርቶ ማሟላት ያቃተው ህዝብ (በተለይ ገጠሩ) ተፈጥሯል:: እናም እነዚህ አመራሮች እውነትም ለዚህ ህዝብ ታግለንለታል ካሉ ያ ህዝብ ነጻ መውጣት ነበረበት:: ቢያንስ ትንሽ እንኳን መሻሻል ማሳየት ነበረበት:: ስለሆነም እኔ ለትግራይ ህዝብና ለትግራይ ልሂቃንና ሌላውም የህብረተሰብ ክፍል የማስተላልፈው ይሄ ለህዝቡ የጠቀመው ነገር የለምና ለህዝቡ የሚጠቅም ፓርቲ ማግኘት ስላለባቸው ለእርሱ የሚያደርጉት ድጋፍ ማቆም መቻል አለባቸው:: ምክንያቱም ይህ ፓርቲ ድጋፍ እያጣ አሁንም ወደ ከተማ የተሰበሰበ እንደመሆኑ፤ አሁን ያለውና የቀረውም ማቆም አለበት:: ይሄን በማድረግም ለራሳቸው የሚበጀውን ማሰቡ በጣም ጠቃሚ ነው፡፡
በየክልሉ ተበትነው ያሉም ሆኑ በውጭ አገራት ያሉ የትግራይ ተወላጆችም ለህወሓት የሚያደርጉትን ቆም ብለው ማሰብ መቻል አለባቸው:: በሚያደርጉት ድጋፍ በአገሬ ላይ ምን ለውጥ መጣ? ምንስ ታየ፣ የትስ ደረሰ? ማለት አለባቸው:: ህወሓት 27 ዓመት ኢትዮጵያን ሲገዛና ሀብቱን እንደፈለገው ሲያሽከረክር ለእኛ ለትግራይ ህዝቦች ምን አደረገ? ብለው ቆም ብለው ማሰብ አለባቸው::
ምክንያቱም እነዚህ ቡድኖች ዛሬ ችግር ሲመጣ ወደዛ ተሰበሰቡ እንጂ አካባቢውን እንኳን ሄደው አይተው የማያውቁ ብዙዎች ናቸው:: ለዚህ ምሳሌ ለመጥቀስ ያክል፤ ክልሉን ባስጎበኙኝ ጊዜ ከተመለከትኳቸው አከባቢዎች አንዱ የአምባሳደር ስዩም መስፍን የትውልድ አካባቢ ነበረ:: በወቅቱ ስንጎበኝ እርሱም አብሮን ነበር:: የአካባቢው ነዋሪዎች ሲናገሩ እንደሰማሁት ግን አምባሳደር ስዩም ከዛን እለት በስተቀር እንደማንኛውም ሰው በቴሌቪዥን ከማየት ውጪ በአካል አይተውት እንደማያውቁ ሲገልጹ ነበር፡፡
እናም በዚህ መልኩ አካባቢያቸውን በልማት ማገዝ ቀርቶ በአካል ሄዶ መመልከት ሳይችሉ የኖሩ አመራሮች፣ ዛሬ ችግር ሲገጥማቸው ወደ ህዝቡ ገብተው ህዝቡን ለሌላ ጭንቀት ይባስ ብሎም ከሌላው ህዝብ ለመነጠል የሚያደርጉትን ጥረት በግልጽ ይታያል:: እነርሱ ሲደላቸው እርሱ ሲቸገር የነበረው ህዝብ በእነርሱ ሴራ ዛሬ ከእነርሱ ጋር ተጨፍልቆ እንዲታይ እያደረጉትም ይገኛል:: እናም በክልሉ ያለውም ሆነ በሌሎች ክልሎች ብሎም በውጭ አገራት ያለው የትግራይ ተወላጅ ይሄን ሊያውቁ፤ ለህዝቡ ምን አደረገለት ወይም ምን አደረገበት ብለው ሊመረምሩ እና እነዚህን ግለኛ አመራሮች በቃ ሊሏቸው፤ እንደ ሌሎች ኢትዮጵያዊያን ወንድሞቹ ሁሉ የሚፈልገውን ፓርቲ ደግፎ የነጻነት አየር መተንፈስ መቻል አለበት፡፡
ሌላው የኢትዮጵያ ብሔር፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች መገንዘብ የሚኖርባቸው ደግሞ፤ የትግራይ ህዝብ ትክክለኛ ኢትዮጵያዊና ትክክለኛ አካሄድ የሚሄድ ህዝብ መሆኑን ነው:: ዛሬ ላይ የትግራይን ህዝብ እገነጥላለሁ ብሎ የሚፎክረው ህወሃትም የግል ስሜትና ፍላጎቱን እንጂ በህዝቡ ፍላጎትና ድጋፍ እንዳልሆነም ማወቅ ይኖርበታል::
ለዚህ ደግሞ ህዝቡ ወጥቶ የድጋፍ ድምጽ እንዲሰጥ ይደረግ ቢባል እንኳን አምስት በመቶ እንኳን አያገኝም:: ይሄንንም በክልሉ ቆይታዬ በነበረኝ ጉብኝት ከተለያዩ አካላት (ምሑራንና ህዝቡን ጨምሮ) ባደረኩት የሀሳብ ልውውጥና ውይይት መገንዘብ ችያለሁ:: ህዝቡ ለህወሃት ባዶ ፉከራ ሳይሆን ለኢትዮጵያዊነቱ ቅድሚያ የሚሰጥ እና ኢትዮጵያዊነቱን አክብሮ የሚኖር ህዝብ ነው፡፡
ህወሓትም ቢሆን እንደሚያወራው ለብሔር ብሔረሰቦች የሚሰራው ስራ የለም:: ይልቁንም ለራሱ ጥቅምና ስልጣን ማስቀጠያ በሚያመች መልኩ እንጂ ለክልሉ ህዝብም ሆነ ለክልሉ የተሻለ እድገት ሲል ያከናወነው ነገር አይታይም:: ለዚህ ማሳያው ደግሞ በትግራይ ውስጥ በክልሉ ከተወለዱ ህዝቦች እና ጥቂት የመንግስት ስራን ማዕከል አድርገው ካሉ ዜጎች ውጪ በትግራይ የሚኖርም፤ በኢንቨስትመንት ተሳትፎ እንዲኖረውም አለመደረጉ ነው:: ለምሳሌ፣ በክልሉ አንድም ኦሮሞ ወይም ሌላ ብሔር ሆቴል ያለው፤ ፋብሪካ የከፈተም የለም:: በአንጻሩ በሌሎች የክልል ከተሞችና ክልሎች በርካታ ብሔር ብሔረሰቦች በሆቴልም ሆነ በሌሎች በርካታ ኢንቨስትመንት ስራዎች ላይ ተሰማርተው እየሰሩ ይገኛል:: በትግራይ ክልል እየሆነ ያለው የማግለል ተግባር ግን የህወሓት ስራ ውጤት እንጂ የህዝቡ ፍላጎትም ተግባርም አይደለም::
በዚህም ዛሬም ቢሆን የትግራይ ህዝብ በድህነት ውስጥ ያለ፤ የነጻነት አየርን በወጉ ያላጣጣመና በአፈና ውስጥ ያለ፤ ዛሬም ቢሆን ከስጋት ያልተላቀቀ ህዝብ ነው:: ዛሬም እንደሌሎች ኢትዮጵያዊ ወገኖቹ የፈለገውን የመደገፍ ፍላጎት ያለውና ከተወሰኑ የህወሓት ቡድኖች አፈና መውጣትን የሚናፍቅ ህዝብ ነው:: ከዚህ አንጻር የኢትዮጵያ ህዝብም ለህወሓት ባዶ ፉከራ ሳይሆን ለዚህ እውነተኛ ኢትዮጵያዊ የትግራይ ህዝብ ጆሮ ሰጥቶ የህዝቡን እውነት ማድመጥ ይኖርበታል:: ህወሓት እንደሚለውም ሁሉም ትግሬ የህወሓት አባል ወይም ደጋፊ ነው ብለው ማሰብም የለባቸውም:: በአንጻሩ ሁሉም ትግሬ ኢትዮጵያዊ ነው ብለው ማሰብ፤ ንጹሁን ህዝብም ከሰላዩና ዘራፊው ለይተው ማየት አለባቸው:: ምክንያቱም ዛሬ ከህወሓት ጥቂት ቡድኖች ጋር ያሉት አንድም እነዚሁ የቡድኑ አባላት፤ ሁለትም ከህወሓት ጋር በፈጠሩት ትስስር እርሱንም መከታ አድርገው ሲዘርፉና የሰውን ንብረት ጭምር ሲበዘብዙ የነበሩ ቡድኑን ከተውት ያላቸውን የሚያጡ የሚመስላቸው ጥቂት ግለሰቦች ናቸው ፡፡

