Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Horus
Senior Member+
Posts: 30914
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

መስቀል ምን ማለት ነው?

Post by Horus » 19 Sep 2020, 00:01

መስቀል በጉራጌዎች ዘንድ የፍጥረት ሁሉ፣ የህይወት ሁሉ ምንጭና ምክንያት የሆነው ብርሃን የተወለደበት ወቅት፤ ያለም ሁሉ ብርሃን የሆነው ጸሃይ የወጣበት ወቅት፤ የሰማየ ሰማያት ኢምሮች፣ ከዋክብት የደመቁበት አዲሱ አመት የሚከሰትበት ቀንና ወር የሚከበርበት የፍጹም ደስታና የምርቃት በዓል ነው ። ደመራ፣ ምጅር፣ መጅራ አንድ ትርጉሙ እሳት ነው፣ የብርሃን ምልክት ነው ። ሌላው ጅመራ፣ ያመት መጀመሪያ ማለት ነው !!

የብርሃን ልጆች ሁሉ፣ የወልድ ልጆች ሁሉ እንኳን አደረሳችሁ !!!

መስቀል የኬር በዓል ነው

ኬር ምን ማለት ነው? ኬር እምነትም፣ ፍልስፍናም፣ ባህልም ነው። ለጉራጌ እግዚአብሄር ከሚለው ክቡር ቃል ቀጥሎ ያለው ክቡር ቃል ኬር ነው። ኬርነት ኬርታ የህይወት ፍልስፍና ብቻ ሳይሆን የመጨረሻው የሞራል እና የስነ ምግባር መሰረት ነው። መልካም ነገር ሁሉ፣ ሙሉ ነገር ሁሉ፣ ስኬታማ ተግባር ሁሉ መሰረቱ ኬርነት ነው።

መስቀል የኬር ክብረ በአል ነው። ሁሉም ነገር ሙሉ መሆኑን፣ ትክክል መሆኑን፣ ሰላም መሆኑን፣ ጤነኛ መሆኑን፣ ስኬታማ መሆኑን፣ ሰውም እንሰሳም እጽዋትም፣ አፈርም፣ አየርም፣ ዉሃም ፣ አለምም አለመጉደሉ፣ አለመበላሸቱ እና በደስታ፣ በእርካታ በደህንነት ላይ መሆኑ የሚገለጸው ኬር በሚባለው ነገርን ሁሉ መመልከቻ በሆነው ፍልስፍናና የባህርይ ስነ ምግባር መሰረት በሆነው በዚህ ጽንስ ነው።

ኬር ለጉራጌ ብቸኛው የካልቸሩ መሰረት ነው። ኬር ለጉራጌ አንድ ብቸኛ የኮስሞልጂው መጥሪያ ቃል ነው። ኬር ማለት ሁሉም መልካም ነገር ማለት ነው።

ባንድ ቃል፣ የጉራጌ መስቀል የኬር ክብረ በዓል ነው። ከዋና ዋና ይዘቶችሁ መካከል ከግማደ መስቀሉ መገኛ እስከ የመልካምነት በጎ ተግባር ያሉት የኬርነት አካላት ናቸው ። መስቀሉን ማሰብ፣ ምርቃት፣ ምስጋና፣ ያዲስ አመት ፌስታ (ጌሳት)፣ እርቅ፣ ፍቅር፣ እና ቸርነት ጥቂቱ የኬር መገለጫዎች ናቸ።

በመስቀል እለታት ፈጣሪ ይቀደሳል፣ ልጅ ይመረቃል፣ ወላጅ ይመሰገናል፣ አዲስ አመት ይባረካል፣ ቤት ንብረት ፍጥረት ሁሉ ይባረካል፣ ላለፈው አመት ስኬት ምስጋና ይሰጣል፣ የወደፊቱ አላማ እንዲሟላ አሚን ዬሁን ይባላል፣ ጠብ እርቅ ይሆናል፣ ወጣት ፍቅረኛውን/ዋን ታገኛል፣ የተቸገረ ይረዳል፣ ቤተሰብ አንድ ይሆናል፣ ማህበረሰብ ይተሳሰራል።

ይህ ረዕስ ሙሉ መጽሃፍ የሚሻ ቢሆንም ባንድ ቃል ጉራጌ መስቀልን ሲያከብር ምንን አስቦ ነው ለሚለው አጭር መልሱ ይህ ነው ፣

በጉራጌ ምስጢሩ ይህ ነው መስቀል ማለት ብርሃን ማለት ነው !! ኬር ዬሁን ብርሃን ይሁን !!!

