Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Post Reply
Fiyameta
Member
Posts: 1116
Joined: 02 Aug 2018, 22:59

(ወያኔ 1970s and 80s) "እንገነጠላለን! ከኢትዮጵያ ህዝብ ጋር የሚያገናኘን ነገር የለም። ከአማራ ጋር በአንድ ላይ መኖር ይቅርና አብረን መለመንም አንፈልግም!"

Post by Fiyameta » 15 Oct 2020, 09:42

በ1970ዎቹና በ1980ዎቹ የመጨረሻ ዓመታት ከወያኔ ጋር ያነጋግረን የነበረው ጉዳይ ፡ ኢትዮጵያን በተመለከተ ወያኔ ያራምድ የነበረዉን የተዛባ አካሄድ ለማረም ነበር እንታገል የነበረው ። የመጀመርያው የወያኔ ፕሮግራም (ወይም ማኒፌስቶ) ሲወጣ የህወሃት ትጥቃዊ ትግል በትግራይ ነፃነት ብቻ ነው የሚደመደመው እያሉ ሲናገሩ...እኛም “እንደዚህ አይደለም ። ኤርትራ አገር ናት ። ስለ አገሮች ስንናገር ፡ የቅኝ ግዛት ታሪክን ነው አስታከን የምንናገረው ። ከሺዎች ዓመታት በፊት ህዝቦች የት ነበሩ ብለን አንናገርም ። እንዲህ መሰሉ የፍልስፍና ፕሮግራም አያስፈልጋችሁም"... ብለን ስንመክራቸው፣ "አይሆንም – እንገነጠላለን፣ ከኢትዮጵያ ህዝብ ጋር የሚያገናኘን ነገር የለም ። ከአማራ ጋር በአንድ ላይ መኖር ይቅርና አብረን መለመንም አንፈልግም" የሚል መልስ ይሰጡን ነበር። (ፕረዚደንት ኢሳይያስ አፈወርቂ - January 2018)
:oops: :oops:በJanuary 14, 2018 ከኤርትራው ፕረዚደንት ኢሳይያስ አፈወርቂ ጋር የተካሄደው የኤሪ-ቲቪ ቃለ መጠይቅ የአማርኛ ትርጉም

እሺ ክቡር ፕረዚደንት፡ ወደ ኢትዮጵያ ሁኔታ እንሻገር። የኢትዮጵያ ፖለቲካዊ ቀውስ ኣዘቅት ውስጥ ነው ያለው። በክልሎች መካከል በቀጣይ የሚከሰቱ ግጭቶች ኣሉ። በመንግስት ላይ ያነጣጠሩ ታላላቅ ህዝባዊ ተቃውሞዎችም ኣሉ። የኢህኣዴግ ኣባል በሚባሉት ድርጅቶች መካከልም ኣለመግባባት ኣለ። የኢትዮጵያ ሁኔታ ወዴት እያመራ ነው?