አዲስ ዘመን፡- አሁን ላይ ላይ ያለውን የኢትዮጵያ የፖለቲካ ሁኔታ እንዴት ይገለጻል? ምንስ ይፈልጋል?
አቶ ደረጀ፡- አሁን ያለውን የኢትዮጵያ ፖለቲካ ወቅታዊ ጉዳይ ስናይ የታየውን አገራዊ ለውጥ/ሪፎርም ተከትሎ አገር እየመራ ያለው የብልጽግና ፓርቲ ነው:: አገር ያለ መሪ ልትኖር ስለማትችልም ይህ መሆኑም ያለበት ነው:: በዚህ ሁኔታ ላይ እንዳለች ይህ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ተከሰተ:: ይህ በሽታ ሲገባ ደግሞ ቅድሚያ የሚሰጠው ለህዝብ ነው እንጂ ፖለቲካ ፓርቲ ወይም አስተዳደር ወይም ሚኒስትርና ጠቅላይ ሚንስትርነት አይደለም:: ህዝቡ ደህና መሆን ስላለበት መጀመሪያ ለህዝብ ጤንነትና ደህንነት ነው::
ሆኖም አሁን የፖለቲካ አሰላለፉን ስናይ በአብዛኛው አንድ ላይ እየተሰበሰበ ነው ያለው:: እኛም በዚህ መልኩ ሰብሰብ ማለታችን ይሄ አስፈላጊ በመሆኑ ነው:: ስለዚህ ወቅታዊ የፖለቲካ ሁኔታው ይሄንን ማድረግን ወይም ሰብሰብ ማለትን ይፈልጋል፡፡ ምክንያቱም በዚህ መልኩ አንድ ላይ መምጣት ይገባል እንጂ፤ እኔ የመንደር ፖለቲካ አቋቁሜ ኢትዮጵያ ላይ እንደፈለኩ መጮህ አልችልም:: አንድ ላይ ከመጣንና ድምጻችን መሰማት ከጀመረ ግን የሁሉም ኢትዮጵያዊ መሆን አለብኝ:: የሁሉም ኢትዮጵያዊ መሆኔ ወይም ስሆን ደግሞ ኦሮሞን አስደስቼ አማራን ማስከፋት የለብኝም፤ አማራን አስደስቼ የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችን ማስከፋት የለብኝም፤ ሁሉንም አንድ ላይ ነው ማየት ያለብኝ:: የእኛም ጥምረት ለዛ ነው ኢትዮጵያን በሙሉ ያቀፈውና በሁሉም ክልሎች ላይ እየተንቀሳቀሰ ያለው:: ይህ ደግሞ አንድ ቦታ ላይ ለሚደርስ ችግርና ተጽዕኖ ሁላችንም ተጠያቂ ነን፤ ሁላችንም ይመለከተናል ከሚል እሳቤ የመነጨ ነው፡፡
በመሆኑም በአገራችን ላይ ያለው የፖለቲካ አመራር በያዘው አካሄድ አገር አቀፍ ሆኖ ቢንቀሳቀስ ጥሩ ነው:: በዚህ እንቅስቃሴው ሌሎችንም ለማሳተፍ መሞከሩም ጥሩ ነው:: ጠቅላይ ሚኒስትሩም ሲናገሩ “ልንረዳችሁ የምንችለው የፖለቲካ ፓርቲዎች አንድ ላይ ስትሰባሰቡ ነው” ነው ያሉት:: በዚህ ንግግራቸው “ስትጨፈለቁ ነው” አላሉም፤ “ስትሰባሰቡ” ነው ያሉት:: ስትሰባሰቡ ግን እንደማንኛውም አገር አስርም እንሁን አምስትና አስራ አምስት በእውነት ለህዝብ የምንታገል፣ ለፍትህና ለዴሞክራሲ የምንታገል ከሆነ በዓላማ የምንገናኝ ሰብሰብ ማለት እንችላለን፡፡
ለምሳሌ፣ እኔ ኦሮሞ ነኝ፤ በኦሮሞነቴ ሶማሌውን እንደራሴ ነው ማየት ያለብኝ:: አንዱ አማራም አንዱን ደቡብ እንደራሱ ነው ማየት ያለበት:: በዚህ መልኩ አንዱ ሌላውን እንደራሱ ማየት እንጂ ነጣጥሎ ማየት የለበትም:: በዚህ መልኩ እንደ ኢትዮጵያዊነት ማየት እና በኢትዮጵያዊነት መታገል፤ በህዝባችን ላይ ፍትህ ሲጓደል ለፍትህ መቆም ይገባል:: የፖለቲካ መሪ ማለትም ለህዝብ መስዋዕትነት ለመክፈል የተዘጋጀ እንጂ ለመዝናናት የተዘጋጀ አይደለም:: ሞት እንኳን ቢመጣ እቀበላለሁ ብሎ የገባ ነው:: በመሆኑም በዚህ መልኩ ሞት እንኳን ቢመጣ ካንተ በፊት እኔ እቀበላለሁ ብዬ እስከገባሁ ድረስ በኢትዮጵያዊነቱ አንድ ለሆነው የኢትዮጵያ ህዝብ ሰብሰብ ብለን በጋራ መስራት ይኖርብናል፡፡
ካልሆነ ለአንዷ የጠቅላይ ሚኒስትርነት ቦታ ወይም ለሚኒስትርነት ቦታ ሁሉም ሊደርስ አይችልም:: 110 ሚሊዬን ህዝብም ሆነ 107 ፓርቲ ይሄን ማድረግ አይችልም:: ሆኖም 110 ሚሊዬኑም ህዝብ አገሬ ነው ብሎ በእኩልነት ያለመሳቀቅ ህግን አክብሮ እንደ ልቡ የሚኖርበትን አገር መፍጠር ይቻላል:: አሁን ያለው አመራርም ከልምድ የሚመነጭ የፖለቲካ አመራርነት ብስለት ይጎድለው እንደሆን እንጂ ይሄን ከማድረግ አኳያ አቅም አለው:: ለምሳሌ፣ እኔ ባለሁበት ኦሮሚያ ክልልን ብንወስድ በዞንና ወረዳ እስከ ቀበሌ በአንዳንድ ቦታዎች ላይ የሚቀመጡ አመራሮች በህዝብ አስተዳደር ልምድ ማነስና በፖለቲካው ካለመብሰል የተነሳ የውሳኔ ሰጪ አካላት ማነስ ይስተዋላል:: እነዚህ ደግሞ በመቀራረብ ወይም በጓደኝነት የመጡ እንጂ በህዝብ ተተችተውና ይሁንታ አግኝተው ስላልሆነ ነው:: ከዚህ ውጪ ግን እንደ ብልጽግና ፓርቲ እንዳየሁት ጥሩ ፕሮግራም ነድፏል:: ይህ ፕሮግራምም ኢትዮጵያም ብዝሃነቷን ጠብቃ አንድ የሚያደርጋት መሆኑንም ተመልክቻለሁ:: ባህርዳር፣ ጅግጅግጋ፣ ሐዋሳ፣ ሰመራ፣ አሶሳ፣ ጋምቤላ፣ ጅማም ሆነ ነቀምቴ፣ ወዘተ. ያለው ብልጽግና ፓርቲም አንድ አይነት በሆነ አሰራርና ፕሮግራም የሚመራ መሆኑም ደስ የሚያሰኝ ነው፡፡
ለምን ከተባለ ብዝሃነትን አስጠብቆ ኢትዮጵያዊ አንድነትን ያመጣልና ነው:: እኛም ለዛ ነው ፌዴራሊስት ብለን ከሶማሌውም፣ ከአፋሩም፣ ከአማራውና ከሁሉም ብሔር ብሔረሰቦች ጋር አንድ ላይ ሆነን ስንቀሳቀስ ኢትዮጵያዊነትን ለመፍጠር ነው:: ለምሳሌ፣ የኢትዮጵያ ፌዴራሊስት ኃይሎች ጥምረት ለምርጫ ሲቀርብ በኦሮሚያ ክልል የሚወዳደረው የኦሮሞ ነጻነት ንቅናቄ በራሱ አርማ ቢወዳደርም እንደ አገር የሚንቀሳቀሰው በጥምረቱ ዓርማ ጥላ ስር ሆኖ ነው:: ስለዚህ ሁላችንም ማድረግ ያለብን የነበረብን በጋራ ነው:: ሆኖም ወደ 20 የሚሆኑት የጥምረቱ አባላት ምርጫውን አናካሂድም እያሉ ባለበት ሁኔታ ህወሓት ለብቻው ይሄን ውሳኔ ማሳለፉ ተገቢም ትክክልም አይደለም፡፡ ምክንያቱም ሰው ሊመርጠን የሚችለው ሰላምና ጤነኛ ሆኖ ሲኖር ነው:: አገርም ተማምኖ መሄድ ሲችል ነው:: ካልሆነ በጀብደኝነት ተነስቼ ምርጫ ላካሂድ ብል አያዋጣም:: እኛም ይሄን ስለምንገነዘብ ለምን እኛን ሳታማክሩ መግለጫ ሰጣችሁ ብለንም ጠይቀናል:: ሆኖም ይህ የግሌ ነው፣ በዚህ ጉዳይ ላይ አይመለከታችሁም የሚል ሀሳብ ይዞ ነው የመጣው:: እኛም በበኩላችን የስብስቡ አባል እስከሆናችሁና የጋራ ስምምነት እስካለ ድረስ መፈጸም ያለበት በጋራ እንጂ በአንድ ፓርቲ የግል ፍላጎት አይደለም፤ አካሄዱም አንድነት አያመጣም፤ ምክንያቱም፣ ሶማሌው ለብቻ አንድ ሲል፣ አፋሩም ሌላ ሲል፣ ኦሮሞውም ለብቻው ሌላ ሲል ነገሮች ልክ አይመጡምና ምርጫውን ማካሄድ አትችሉም በማለታችን በመካከል ጭቅጭቅ ነበር:: የአዲስ አበባው ስብሰባ መሰረትና አንዱ ዓላማ በዚህ መልኩ ከጥምረቱ አቋም ውጪ ህወሓት ምርጫ አካሂዳለሁ ብሎ የወሰነው ግላዊ ውሳኔ ተገቢም ትክክልም አለመሆኑን ለመግለጽ ነው::

