Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Abaymado
Member
Posts: 4191
Joined: 27 Sep 2017, 21:56

እንቦጭ ማጥፍያ መድሃኒት ቢገኝም ብአዴን አልቀበለውም አለ

Post by Abaymado » 11 Oct 2020, 09:38

ከሰሞኑ አንዱ መወያያ ነገሮች አንዱ የእንቦጭ ጉዳይ ነው:: መሪጌታ በላይ አዳሙ የተባሉ ሰው መድሃኒቱን እንዳገኙት ሲነገር ከጀመረ ቆይቷል:: ያገኙት መድሃኒት ከእፀዋት የተቀመመ ሲሆን እንቦጩን ድራሹን እንዳጠፋው ተገልፅዋል::

ለዚህም ባህርዳር ዩኒቨርሲቲ ይህንን ሞሞሆኑን እንዳረጋገጠ ተነግሯል::እንደመሰለኝ ችግሩ የመጣው የአማራ ክልል ሙሁራን ነን ባዮች እና ይህንን የሚመለከተው የአገሪቱ ጥቅዋም ጋር በተፈጠረ እሰጥ እገባ ነው:: እነዚህ ሰዎች መርጌታ በላይን መድሃኒቱ ያግኘህበትን አሳየን ብለው ድርቅ ይላሉ:: ሰውየው ደሞ እውቅና ካልተሰጠኝ አላሳይም ይላሉ::በመጨረሻም የአማራ ክልል በአንድ ዶክተር የሚመራ ቡድን በሰውየው መድሃኒት ላይ ያለውን ውጤት ገልፅዋል::
እነሱ እዳሉት መድሃኒቱ ውጤታማ የሆነው በከፊል ነው የሚል ነው: : እናም ውጤታማ አይደለም ነው የሚሉት::

እንደ እዚህ አገር ያለ ምቀኛ ሕዝብ አለ እንዴ? መድሃኒቱ ውጤታማነቱ በመጠኑ ነው ብሎ መልስ አለ እንዴ? ደሞስ ማን ያምናቸዋል? ቅናት ነው ሌላ ምን ይባላል?

ብአዴን ከአማራ ላይ መቼ ነው የሚነቀለው? ከአማራ ላይ ወርዶ በራሱ ሳንባ የሚተነፍሰው መቼ ነው?

https://www.youtube.com/watch?v=OM6zLTzLxPQ