እንዴት እንገመግመዋለን ? ለወደፊቱስ በእንዴት አይነት መልኩ እንመለከተዋለን የሚለው ነገር በእጅጉ አስፈላጊ ነው ። በዚህ ቀጠና ወይም አዋሳኛችን በምንለው አካባቢ ከማንኛዉም አገርና ህዝብ በላይ የኢትዮጵያ ሁኔታ እኛን ይመለከተናል ። ግልጽ በሆነ ምክንያት ። ለዚህ ሰፊ ትንታኔ አያስፈልገዉም ። እንዲሁ በግምገማ 25 ወይም ከዚያ በላይ የሆኑ ዓመታት አልፈዋል ብለን ለመናገር እንችላለን ። ምንድን ነው የመጣው ነገር ። ሁልግዜም ቢሆን ቀልድ ወይም ጆክ ነው ። አሁን በቅርቡ ለምሳሌ በአንድ የዜና ትንታኔ ላይ አንድ ቀልድ አንብቤ ነበር ። እነሱ የኢትዮጵያ ፓርላማ በሚሉት የወያኔ ፓርላማ ዉስጥ ፡ በክልሎች ወይም በጎሳ ቡድኖች መካከል ያለዉን ግጭት የሚመረምር ተቋም ተመሰረት ተባለ ። የኢፌድሪ ህገመንግስት ዓንቀጽ 39 ምን እንደሚል ማየት ይቻላል ።ይህ ምን ያመለክተናል ከተባለ ፡ የወያኔ ቁጥር አንድ አጀንዳ ኢትዮጵያ በጎሳና በብሄር እንድትከፋፈልና እንድትበታተን ነው ። ባለፉት 25 ዓመታት ኢትዮጵያ ዉስጥ ምን ተከሰተ ? ክስተቱስ እንዴት ሊመጣ ቻለ ? የሚል የፖለቲካ ግምገማ የምናደርግ ከሆነ ፡ እኔ የኢትዮጵያውን ውድመት የወያኔ ጤናማ ያልሆነ አእምሮ የወለደው ነው ‘ ነው የምለው ። በመካከላችን ያለው ግንኙነት ደህና በነበረበት የ1990ዎቹ የመጀመሪያ ዓመታት ወቅት ፡ እንዴት ቢሆን ይሻላል እንባባልና እንመካከር ነበር ። ምክንያቱም የሁለቱን ህዝቦችና ትዉልዶች የወደፊት እድል ልታራርቀው አትችልም ። በጋራ መስዋእትነት ከፍለንበታል ። ከወያኔ ታሪክን ከመጠምዘዝ ባህሪ ዉጭ ፡ የወደፊቱን በመመልከት ተነጋግረንበታል ። የኢፌድሪ ህገ – መንግስት ረቂቅ ከመዉጣቱ በፊት ፡ ከዚያም በፊት ፡ ከ1991 ና ከ1990 በፊት ፡ በ1970ዎቹና በ1980 ዎቹ የመጨረሻ ዓመታት ከወያኔ ጋር ያነጋግረን የነበረው ጉዳይ ፡ ኢትዮጵያን በተመለከተ ወያኔ ያራምድ የነበረዉን የተዛባ አካሄድ ለማረም ነበር እንታገል የነበረው ። የመጀመርያው የወያኔ ፕሮግራም ሲወጣ “ እንደዚህ አይደለም ። ኤርትራ አገር ናት ። ስለ አገሮች ስንናገር ፡ የቅኝ ግዛት ታሪክን ነው አስታከን የምንናገረው ። ከሽዎች ዓመታት በፊት ህዝቦች የት ነበሩ ብለን አንናገርም ። እንዲህ መሰሉ የፍልስፍና ፕሮግራም አያስፈልጋችሁም"... ብለን ስንመክራቸው፣ "አይሆንም – እንገነጠላለን፣ ከኢትዮጵያ ህዝብ ጋር የሚያገናኘን ነገር የለም ። ከአማራ ጋር በአንድ ላይ መኖር ይቅርና አብረን መለመንም አንፈልግም" የሚል መልስ ይሰጡን ነበር። ይህ አልፎ አንድ መድረክ ላይ ደረስን ። በመጨረሻ ላይ ደግሞ ከዚህ በእጅጉ አክራሪነት የተንጸባረቀበትና ምክንያት አልባ የሆነ ሌላ የኢትዮጵያ አጀንዳ መጣ ። ስነአእምሮው ግን ገና አልተቀየረም ።” እኛ ጥቂቶች ወይም ደግሞ አናሳዎች ስለሆንን ፡ ኢትዮጵያን ለማስተዳደር አልያም ደግሞ ለመግዛት ፡ የግድ መበታተን አለብን ‘’የሚለው ነው ዋነኛ ነገረ ስራቸው የነበረው ።

ቀጥሎ የኢትዩጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሕገ መንግስት ተራማጅ ነው ተብሎ ተነገረ። ከዛ በኋላ በወያኔ ኣእምሮ ውስጥ የሰፈረው ኣጀንዳ ኢትዮጵያን በታትነህ እንዴት ታስተዳድራታለህ ነው። ኣሁን ወደ ኋላ ተመልሰን ፖለቲካዊ ኣጀንዳውን ከተመለከትንነው ፍጹም ኣልሰራም። ኢህኣዲግ ከመመስረቱ በፊት ብሄር ከብሄር ነውጥና፥ ህውከት ማነሳሳት ኣያስፈልግም የምንላቸው ጉዳዮች ነበሩ። ከ 1991 ዓ/ም በኋላ የኢትዩጵያ ህዝብ ወዴት ኣቅጣጫ ሊጓዝ እንደሚችል እንዲወስን የሽግግር ሕገ- መንግስት መኖር ኣለበት ኣልን። በዚያን ጊዜ ጉዳያችን ስላልሆነ ኣይደለም የገባነው ሸሪኮች ስለነበርን እንጂ። ቢያንስ የ10 ዓመት የሽግግር ወቅት ይኑርና ከዚያ በኋላ ወደ ሌላ መድረክ ያመራል ኣልን። ይህንን ትተህ ሌላ ምንም ነገር ልታመጣ ኣትችልም። ያለውን የብሄሮች እንቅስቃሴ ማንኛውም ሰው ሊክደው ኣይችልም። ለወደፊት ከኣዲሱ የኢትዩጵያ ሁኔታ ጋር እንዲሁም ከኣካባቢው ጋር የሚስማማ የሽግግር ወቅት መኖር ኣለበት። እንዲህ ኣይነት ሁኔታ ኣያስፈልግም ተባለ። ወያኔ ኢትዮጵያን በፖለቲካ ከፋፍለህ ለመቆጣጠር ኣንድ የኣስተዳደር ጥላ መፈጠር ኣለበት ኣለ ። ይህም በኢህኣዲግ ስር ማለት ነው። ኢህኣዲግን መቶ በመቶ ብቻ ሳይሆን ከዚያም በላይ ህወሃት ብቻውን የሚቆጣጠረው እንዲሆን ሁኔታውን ኣመቻቹት። ሌሎቹ ድርጅቶች ተቀጥያ ናቸው ማለት ነው። ወይም መገልገያ ናቸው። ይህ ከውስጥ የሚሰጠው ምስል ብዙዎች ብሄሮችን ያካተተ ድርጀት እንደተመሰረተ የሚያስመስል ነው። ነገርግን በድርጅቶቹ መካከል መተማመንም ኣልነበረም።