አዲስ ዘመን፡- በዚህ ሁሉ ሂደት ውስጥ ከህወሓት ጋር በጥምረት በቆያችሁባቸው ጊዜያት ቀደም ሲል ከውጭ ስትሰሙትና ስትገምቱት ከነበረው አንጻር ስለ ህወሃት ባህሪና እውነተኛ ማንነት ምን የተለየ ነገር ተገነዘባችሁ?
አቶ ደረጀ፡- እውነት ለመናገር፣ ከህወሓት የተረዳነው ባህሪ አንዱ፣ ህወሓት ማለት የተወሰኑ ቡድኖች ናቸው:: የተወሰኑ ቡድኖች ብዬ ስል የትግራይ ህዝብ ወይም በትግራይ ክልል የሚገኙ ወጣቶች፣ አዛውንቶች፣ ተማሪውም ሆነ ሌላው የህብረተሰብ ክፍልን ስታይ ህወሓት በከተማ ውስጥ እንጂ በገጠር የለም:: ይሄንንም ከመቐሌ እስከ ደደቢት እና ዛላንበሳን ጨምሮ ሌሎችም የትግራይ ክልል ክፍሎችን ባስጎበኙኝ ወቅት ተመልክቼ ተገንዝቤያለሁ:: በእነዚህ የክልሉ ዞኖችና ወረዳዎች በነበረኝ ጉብኝት የተመለከትኩት እና አንዳንዴም አማርኛ የሚናገሩ/የሚችሉ ሰዎችን አነጋግሬ እንደተረዳሁት፤ ህወሓት ከህዝቡ ጋር የለም:: ምናልባት የተወሰነ ህዝብ ነው ከህወሓት ጋር ያለው፡፡ ይሄ የተወሰነ ህዝብ ደግሞ በመቐሌ ከተማ እና ዙሪያዋ ያሉ ጥቂት ሰዎችን የሚመለከት ሲሆን፤ ሌላው ቀርቶ ወደ አድዋና አክሱም ስንሄድ እውነት ለመናገር ህዝቡ የሚያሳዝን ህዝብ ነው:: ምክንያቱም ሰፊው የትግራይ ህዝብ አንደኛ፣ በአሁን ጊዜ በዚህ ዘመን ለእግሩ እንኳን ጫማ የሌለው ህዝብ ነው:: ልብስ በረከሰበት በዚህ ወቅት ልብስ እንኳን መልበስ ያልቻለ ህዝብ ነው:: ይህ ደግሞ ጥቂት የህወሓት አመራሮችና አባላት ገንዘቡንም ለራሳቸው፤ አገሩንም የራሳቸው አድርገው እንደያዙት የሚያሳይ ነው፡፡ እንዳየሁት ከሆነ ህዝቡ መፈናፈኛ ስላጣ ነው ዝም ያለው:: ለዚህ ደግሞ ወደ ዛላንበሳ በሄድኩበት ወቅት ያነጋገርኳቸው አንድ አዛውንት ያጫወቱኝ ትልቅ አብነት ነው:: እኚህ አዛውንት እንዳጫወቱኝ፣ እዚሁ ነው:: ፌዴራሊዝም ስንልም የጋራ አስተዳደር ማለታችንም ነው:: ህወሓት ግን የእኩል አስተዳደር ብሎ ነገር የለውም:: ህወሓት የበላይነቱን ለማንጸባረቅ ብቻ የሚንቀሳቀስ ቡድን ነው:: የህወሓት አመራሮች ቦረና ያለውን ከብት አርቢ ነው፤ ሶማሌ ያለውን እንዲህ ነው እያሉ ከመናገር ውጪ፤ ቦረና ያለውም ራሱን ለማስተዳደር ይችላል፤ ሶማሌ ያለውም ራሱን ለማስተዳደር ይችላል፤ እንዲሁም የአካባቢውን ልማት መምራት ይችላል ብሎ የሚያስብ ቡድን አይደለም:: የራሱን የበላይነት ብቻ ለማንጸባረቅ የሚንቀሳቀስ ቡድን ነው:: ይሄን የበላይነቱን ለማረጋገጥም በየቦታው የራሱን የስለላ መረብ በመዘርጋት የሚሰራ ቡድን ነው፡፡ ፌዴራሊዝም ማለትኮ የመጀመሪያው ጉዳይ ራስን ማስተዳደር ነው:: በራስ መዳኘት ነው:: በራስ ቋንቋ መማር ነው:: ህወሓት ግን ያንን ለይምሰል ይናገር እንጂ ውስጥ ገብተን ስናየው የራስን በራስ የማስተዳደር መብትን የሚጨፈልቅ ቡድን ነው:: ይሄንን መብት ጨፍልቆም እሱ እንዴት መግዛት እንደሚችል የሚያስችለውን የወጥመድ መረብ የሚዘረጋ ነው:: ለዚህ ደግሞ በስለላ መረብ በጣሙን የተሳሰረ ነው:: በሆቴልም ሆነ በየትም ያለ ሰራተኛን በዚህ መረብ ውስጥ በማስገባት የስለላ መረቡ አባል አድርጎታል:: ከዚህ አንጻር ለምሳሌ እኔ በጅማ ወይም ኢሉባቦር አካባቢ ሄጄ አንድ ነገር ስፈጽም የህወሓት ሰላዮች እዛው ስላሉ ወዲያው መረጃው ይደርሰዋል:: ስለዚህ እኔ በጥምረቱ ውስጥ ካለሁት ሰው ይልቅ እነርሱን ይቀበላል:: ይህ ደግሞ የፌዴራሊዝሙን ራስን በራስ ማስተዳደር የሚለውን የሚያፋልስ ነው፡፡ የዚህ ጨፍላቂነቱ ማረጋገጫ የሚሆነው ደግሞ፤ እነዚህ ሁሉ ፓርቲዎችና ምርጫ አናካሂድም ሚሉበት ወቅት እርሱ አካሂዳለሁ ማለቱ የራሱን የበላይነት ለማንጸባረቅ የሚያደርገው ድርጊት ነው:: ከዚህ ባለፈ ስለ ህዳሴው ግድብ ያገባናል ብለን ሁላችንም ፓርቲዎች ስንናገር፤ ስለሱ ጉዳይ መንግስትን እንጂ እኛን አይመለከትም ማለቱ ነው:: ይሄን የሚል ድርጅት ደግሞ የፌዴራሊዝም ጠበቃ ሊሆን አይችልም:: ምክንያቱም ይህ ፕሮጀክት ከዳር እስከዳር ያሉ የፌዴራል መንግስቱ አባል ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች ውስጥ ያሉ ህዝቦች ፕሮጀክት ሆኖ ሳለ፤ ይሄን የኢትዮጵያ ህዝብ አንጡራ ሀብት ስለሆነው ግድብ አያገባንም ብሎ መናገር አግባብነት የሌለው፣ ስለፌዴራሊዝም የማያስብና የራሱን ኑሮ ብቻ ለማንቀሳቀስ የሚጥር ድርጅት መሆኑን ነው የተረዳሁት፡፡

አዲስ ዘመን፡- እርሱ ከውጪ ሆነው ሲያዩት እና በውስጡ ሆነው ሲያዩት ስለ ህወሓት ከተገነዘቡት አንጻር፤ የትግራይ ህዝብም ሆነ የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች ስለ ህወሓት ሊያውቁት ይገባል ብለው የሚነግሩትና የሚያስተላልፉት መልዕክት ምንድን ነው?
አቶ ደረጀ፡- አንደኛ ለትግራይ ህዝብ ነው መልዕክት የማስተላልፈው:: ይሄውም ህወሓት ላለፉት 40ም ይሁን 50 ዓመት ታግሏል:: አንድ ትግል ደግሞ ወደ ህዝቡ ሰርፆ ይገባና ያድጋል፤ ያለበለዚያ ደግሞ ይከስማል:: አሁን በህወሓት ላይ የምናየው ይሄንኑ ነው:: ምክንያቱም ላለፉት 45 ዓመታት የዘለቀው የህወሃት ትግል የጉዞ ምዕራፉ ወደ መጠቃለሉ እንደመሆኑ መጠን፤ አሁን ላይ የትግራይ ወጣት የህወሓትን ወቅታዊ አካሄድ አይቀበለውም:: ህዝቡም አሁንም በድህነቱ ያለ እንደመሆኑ ከድህነት መውጣትን ይፈልጋል:: ምክንያቱም ህወሓት የዘረፈውን ወደ አውሮፓና መሰል አገሮች ከማሸሽ የዘለለ ለህዝቡ የሰራለት ነገር የለም:: ስለዚህ በተለይ በትግራይ ያለው የገጠር ህዝብ ስለ ህወሓት መሰሪነትና ተንኮል በደንብ ተረድቷል:: የትግራይን ህዝብ ከሌላው የኢትዮጵያ ህዝብ ለመነጠል የሚያደርገውንም አካሄድ ተገንዝቧል:: ይሄን የተገነዘበ ህዝብ ደግሞ ህወሓትን በቃህ ሊለው ይገባል:: የትግራይ ተወላጆችና የትግራይ ህዝብ ደግሞ በዚህ ረገድ ትልቅ ድርሻቸውን መወጣት ይኖርባቸዋል:: የትግራይ ወጣቶች፣ የትግራይ ምሑራን፣ በትግራይ ውስጥ የሚንቀሳቀሱ ፓርቲዎች ህወሓትን በቃህ ሊሉት ይገባል:: ለዚህ ደግሞ አንድም፣ ላለፉት 45 ዓመታት ያደረጋቸውን በማሰብ፤ ሁለተኛም አንድ ነገር የተወሰነ ደረጃ ላይ ሲደርስ የሚያቆም መሆኑን መገንዘብ ይኖርባቸዋል:: በመሆኑም የትግራይ ህዝብ የህወሓትን አመራሮች እዚህ ጋር በቃችሁ ሊሏቸው ይገባል፡፡ ለምን ቢባል፣ እነዚህ አመራሮች የራሳቸውን ሀብት አካብተዋል:: ይህ ሀብት ደግሞ በመቐሌ ብቻ ሳይሆን በአዲስ አበባና በሌሎች ክልሎች ጭምር ከህንጻ እስከ ተሽከርካሪ የሚገለጽ ሀብት ነው:: በክልሉ ደግሞ ለእለት ጉርሱም ሆነ ለእግሩ ጫማ እና ለሰውነቱ ልብስ መለወጥ ቀርቶ ማሟላት ያቃተው ህዝብ (በተለይ ገጠሩ) ተፈጥሯል:: እናም እነዚህ አመራሮች እውነትም ለዚህ ህዝብ ታግለንለታል ካሉ ያ ህዝብ ነጻ መውጣት ነበረበት:: ቢያንስ ትንሽ እንኳን መሻሻል ማሳየት ነበረበት:: ስለሆነም እኔ ለትግራይ ህዝብና ለትግራይ ልሂቃንና ሌላውም የህብረተሰብ ክፍል የማስተላልፈው ይሄ [ገጽ 14 አዲስ ዘመን እሁድ ግንቦት 16 ቀን 2012 ዓ.ም] ለህዝቡ የጠቀመው ነገር የለምና ለህዝቡ የሚጠቅም ፓርቲ ማግኘት ስላለባቸው ለእርሱ የሚያደርጉት ድጋፍ ማቆም መቻል አለባቸው:: ምክንያቱም ይህ ፓርቲ ድጋፍ እያጣ አሁንም ወደ ከተማ የተሰበሰበ እንደመሆኑ፤ አሁን ያለውና የቀረውም ማቆም አለበት:: ይሄን በማድረግም ለራሳቸው የሚበጀውን ማሰቡ በጣም ጠቃሚ ነው፡፡ በየክልሉ ተበትነው ያሉም ሆኑ በውጭ አገራት ያሉ የትግራይ ተወላጆችም ለህወሓት የሚያደርጉትን ቆም ብለው ማሰብ መቻል አለባቸው:: በሚያደርጉት ድጋፍ በአገሬ ላይ ምን ለውጥ መጣ? ምንስ ታየ፣ የትስ ደረሰ? ማለት አለባቸው:: ህወሓት 27 ዓመት ኢትዮጵያን ሲገዛና ሀብቱን እንደፈለገው ሲያሽከረክር ለእኛ ለትግራይ ህዝቦች ምን አደረገ? ብለው ቆም ብለው ማሰብ አለባቸው:: ምክንያቱም እነዚህ ቡድኖች ዛሬ ችግር ሲመጣ ወደዛ ተሰበሰቡ እንጂ አካባቢውን እንኳን ሄደው አይተው የማያውቁ ብዙዎች ናቸው:: ለዚህ ምሳሌ ለመጥቀስ ያክል፤ ክልሉን ባስጎበኙኝ ጊዜ ከተመለከትኳቸው አከባቢዎች አንዱ የአምባሳደር ስዩም መስፍን የትውልድ አካባቢ ነበረ:: በወቅቱ ስንጎበኝ እርሱም አብሮን ነበር:: የአካባቢው ነዋሪዎች ሲናገሩ እንደሰማሁት ግን አምባሳደር ስዩም ከዛን እለት በስተቀር እንደማንኛውም ሰው በቴሌቪዥን ከማየት ውጪ በአካል አይተውት እንደማያውቁ ሲገልጹ ነበር፡፡ እናም በዚህ መልኩ አካባቢያቸውን በልማት ማገዝ ቀርቶ በአካል ሄዶ መመልከት ሳይችሉ የኖሩ አመራሮች፣ ዛሬ ችግር ሲገጥማቸው ወደ ህዝቡ ገብተው ህዝቡን ለሌላ ጭንቀት ይባስ ብሎም ከሌላው ህዝብ ለመነጠል የሚያደርጉትን ጥረት በግልጽ ይታያል:: እነርሱ ሲደላቸው እርሱ ሲቸገር የነበረው ህዝብ በእነርሱ ሴራ ዛሬ ከእነርሱ ጋር ተጨፍልቆ እንዲታይ እያደረጉትም ይገኛል:: እናም በክልሉ ያለውም ሆነ በሌሎች ክልሎች ብሎም በውጭ አገራት ያለው የትግራይ ተወላጅ ይሄን ሊያውቁ፤ ለህዝቡ ምን አደረገለት ወይም ምን አደረገበት ብለው ሊመረምሩ እና እነዚህን ግለኛ አመራሮች በቃ ሊሏቸው፤ እንደ ሌሎች ኢትዮጵያዊያን ወንድሞቹ ሁሉ የሚፈልገውን ፓርቲ ደግፎ የነጻነት አየር መተንፈስ መቻል አለበት፡፡ ሌላው የኢትዮጵያ ብሔር፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች መገንዘብ የሚኖርባቸው ደግሞ፤ የትግራይ ህዝብ ትክክለኛ ኢትዮጵያዊና ትክክለኛ አካሄድ የሚሄድ ህዝብ መሆኑን ነው:: ዛሬ ላይ የትግራይን ህዝብ እገነጥላለሁ ብሎ የሚፎክረው ህወሃትም የግል ስሜትና ፍላጎቱን እንጂ በህዝቡ ፍላጎትና ድጋፍ እንዳልሆነም ማወቅ ይኖርበታል:: ለዚህ ደግሞ ህዝቡ ወጥቶ የድጋፍ ድምጽ እንዲሰጥ ይደረግ ቢባል እንኳን አምስት በመቶ እንኳን አያገኝም:: ይሄንንም በክልሉ ቆይታዬ በነበረኝ ጉብኝት ከተለያዩ አካላት (ምሑራንና ህዝቡን ጨምሮ) ባደረኩት የሀሳብ ልውውጥና ውይይት መገንዘብ ችያለሁ:: ህዝቡ ለህወሃት ባዶ ፉከራ ሳይሆን ለኢትዮጵያዊነቱ ቅድሚያ የሚሰጥ እና ኢትዮጵያዊነቱን አክብሮ የሚኖር ህዝብ ነው፡፡ ህወሓትም ቢሆን እንደሚያወራው ለብሔር ብሔረሰቦች የሚሰራው ስራ የለም:: ይልቁንም ለራሱ ጥቅምና ስልጣን ማስቀጠያ በሚያመች መልኩ እንጂ ለክልሉ ህዝብም ሆነ ለክልሉ የተሻለ እድገት ሲል ያከናወነው ነገር አይታይም:: ለዚህ ማሳያው ደግሞ በትግራይ ውስጥ በክልሉ ከተወለዱ ህዝቦች እና ጥቂት የመንግስት ስራን ማዕከል አድርገው ካሉ ዜጎች ውጪ በትግራይ የሚኖርም፤ በኢንቨስትመንት ተሳትፎ እንዲኖረውም አለመደረጉ ነው:: ለምሳሌ፣ በክልሉ አንድም ኦሮሞ ወይም ሌላ ብሔር ሆቴል ያለው፤ ፋብሪካ የከፈተም የለም:: በአንጻሩ በሌሎች የክልል ከተሞችና ክልሎች በርካታ ብሔር ብሔረሰቦች በሆቴልም ሆነ በሌሎች በርካታ ኢንቨስትመንት ስራዎች ላይ ተሰማርተው እየሰሩ ይገኛል:: በትግራይ ክልል እየሆነ ያለው የማግለል ተግባር ግን የህወሓት ስራ ውጤት እንጂ የህዝቡ ፍላጎትም ተግባርም አይደለም:: በዚህም ዛሬም ቢሆን የትግራይ ህዝብ በድህነት ውስጥ ያለ፤ የነጻነት አየርን በወጉ ያላጣጣመና በአፈና ውስጥ ያለ፤ ዛሬም ቢሆን ከስጋት ያልተላቀቀ ህዝብ ነው:: ዛሬም እንደሌሎች ኢትዮጵያዊ ወገኖቹ የፈለገውን የመደገፍ ፍላጎት ያለውና ከተወሰኑ የህወሓት ቡድኖች አፈና መውጣትን የሚናፍቅ ህዝብ ነው:: ከዚህ አንጻር የኢትዮጵያ ህዝብም ለህወሓት ባዶ ፉከራ ሳይሆን ለዚህ እውነተኛ ኢትዮጵያዊ የትግራይ ህዝብ ጆሮ ሰጥቶ የህዝቡን እውነት ማድመጥ ይኖርበታል:: ህወሓት እንደሚለውም ሁሉም ትግሬ የህወሓት አባል ወይም ደጋፊ ነው ብለው ማሰብም የለባቸውም:: በአንጻሩ ሁሉም ትግሬ ኢትዮጵያዊ ነው ብለው ማሰብ፤ ንጹሁን ህዝብም ከሰላዩና ዘራፊው ለይተው ማየት አለባቸው:: ምክንያቱም ዛሬ ከህወሓት ጥቂት ቡድኖች ጋር ያሉት አንድም እነዚሁ የቡድኑ አባላት፤ ሁለትም ከህወሓት ጋር በፈጠሩት ትስስር እርሱንም መከታ አድርገው ሲዘርፉና የሰውን ንብረት ጭምር ሲበዘብዙ የነበሩ ቡድኑን ከተውት ያላቸውን የሚያጡ የሚመስላቸው ጥቂት ግለሰቦች ናቸው ፡፡

