Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Post Reply
yaballo
Member
Posts: 3944
Joined: 16 Feb 2013, 02:30

EVIL! በሻሸመኔ በቄሮዎች ተሰቀሎ ተገደለ ተብሎ ያሁሉ ዳንኪራ የተመታለትን ግድያ ያቀናበረው ትናንት የመዳ-ወላቡ ዩኒቨርሲቲ መምህርን የረሸነው የብልፅግና አባልና የፀጥታ ክፍል ሃላፊ ነው

Post by yaballo » 29 Oct 2020, 07:31

ETHIOPIA REMAINS TO BE AN EVIL የሴረኞች EMPIRE. በሻሸመኔ በቄሮዎች ተሰቀሎ ተገደለ ተብሎ ያ ሁሉ ዳንኪራ የተመታለትን ግድያ ያቀናበረው ትናንትና የመዳ-ወላቡ ዩኒቨርሲቲ መምህርን የረሸነው የብልፅግና ፓርቲ አባልና የፀጥታ ክፍል ሃላፊ መሆኑ ተረጋገጠ። የሴረኞች ሃገር ከቶዉንም የፍትህና የዲሞክራሲ ሃገር አትሆንም። :oops:


photo: this was a youth ostensibly murdered by Oromo "qeerros" in Shashamane town about two years ago. However, reports are coming-in that indicate that the murder was orchestrated by regime cadres to besmirch/darken the name of the qeerros & redefine them as "a bunch of hooligans". The same town has seen several deadly plots staged by Abiy's own cadres to frame his Oromo political opponents & tarnish the name of the qeerros. The recent murder of a Mada-Wolabu's university teacher in Shashamene is also being reported as a staged plot by the same bunch of non-Oromo PP cadres & security officers.
#inbox [29-10-20]
የሻሸመኔዉን የተሰቀለ ወጣት ስቅላት ያቀናበረዉ ሰዉ ነዉ ዛሬም በዛች የምዕራብ አርሲ ዞን ከተማ በሆነች ብዙ የተቀናበሩ ወንጀሎችን እየከወነ ነው። በዕለቱ በከተማዋ ለጀዋር የአቀባበል ሥነ-ሥርዓት ለማድረግ ከዞኑ ዙሪያ የገጠር ወረዳዎች ከ4,000,000 በላይ ሕዝብ በከተማዋ ተገኝቶ ነበር፥ከፍተኛ መጨናነቅ ስለነበር በከተማዋ በየትኛዉም አከባቢ የእግር መርገጫ ችግር ነበር።

በዕለቱ የዚህች ከተማ ፀጥታ ዘርፍ ኃላፊ የነበረዉ አቶ ናደዉ በአሁን ሰዓት ከኃጫሉ ግድያ በኋላ በሻሸመኔ ከተማ በተፈጠረዉ ግርግር ምክንያት በእስር ላይ የሚገኝ ሲሆን በዕለቱ ከጀዋር ጋር በሻሸመኔ ከተማ ስታዲዬም ፕሮግራሙን ለመታደም ተቀምጦ ነበር።የከተማዋም ከንቲባ አብሯቸዉ ነበር። በከተማዋ ዉስጥ ግን በአሁን ሰዓት የከተማዋ ፀጥታ ዘርፍ ኃላፊ ሆኖ የሚሠራዉ ስንታየሁ ጥላሁን በወቅቱ አቶ ናደዉ ይይዛት የነበረችዋን የማዘጋጃ ቤቱን መኪና ይዞ ይንቀለቀል ነበር። ሌሎችም የተለያዩ በከተማዋ ዉስጥ ይንቀሳቀሱ የነበሩ የደኅንነት ሠራተኞችም በልብሳቸዉ ላይ የሚጣበቅ ካሜራ ሳይቀር ታጥቀዉ በከተማዋ ዉስጥ ይንቀሳቀሱ ነበር።

በመሐል ሆን ተብሎ አንድ ወጣት በጀዋር ላይ ጥቃት ሊያደርስ ነዉ ተብሎ በቁጥጥር ስር ዋለ። በመቀጠልም የፀጥታ ሠራተኞች ወስደዉ በአቅራቢያዉ የሚገኝ የቀበሌ እስር ቤት ዉስጥ ካሰሩት በኋላ አመፀኛ መስለዉ በእነ ስንታየሁ ጥላሁን ተዘጋጅተዉ የነበሩ ከተለያየ የዞኑ ከተማዎች የመጡ ቦዘኔዎች ካላወጣችሁልን ካልገደልነዉ ብለዉ ከፍተኛ አመፅ አነሱ። በዚህም መሐል ያ መጀመሪያ የተያዘ ሰዉ ይሁን ወይንም ሌላ ለመስዋዕትነት ያዘጋጁት ሰዉ ከእስር ቤት ወጥቶ በፀጥታ ሠራተኞች አማካኝነት ተሰጣቸዉ። የተሰጣቸዉንም ወጣት ያንን ድፍን አለም ያየዉን ዓይነት ትዕይንት ፈፀሙበት። በመቀጠል ወጣቱ አስከሬኑን ቤተሰቦቹ ወስደዉ የትዉልድ መንደሩ ቀብረዉታል ተብሎ በእነ ዶክተር ነገሪ ሌንጮ ሳይቀር የተነገረዉ ዜና ፈፅሞ ዉሸት እና ከእዉነት የራቀ ሲሆን ዕሁድ የተገደለዉ ወጣት ረቡዕ ማታ የከተማዉ ማዘጋጃ ቤት እንደቀበረዉ መረጃዎች አሉ። ድርጊቱ ግን የቄሮን ሥም ለማጠልሸት በእነ አቶ ስንታየሁ ጥላሁን የተቀናበረ አደገኛ ሴራ ነበር።

በዛኑ ቀን አቶ ስንታየሁ ይዟት የነበረችዉ እና ይህን ጉዳይ ለማቀናበር ይዟት ይንቀለቀል የነበረች መኪና በእነዚሁ እራሱ ከተለያዩ የዞኑ ከተማዎች ባሰባሰባቸዉ አደገኛ ቦዘኔዎች አራት እግሯን ወደ ላይ ሰቅለዉ አንድደዉ አመድ አድርገዋታል። በአሁን ሰዓት ስንታየሁ ጥላሁን የሻሸመኔ ፀጥታ ዘርፍ ኃላፊ ነዉ። የቅርብ ቀኗንም የመደ ዋላቡ መምህር ፍቃዱ ቶሌራን ግድያ ያቀናበረዉ እና ቃታ ሳይቀር የሳበዉም እራሱ ነበር፤ይህን መሰል ቅንብሮች በመላዉ ኦሮሚያ መኖራቸዉ የማይታበል ሐቅ ነዉ። ኦሮሞ ንቃ!።


photo: The recent murder of a Mada-Wolabu's university teacher in Shashamene is also being reported as a staged plot by PP cadres & their allies [Gash Biramtu-saynega's gangs].MEANWHILE/u], THE LOVE AFFAIR BETWEEN THE VAMPIRE OF AFRICA'S NORTH KOREA & HIS PROTEGE IN AETHIOPIA IS BLOSSOMING THROUGH MURDERS, MASS JAILING & DISAPPEARANCES OF POLITICAL OPPONENTS ...

Post Reply