Last edited by Horus on 21 Sep 2020, 17:00, edited 3 times in total.

Horus
Senior Member+
Posts: 30914
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: መስቀል ለጉራጌ ምኑ ነው?

Post by Horus » 19 Sep 2020, 03:12

Horus
Senior Member+
Posts: 30914
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: መስቀል ለጉራጌ ምኑ ነው?

Post by Horus » 19 Sep 2020, 03:23

Horus
Senior Member+
Posts: 30914
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: መስቀል ለጉራጌ ምኑ ነው?

Post by Horus » 19 Sep 2020, 03:36

Horus
Senior Member+
Posts: 30914
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: መስቀል ለጉራጌ ምኑ ነው?

Post by Horus » 19 Sep 2020, 03:55

Horus
Senior Member+
Posts: 30914
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: መስቀል ምን ማለት ነው?

Post by Horus » 21 Sep 2020, 16:26

የንግሊዝ ጉራጌዎች

Horus
Senior Member+
Posts: 30914
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: መስቀል ምን ማለት ነው?

Post by Horus » 21 Sep 2020, 17:11

ይህቺ ሞጥሟጣ የወልቂጤ ድምቡሼ እስቲ በዚህ መስቀል ባል ቢቀናት ??? !!!!

kerenite
Member
Posts: 4478
Joined: 16 Nov 2013, 13:15

Re: መስቀል ምን ማለት ነው?

Post by kerenite » 22 Sep 2020, 13:32

Horus wrote:
19 Sep 2020, 00:01

መስቀል በጉራጌዎች ዘንድ የፍጥረት ሁሉ፣ የህይወት ሁሉ ምንጭና ምክንያት የሆነው ብርሃን የተወለደበት ወቅት፤ ያለም ሁሉ ብርሃን የሆነው ጸሃይ የወጣበት ወቅት፤ የሰማየ ሰማያት ኢምሮች፣ ከዋክብት የደመቁበት አዲሱ አመት የሚከሰትበት ቀንና ወር የሚከበርበት የፍጹም ደስታና የምርቃት በዓል ነው ። ደመራ፣ ምጅር፣ መጅራ አንድ ትርጉሙ እሳት ነው፣ የብርሃን ምልክት ነው ። ሌላው ጅመራ፣ ያመት መጀመሪያ ማለት ነው !!

የብርሃን ልጆች ሁሉ፣ የወልድ ልጆች ሁሉ እንኳን አደረሳችሁ !!!

መስቀል የኬር በዓል ነው

ኬር ምን ማለት ነው? ኬር እምነትም፣ ፍልስፍናም፣ ባህልም ነው። ለጉራጌ እግዚአብሄር ከሚለው ክቡር ቃል ቀጥሎ ያለው ክቡር ቃል ኬር ነው። ኬርነት ኬርታ የህይወት ፍልስፍና ብቻ ሳይሆን የመጨረሻው የሞራል እና የስነ ምግባር መሰረት ነው። መልካም ነገር ሁሉ፣ ሙሉ ነገር ሁሉ፣ ስኬታማ ተግባር ሁሉ መሰረቱ ኬርነት ነው።

መስቀል የኬር ክብረ በአል ነው። ሁሉም ነገር ሙሉ መሆኑን፣ ትክክል መሆኑን፣ ሰላም መሆኑን፣ ጤነኛ መሆኑን፣ ስኬታማ መሆኑን፣ ሰውም እንሰሳም እጽዋትም፣ አፈርም፣ አየርም፣ ዉሃም ፣ አለምም አለመጉደሉ፣ አለመበላሸቱ እና በደስታ፣ በእርካታ በደህንነት ላይ መሆኑ የሚገለጸው ኬር በሚባለው ነገርን ሁሉ መመልከቻ በሆነው ፍልስፍናና የባህርይ ስነ ምግባር መሰረት በሆነው በዚህ ጽንስ ነው።

ኬር ለጉራጌ ብቸኛው የካልቸሩ መሰረት ነው። ኬር ለጉራጌ አንድ ብቸኛ የኮስሞልጂው መጥሪያ ቃል ነው። ኬር ማለት ሁሉም መልካም ነገር ማለት ነው።