አዲስ ዘመን፡- አሁን ላይ ላይ ያለውን የኢትዮጵያ የፖለቲካ ሁኔታ እንዴት ይገለጻል? ምንስ ይፈልጋል?
አቶ ደረጀ፡- አሁን ያለውን የኢትዮጵያ ፖለቲካ ወቅታዊ ጉዳይ ስናይ የታየውን አገራዊ ለውጥ/ሪፎርም ተከትሎ አገር እየመራ ያለው የብልጽግና ፓርቲ ነው:: አገር ያለ መሪ ልትኖር ስለማትችልም ይህ መሆኑም ያለበት ነው:: በዚህ ሁኔታ ላይ እንዳለች ይህ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ተከሰተ:: ይህ በሽታ ሲገባ ደግሞ ቅድሚያ የሚሰጠው ለህዝብ ነው እንጂ ፖለቲካ ፓርቲ ወይም አስተዳደር ወይም ሚኒስትርና ጠቅላይ ሚንስትርነት አይደለም:: ህዝቡ ደህና መሆን ስላለበት መጀመሪያ ለህዝብ ጤንነትና ደህንነት ነው:: ሆኖም አሁን የፖለቲካ አሰላለፉን ስናይ በአብዛኛው አንድ ላይ እየተሰበሰበ ነው ያለው:: እኛም በዚህ መልኩ ሰብሰብ ማለታችን ይሄ አስፈላጊ በመሆኑ ነው:: ስለዚህ ወቅታዊ የፖለቲካ ሁኔታው ይሄንን ማድረግን ወይም ሰብሰብማለትን ይፈልጋል፡፡ ምክንያቱም በዚህ መልኩ አንድ ላይ መምጣት ይገባል እንጂ፤ እኔ የመንደር ፖለቲካ አቋቁሜ ኢትዮጵያ ላይ እንደፈለኩ መጮህ አልችልም:: አንድ ላይ ከመጣንና ድምጻችን መሰማት ከጀመረ ግን የሁሉም ኢትዮጵያዊ መሆን አለብኝ:: የሁሉም ኢትዮጵያዊ መሆኔ ወይም ስሆን ደግሞ ኦሮሞን አስደስቼ አማራን ማስከፋት የለብኝም፤ አማራን አስደስቼ የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችን ማስከፋት የለብኝም፤ ሁሉንም አንድ ላይ ነው ማየት ያለብኝ:: የእኛም ጥምረት ለዛ ነው ኢትዮጵያን በሙሉ ያቀፈውና በሁሉም ክልሎች ላይ እየተንቀሳቀሰ ያለው:: ይህ ደግሞ አንድ ቦታ ላይ ለሚደርስ ችግርና ተጽዕኖ ሁላችንም ተጠያቂ ነን፤ ሁላችንም ይመለከተናል ከሚል እሳቤ የመነጨ ነው፡፡ በመሆኑም በአገራችን ላይ ያለው የፖለቲካ አመራር በያዘው አካሄድ አገር አቀፍ ሆኖ ቢንቀሳቀስ ጥሩ ነው:: በዚህ እንቅስቃሴው ሌሎችንም ለማሳተፍ መሞከሩም ጥሩ ነው:: ጠቅላይ ሚኒስትሩም ሲናገሩ “ልንረዳችሁ የምንችለው የፖለቲካ ፓርቲዎች አንድ ላይ ስትሰባሰቡ ነው” ነው ያሉት:: በዚህ ንግግራቸው “ስትጨፈለቁ ነው” አላሉም፤ “ስትሰባሰቡ” ነው ያሉት:: ስትሰባሰቡ ግን እንደማንኛውም አገር አስርም እንሁን አምስትና አስራ አምስት በእውነት ለህዝብ የምንታገል፣ ለፍትህና ለዴሞክራሲ የምንታገል ከሆነ በዓላማ የምንገናኝ ሰብሰብ ማለት እንችላለን፡፡ ለምሳሌ፣ እኔ ኦሮሞ ነኝ፤ በኦሮሞነቴ ሶማሌውን እንደራሴ ነው ማየት ያለብኝ:: አንዱ አማራም አንዱን ደቡብ እንደራሱ ነው ማየት ያለበት:: በዚህ መልኩ አንዱ ሌላውን እንደራሱ ማየት እንጂ ነጣጥሎ ማየት የለበትም:: በዚህ መልኩ እንደ ኢትዮጵያዊነት ማየት እና በኢትዮጵያዊነት መታገል፤ በህዝባችን ላይ ፍትህ ሲጓደል ለፍትህ መቆም ይገባል:: የፖለቲካ መሪ ማለትም ለህዝብ መስዋዕትነት ለመክፈል የተዘጋጀ እንጂ ለመዝናናት የተዘጋጀ አይደለም:: ሞት እንኳን ቢመጣ እቀበላለሁ ብሎ የገባ ነው:: በመሆኑም በዚህ መልኩ ሞት እንኳን ቢመጣ ካንተ በፊት እኔ እቀበላለሁ ብዬ እስከገባሁ ድረስ በኢትዮጵያዊነቱ አንድ ለሆነው የኢትዮጵያ ህዝብ ሰብሰብ ብለን በጋራ መስራት ይኖርብናል፡፡ ካልሆነ ለአንዷ የጠቅላይ ሚኒስትርነት ቦታ ወይም ለሚኒስትርነት ቦታ ሁሉም ሊደርስ አይችልም:: 110 ሚሊዬን ህዝብም ሆነ 107 ፓርቲ ይሄን ማድረግ አይችልም:: ሆኖም 110 ሚሊዬኑም ህዝብ አገሬ ነው ብሎ በእኩልነት ያለመሳቀቅ ህግን አክብሮ እንደ ልቡ የሚኖርበትን አገር መፍጠር ይቻላል:: አሁን ያለው አመራርም ከልምድ የሚመነጭ የፖለቲካ አመራርነት ብስለት ይጎድለው እንደሆን እንጂ ይሄን ከማድረግ አኳያ አቅም አለው:: ለምሳሌ፣ እኔ ባለሁበት ኦሮሚያ ክልልን ብንወስድ በዞንና ወረዳ እስከ ቀበሌ በአንዳንድ ቦታዎች ላይ የሚቀመጡ አመራሮች በህዝብ አስተዳደር ልምድ ማነስና በፖለቲካው ካለመብሰል የተነሳ የውሳኔ ሰጪ አካላት ማነስ ይስተዋላል:: እነዚህ ደግሞ በመቀራረብ ወይም በጓደኝነት የመጡ እንጂ በህዝብ ተተችተውና ይሁንታ አግኝተው ስላልሆነ ነው:: ከዚህ ውጪ ግን እንደ ብልጽግና ፓርቲ እንዳየሁት ጥሩ ፕሮግራም ነድፏል:: ይህ ፕሮግራምም ኢትዮጵያም ብዝሃነቷን ጠብቃ አንድ የሚያደርጋት መሆኑንም ተመልክቻለሁ:: ባህርዳር፣ ጅግጅግ፣ ሐዋሳ፣ ሰመራ፣ አሶሳ፣ ጋምቤላ፣ ጅማም ሆነ ነቀምቴ፣ ወዘተ. ያለው ብልጽግና ፓርቲም አንድ አይነት በሆነ አሰራርና ፕሮግራም የሚመራ መሆኑም ደስ የሚያሰኝ ነው፡፡ ለምን ከተባለ ብዝሃነትን አስጠብቆ ኢትዮጵያዊ አንድነትን ያመጣልና ነው:: እኛም ለዛ ነው ፌዴራሊስት ብለን ከሶማሌውም፣ ከአፋሩም፣ ከአማራውና ከሁሉም ብሔር ብሔረሰቦች ጋር አንድ ላይ ሆነን ስንቀሳቀስ ኢትዮጵያዊነትን ለመፍጠር ነው:: ለምሳሌ፣ የኢትዮጵያ ፌዴራሊስት ኃይሎች ጥምረት ለምርጫ ሲቀርብ በኦሮሚያ ክልል የሚወዳደረው የኦሮሞ ነጻነት ንቅናቄ በራሱ አርማ ቢወዳደርም እንደ አገር የሚንቀሳቀሰው በጥምረቱ ዓርማ ጥላ ስር ሆኖ ነው:: ስለዚህ ሁላችንም ማድረግ ያለብን ማድረግ የሚገባንን ነው:: እናም ህብረ ብሔራዊ የሆነ ኢትዮጵያዊነትን እንዴት ወደላይ እናውጣ የሚለውንማሰብ አለብን:: የወቅቱም ፖለቲካ በዚህ መልኩ መስራትና መተባበርን ነው የሚፈልገው፡፡ ይህ ካልሆነና በመንደር ካሰብን እንደ ህወሓት ተመልሰን እንገባለን:: እናም እንደዛ ማሰብ የለብንም:: እኛ የተለያየን ቢሆንም ለአንድነት ነው የምንታገለው:: ለአንድ ኢትዮጵያም ነው የምንታገለው:: እናም ይሄንን በጥንካሬና በአንድነት በሁላችንም ፖለቲከኞች ዘንድ መሆን ያለበት ነው እንጂ፤ እኔ ግዙፍ ነኝ፣ እኔ ትንሽ ነኝ፣ እኔ አገሪቷን መጠበቅ እችላለሁ፣ እኔ አገሪቷን ማረጋጋት እችላለሁ የሚለው አይሰራም:: ይሄ ቦታም የለውም:: ምክንያቱም አገር ከተበጠበጠ ይሄ ትርጉም የለውም:: በአገር ሰላም ከሌለ የትም ቢሆን ወልዶ ሊስም፣ ንብረት ሊያፈራም አይችልም:: በመሆኑም የወቅቱ ፖለቲካ ጎጠኝነትና መንደርተኝነትን መተው የሚጠይቅ ነው:: እኔም ይሄ ጎጠኝነትና መንደርተኝነት ቢቀር ደስ ይለኛል፡፡

