Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum

Qurunde
Member
Posts: 450
Joined: 18 Feb 2014, 10:42

Re: ስበር ዜና ፕሮፌሰር መስፍን በኮኖና ታመው ህይወታቸው አልፏል፡፡ በሰላም ይረፉ! ነፍስ ይማር

Post by Qurunde » 30 Sep 2020, 12:21

[deleted] Mesfin W/Mariam of the Dorze Sefer was the one who advised Derg to kill the 60 Hailesellasie officials. He was the sadist and greedy person who lived alone more than half of his life.

( ͡° ͜ʖ ͡°)
Member
Posts: 2312
Joined: 11 Jan 2020, 21:22

Re: * ስበር ዜና * '' እውቁ ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም በኮሮና ታመው ህይወታቸው አልፏል፡፡ '' በሰላም ይረፉ! ነፍስ ይማር

Post by ( ͡° ͜ʖ ͡°) » 30 Sep 2020, 13:05


የሰው አገርን በመውረር ምን ይገኛል?


መስፍን ወልደማርያም (ፕ/ር)



በዛሬው ጊዜ ዓለም አቀፍ ሕጎች፣ በተለያዩ የአካባቢ ማኅበሮችና በተባበሩት የዓለም መንግሥታት ማኅበር ታትመውና ታውጀው፣ ተሰብከው፣ ብዙ ዲስኩሮችም በታላላቅ ሰዎች በተደጋጋሚ ተደርጎባቸዋል። ከብዙ ዓመታት በፊት ቻይና ቲቤትን ስትውጥ፣ ለጥቂት ጊዜ ተወራና ተረስታ፤ እኛም ካልረሳነው ኢጣሊያ ኢትዮጵያን ስትወር እንዲሁ ነበር፤ ዛሬ እኛም ወግ ደርሶን ከወራሪዎች ጋር መሰለፋችን በሰፊው እየተወራ ነው። አሁን ደግሞ የአውሮፓ ሕብረት “ቲቤት የቻይና አካል ነች” ብሎ ዐወጀ ይባላል። እንግዲህ ወረራ በይርጋ ይጸድቃል ማለት ነው፤ ጉልበተኞች ጨክነው ዘመናትን ካስቆጠሩ፣ ወረራው በይርጋ እንደሚጸናላቸው አዲስ ትምህርት እየተገኘ ነው። አሜሪካ በኢራቅ ስድስተኛ ዓመቱን እያስቆጠረ ነው፤ ስንት ዓመት ይቀረዋል? ሆኖም የአሜሪካ መንግሥት ከህዝብ ፈቃድ ውጭ ጉልበት የለውምና ወረራው በአሜሪካ ህዝብ ትዕዛዝ የሚያበቃበት ጊዜ ያለ ጥርጥር ይመጣል።

በደርግ ዘመን ሱዳን ከአሜሪካ ጋር ኢትዮጵያን ለመጥለፍ በተወዳጀችበት ጊዜ፣ ሊቢያ ደግሞ ሱዳንን ለመጥለፍ በቢሊዮን የሚቆጠር ዶላር እሰጣለሁ ብሎ ኢትዮጵያን ሲያባብል ነበር። እሳትን የሚያነድድና የሚያቀጣጥል ዶላር፣ እሳቱን ለማጥፋት በመሞከር ላይ ይውላል እንጂ ሌላ ፋይዳ አይሠራም።