ባንድ ቃል፣ የጉራጌ መስቀል የኬር ክብረ በዓል ነው። ከዋና ዋና ይዘቶችሁ መካከል ከግማደ መስቀሉ መገኛ እስከ የመልካምነት በጎ ተግባር ያሉት የኬርነት አካላት ናቸው ። መስቀሉን ማሰብ፣ ምርቃት፣ ምስጋና፣ ያዲስ አመት ፌስታ (ጌሳት)፣ እርቅ፣ ፍቅር፣ እና ቸርነት ጥቂቱ የኬር መገለጫዎች ናቸ።

በመስቀል እለታት ፈጣሪ ይቀደሳል፣ ልጅ ይመረቃል፣ ወላጅ ይመሰገናል፣ አዲስ አመት ይባረካል፣ ቤት ንብረት ፍጥረት ሁሉ ይባረካል፣ ላለፈው አመት ስኬት ምስጋና ይሰጣል፣ የወደፊቱ አላማ እንዲሟላ አሚን ዬሁን ይባላል፣ ጠብ እርቅ ይሆናል፣ ወጣት ፍቅረኛውን/ዋን ታገኛል፣ የተቸገረ ይረዳል፣ ቤተሰብ አንድ ይሆናል፣ ማህበረሰብ ይተሳሰራል።

ይህ ረዕስ ሙሉ መጽሃፍ የሚሻ ቢሆንም ባንድ ቃል ጉራጌ መስቀልን ሲያከብር ምንን አስቦ ነው ለሚለው አጭር መልሱ ይህ ነው ፣

በጉራጌ ምስጢሩ ይህ ነው መስቀል ማለት ብርሃን ማለት ነው !! ኬር ዬሁን ብርሃን ይሁን !!!

Greetings horus,

I read in one of your posts somewhere that the gurages are decent people and hard working.They detest beggary and robbery. I wholeheartedly concur with you.

This reminds me of our bilen ethnic group in Eritrea. There is a bileni adage which goes [bilen yiseriQ weyi remiQ] roughly translated, a bileni neither begs nor robs.

True, you won't find a single bileni begging or robing other's properties. Same as the gurages they are hard working people.

Finally, I love gurage folklore songs and dances and I enjoy it. Besides the gurage kitfo. Apropos kitfo, if you happen to visit addis do not miss to visit YOHANNES KITFO restaurant located in 22 mazoria, it is famous and any taxi driver knows the location.

KHEIR as the arabs same as the gurages say.

Horus
Senior Member+
Posts: 30914
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: መስቀል ምን ማለት ነው?

Post by Horus » 22 Sep 2020, 14:22

kerenite wrote:
22 Sep 2020, 13:32

ሰላም ከረናይት፣

አመሰግናለሁ ! አው ጉራጌም ተመሳሳይ ተረቶች አሉት ። አንዱ 'ባለነን ንበላ፣ በሌለ ትኒላ' ይላል፤ እሱም 'ካለን እንበላለን ከሌለን አንለምንም' ማለት ነው። አንዱ ደሞ 'ዉዘየም ያልገራ፣ ቲሰርቅም ቲገራ' ይላል ። እሱም 'ሰርቶ ያልጠገበ ሰርቆ አይጠግብም' ማለት ነው ።

የደስታ መስቀል ይሁንልህ !!

Hawzen
Member+
Posts: 7274
Joined: 07 Jun 2012, 05:03

Re: መስቀል ምን ማለት ነው?

Post by Hawzen » 22 Sep 2020, 19:14

መልካም መስቀል በዓል, brother Hours::

I have eaten Kitfo in different Ethiopian restaurants many times. But I will never forget the Kitfo that I ate at my በጉራጌ friend house for the first time. That was the most delicious food and it was definitely second to none. I believe Kitfo might be my favourite food.

ላንተም የደስታ መስቀል ይሁንልህ !!

God bless the people of Gurage and Ethiopia!!

Dedebit is always dedeb
R.I.P Abay Tigray and TPLF

Horus
Senior Member+
Posts: 30914
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: መስቀል ምን ማለት ነው?

Post by Horus » 23 Sep 2020, 01:03

Hawzen wrote:
22 Sep 2020, 19:14
መልካም መስቀል በዓል, brother Hours::

I have eaten Kitfo in different Ethiopian restaurants many times. But I will never forget the Kitfo that I ate at my በጉራጌ friend house for the first time. That was the most delicious food and it was definitely second to none. I believe Kitfo might be my favourite food.