አዲስ ዘመን፡- እርሶም እንዳነሱት ወቅቱ ለህዝብ ሰላምና ደህንነት ቅድሚያ መስጠትን የሚጠይቅ እንደመሆኑ ምርጫ 2012 መራዘሙ ይታወቃል:: ሆኖም የምርጫውን መራዘም ተከትሎ ህወሓት ምርጫው መካሄድ አለበት ሲል፤ ሌሎች ኃይሎች ደግሞ የሽግግር መንግስት መመስረት አለበት ሲሉተደምጧል:: እርሶ በዚህ ላይ ያለዎት እይታ ምንድን ነው?
አቶ ደረጀ፡- እኔ በመጀመሪያ ደረጃ ምርጫው መራዘም አለበት ከሚሉት ቡድን ነኝ:: ምክንያቱም ምርጫ የሚመርጠን ዛፍ ቅጠሉ አይደለም፤ ሕዝብ ነው:: ህዝብደግሞ ሊመርጠን የሚችለው ጤና ሰላም ሲሆን፤ እንደልቡ ወጥቶ መግባት ሲችል ነው:: ልጁን እንደ ልቡ ማሳደግ ሲችል ነው:: እኔም የምመርጠው ህዝብ ለማስተዳደር ነው እንጂ መሬቷን ብቻ ለማስተዳደር አይደለም:: ህዝብ ለማስተዳደር ደግሞ ህዝቡ ሰላም ሆኖ እኔን መምረጥ መቻል አለበት:: ይሄን መሰረት በማድረግም ነው እኔ ምርጫው ይራዘም ከሚሉት ውስጥ የሆንኩት፡፡ የኦሮሞ ነጻነት ንቅናቄ (ኦነን)ም የወረርሽኙን ዓለማቀፋዊ ሁነቱን በመመልከትና እንደ ስፔንና ጣሊያን ባሉ አገራት የተስተዋለውን የሰው ልጆች እንደ ቅጠል መርገፍ በማየት ገና ቫይረሱ በኢትዮጵያ እንደተከሰተ ነው ችግሩ በኢትዮጵያ እንዳይከሰት በማሰብ ምርጫው መካሄድ የለበትም ቅድሚያ ለህዝብ ደህንነት ሊሰጥ ይገባልና መራዘም አለበት የሚል አቋሙን ያሰማው:: አሁን ላይ ደግሞ ቫይረሱ በኢትዮጵያ እየተስፋፋ ነው:: ይህ ሂደት ደግሞ በከተሞች ያለውን ያክል የጤና መሰረተ ልማት በሌለው ብሎም ጠንካራ ማህበራዊ ትስስር ባለበት የገጠሩ ክፍል ከገባ ደግሞ አደጋው የከፋ እንደሚሆን እሙን ነው:: ትልቁ ስጋትም ይሄው ነው፡፡ ወረርሽኙ ወደገጠር እንዳይገባ ደግሞ በጸሎት ጭምር ፈጣሪን መማጸን ይገባል:: ህብረተሰቡም ጥንቃቄ እንዲያደርግ ማስገንዘብ እና ገበያ መውጣት ቢያስፈልገው እንኳን ሁሉም ከመሄድ ይልቅ የየሰፈሩን ሰብሰብ እያደረገ አንድ ሰው ገብይቶ እንዲመለስ በማድረግ ራሱን እንዲጠብቅ ማስቻል ይገባል:: ይሄን በሃላፊነት የሚመራ መንግስት አስፈላጊ እንደመሆኑም ምርጫው ተራዝሞ አሁን ያለው መንግስት ምርጫ እስኪካሄድ መቆየትም ግድ የሚለው ተግባር ነው:: እኛም ታግለን አታግለንም በአሸናፊነት ብንመረጥ ሌላውም ፓርቲ ቢመረጥ ይሄንኑ ህዝብ ለማስተዳደር ነው:: ለዚህ ደግሞ አሁን ምርጫ ይካሄድ የሚለው ሀሳብ ጤነኛ ያልሆነ፣ ከራስ ጥቅም በዘለለ ለህዝብ ደህንነት ያላሰበ ፍላጎት በመሆኑ ተገቢ አይደለም:: እናም ቅድሚያ ለህዝብ ጤናና ደህንነት መሰጠቱ ተገቢ ነው፡፡ የሽግግር መንግስት ይቋቋም የሚለው ሀሳብም ለእኔ የብጥብጥ ሀሳብ ነው:: እንደ ገና ወደ ብጥብጥ እንመለስ ማለት ነው:: ምክንያቱም በዚህ የሽግግር መንግስት ውስጥ እነማን ናቸው የሚሳተፉት? 107 ፓርቲዎች ይግቡ ወይስ 107 ሽማግሌዎች ይካተቱ ወይስ 107 ምሑራን ይግቡ? የሚለው ጉዳይ ትልቅ የውዝግብ ምክንያት የሚሆን ነው:: እንደ እኔ ግን ከዚህ ሁሉ ውዝግብ አሁን ያለው መንግስት ወይም አመራር ላይ ያለው አካል የህዝቡን ድምጽ ሰምቶ ማሻገር ከቻለ መቀጠል የማይችልበት ምክንያት አይታየኝም:: የሽግግር መንግስት እንደገና ማቋቋምም አስፈላጊ አይሆንም:: የሽግግር መንግስት ይቋቋም ማለት ወንበር እንያዝ ማለት ካልሆነ በስተቀር ትርፍ የለውም:: ምክንያቱም የሽግግር መንግስት የሚያስፈልገው ቢያንስ አገር ችግር ውስጥ ስትወድቅ እና ህዝቡ ባለው መንግስት አመኔታ ሲያጣ ሊተገበር ይችል ይሆናል እንጂ አሁን በኢትዮጵያ ባለው ሁኔታ የሽግግር መንግስት አስፈላጊ አይደለም:: ሆኖም አሁን ያለው መንግስት እስከ ምርጫ ድረስ ሲቀጥል የህዝቡን ድምጽ ሰምቶ መስራት፤ ይሄን በሽታ እንዴት እንለፈው በሚል ከጤና ሚኒስቴር የሚተላለፉ መልዕክቶችን ተፈጻሚ በማድረግ፤ ተገቢውን የመከላከልና የህክምና ቁሳቁስ አቅርቦት ስራን በማከናወን ህዝቡን ለማሻገር መስራት ይኖርበታል፡፡