ይህ ኣሁን በኢትዮጵያ የምንመለከተው ሁኔታ የዚያ ኣጀንዳ ውጤት ነው። በዚያን ወቅት ስንሰጥ ለነበረው ምክር በተቃራኒው ይሰሩ እንደነበር ግልጽ ቢሆንም እንኳን ወያኔ የነደፈው የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ተራማጅ ህገ መንግስት መተግበሩ፡ በኢትዮጵያ ከተፈጠሩ ከፍተኛ በደሎች ዋነኛውና ለዚህ ኣሁን ለምንመልከተው ፖለቲካዊ ቀውስ ጠንቅ ሆነ። ይህ ደግሞ ከሰማይ የወረደ ችግር ኣይደለም። ወያኔ የቀየሰው ችግር ነው። ለጉራ ወይም የኔን ድርሻ ለማጉላት ሳይሆን የመጀመሪያውን የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ረቂቅ ሕገ- መግስትን ከተመለከቱት ሰዎች ኣንዱ ነኝ። በነበረን መልካም ግንኙነት የማንወያይበት ኣርእስት ኣልነበረም። ሁሉንም ነገር ኣንስተን እንመካከርበት ነበር። ብሄሮች የራስን እድል በራስ የመወሰን መብት እስከ መገንጠል ኣንቀጽ 39 ምን ማለት ነው? "ከተሳካልን ከሌሎች ኢትዮጵያውያን ጋር ኣብረን እንዘልቃለን፡ ካልተሳካ ደግሞ እንገነጠላለን ማለት ነውን?" ይህ የብሄረሰቦች ኣመሰራረት የሚባለው ቀስ በቀስ በኣገር ግንባታ እየተቀናጀ ወደ ኣንድነት እንዲያመራ ማድረግ እንጂ እንዳለ እስኪደህ ተቋማዊ ቅርጽ ለማስያዝ መሞከር ኣደገኛነቱ ማለቂያ የለውም። በማንኛውም ኣገርም ይሁን ኣካባቢ ኣይሰራም። ብዙሃነትን ተገንዝበህና ኣምነህ ወደ ኣስተማማኝ ውህደት እንዲያመራ መስራት ኣለብህ። ካልሆነ ግን የነበረው ክፍፍል እንዲቀጥል ኣድርገህ በህብረተሰብ መካከል የጎጥ፥ የጎሳና፥ የብሄር፥ ልዩነት በመፍጠር በጎሪጥ የመተያየት ሁኔታ እንዲከሰት ማድረግ በእጅጉ ኣደገኛ የፖለቲካ ጨዋታ ነው። ይህንኑ ኣደገኛ ጨዋታ በኢትዮጵያ ተግባራዊ ያደረገው ወያኔ ነው።

ይህ ብቻ ግን ኣይደለም። ወያኔ የፈጸማቸው ኣራት ከፍተኛ ስህተቶች ኣሉ። ይህ በኣሁኑ ሰዓት የኢትዮጵያን ህዝብ እያተራመሰ ያለው የወያኔ የፖለቲካ ኣጀንዳ መጨናገፍ ብቻ ሳይሆን በፖለቲካ ከፋፍለህ የኢትዮጵያን ህዝብ ለማስተዳደር መሞከር ኣንዱ ኣጀንዳ ነው። ከሱ ጋር በተያያዘ ደግሞ ኢኮኖሚውን ለመቆጣጠር መወሰኑ ነው። ይህ ሁኔታ የሚያስከትለውን መዘዝ ግን ወያኔ ኣልተገነዘበውም። በኣንዲት ኣገር ውስጥ ኣንድ ኣናሳ ቡድን ኢኮኖሚውን እንዲቆጣጠር ማድረግ ማለት ሌሎችን ማግለል መዘዙ በጣም ኣደገኛ ነው። ከዚህ የከፋ ኣደገኛ ጨዋታ ኣልነበረም። በተለያዩ የኣውሮፓና የኣሜሪካ ኣካባቢዎች ጉዳይ-ኣስፈጻሚዎች እየቀጠርክ ኢትዮጵያ ለኢንቨስትመንት ምቹ ኣገር ናት። ባለሁለት ኣሃዝ የኢኮኖሚ እድገት እያስመዘገበች ነው እያልክ የሆነ ያልሆነ ወሬ በመንዛት መኖርና በመጨረሻ የኣገርህን መሬት እየሸጥክ የኣንድ ጠባብ ቡድን የኢኮኖሚ የበላይነትን መፍጠር ያስከተለው መዘዝ ኣሁን ኣየተመለከትነው ያለነውን የኢትዮጵያ ሁኔታ ነው። በኣጠቃላይ ሲታይ የኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ውድመት – የወያኔ ፕሮፖጋንዳ ከግምት ውስጥ ሳይገባ – በኣሁኑ ወቅት የታየውን የኢኮኖሚ ቀውስ ኣስከትሏል። ወያኔ ከፈጠረው የፖለቲካ ችግር በተጨማሪ ህዝቡ የኢኮኖሚ መብቱን ለማስከበር ባለመቻሉ ምሬቱን እየገለጸ ነው። በኣሁኑ ወቅት ያለው የኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ሁኔታ ምን ደረጃ ላይ ይገኛል ካልን፥ የኣለም የገንዘብ ድርጅትና የኣለም ባንክ በሰጡት ማሳሰቢያና ምክር የብርን የምንዛሬ መጠን በማጉደል ኢኮኖሚውን ማስተዳደር ኣይቻልም። ባለሁለት ኣሃዝ እድገት ኣስመዘገቧል እየተባለ ሲነገርለት የነበረ ኢኮኖሚ እንዴት ወደ እንዲህ ኣይነቱ ሁኔታ ሊገባ ይችላል? ይህ ደግሞ የወያኔ ሁለተኛው ከፍተኛ ስህተት ነው።

