Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum

Dawi
Member
Posts: 4311
Joined: 30 Aug 2016, 03:47

Re: የኢንሳው ጸጋዬ ተክሉ ምስጢር ትግሬዎቹ የአቢይን የፖለቲካ አምቢሽን ለመቅጨት ያደረጉት ሙከራ ነበር ወይስ ኢሳትን ለማውረድ?

Post by Dawi » 21 Sep 2020, 18:28

Horus,

የፖለቲካ አምቢሺን ለመቅጨት እንዳንል ከላይ ያሉት ባለስልጣናት ንቀት ስለነበራቸው ያን ያህል አይሄዱም ማለት ይቻላል፣

በነፀጋዬ ደረጃ ግን ትንሽ ይኖራል፣ ትንሽ የወረፈውም ለዚያ ይሆናል፤

በነገራችን ላይ መለስ ወጣቶችን ሁኑ እያለ ይመክር የነበረውን ነው ዐብይ የሆነው፣ በብቃት ሥልጣንን ውሰዱ ማለት በጠመንጃ ሳይሆን ሰብስቦ ይላቸው ነበር። የአይምሮ ደረቅ የሆነ ሰው የመለስ ምክር ይተገበራል ብሎ ማሰብና ማመን ይቸገራል፣ ጉዳዩም ይገባዋል ማለት እይቻልም፣ ስለዚህ መቀሌ የገቡት ዐብይን እዚህ ይደርሳል አላሉም።

That is why more or less, Abiy's mission is accomplished.
Horus wrote:
21 Sep 2020, 14:13

Horus
Senior Member+
Posts: 30911
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: የኢንሳው ጸጋዬ ተክሉ ምስጢር ትግሬዎቹ የአቢይን የፖለቲካ አምቢሽን ለመቅጨት ያደረጉት ሙከራ ነበር ወይስ ኢሳትን ለማውረድ?

Post by Horus » 22 Sep 2020, 01:04

ዳዊ
ካንተ ጋር እስከ ተወሰነ ምስምማው ለምን መሰልህ?

አቢይ ለብዙ አመታት መሪ የመሆን፣ በተለይም ጠ/ሚ መሆን የኦሮሞ ተራ ሲሆን (ትግሬ ሆኖዋል፣ ደቡብ ሆኖዋል ፣ አማራ ይቀጥላል፣ ከዚያ ኦሮሞ ነበር ረድፉ !) ይህ ተራ ሲመጣ አቢይ ቦታውን እንደ ሚወስድ ብዙ መለስ ጭምር ያውቁ ነበር ። ትግሬዎቹ ያላወቁት፣ ወይ አውቀው የናቁት ነገር አቢይ ጽረ ዎያኔ፣ ጸረ ዘር ፖለቲካ እንደ ሚሆን በውል ያወቁ አይመስለኝ፤ ቢያውቁም በዚህ ደረጃ ማህበርዊ መሰረቱን ወደ ኢትዮጵያ አዙሮ ከኢሳያስ ጋር ገጥሞ ይህን ያክል መንቀጥቀጥ ያመጣል ብለው አላሰቡም ። አማራና ኦሮሞ ፈጽሞ አንድ አይሆኑም ብለው አላሰቡም ። ሌላው ቀርቶ የመጨረሻው ያዋሳ ስብሰባ ላይ ከደቡብ 18 ድምጽ ያገኛል ብለው አላሰቡም ። ስለዚህ በእኔ ግምት ያቢይ አምቢሽን አውቀው ግ ን በፈለግ ነው ግዜ እናስቆመዋለን የሚል እብሪት የነበራቸው ይመስለኛ ። በራሳቸው ሃይማኖት የሚያምኑ ዲክታተሮች ችግር ሁሉ ይህ ነው፣ ቀስ በቅስ የርሳቸውን ህልም ማመን ይጀምራሉ ። ይህ ሁሉ ሆኖ ግ ን ጸጋዬ ተክሉ ረቂቅ የሰላይ ምሽን ይዞ ነው የከዳ የመሰለው። እሱ የሰራ አንዱ የሰላዮች ዘዴ ነው ።

Post Reply