አዲስ ዘመን፡- ከዚህ ጋር በተያያዘ ህወሓት ምርጫው መካሄድ አለበት፤ ይህ ደግሞ የትግራይ ህዝብ ራስን በራስ የማስተዳደር ህገ መንግስታዊ መብቱን ተግባራዊ የሚያደርግበት ነው:: በመሆኑም ሌሎች ክልሎችም ይሄንኑ ተገንዝበው ምርጫ ለማካሄድ መወሰን አለባቸው፤ ሲል ይደመጣል:: በዚህ ላይ የእርሶ እይታ ምንድን ነው?
አቶ ደረጀ፡- ህወሓት ምርጫ ይካሄድ ብሎ የሚያወራው ለህዝቡ አስቦ አይደለም፤ ለራሱ ነው:: ይሄም ለራሱ አፍኖ በያዘው አካባቢ ለቀጣይ አምስት ዓመት ቀጣይ ኮንትራት ለማግኘት እና ያንን ዋስትና ለመያዝ ነው:: ይሄ በዚህ ጊዜ ምርጫ ይካሄድ ማለት ደግሞ ለህዝብ አለማሰብ ነው:: ይሄንን አይነትና አባባልና አካሄድ ደግሞ ማንኛውም ክልል አይቀበለውም:: ይሄንንም ምናልባት ከህወሓት ጋር አብረው የቆሙት አራት ያክሎቹ ካልሆኑ በስተቀር በቀላሉ ከጥምረቱ አባል ፓርቲዎች መረዳት ይቻላል:: ለምሳሌ፣ ጎረቤቱ ያሉ የአፋር ፓርቲዎች ይሄን አካሄድ ስለማይቀበሉ እዚሁ አዲስ አበባ ነው ስብሰባ የመጡት:: ከእኛው ጋር ምርጫው መራዘም አለበት ብለው ወስነው ነው የሄዱት:: ከአፋር ድረስ የመጡትም ሆነ የሌሎች ብሔር ብሔረሰቦች አባል ፓርቲዎች በዚህ መልኩ ምርጫው መራዘም አለበት ብሎ የጋራ ውሳኔ ላይ መድረስ ደግሞ ለራስ ስልጣን ሳይሆን ለህዝብ ከማሰብ የሚመነጭ ቅድሚያ ለህዝብ ደህንነት መስጠት እንደሚገባ በግልጽ ያሳየ እርምጃ ነው፡፡ ይሁን እንጂ ስለ ምርጫ የትግራይ ህዝብ ከሌላው የኢትዮጵያ ህዝብ የሚለይበት ሁኔታ የለውም:: የትግራይ ህዝብና የኢትዮጵያ ህዝብ አንድ እስከሆነ ድረስ ህወሓት ብቻውን ተነስቶ ምርጫ ላካሂድ ማለቱ ለምንድን ነው? የሚለው በራሱ መታየት ያለበት ነው:: ምክንያቱም ብቻውን ምርጫ ቢያካሂድ እንኳን ፓርላማ እዛ ሊቋቋም ነው ወይስ 38 የፓርላማ አባላት ከተመረጡ በኋላ እዚህ ያሉትን ተክተው አዲስ ሊገቡ ነው? ወይስ በትግራይ ብቻ ተወስኖ ሊቀር ነው? የሚለውን እንኳን በወጉ ያላገናዘበ ነው:: እናምአገራዊ ምርጫ ሲካሄድ አንድ እና የፌዴራል ምክር ቤቱን ጨምሮ እስከ ወረዳ ያሉ የምክር ቤት አባላት የሚመረጡበት ነው:: የምርጫ ዘመናቸውም አንድ ነው:: ይሄን ችግር ተከትሎ ምርጫው የተላለፈው እንደ አገር እንደመሆኑም፤ ሶማሌ፣ አፋር፣ አማራ፣ ኦሮሞ፣ ሐረሪ፣ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ፣ ጋምቤላ፣ አዲስ አበባ፣ ደቡብ፣ ወይም ድሬዳዋ ለብቻዬ አካሂዳለሁ ሳይሉ ሁሉም ናቸው እንዲተላለፍ የወሰኑት፡፡ ይህ ደግሞ ሊሆን የሚገባው እና ተገቢም እርምጃ ሲሆን፤ ለህዝቦቻቸው ደህንነት ያላቸውን ተቆርቋሪነት እና ከምንም በፊት ለህዝብ ጤንነት መጨነቃቸውን ያሳያል:: ከዚህ ባለፈም እንደ አገር የተላለፈ ውሳኔን አንዱ ክልል ተነስቶ እኔ ውሳኔውን አልቀበልም ስለዚህ በክልሌ ምርጫ አደርጋለሁ ሊልም አይችልም:: ቢልም ማድረግ አይችልም:: ምክንያቱም አካሄዱ ሰዋዊም ሆነ ህጋዊ መሰረት የለውም:: እናም እንደ አገር የተወሰነ ውሳኔን አንዱ እንደፈለገ ተነስቶ ካላካሄድኩ ብሎ ቡራ ከረዩ ካለ ይህ ለእኔ ሕገ ወጥነት ነው:: ከዚህ አኳያ የህወሓት ፉከራም ሆነ ነገ አንዱ ክልል ተነስቶ ምርጫ ላካሂድ ቢል ይህ ህገ ወጥ ከመሆኑም ባለፈ በህዝቦች ጤናና ደህንነት ላይ መቀለድ ነው:: እናም ይህ አካሄድ የቀልድ እና በህዝብ መጫወት፣ ከማን አለብኝነት የሚመነጭ ለህዝብም ክብር አለመስጠት ነው:: ከዚህ ባለፈ ግን ተግባሩ አጀንዳ ፈጥሮ የትግራይን ህዝብ አዕምሮ በዚህ የመያዝ ጉዳይ ካልሆነ በስተቀር አንድ ምርጫ ቦርድ እንዳለ እና ምርጫውም በአገር አቀፍ ደረጃ እንደሚካሄድ እየታወቀ ምርጫው እንደማይካሄድ እሙን ነው:: ይሄንንም ህወሓት በደንብ ያውቀዋል፡፡
[አዲስ ዘመን እሁድ ግንቦት 16 ቀን 2012 ዓ.ም ገጽ 15]

https://vdocuments.mx/-oe-oe-f-oe-aa.html
eden wrote:
31 Oct 2020, 09:27
Hey guys

Need your input for my new research.

Here's a question for you to reflect on and answer.

If TPLF changes its long standing position and rejects nation & nationalities based organization in Ethiopia, will this change your heart and mind on whether you oppose or support and how intensely you oppose or support it?

Would and should Abiy and Isayas work with TPLF if TPLF renounces nation & nationalities based organization?



.
Last edited by YAY on 01 Nov 2020, 01:21, edited 1 time in total.

tolcha
Member
Posts: 3585
Joined: 27 Feb 2013, 16:51

Re: Your opinion is needed here please

Post by tolcha » 01 Nov 2020, 00:00

Eden,
The notion of ethnic based federal system has a lot of problems, especially for those ethnics with large population like Oromo and Amharas. There will be a fight between subclans/ regions/ religion based in each ethnics for power. Forget the conflict between different ethnics. The solution is simple. Let the war erupts and those who survived would come to their sense and live in harmony.

YAY
Member
Posts: 943
Joined: 21 Aug 2013, 11:51

Re: Your opinion is needed here please

Post by YAY » 01 Nov 2020, 00:03

Dear Eden: You may consider this as background knowledge for your research

Any improvement displayed by the MLLT/TPLF (Tigraiy People's Liberation Front) might appear to be better than never, but the issues that cause problems to Etiyopiya and Eritrea are more than just the case of a federal State structure based on nations and nationalities. The fundamental problem with MLLT/TPLF leaders is the fact that they are not true to themselves and others. Do you know how one could tell when they are lying? When they open their mouths to talk. Deception seems to be their over-arching modus operandi (i.e. their established way of doing things). Read the following interview (part 3) carefully as well as patiently.