ሶስተኛው ኣጀንዳ ደግሞ ወታደራዊና ጸጥታዊ ቁጥጥር ነው። በኣሁኑ ወቅት በኣገሪቱ ያለው የጸጥታ ሁኔታ እንዴት ተከሰተ? በሶማሊያ ድረስ ሄዳ የምትዋጋ ወደ ሌሎችም ኣገሮች የሰላም ኣስከባሪ ሰራዊት የምታሰማራ ከኤርትራ ጋርም በተደጋጋሚ ጦርነት የገጠመች ይህች "የቀጠናው ሃያል ነኝ" የምትል ኣገር ፡ ይህ ሃያል የሚሉት ተጫባጭነት የሌለው ጉራ ለምን ኣስፈለገ?. . . .ከኤርትራ ጋር በሰላም ለመኖር ሰራዊትም ሆነ የጸጥታ ሃይል ባላስፈለገ። በጋራ የምትኖር ከሆነ የጋራ የጸጥታ ሃይል ታቋቁማለህ ። ወደ ሶማሊያ የሚያስኬድ ምክንያት የለም። በተለያዩ ኣካባቢዎች የኣንድን ጠባብ ቡድን የበላይነት በወታደራዊ ሃይል ልታረጋግጥ ኣትችልም። መጀመሪያ ላይ በርግጥ ሊመስል ይችላል። በእንዲህ ኣይነት የወታደር ሃይል ህዝብን ኣንበርክኬ እገዛለሁ ብለህ ታስብ ይሆናል ። ይሁን እንጂ ይህ ኣስተሳሰብ እሩቅ ሊያስኬድ ኣይችልም። ያለ ከፍተኛ ወታደራዊና የጸጥታ ሃይል ዘላቂ ሰላምና መረጋጋት ማረጋጋጥ መቻል ኣለብህ። ገና ከመጀመሪያውም ለዚህ የሚሆን ምቹ መድረክ መፈጠር ኣለበት።

አራተኛው የወያኔ አጀንዳ ወይንም ችግር ከዉጭ ሃይሎች ጋር ተጎዳኝትህ ወይም ተስማምተህ ቁጥጥርህን ለማጠናከር መሞከር ነው ። ስለሆነም ደግሞ ለዉጭ ሃይሎች ትገዛለህ ማለት ነው ። የወያኔ ፈላስፋዎች በተደጋጋሚ ይሉን የነበረውና ፡ ይህ ነገር አያዋጣችሁም ይባል በነበረበት ወቅት የነርሱ ፍልስፍና “ ከሃያላን ጋር ተስማምተህ እደር” ነው ። ከሃያላን ጋር ተስማምተህ እደር ማለት ፡ ከነርሱ ጋር በምንም ዓይነት አቋምም ቢሆን ተስማምተህ ተጓዝ እንደ ማለት ነው ። ከዚህ የባሰው ነገር ደግሞ ፡ የኢትዮጵያን ህዝብ የመቆጣጠርና የአካባቢው አንኳር የመሆን ፍላጎት ብቻ ሳይሆን ፡ የትግላቸው አጋር የሆነዉን የኤርትራን ህዝብ በመካድና ጭዳ በማድረግ ፡ ከዉጭ ሃይሎች ጋር ተስማምተው የኢትዮጵያን ህዝብ እየበደሉ የመቀጠል ፍላጎታቸው ነው ። ይህ የፍልስፍና ምርምር ምናልባት መጀመርያ ላይ ለወያኔ እንደ ከፍተኛ የዲፕሎማሲ ትርፍ ወይም እንደ ታላቅ የስትራቴጂ ድል መስሎት ሊሆን ይችላል። መጨረሻ ላይ ግን ሁሉንም የመቆጣጠሩ ጉጉት አልሰራም ። የኤርትራን ህዝብ ክደህ ፡ ሻእቢያ አጋርህና የትግል ጓድህ እንዳልነበረ ሁሉ እንደ ቀዳሚ ጠላትህ ቆጥረህ ፡ ከዉጭ የሚመጣዉን ሁሉንም ዓይነት ጠብ አጫሪነት ስታስተናግድ ፡ ከሁሉም በላይ ደግሞ የኢትዮጵያን ህዝብ ከኤርትራ ህዝብ ጋር የጎሪጥ እንዲተያይ ልታደርገው ፡ ያዉም ደግሞ የትግራይን ህዝብ ከኤርትራ ህዝብ ልታራርቀውና ልታጋጨው መሞከር በምን ኣመክንዮ ሊገለጽ ይችላል ? በ25 ዓመታት ዉስጥ የተመለከትነውን የወያኔ ፖለቲካዊ ፡ ኢኮኖሚያዊ ፡ ደህንነታዊና የዉጭ ጉዳይ ግንኙነቱንና አጀንዳዎቹን አንድ ባንድ ካየነው ፡ የጎላ ስህተቱን መገንዘብ እንችላለን ።