ላንተም የደስታ መስቀል ይሁንልህ !!

God bless the people of Gurage and Ethiopia!!

Dedebit is always dedeb
R.I.P Abay Tigray and TPLF
Hawzen,

የኬር አመትና የደስታ መስቀል ላንተም !!

Horus
Senior Member+
Posts: 30914
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: መስቀል ምን ማለት ነው?

Post by Horus » 23 Sep 2020, 16:44

የጉራጌ መስቀል በዚህ ዘመን የቅድመ ክርስትናን የኦሪትን የኦርቶዶክስን እምነት ምልክቶች ያዋህዳል። ተራ ቃሉ መስቀል መስቀለኛ መሰቀያ እንጨት ነው ። ያ አይደለም የጉራጌው ትርጉም ። በግሬክ ኪይሮ የተቀባ አኖይትድ ማለትም ክርስቶስ ማለት ነው ። በእብራይስት መሲያ የሚባለው የተቀባ ወይም ቅብ የሚባለው ማለት ነው ። በኢትዮጵያም የቅብ እና የወልድ ልጆች የሚባለው ያ ነው ። ስለዚህ መስቀል ሌላው ትርጉሙ የተቀባው መሲያ ማለት ሲሆን ያው የክርስቶስ ስም ነው።

ሌላው መስቀል ምስራቅ ከሚለው ከልደት፣ ከክርስቶስ ልደት ከገና ጋር የተያያዘው ነው ። ይህ ከክርስትና በፊት የብርሃን ልደት (ምስራቅ) ልደተ ብርሃን የሚለው ነው ። ይህ ድሮ ካዲስ አመት፣ ከመስከረም (መስቀለም) የብርሃን ልደት ጋር ያለው ነው ። የጉራጌ መስቀል ያ ነው ። የልደተ ብርሃን ምልክቱ እሳት ነው ። ያ ደመራ ነው (የእሌኒ ታሪክ ኦርቶዶክሱ ነው) ። ደመራ በጉራጌኛ ምጅር ይባላል፣ መጀመሪያ ወይም የፍጥረት መጀመሪያ ይባላል። አዲስ አመት አክራሚ ይባላል። ሁለቱ ቃልት ግንዳቸው አንድ ነው ። ያመት መጀመሪያ፣ የመከር ወቅት፣ ወዘተ ማለት ነው ። የምጅር እሳት ሚነደው የብርሃን፣ የጸሃይን መወለድ ለማክበር ነው። ይህም ብርሃነ መስቀል ይባላል። ክርስቶስም ቢሆን ሌላ ስሙ ብርሃን ነው።

ስለዚህ በጉራጌ አንዱ መስቀል ደንጌሳት (የልጆች፣ የህጻናት እሳት) ሲሆን ሌላው ያጼው መስቀል ይባላል። የዴንጋ ኧሳት ትርጉሙ ያው ለወጣቱ ብርሃን ለብርሃነ ወልድ ማመልክቻ ማለት ነው ። ያው እንደ ሚባለው ማ ያርዳ የቀበረ፣ ማ ይንገር የነበረ ስለሆነ ገና ብዙ ምስጢር ይገለጻል !! ሁሉም በኬር አምላክ ዘንድ አ

Horus
Senior Member+
Posts: 30914
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: መስቀል ምን ማለት ነው?

Post by Horus » 23 Sep 2020, 23:41

Naga Tuma
Member+
Posts: 5545
Joined: 24 Apr 2007, 00:27

Re: መስቀል ምን ማለት ነው?

Post by Naga Tuma » 24 Sep 2020, 01:55

ሆረስ፤

ኬር የሚለዉን ቃል ጽንሰ ሀሳብ በጥልቀት መረዳት ሞክሬ ኣልቻልኩም ነበረ። እዚህ የጻፍከዉ ኣንድ ጊዜ ኣንድ ቻይናዊ ወይም መሰረቷ ቻይና የሆነ ሰዉ ቶስትማስተር የሚባል ክበብ ላይ የተናገረችዉን ሀሳብ ኣስታወሰኝ።

የንግግርዋ ጽንሰ ሀሳብ ሃርሞኒ (harmony) የሚለዉ የእንግሊዘኛ ቃል ነዉ። ቀልቤን ስቦት የነበረዉ ንግግሯ ኣንተ እዚህ ከጻፍከዉ ጋር ተመሳስሎብኝ ጽንሰ ሀሳቦቹ ይገናኙ ይሆን ብዬ እራሴን ጠየኩኝ። መልሱን ባላዉቅም የሃርሞኒን መነሻ (origin) ኣየሁኝ። በግሪክ ቋንቋ (ቆንቆ) ሃርሞኒያ ነዉ።