አዲስ ዘመን፡- የጥምረቱን ስብሰባ በአዲስ አበባ ማድረጋችሁን እና የህወሃትን አቋም ማውገዛችሁን ተከትሎ “በገንዘብ ተገዝተው ነው” የሚል ድምጽ እየተሰማ ነው:: ይሄን ምን ያክል እውነት ነው? ከዚህ በኋላስ የጥምረቱ የፖለቲካ ተሳትፎና አካሄድ በምን መልኩ የሚቀጥል ነው?
አቶ ደረጀ፡- ከስም ማጥፋቱ ጋር በተያያዘ እኔ በፊትም ከህወሓት ጥሩ ነገር አልጠብቅም:: ከበደ ወይም ደረጀ ገንዘብ ወሰደ የሚሉትንም በተመለከተ ሁሉም እዚሁ ስላሉ ማረጋገጥም ይቻላል:: ካለም ከማን ወሰዱ የሚለውን በግልጽ መናገር ይገባቸዋል:: ዋናው ነገር ይሄን ያናገራቸው እነርሱ በፋይናንስ ምክንያት የዓላማቸው ማስፈጸሚያ ሊያደርጉ ያሰቡበትን አካሄድ ሰብረን አዲስ አበባ ስብሰባችንን ማድረጋችን የፈጠረባቸው ስብራት ለማካካስ የሚያደርጉት ስም የማጥፋት ሙከራ መሆኑን መረዳት ይገባል፡፡ አዲስ አበባ ያካሄድነው ስብሰባም ቢሆን ቀደም ብዬ እንደገለጽኩት ህወሓት ይናንሱን ለመደገፍ ፈቃደኛ አለመሆኑን ተከትሎ ሁለት ባለሃብቶች ስፖንሰር አድርገውን ያካሄድነው ነው፤ በዚህ ድጋፍ ሂልተን ሆቴል ተከራይተን ስለተሰበሰብን መንግስት ወይም ብልጽግና ፓርቲ ሰጣቸው ብለው የሚናገሩትን የተሳሳተ ነገር ከጭንቅላታቸው ቢያስወጡ መልካም ነው:: ምክንያቱም ይሄ የስም ማጥፋት ዘመቻቸው ድሮም የተለመደ እና የተካኑበትም ስለሆነ፤ ሲያደርጉትም የኖሩት ስለሆነ እንጂ እኛ አሁንም ሆነ ድሮም የምንኖረው በራሳችን ነው፤ በቀደም ያካሄድነውን ስብሰባም እነዚህ ሁለት ድርጅቶች ናቸው የረዱን እንጂ ከመንግስት ያገኘነው አምስት ሳንቲም የለም:: ብልጽግና የሚባል ፓርቲ ለእኛ ምንም አይነት ድጋፍ አላደረገልንም፡፡ በመሆኑም እኛ አሁንም ቢሆን ለወደፊቱ ስብሰባ ብንጠራም ሆነ ቢሮ ብንከፍት በእነዚህ በፌዴራሊዝም እምነት ባላቸው ባለሃብቶች ድጋፍ ነው:: ይሄን የሚያደርጉትም በፌዴራሊዝሙ ማንነታችን ይከበራል ብለው ስለሚያምኑ፤ እኛም እንደ ተፎካካሪ ፓርቲ ጠንክረን እንድንወጣ ፍላጎት ስላላቸው ነው:: ለምሳሌ፣ ጽህፈት ቤት ፈልጉ ለአንድ ዓመትና ለሁለት ዓመት እንከፍልላችኋለን፤ የቢሮ ቁሳቁስ እናሟላላችኋለን ያሉን የግል ድርጅቶች አሉ::የሂልተንን ክፍያ በራሱ ለጥምረቱ ተሰጥቶ የተከፈለ ሳይሆን ራሳቸው ናቸው ሄደው የከፈሉት:: ይሄን መንግስት ወይም ብልጽግና ፓርቲ ወይም ሌላ ድርጅት ሳይሆን ባለሃብቱ ነው እያደረገ ያለው:: አለ ካሉ ደግሞ ማቅረብ ይችላሉ፤ ይኖርባቸዋልም:: ደግሞም አላደረገውም እንጂ እንዳሉት ብልጽግና ፓርቲ የደገፈን ቢሆን ኖሮ እነርሱስ ሲሰጡን ከርመው የለም እንዴ? እነርሱ ከየት አምጥተው ነው ሲሰጡን የነበረው? ከህዝብ ጉሮሮ ነጥቀው፣ ከመንግስት ካዝና አውጥተው ነው እኮ:: ለራሳቸው ጥቅም ሲሉ ህዝባቸው ስንት የሚያስፈልገው ነገር እያለ አይደል እኛን የአውሮፕላን ትኬት ቆርጠው፤ ሆቴል ይዘው፤ ምግብ ችለውና አበል ከፍለው ሲያመላልሱንና ሲያዝናኑን የነበረው:: አልሆነም እንጂ ቢሆንና እንደነርሱ ሁሉ አንዱ ፓርቲ መጥቶ ቢረዳን ምን ችግር አለው? እናም ይህ ውንጀላ ሀሰተኛ የህወሓቶችና ግብራበሮቻቸው ሩጫ አካል ነው ፣ የራሳቸውን ለመደበቅ ሌሎችን ስም ባልሆነ መንገድ ለማጠልሸት የሚደረግ ጥረት መሆኑ ሊታወቅ ይገባል፡፡ ከዚህ ባለፈ ቀጣይ የእኛ የፖለቲካ ተሳትፎ የሚሆነው እና በተሳትፏችንም ለመስራትም እንዲሆንም የምናስበው በኢትዮጵያ የተረጋጋ መንግስት እንዲኖር፤ ኢትዮጵያም ልማቷ እንዲፋጠን፤ የኢትዮጵያ ህዝብ ደህንነቱ ተጠብቆ በሰላም አብሮ እንዲኖር፤ ባህልና እሴቱን አጎልብቶ ታሪክ ሰሪም የታሪክ ባለቤትም የሚሆንበት ሁኔታ እንዲፈጠር ነው:: ከዚህ በተጓዳኝ አሁን ላይ የምንሰራውም ሆነ የምንመኘው ህዝባችን የህዝባችን ጤና ተጠብቆ በሳላም ይሄን ወረርሺኝ እንዲያልፈውና ቀጣይ የሚከናወነው ምርጫም ህዝብ በነጻነት የሚፈልገውን መምረጥ የሚችልበት እድል እንዲፈጠር ነው:: ምክንያቱም ሁሉም ነገር የሚሆነውና የሚያምረው ህዝብ ሰላምና ጤና ሲሆንና የህዳሴ ግድባችንን ስናጠናቅቅ ነው:: ምርጫ ከዛ በኋላ ነው መሆን የሚችለው፡፡ ምክንያቱም ምርጫ ማለት ለጥቅም የሚፈልጉት ካልሆነ በስተቀር የምትመረጠው ህዝብን ዝቅ ብሎ ለማስተዳደርና ለህዝብ ለመገዛት እንጂ እንደከዚህ ቀደሙ በህዝብ ጭንቅላት ላይ ለመቀመጥ አይደለም:: እናም ምርጫው የተፈለገው ህዝብን ለማገልገል ከሆነ ይሄን ያህል ሩጫና ጥድፊያም አያስፈልግም:: ህዝቡ ከፈለገህ በማንኛውም ጊዜ ይመርጥሃል:: ይሄንንም እኔ ቀደም ሲል ወደ ምክር ቤት ስገባ የበደሌ ህዝብ በመረጠኝ ጊዜ ተገንዝቤያለሁ:: እናም የራስን የምርጫ ዓላማ ከህዝቡ ፍላጎት ጋር አጣጥሞ ማስኬድ፤ ለራስ ጥቅም ሳይሆን ህዝብን ለማገልገል፤ እንዲሁም በህዝብ ምርጫም ማንኛውም ፓርቲ አሸንፎ ስልጣን ላይ ቢወጣም አሜን ብሎ ለመቀበልም ዝግጁ መሆን ይገባል እንጂ በጀብደኝነትና በማን አለብኝነት የሚሆን መሆን የለበትም:: እኛም በቀጣይ የሚኖረን ተሳትፎና አካሄድም ይሄንን መሰረት ያደረገ ነው የሚሆነው፡፡

አዲስ ዘመን፡- ዛሬ ላይ ኮሮናን ተቋቁሞ ከማለፍ እና ነገ ውጤታማ/የተሳካ ምርጫ ከማካሄድ አኳያ በማን ምን መሰራት ይኖርበታል?
አቶ ደረጀ፡- ከሁሉም በፊት ቅድሚያ የሚሰጠው ይሄን አስቸጋሪ ጊዜ ማለፍ ነው:: ምክንያቱም ምርጫ የሚመረጠው ህዝብ ሲኖር እንደመሆኑ፤ ወጣቱም ሆነ ሁሉም ዜጋ ከዚህ በሽታ ራሱን መጠበቅ አለበት:: ባለው ሁኔታም የሞቱትን ነፍስ በሰላም እንዲያርስ፤ የታመሙትን ፈውስን እንዲያገኙ ምኞትም ጸሎታችንም ነው:: በህመሙ ያልተያዙት ደግሞ ራሳቸውን መጠበቅ ያለባቸው ሲሆን፡ ለዚህም የጤና ሚንስትር የሚየወጣውን መመሪያና ምክረ ሀሳብ መተግበር ይገባለ፣ ርቀትን መጠበቅ፣ በተቻለ መጠን ቤት መቆየት፣ እጅን መታጠብና የመሳሰሉት ደግሞ ተገቢ ነገሮች ናቸው:: በዚህ መልኩ ህዝቡ ራሱን ከጠበቀ እና በመንግስት በኩልም አስፈላጊው ስራ ከተሰራ ኢትዮጵያ ከዚህ ወረርሽን ነጻ ትወጣለች:: ይህ ሲሆን ነው ስለምርጫ ማሰብ የሚቻለው:: በዚህ ወቅትም ወረርሽኙን በመከላከል ሂደት ውሰጥ ሁሉም የየራሱ ሃላፊነት ይኖረዋል፡፡ ለምሳሌ፣ በመንግስት በኩል ህዝቡ በፍላጎቱ እንዲመርጥ የሚችልበትን እድል መፍጠርና መስጠት አለበት:: የአንድ ፓርቲ ምክር ቤት ማየት ስለማንፈልግ ህዝቡ የፈለገውን ይምረጥ:: ምክንያቱም የተለያዩ ፓርቲዎች የተሰባሰቡበት ምክር ቤት እንዲኖረን ያስፈልጋል:: የሀሳብ ልዩነቶች የሚንሸራሸሩበትም የሚስተናገዱበትም ምክር ቤት ማየት እንፈልጋለን:: የህዝባችን ጥያቄ የሚሰማበት ምክር ቤትም ማየት እንፈልጋለን:: አንድ አዋጅ ሲቀርብ ክርክር የሚነሳበትና በክርክር ዳብሮ የሚያልፍበትን ሁኔታ ማየት እንፈልጋለን:: ምክንያቱን አሁን እንዳለው የአንድ ፓርቲ ስብስብና አንድ አይነት ሀሳብ የሚንጸባረቅበት ሳይሆን አገራዊ ሁነቶችና ፍላጎቶች ተነስተው ሰፊ ውይይትና የህዝብ ሀሳቦች የሚንሸራሸሩበት የክርክር አውድ ሊኖረው ያስፈልጋል:: በዚህ መልኩ የህዝቦች ድምጽ የሚሰማበት፣ ተወካዮቹም የአከባቢያቸውን ድምጽ ለፓርላማው ማቅረብ፣ የአገራቸውን ፍላጎትም ለዓለም አቀፍ መድረክ ማሰማት የሚችሉ መሆን አለባቸው:: ይህ ሲሆን ነው ኢትዮጵያ ኢትዮጵያን መሆን የምትችለው፡፡ ለዚህ ደግሞ መንግስትም ሆነ ያሉት ድርጅቶች ህዝብን ነጻ በማድረግ በነጻ ፍላጎታቸው እንዲመርጡ እድል መስጠት አለባቸው:: አንተ አገሌን መረጥክ ተብሎ ተጽዕኖ ሊደረግበት እና ሊታሰር ሊገረፍ ሊሰደድ አይገባም:: ምክንያቱም ሁሉም ዜጋ የአገሩ ባለቤት፤ ለአገሩም ተጠያቂ ነውና :: ስልጣን ላይ ያለው ብቻም ሳይሆን ተፎካካሪውም የአገሩ ባለቤት እንደመሆኑ ይሄን ታሳቢ አድርጎ ሊንቀሳቀስም ሊሰራም ያስፈልጋል:: ከህዝባችን የሚጠበቀውም፣ ህዝብ የአገር ባለቤትነቱን በተግባር የሚያረግግጥበትን አካሄድ መከተልና ለጋራ ሰላሙና ደህንነቱ በጋራ ሊሰራ ያስፈልጋል::ስለዚህ ምርጫው በዚህ መንፈስ መካሄድም፤ እስካሁን የተለመደውን የሌብነትና ማጭበርበት አስቀምጦ ትቶ በነጻነት መመረጥም አለበት:: በህዝብ የተመረጠውንም አሜን ብለን መቀበል አለብን:: በመሆኑም ምርጫው አዲስ አካሄድና አጀንዳ የሚታይበት አዲስ ምዕራፍ መክፈቻ ሊሆን ይገባል:: ለዚህም መንግስት፣ የፖለቲካ ፓርቲዎችና ህዝቡ የሚጠበቅበትን አውቆ በአገራዊ ሃላፊነት ስሜት መንቀሳቀስም መስራትም ይጠበቅባቸዋል፡፡