አሁን እየተባለ እንዳለው ፡ “ ግብጽ በዚህ በኩል መጣች ፥ ከሱዳን ጋር ተወዳጅተናል ፥ በኤርትራ ላይ እንዲህ ዓይነት ነገር እየሰራን ነው" ወ.ዘ.ተ የሚባለው ነገር ባላስፈለገ ። በዋነኝነት ግን ወያኔ የተጓዘበት የፖለቲካ ፥ የኢኮኖሚ ፥ የጸጥታም ሆነ የዉጭ ጉዳይ ፕሮግራሞች ይህን ያህል ሊቀጥል መቻሉ በተናጠል ሊታይ የሚችል አይደለም ። ወደ ኋላ መለስ ብለን ፡ የክሊንተን ፥ የቡሽና የኦባማ ሶስቱም አስተዳደሮች የነበራቸዉን አስተዋጽኦ መመልከት እንችላለን ። እንዲህ አይነቱ ስህተት እየተፈጸመ እያለ ፡ ለምን ይሆን “ አይዞህ በርታ “ ይሉ የነበረው ? በአዉሮፓ የሚገኙ የተለያዩ አገራት ለምን ይሆን ይህንን አካሄድ ሲያበረታቱ የነበረው ? ለምን ይሆን የቀውሱ ግዜ የተራዘመው ? ከተባለ በራሱ በወያኔ የዉስጥ ፕሮግራም ወይም በራሱ በወያኔ የዉስጥ አጀንዳ ብቻ እንደሆነ አድርገን የምንመለከተው አይደለም ። ወያኔ ይህንን የማድረግ ሃይል የለዉም ። ጉዳዩም ይበልጥ እየተወሳሰበ ባልሄደ ነበር ። በራሱ በወያኔ የዉስጥ አቅምና በኢትዮጵያ ፕሮግራም ብቻ ቢሆን ኖሮ ፡ ይህን ያህል ግዜ ባልተራዘመ ነበር ። ለተፈጠረው የተወሳሰበ ሁኔታ ከፍተኛዉን አስተዋጽኦ ያበረከተው ፡ ከዉጭ የሚደረገው የኢኮኖሚና የፖለቲካ ድጎማ ነው ። ኢነቨስተሮች ነን ሃብታሞች ነን በማለት መዋእለ ንዋያቸውን በኢትዮጵያ ላይ የሚያፈሱና ሌሎችም ቢሆኑም ፡ ይህንን ሁኔታ እያመቻቹ እድሜው እንዲራዘም አድርገዋል ። ይህ ከፍተኛ እንክብካቤ የሚባለው በኢትዮጵያ ያለው ሁኔታ ግን ዘላቂነት የለዉም ። ሊቀጥል አይችልም ። ይህን ነገር ደግሞ ፡ እኛ ስለተካድን ወይም ደግሞ ሰለባ ስለተደረግን የምንናገረው ነገር አይደለም ። የኢትዮጵያን ተጨባጭ ሁኔታ ገምግሞ ፡ ከዚህ ዉጭ የተለየ ሁኔታ ነው ያለው የሚል ካለ ፡ ባለፉት 25 ዓመታት ወስጥ ሲቀጥል የቆየው የፖለቲካ ፡ የኢኮኖሚ ፥ የጸጥታና የዉጭ ግንኙነት እንዴት አሁን የሚገኝበት ደረጃ ላይ ሊደርስ እንደቻለ ነቂስ በነቂስ ተንትኖ ይመልከተው ።

