Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Post Reply
yaballo
Member
Posts: 3945
Joined: 16 Feb 2013, 02:30

NO KIDDING! "ኢትዮጲያ የቃልኪዳን ምድር ናት"። .. ከመንግስት ከተሰጠ መግለጫ የተወሰደ

Post by yaballo » 25 Oct 2020, 22:56

NO KIDDING! "ኢትዮጲያ የቃልኪዳን ምድር ናት"። .. ከመንግስት ከተሰጠ መግለጫ የተወሰደ"ኢትዮጲያ የቃልኪዳን ምድር ናት።
ኢትዮጲያን ነክቶ በሰላም የኖረ የለም።
ኢትዮጲያ በፈጣሪዋ ታምና የቆመች ሀገር ነች።"

…………………………………

<<"ኢትዮጲያ የቃልኪዳን ምድር ናት።
ኢትዮጲያን ነክቶ በሰላም የኖረ የለም።
ኢትዮጲያ በፈጣሪዋ ታምና የቆመች ሀገር ነች።"

................................
ይህ ከመንግስት ከተሰጠ መግለጫ የተወሰደ ነው።
ምን ትዝ አለኝ መስላችሁ?
የእኛ ማህበረሰብ አንድ ከባድ ሀዘን የደረሰበት ሰው ሲያጽናኑ …
"ፈጣሪ የሚወደውን ነው የሚፈትነው። ሁሉም ለበጎ ነው።" ይሉና ስጋታቸውን ደግሞ ሲገልጹ " ከዚህ የባሳ አታምጣ" በማለት ያሳረጋሉ።
………………………………………
አሁን ማን ይሙት ኢትዮጵያ "የቃል-ኪዳን" አገር ብትሆን/ ከማን ጋር ቃል ኪዳን እንዳደረገች እንጃ/ በረሃብ፡ በድርቅ፡ በእርስ በርስ ጦርነት፡ በጎርፍ፡ በአብይ፡ በስደት በግዞት በመፈናቀል… ቀዳሚ ትሆን ነበር?
እሺ "ኢትዮጵያን ነክቶ በስላም የኖረ የለም" አሁን ጣሊያን ናት በሰላም ያልኖረቺው ጭራሽ ከእኛ ተሽላ አይደለም ወይ ግዙፍ የኮንስትራክሽ ካምፓኒዋ ሳለኒ የአባይ ግድ ከፈለነው እያገነባ ያለው። ሱማሌስ ብትሆን ሌላው ቢቀር ዜጎቿ በጠረጼዛ ዙሪያ መነጋገር ችለው አይደለም ወይ አገራቸውን ማረጋጋት የቻሉት?
"ኢትዮጵያ በፈጣሪዋ ታምና የቆመች አገር ነች" እረ ለመሆኑ በምንድነው የታመነቺው? ሌላው ቢቀር ቤተ እምነቶቿ እንኳን ለፈጣሪያቸው ሊታመኑ እርስ በራሳቸው መተማመን አቅቷቸው ጎራ ፈጥረው የሚነታረኩ፡ በፈጣሪ ከመታመን ይልቅ ምዕመናኗ የጦር መሳሪያ እንዲታጠቁ ጥሪ የምታቀርብ አገር አይደለችም ወይ?
እረ ተው ጃል… ከግዞትና ከሞት የተረፈነውን በሳቅ አትገደሉን።>>


https://scontent.fsyd7-1.fna.fbcdn.net/ ... e=5FB9D636


ALSO:

"ከታች ባያያዝኩት መግለጫ "ኢትዮጵያን የፈጠራት እግዚያብሄር ነው" የሚለው የ"ጠቅላይ ሚንትሩ" ገለፃ ሶስት ነገሮችን ያመለክታል፦

1# እኔም ወደ ስልጣን የመጣሁት በህዝባዊ ትግል ሳይሆን በፈጣሪ ተመርጬ ነዉ የሚል እሳቤ ያለ መሆኑን። ፈጣሪ ኢትዮጵያን ፈጥሮ እኔን በህዝቦቿ ላይ አነገሰ አይነት ነገር ። እዚህ ጋ በአንድ ወቅት "የሰባት አመት ልጅ እያለው እናቴ ንጉስ እንደምሆን ነግራኝ ነበር" ያለውን ቅዠት ማስታወስ ጠቃሚ ነው።

2# አብዛኛው ኢትዮዽያዊ አማኝ ስለሆነ ያ ማህበራዊ ሁኔታውን manipulate እናድርግ በሚል ቅንነት የጎደለው አመለካከት በመሃል የገባ ሃረግ ሊሆን መቻሉን።
ኮረኔሉ ይህን "የአማኝ ነኝ" ካርድ ሁሌ የሚጫወት ሲሆን ዘዴው በተወሰነ መልኩ (በተለይ በፔንጤዎች ዘንድ) ሰርቶለታል

3# ሰውየው ዘመናዊ የስነ-መንግስት ፅንስ ሃሳብ ያልገባውና ያረጀ ያፈጀ የፊውዳል የመንግስት እሳቤን የሚያራምድ መሆኑን ያሳብቃል
ይህ ሰው ፈፅሞ ዘመኑንና አለም የደረሰበትን ደረጃ አይመጥንም።
******************
ሌላው በመግለጫው ኢትዮጵያውያን "አንድ እንዲሆኑ" ጥሪ ቀርቧል።
አንድነት ይኖር ዘንድ ፍትህ እና እኩልነት ሊሰፍን ይገባል። ፍትህ በሌለበት ፣ ሰዎች በጅምላ በሚታሰሩበትና እንደ ሚዳቆ እየታደኑ በየሜዳው በሚገደሉበት ሁኔታ አንድነት ሊኖር አይችልም።
ስለዚህ በአስቾካይ የፖለቲካ እስረኞችን ፈቶ የሽግግር መንግስት እንዲቋቋም በማመቻቸት ሃገሪቱን መታደግ ግድ ይላል።
በተረፈ የውስጥ የፖለቲካ ችግርን ሳይፈቱ የትራምፕን ዛቻ በማጉላት ብቻ ነገሮችን ሸፋፍኖ ህዝብን በአንድ ላይ ማቆም ይቻላል ብሎ ማሰብ የዋህነት ነው።"Abere
Member
Posts: 1187
Joined: 18 Jul 2019, 20:52

Re: NO KIDDING! "ኢትዮጲያ የቃልኪዳን ምድር ናት"። .. ከመንግስት ከተሰጠ መግለጫ የተወሰደ

Post by Abere » 26 Oct 2020, 11:37

I really liked the way Abiy Ahmed communicated to the world about the sacred Sovereign Nation of Ethiopia. At least he hold everyone's the bottom line,that is Ethiopia. But, I again ask him to stop flip-flopping and stay Ethiopia and stirp himself off his tribal centric(Oromumma ኬኛ) crap. Yes, Ethiopia is a sacred country. No country is mentioned in the Holy Book a dozen times, next to Israel than Ethiopia. Ethiopia preserved the oldest and complete Holy Scriptures for all the world. God's favor is not measured by the amount of Gold, Dollar, Wealth ( that is Cesar's possession), but God's favor is the promise he made to his chosen Children. The Lord your God has chosen you to be a people for his treasured possession, out of all the peoples who are on the face of the earth. John 15:16 ESV. And God tests our faith that we might know it is genuine.

Yes, the God of Ethiopia always keep His eyes on Ethiopia guarding her against her sworn monstrous enemy. Almighty God, directed the Mediterranean sea to swallow the Pharaoh and freed Israelites. Yes, God whipped a dozen times the enemies of Ethiopia. And He will do the same forever.

Post Reply