አዲስ ዘመን፡- በመጨረሻም እድሉን ልስጥዎ እና በወቅታዊና አገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ የሚያስተላልፉት መልዕክት ካለ ቢያስተላለፉ?
አቶ ደረጀ፡- እኔ የምለው ህዝባችን በተለያዩ ፓርቲዎች ወይም ድርጅቶችና ግለሰቦች ሳይወናበድ አገሩን በአንድነት መጠበቅ አለበት:: ለህዳሴ ግድቡም ከዳር መድረስ በአንድነት መስራት አለበት:: ለዚህ እውን መሆንም ሆነ አሁን ወረርሽኝ ሆኖ አደጋ እየጋበዘ ያለውን የኮሮና ቫይረስ ለመከላከል የሚያደርገው ጥረት እንደ አንድ ሰው መስራት ይኖርበታል:: በመንግስትና ጤና ሚኒስቴር የሚያወጣውን መመሪያ መፈጸም ይጠበቅባቸዋል:: ምክንያቱም ፖለቲካ ያልፋል፤ ፓርቲና አስተዳደርም ያልፋል፤ እንደ ንጉሳውያኑ፣ የደርግ እና የኢህአዴግ ስርዓት ማለፍ ሁሉ የብልጽግና ፓርቲ ዘመንም ጊዜውን ጠብቆ ያልፋል:: የማያልፉት ህዝብና አገር ናቸው:: እኛ እንኑርም አንኑርም አገር እንደ አገር ትኖራለች፤ ህዝብም በትውልድ ቅብብሎሽ ውስጥ ይዘልቃል:: ስለዚህ ይሄን ተገንዝበን፣ እኛ እንደ ሰው የምናልፍ ቢሆንም አገርና ህዝብ ዘላቂ መሆናቸውን ተገንዝበን ለአገርና ህዝብ ደህንነት ቅድሚያ ሰጥተን መስራት ይገባናል፡፡ ከዚህ ውጪ ለፖለቲካ ብለን ወይም በአንዳንድ ምክንያቶች መተሳሰርና መገዳደል የመሳሰሉትን መተውና ማቆም፤ በአንድነትም መንቀሳቀስ አለብን:: አንድ ከሆንን እንጠነክራለን፤ ከተለያየን ግን እንላላለን፤ እንፈርሳለን::ስለዚህ አንድነታችንን ማጠናከርና በአንድነት መነሳት አለብን:: ፖለቲካውም ሆነ ሁሉ ነገር አላፊ ነው፤ አንድነታችን ግን ማለፍ የለበትም:: ከዚህ ውጪ እና እንደ ፓርቲ የፌዴራሊስት ኃይሎች በመላው ኢትዮጵያ ይንቀሳቀሳል:: በመላ ኢትዮጵያ የሚንቀሳቀሰውን ኃይል ደግሞ ሕዝባችን ከጎኑ ሊሆንና ካጠፋ ከጥፋቱ እንዲታረም፤ ካለማም በልማቱ እንዲጠነክር ሊያግዘው ያስፈልጋል:: የጥምረቱ አባሎች ደግሞ ከህብረተሰቡ ጎን ሆነው በተለይም አርሶ አደሩ ከወረርሽኙ ራሱን ጠብቆ የምግብ እህል እጥረት እንዳያጋጥም ጠንክሮ እንዲሰራ ከጎኑ ሆነው ሊያግዙትና ሊያበረታቱት ይገባል፡፡

አዲስ ዘመን፡- ለቃለ ምልልሱ ስለተባበሩኝ አመሰግናለሁ፡፡
አቶ ደረጀ፡- እኔም አመሰግናለሁ፡፡

https://vdocuments.mx/-oe-oe-f-oe-aa.html

eden wrote:
31 Oct 2020, 09:27
Hey guys

Need your input for my new research.

Here's a question for you to reflect on and answer.

If TPLF changes its long standing position and rejects nation & nationalities based organization in Ethiopia, will this change your heart and mind on whether you oppose or support and how intensely you oppose or support it?

Would and should Abiy and Isayas work with TPLF if TPLF renounces nation & nationalities based organization?



.

EPRDF
Member
Posts: 2162
Joined: 26 Jan 2010, 12:58

Re: Your opinion is needed here please

Post by EPRDF » 01 Nov 2020, 01:02

eden wrote:
31 Oct 2020, 09:27
Hey guys

Need your input for my new research.

Here's a question for you to reflect on and answer.

If TPLF changes its long standing position and rejects nation & nationalities based organization in Ethiopia, will this change your heart and mind on whether you oppose or support and how intensely you oppose or support it?

Would and should Abiy and Isayas work with TPLF if TPLF renounces nation & nationalities based organization?
ehte eden

The answer to your question depends on one own ethnic political perspective. So if you go to the house of nation nationalities of Ethiopia, the overwhelming majority of Ethiopians had supported TPLF for its Ethnic politics assuming that it will bring some sort of ethnic equality to the nation. But the experiment brought them disaster than the anticipated equality and prosperity hence as of today they might have a different outlook towards politics of identity so if TPLF abandons its Behereseb policy, well it may not lose much of its support base rather a new and different political approach may renew and strengthen its relationship with Bhereseboch in particular and with Ethiopian politics at large.

If you go to Amhara political house with this same question, for sure you will be getting a different answer.

Amharas grievance towards TPLF is not only about its ethnic politics but it is more of its bringing ye Amhara solomonite Ethiopia to its grave to be buried for good. And for this very reason, Amharas have no mercy for TPLF no matter what. Whether TPLF abandons its stance on Ethnic politics or not, Amharas will not rest until TPLF is going 6feet under and buried just like TPLF had buried emama Ethiopia they created in their image.

Well if you go searching for an answer to your question in Geza Isayas and Eritreans, the feeling of hate and grudge towards TPLF is going to be even worse than that of Amharas have in heart towards TPLF. Isayas or Eritreans do not care whatever form of a political program is being adopted by TPLF or any other political entities. The former Tegadelti comrade in liberating Tigray and Eritrea, TPLF, had betrayed Shaabiya its alliance in blood and controlled Ethiopian resource, kicked all Eritreans out of Ethiopian soil barefoot, and lived fattening its bank account for twenty-seven years is too much for Eritreans to forget and forgive for generations to come. The beef between TPLF and Eritrea is not politics of ethnicity or politics, it is rather a personal family feud.

I am optimistic to say that my insight is very helpful for your research because I'm here not to appease or to offend someone, but to tell the truth as it should be. So please take my account seriously with Regards.

Noble Amhara
Senior Member
Posts: 11715
Joined: 02 Feb 2020, 13:00
Location: Abysinnia Highlands

Re: Your opinion is needed here please

Post by Noble Amhara » 01 Nov 2020, 01:15

EPRDF

you big fcking lair giving credit where it does not belong DERG got rid of Solomonic Ethiopia not TPLF. Amharas hate TPLF because they made us live and go through hell sterilization genocide massacre oppression marginalization and poverty for over 30 years the “Ethnic Sustem” literally wasn’t even that ethnic it gave Tigrayan AGAMES from Adwa 96% control of the government for decades only Tigray benefited during those dark days they also brainwashed millions of oromos and other tribes to demonize and hate amharas TPLF would create Fairy tales in order to dehumanize amharas basically millions of amharas outside of Amhara region lost there right to life and right to being Ethiopian/human being and were propagated by TPLF devils to be subhuman cockroaches TPLF also looted Amhara region and her lands. Metekel Alamata Welkait Debre Libanos (North Shewa) belong to Amhara! Shewan cities like Nazret/Debrezeyt should have been there own municipalities in order to serve a MULTIETHNIC Ethiopia! TPLF designed a system where oromi gets all the land and regions having full federal rights as seen in the region/zone system

info
Member
Posts: 3637
Joined: 05 Dec 2014, 11:33

Re: Your opinion is needed here please

Post by info » 01 Nov 2020, 01:38

EPRDF wrote:
01 Nov 2020, 01:02
Amharas grievance towards TPLF is not only about its ethnic politics but it is more of its bringing ye Amhara solomonite Ethiopia to its grave to be buried for good.
eden wrote:
31 Oct 2020, 09:27
Hey guys
Need your input for my new research.
Here's a question for you to reflect on and answer.
If TPLF changes its long standing position and rejects nation & nationalities based organization in Ethiopia, will this change your heart and mind on whether you oppose or support and how intensely you oppose or support it?
Would and should Abiy and Isayas work with TPLF if TPLF renounces nation & nationalities based organization?
EPRDF, the problem with many TPLF cadres is that they don't use their brains but simply chew TPLF propaganda without questioning. The fact is TPLF never fought against Amhara Solomonite as you described or any so called neftegna system. Never! Derg is the one that destroyed the solomonite dynasty and also the so called neftegna/feudal system. TPLF is just claiming what they never fought against and never won as liars they are and the cadres of course repeat the lies as dumb as they are.

eden, TPLF has a much deeper problem than that can be fixed by a policy change. TPLF is a very authoritarian junta, very divisive (always tries to gain something by creating enmity between two camps like you always try to do between Eritreans and Ethiopians). It never sees it can gain something from positive energy like cooperation, mutual benefit etc. It is a very destructive and negative force, always seeking and manipulating enmity, hatred, division etc. That is where it thinks to gain not from mutual benefit and the good and positive. TPLF is also a very insecure organization even in Tigray it always sees its opponents as deadly enemies and tries to label and eliminate them and most of all it has a huge credibility problem because of its endless lies. Lies and TPLF are like twins. It has simply no shame when it lies. Even if tomorrow it declares it has changed its policies, I doubt any sane man would believe it unless may be a new generation of honest leadership comes to the front. No one will believe the old guard no matter what they say and do in my view. 27 years is more than enough to know the character of an organization and only low IQ fools will trust TPLF while the old guard is leading. I have no idea why but TPLF and its cadres always think in gaining something by doing and manipulating evil. They love negative energy and divisiveness for some weird reason. I never understood their mentally sick nature.
The best outcome for TPLF is for the moderators (if they exist any) to work with the federal government and get rid of the radical, wicked and evil who are leading tigray into a catastrophic path. Then bring new fresh leadership that believe in positive energy than evil and negativity. Leadership change and getting rid of the radicals is a must if TPLF wants to start a fresh.

Naga Tuma
Member+
Posts: 5545
Joined: 24 Apr 2007, 00:27

Re: Your opinion is needed here please

Post by Naga Tuma » 15 Nov 2020, 17:59

eden wrote:
31 Oct 2020, 09:27
If TPLF changes its long standing position and rejects nation & nationalities based organization in Ethiopia, will this change your heart and mind on whether you oppose or support and how intensely you oppose or support it?
eden,

The inconsistency of wanting a country and not wanting a nation notwithstanding, how do you logically reconcile the inconsistency in the reporting in the international media and your old position? There are many instances when the international media refers to Ethiopia as a nation. A case in point is when it reports about the negotiations between Ethiopia, Sudan, and Egypt. It says the negotiations between the three nations instead of the nations of Egypt, Sudan, and the nation and nationalities of Ethiopia. I know you are a man of logic. So, have you found a logical reconciliation for these inconsistencies? In addition, don't you think the description nation and nationalities is a hangover from the old quest to destabilize the country and that it is an arrogant reference to the nationalities that they are equal and less equal at the same time?

I am hearing in the news that cities in the north of Ethiopia are falling into the hands of federal forces. አቦይ ስብሃት በስተእርጅና መዘለፍ መሮት ኣንዱን የኣክሱም ሃዉልት ነቅሎ እየዞረ በቆረጣ ያሳድድ ይሆን ብዬ ሳስብ ተራ በተራ እያሳፈሩ ማራገፍ መጣላቸዉ?

Post Reply