ወያኔን ያሳሳቱት ከዋሽንግተን ጀምሮ እስከ አዉሮፓ ርዕሰ መዲናዎች ድረስ ያሉት መንግስታት ሲከተሉት የቆዩት ፖሊሲ ነው፡፡ ወያኔን ማበረታታት ብቻ ሳይሆን ፡ በኤርትራ ህዝብና መንግስት ላይ ያራመዱት የጠብ አጫሪነት አካሄድን አንድባንድ ከተመለከትከው ፡ ምስሉ ቁልጭ ብሎ የሚታይ ነው ። ይህ ሁኔታ ደግሞ ባለበት ሊቀጥል አይችልም ። የእዉነቱን ለመናገር እኛ ፡ የእጃችንን አይደለም ያገኘነው ። ታሪካችንን ደምስሶ ለማደብዘዝና ለማጥፋት ያልተደረገና የማይደረግ ሙከራ የለም ። ያልተሞከረ ማናቆር አልነበረም ። በኤርትራና በኢትዮጵያ ህዝቦች መካከል ፡ መጨረሻ የሌለው ጥላቻ ለመዝራት የተደረጉ ሙከራዎችን በሙሉ ፡ በነቃ ህሊና ስነከታተለው የቆየነው ነገር ነው ። ያለፉት 25 ዓመታት የኪሳራ ዓመታት ናቸው። ያለፉን እድሎች ቀላል አይደሉም ። ይሁን እንጂ ባለፈው ነገር የምንቆጭበት ምክንያት የለንም ። ባለፈው ነገር ተደናግጠን እጅና እግራችን አጣጥፈን የምንቀመጥበት ምክንያትም የለም ። የኤርትራና የኢትዮጵያ ህዝቦችን የወደፊት ግንኙነት በተመለከተ ፡ በጋራ እስከታገልነበት 1991 ድረስ ከነበረው ማለትም ከበፊቱ የተለየ አዲስ ፍልስፍና የለንም ። ከ25 ዓመታቱ ዉድመት በቂ እዉቀት ቀስመናል ። የሁለቱም አገራት ህዝቦች ካለፈው ነገር ብዙ ተምረዋል ። የትግራይ ህዝብም ቢሆን በዋነኝነት ካለፈው ነገር ትምህርት አግኝቶበታል ። ምናልባት በአሁኑ ወቅት ፡ ግዜ ለመግዛትና እድሜ ለመቀጠል ፡ “ጥገናዊ ለውጥ አድርገናል ፥ እስረኞችን እንፈታለን ፥ የጎሳ ችግሮችን እንፈታለን ፥ የኢኮኖሚ ማሰተካከያ እናደርጋለን ፥ እንዲህ እንሰራለን. . . ወዘተ” የሚሉ የተለያዩ ማማለያዎችና ማዘናጊያዎችን በየእለቱ የምንከታተለው ነገር ነው ። ነገር ግን ጉዳዩ አብቅቷል ። የኢትዮጵያ ህዝብ አሁንም ቢሆን የወደፊት እድሉን የሚወስንለትን ማወቅ አለበት ። በህዝቦች እድሜ 25 ዓመታት ማለት ፡ አጭር ግዜ አይደለም ። ረጅም ግዜ ነው ። የኢትዮጵያ ህዝብ መንገዱን ማወቅ አለበት ።

በአሁኑ ወቅት የኤርትራና የኢትዮጵያ ህዝቦችን ለማራራቅ ፡ “ኤርትራ እንዲህ እየፈጸመች ነው ፥ ሻዕቢያ እንዲህ አደረገ ፥ በኢትዮጵያ በእከሌ ክልል እንዲህ ፈጸመ ፥ እየተባለ የሚነዛው ፕሮፓጋንዳ ማንንም የዋህ ሊያታልል ወይም ሊያደናግር አይችልም ። በፊትም ቢሆን’ኮ ታንክና መድፋችን ይዘን አዲስ አበባ ድረስ የዘለቅነው ለሁለቱም ህዝቦች የወደፊት እድል ስንል እንጅ ለጉራ አይደለም። እኛ ጎበዝን እናንተ ግን ሰነፋችሁ ብለን የምንናገርበት ጉዳይም አይደለም ። አሁን ላይ የተከሰተ አዲስ ፍልስፍና የለንም ። የኢትዮጵያ ህዝብም ቢሆን አዲስ ፍልስፍና የለዉም ። በኤርትራና በኢትዮጵያ ህዝቦች መካከል በሚኖረው ግንኙነት ላይ አዲስ የሚባል ፍልስፍና የለም ። የወደፊት እድሎቻችንን እንዴት እንወስናለን ፥እንዴት አድረግን እንተባበራለን ፡ ከማንኛውም ሰው የተሰወረ አይደለም ።

ስለዚህ ይህ ኣሁን ኢትዮጵያ ውስጥ ኣለ የሚባለው ሁኔታ ፡ በተጨባጭ መነበብ መቻል ኣለበት። እንደየስሜትህ የሚነገር ኣይደለም። እነዚህ ኣንድ በኣንድ ስገልጻቸው የቆየሁት ሁሉ የተሰነዱ ናቸው። ትንታኔ ኣይደሉም፡ የተመዘገቡ ጭብጦች ናቸው። ከዚያ የበለጠ የትምህርት መጽሃፍ ደግሞ የለም። በዚያ ላይ ግዜ ለማጥፋት ሳይሆን፡ የሚበቃንን ተምረናል። ብዙ ስለከሰርን ደግሞ ካሁን በኋላ በእንደዚያ ሁኔታ መቀጠል ኣንችልም። የኢትዮጵያ ህዝብ ባለፈው ዓመት ያሳያቸው ተቃውሞዎች፡ ያለመርካቱና የተሳሳተ የወያኔ ስትራቴጂ ገሃድ መግለጫ ነው። ስለዚህ ረጋ ብለን፡ ኣዲስ ፈጠራ ሳናመጣ ፡ ድሮ በተጓዝንበት መስመር መጓዝ ብቻ ነው ያለብን። ይህ ኣሁን ኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን ሁኔታ የሌለ ገጽታ ለመስጠት፡ ኤርትራ እገሌን ደገፈች፡ እንዲህ ኣደረገች እያላችሁ በተባበሩት መንግስታት የጸጥታው ምክርቤት የምትከሱን ታድያ እኛስ ከናንተ ጋር ኣይደለም እንዴ ኣዲስኣበባ የገባነው? ለምን ያኔ በጉዳያችን እጃችሁን እያስገባችሁ ነው ኣልተባለም? ብዙ ሊባል ይችላል።