በአሁኑ ጊዜ አሜሪካ አለ ልማዱ ኢትዮጵያ ሶማልያን እንድትወርለት የፈቀደው፣ አንዳንድ የዋሆች እንደሚያስቡት ኢትዮጵያ ያጣችውን የቀይ ባሕሩን ወደብ፣ በሕንድ ውቅያኖስ ወደብ ለመካስ አይደለም፤ አጼ ኃይለሥላሴ ያጋጠማቸው ክፉ ምርጫ ከቤናድርና (የቀድሞ የሶማልያ ስም) ከኤርትራ ነበር፤ እሳቸው የፈለጉት ሁለቱንም ነበር። ዛሬ አሜሪካ ኢትዮጵያን የሚክስበትም ሆነ ዘላቂ ጥቅምዋን የሚፈልግበት አንድም ምክንያት የለም። ለአሜሪካ የኢትዮጵያ ጥቅም ሦስት ብቻ ይመስለኛል። አንዱ አልገብርም ያለውን ኤርትራን ለማስፈራሪያ ነው፤
ሁለተኛው ኢትዮጵያን ከእስልምና ጋር በዘላቂ ቅራኔ ለማጣመድ ነው፤ ሦስተኛው በይፋ እንደሚባለው አክራሪ የእስልምና ሽብርተኞች በሶማልያ ውስጥ እንዳይገቡ ለመከላከል ነው። ሁለተኛውና ሦስተኛው የተያያዙ ናቸው። ሦስቱም የአሜሪካ ዓላማዎች የኢትዮጵያን መሠረታዊና የዘለቄታ ዓላማዎች የሚቃረኑ ናቸው።



ለአሜሪካ ጥቅም ስትል ሶማልያን በመውረር ኢትዮጵያ የምታገኘው ጥቅምስ ምንድን ነው? መሣሪያና ስንዴ። በተረፈ ጉዳቱ፣ ሰፊና ዛሬ በሕይወትም ሆነ በአካል ከሚያስከትለው ጉዳትና በውስጥ ፖለቲካም ሆነ በውጭ በተለይ የጎረቤቶች ፖለቲካ ላይ ከሚያሳድረው ተፅዕኖ በላይ ለብዙ ዘመናት የሚቆይ የቆላ ቁስል ይሆናል የሚል ብርቱ ስጋት አለኝ። በገንዘብ በኩል የሚያስከትለውን የማላነሳው ምናልባት የኢትዮጵያ አይሆንም በማለት ነው። ከአካባቢው አገሮች መማር ይቻላል፤ ሶማልያ ለአሜሪካ ገብራ ምን አገኘች? ሱዳንስ? ፓኪስታንስ? በሰሜን በኩል በአንድ የከፋ ጦርነት ከወገኖቻችን ጋር ተፋጅተን ክፉ ቂምን አተረፍን፤ አሁን ደግሞ በደቡብ በኩል ከሌሎች ወገኖቻችን ጋር ተፋጅተን ሌላ ቂምን የምናተርፈው ማን ይድላው ብለን ነው? የአሁኑ ቂም ግን ይሰፋልም፤ ይጠልቃልም። የሶማልያን ድንበር ያልፋል። ስለዚህ ቶሎ መላ ሊፈለግለት ይገባል።

Fiyameta
Senior Member
Posts: 12679
Joined: 02 Aug 2018, 22:59

Re: * ስበር ዜና * '' እውቁ ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም በኮሮና ታመው ህይወታቸው አልፏል፡፡ '' በሰላም ይረፉ! ነፍስ ይማር

Post by Fiyameta » 30 Sep 2020, 13:16

Rest In Peace Ethio Lion!
Please wait, video is loading...


simbe11
Member
Posts: 2087
Joined: 23 Feb 2013, 13:02
Location: Addis Ababa

Re: * ስበር ዜና * '' እውቁ ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም በኮሮና ታመው ህይወታቸው አልፏል፡፡ '' በሰላም ይረፉ! ነፍስ ይማር

Post by simbe11 » 30 Sep 2020, 15:05

I don't really like whet he did during his time a special investigator of the 60s.
He never had the nerves to apologize for his part for the demise of those people.
I do like the way he stood against the tyrant.
He was a pain in the a** for Meles and his successors.
I appreciated his stance during the illegal and shameful deportation of Eritreans in 98/99.
We might don't know it. But we lost somebody. We lost a voice.
But now he passed and the only thing I could say is R.I.P.

Post Reply