ከዛም ኬር እና እግዝኣብሄር ዉስጥ ያለዉ ሄር ይገናኙ ይሆን ብዬ እራሴን ጠየኩኝ። መልስ የለኝም።

ከዛም ከ እና ኸ የፊደል ገበታ ዉስጥ ለምን ጎን ለጎን ተቀመጡ፣ ለምን ተመሳሰሉ ብዬ እራሴን ጠየኩኝ። ኣሁንም መልስ የለኝም።

በመጨረሻም ከ እና ኸ በታሪክ የተወራረሱበት ቋንቋ ይኖር ይሆን ብዬ እራሴን ጠየኩኝ። ለዚህም መልስ ያለኝም።

በግምታዊዉ ኣስተሳሰቤ ከ እና ኸ በታሪክ የተወራረሱበት ቋንቋ የነበረ ከሆነ፣ ኬር ምናልባት ኼርም መባል ይችላል። ኼር እና ሃርሞኒ ደግሞ የተገናኙ ሊሆን ይችላል። ሁለቱ የተገናኙ ከሆነ የኣንተ ስለ ኬር ገለጻ እና የቻይናዊቷ ስለ ሃርሞኒ ገለጻ ሊመሳሰሉ ይችላልሉ።

ካልሆኑ የእኔ ግምቶች ስህተት ናቸዉ ማለት ነዉ። ከሆኑ ይህ የዘመናችን ህዳሴ ሌላ ፍንጣቂ ሊሆን ይችላል። ካልተሳሳትኩ የኣይላንዱ ሴይንት ፓትሪክም ስለ ሃርሞኒ ስያስትምር ኖሯል የሚል የሆነ ቦታ ያነበብኩኝ ወይም የሰማሁኝ ይመስለኛል።

ስለዚህ ለኣንተ ያለኝ ኣጭር ጥያቄ የኬር (ኼር?) እና ሃርሞኒ ጽንሰ ሀሳቦች የምያመሳስላቸዉ ነገር ኣለ? ከሌለ ኬርን መግልጽ የሚችሉ የኣማርኛ ወይም እንግሊዘኛ ቃሎች ምንድናቸዉ? በተጨማሪ፣ በእናት እና ልጅ መሃል ያለዉን ፍቅር ኬር እንዴት ይገልጸዋል?

መልካም መስቀል። መድረክ ላይ ኣንጋፋዉንም ታናሹንም ኣንተ ስላምል ኣንቱ ባለማለቴ ከይቅርታ ጋር ነዉ። የእድሜ ጸጋን ኣልዘነጋሁም።

Horus
Senior Member+
Posts: 30914
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: መስቀል ምን ማለት ነው?

Post by Horus » 24 Sep 2020, 02:38

Naga Tuma,

እንደ ተለመደው ያክብሮት ሰላምታዬ ይድረስህ ! ደሞ የደስታ መስቀል ይሁልህ !!!

ጥያቄዎችህ ሁሉም ትክክል ናቸው፤ ሁሉም መልስ አላቸው ። ያልከው ትክክል ነው፤ የኮንፉሺየስ (የቻይና ጥንታዊና ፊዉዳል) ፊሎሶፊ መሰረታዊ መቆሚያው ስምምነት (ሃርሞኒ ነው) ። የቻይና ቃል ስለማላቅ በቻይና ምን እንደ ሚባል አላቅም። የግሪኩ ቃል ሃርሞኖ ሁለት ክፍለ አለው ። ፤ ሃር ወይም ሄር የሚለው እንዳልከው ነው ፤ካር ወይም ኬር ማለት ነው ። እሱም ትክክል፣ ልክ፣ የተስማማ፣ የተጋጠመ፣ አንድ የሆነ ፣ ሙሉ ፣ ሆል ፣ ሆሊ ፣ ሆሊስቲክ ማለት ነው ። ይህ ትርጉም ከጥንታዊ ግብጽ እስከ ግዕዝ፣ እስከ ላቲን እስከ ሳንስክሪት አንድ ነው። ሞኖ ማለት እንደ ምታቀው ' አንድ' ማለት ነው ። ስለዚህ ሃርሞኒ ማለት 'አንድ መሆን ማለት ነው !!! ስምምነት፣ ሲማ፣ ስሜ ስንል እኔን መሳይ፣ ተመሳዬ ማለት ነው ።