ታሪኩን በሚገባ የሚያውቁ ብዙዎች፡ ‘ ያ ሁሉ ኣብረን በልተን፡ ኣብረን ሰርተን፡ ኣብረን ተሰውተንና፡ ኣብረን ታግለን ኣሁን ያን እንዳልነበረ ለመደምሰስ የሚደረገው ሙከራ ሚስጢሩ ምንድንነው? ይላሉ። ነገር ግን ኣዲስ ታሪክ የለም፡ ሁሉም በሰነድ የተያዘ ነው። በኣካሄዳችን በርግጥ ድሮ ከነበረን እምነት ዛሬ ያለን እምነት ይበልጥ ይጠነክራል። ለወያኔ ብቻ ሳይሆን፡ ለወያኔ ኣሰሪዎችም ቢሆን የምናፍርበት ወይም የምንፈራበት ጉዳይ ኣይደለም።


Read the entire interview translated into the Amharic language
https://ecadforum.com/Amharic/archives/18553/

Fiyameta
Member
Posts: 1116
Joined: 02 Aug 2018, 22:59

Re: (ወያኔ 1970s and 80s) "እንገነጠላለን! ከኢትዮጵያ ህዝብ ጋር የሚያገናኘን ነገር የለም። ከአማራ ጋር በአንድ ላይ መኖር ይቅርና አብረን መለመንም አንፈልግም!"

Post by Fiyameta » 15 Oct 2020, 10:00

ላለፉት ሃያ አመታት በሃሰት "የኤርትራ ተቃዋሚዎች" ነን እያሉ በየድህረ ገፁ ሲያደነቁሩን የነበሩት ከትግራይ የበቀሉ አውሬዎች ዛሬ ስልጣን ሲነጠቁ የበግ ለምዳቸውን አውልቀው እውነተኛ ተኩላነታቸውን ማሳየት ጀምረዋል። :oops: :oops:


Fiyameta
Member
Posts: 1116
Joined: 02 Aug 2018, 22:59

Re: (ወያኔ 1970s and 80s) "እንገነጠላለን! ከኢትዮጵያ ህዝብ ጋር የሚያገናኘን ነገር የለም። ከአማራ ጋር በአንድ ላይ መኖር ይቅርና አብረን መለመንም አንፈልግም!"

Post by Fiyameta » 15 Oct 2020, 10:19

ቀድሞ ነበር እንጂ መጥኖ መደቆስ አሁን ምን ያደርጋል ድስት ጥዶ ማልቀስ! :oops: :oops:

"ኢትዮጵያ ማለት እኛ ወያኔዎች ብቻ የምንገዛት አገር ናት። እኛ ወያኔዎች የምንገዛት ኢትዮጵያ የምትባል አገር ልትኖር አትችልም!" ትለናለች ይቺ ኧጋሜ። በሳቅ ሆዴን ፍርስ ነው ያደርገችኝ! ቂቂቂቂቂቂቂ :oops: :oops:


Fiyameta
Member
Posts: 1116
Joined: 02 Aug 2018, 22:59

Re: (ወያኔ 1970s and 80s) "እንገነጠላለን! ከኢትዮጵያ ህዝብ ጋር የሚያገናኘን ነገር የለም። ከአማራ ጋር በአንድ ላይ መኖር ይቅርና አብረን መለመንም አንፈልግም!"

Post by Fiyameta » 15 Oct 2020, 12:54


የቀድሞው የኢንሳ ዳይሬክተር፣ የዛሬው በትግራይ ተወላጆች የተቋቋመውን "የኤርትራ ተቃዋሚ ቡድኖች" ሊቀ መንበር: ሜ/ጀነራል ተክለብርሃን ወልደአረጋይ :oops: :oops:

Abdisa
Member
Posts: 3743
Joined: 25 Apr 2010, 19:14

Re: (ወያኔ 1970s and 80s) "እንገነጠላለን! ከኢትዮጵያ ህዝብ ጋር የሚያገናኘን ነገር የለም። ከአማራ ጋር በአንድ ላይ መኖር ይቅርና አብረን መለመንም አንፈልግም!"

Post by Abdisa » 15 Oct 2020, 15:16

ጉራ ብቻ! እኮ ተገንጠሉ ማን የግድ አብራችሁ ኑሩ አላችሁ? እውነታው የኢትዮጵያ ህዝብ እራሱ ተገንጠሉ ሂዱ ብሎ አጨብጭቦ ቢሸኛቸውም የትም አይሄዱም። ጥርግ በሉ! ተንኰለኞች እናንተ ብትሄዱ ኢትዮጵያ ከስርቆት ከዝርፍያ ከተንኮል ነጻ ትሆናለች፣ ሂዱ ተገንጠሉ!! ቅቅቅቅቅቅቅ! :lol: :lol: :lol:

Za-Ilmaknun
Member
Posts: 2127
Joined: 15 Jun 2018, 17:40

Re: (ወያኔ 1970s and 80s) "እንገነጠላለን! ከኢትዮጵያ ህዝብ ጋር የሚያገናኘን ነገር የለም። ከአማራ ጋር በአንድ ላይ መኖር ይቅርና አብረን መለመንም አንፈልግም!"

Post by Za-Ilmaknun » 15 Oct 2020, 15:52

TPLF dunces are always exceeded by their own stupefying positions and statements. They manufactured hate as a core value in their struggle for hegemony and, eventually they became hate itself. They think that the rest of the country has also gone to the low they established for themselves. They hate that others get ahead..they hate that there is harmony among people, they hate that there is peace..they hate that somebody speaks ameharic...the list goes on. They sponsor terror and enable murderers everywhere they set their foot on. Let's see if they will live in the oasis of tranquility while the rest of the region is set ablaze. Finally they are now under illegal Regional government whose actions are outlawed and whose standings are illegitimate. :mrgreen:


BAGAMIDOASS
Member
Posts: 71
Joined: 05 Sep 2015, 17:14

Re: (ወያኔ 1970s and 80s) "እንገነጠላለን! ከኢትዮጵያ ህዝብ ጋር የሚያገናኘን ነገር የለም። ከአማራ ጋር በአንድ ላይ መኖር ይቅርና አብረን መለመንም አንፈልግም!"

Post by BAGAMIDOASS » 15 Oct 2020, 21:35

The crook Tigray weyanes Pimpass behavior is astonishing. As if the Eritreans don't speak and Listen Amharic, they edited Isayas Afwerkis interview for their cheap propaganda. The good thing is, the pimpass behavior of Tigray weyanes becomes well known through out Ethiopia and Eritrea. No Eritreans or Ethiopians trust them any more.

abel qael
Member+
Posts: 7710
Joined: 07 May 2007, 03:21
Location: gumamistan

Re: (ወያኔ 1970s and 80s) "እንገነጠላለን! ከኢትዮጵያ ህዝብ ጋር የሚያገናኘን ነገር የለም። ከአማራ ጋር በአንድ ላይ መኖር ይቅርና አብረን መለመንም አንፈልግም!"

Post by abel qael » 16 Oct 2020, 00:33

Fiyamitra gual Asmera aka tra'nny revulsion and your 99 other nicks including bagamidoe, " yabiyen ekek lemiye likek" is what you learned from your amharay father and hamasenay prostitute mother in popolare.
you cannot hide wedimedhi'ns hate of Ethiopia and amharas as he says it eloquently in the video below. If this did not worry you why did beg elias to delete it? But here it is again, the original is with us, we will make even a movie on it. This shows how much hamasenaylootiews like you fear Amharay knowing the truth about cannibal hamasenay hate towards them.

( ͡° ͜ʖ ͡°)
Member
Posts: 1974
Joined: 11 Jan 2020, 21:22

Re: (ወያኔ 1970s and 80s) "እንገነጠላለን! ከኢትዮጵያ ህዝብ ጋር የሚያገናኘን ነገር የለም። ከአማራ ጋር በአንድ ላይ መኖር ይቅርና አብረን መለመንም አንፈልግም!"

Post by ( ͡° ͜ʖ ͡°) » 16 Oct 2020, 02:32

Tigray is under TPLF's illegal occupation and the Ethiopian government must take action to free the Tigray people from oppression, occupation and exploitation.

Fiyameta
Member
Posts: 1116
Joined: 02 Aug 2018, 22:59

Re: (ወያኔ 1970s and 80s) "እንገነጠላለን! ከኢትዮጵያ ህዝብ ጋር የሚያገናኘን ነገር የለም። ከአማራ ጋር በአንድ ላይ መኖር ይቅርና አብረን መለመንም አንፈልግም!"

Post by Fiyameta » 16 Oct 2020, 10:52

An Ethiopian scholar once asked me why the agame have not seceded from Ethiopia as they had promised they would. I told him that they have been waiting for the agame trolls who falsely call themselves "Eritrean opposition" on the internet to place Eritrea under Tigray's occupation, but they have since ran out of time and money trying to do the impossible.

Do you think the Ethiopian people should be allowed to hold a referendum to decide to whether keep Tigray in the union or get rid of it? And what do you think the outcome of such scenario will be? :oops: :oops:


( ͡° ͜ʖ ͡°)
Member
Posts: 1974
Joined: 11 Jan 2020, 21:22

Re: (ወያኔ 1970s and 80s) "እንገነጠላለን! ከኢትዮጵያ ህዝብ ጋር የሚያገናኘን ነገር የለም። ከአማራ ጋር በአንድ ላይ መኖር ይቅርና አብረን መለመንም አንፈልግም!"

Post by ( ͡° ͜ʖ ͡°) » 16 Oct 2020, 22:02

Why do the agame hate the Amhara people, yet they write their TPLF manifesto and express their thoughts to one another in the Amharic language? The broken Tigrigna spoken in Tigray is not developed to be used in a written form, therefore Amharic is the dominant language in Tigray. :PPost Reply