ግ ን ኬር ወይም ኬሮ ማለት ሃይል፣ ዲቫይን ሃይል ወይም ፈጣሪ ሃይል ማለት ነው ፣ ከግብጽ እስከ ዛሬ ። ክራይስት፣ ክርስቶስ የሚለው ቃል ሁሉ ስር ያለው እዚያ ነው ። ተራ ትርጉሙ ጸሃይ ወይም ብርሃን ማለት ሲሆን ሃይማኖታዊ ትርጉሙ ፈጣሪ ማለት ነው ። ኬሮና ክሪኤት አንድ ቃል ናቸው !! በጣም ጥሩ ተመራማሪ ነህ !! ኬር ናጋቲ !

kerenite
Member
Posts: 4478
Joined: 16 Nov 2013, 13:15

Re: መስቀል ምን ማለት ነው?

Post by kerenite » 24 Sep 2020, 12:40

Greetings all,

Here is my 2 cents regarding the word or concept KER:

Originally it is an arabic word and the gurage muslims were (are) applying it.

Let me give examples, the arabs for instance apply such term when they meet any by saying:

SEBAH AL KER or good morning (ቆንጆ tewat yargilachihu) or MESAA AL KER
..good evening (Qonjo mishit yargilachihu) Here the term KER (ኸር) implies good wishes.

It has nothing to do with debtera history attributed to Saba this or greece this or
Roman this etc...no need to roam around the bushes to disprove it ain't arabic word.

Even in lowland eritrea we apply the term KER on daily basis.

It has nothing to do with religion, the term was there prior to the inception of islam.

Selam

Horus
Senior Member+
Posts: 30914
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: መስቀል ምን ማለት ነው?

Post by Horus » 24 Sep 2020, 14:07

Kerenite,

ግድየለም ለትልቅ መደምደሚያ አትቸኩል። ምን ላይ ትክክል እንደ ሆንክ እና ምን ላይ እንደ ማታውቅ ልንገርህ ። ከላይ ያልከው ኬር በአረብኛ ውስጥ በሰፊው ስለመኖሩ ትክልል ነህ ። ሌላው ቀርቶ በጉራጌ ሴራ (የግዕዙ ስርዓት) በአረብኛ ሸሪዓ የሚባለው ነው ። ኬር ከክርስትናም እስልምናም በፊት መኖሩ ሁሉ ትክክል ነህ ። እኔም ከላይ ያልኩትኮ እሱን ነበር።

የዕውቀትህ ውሱንነት አሁን ከታች ተመልከት ....

አንድ፣ የኢትዮጵያ የሴም ሕዝቦች የሚናገሩት የሴም ቋንቋዎች አረብኛን በብዙ መቶና በሺ አመት ይቀድሙታል ። አረብኛ ከታሪክ ርዝመት የተላንት ቋንቋ ነው። ኢትዮ ሴሚቲክ ከሱመሪያ፣ አሲሪያ፣ አረሜይክ ከዚያ በፊት ከነበሩ አሁን ከሞቱ ኡጋሪቴ እና ኢብሊቴ የቅርም ምስራቅ ቋንቋዎች ነው ሚቀዳው። የጉራጌ ቋንቋዎች አረብኛ በሺ አመት ይቀድሙታል።

ሁለት፣ በጉራጌኛ እግዚአብሄር እዝኬር ይባላል ። በግዕዝ እግዚ አብ ሄር (ኬር) ማለት ነው ። ይህ ቃል ነው በጥንታዊ ግብጽ፣ በግሪክ (ከግብጽ ወስደውት)፣ በሳንስክሪት፣ በላቲን (ከግሪክ ወስደውት) ያለው የክራይስት ስምና ጽንሰ ነገር ። ጎበዝ ከሆንክ አረብኛ ሄር የሚለውን ቃል ከየት አመጡት ብለህ ጠይቅ? ለመሆኑ አረብኛ መቼ እንደ ተጀመረ ታቃለህ? ይንን ጉግል አድርገው ! ስለዚህ ኬር ፈጣሪ ሃይል ማለት ነው ። ከዛሬ ጀሞሮ ይህን አትርሳ !!

ሶስተኛ፣
የሴም ቋንቋዎች ሁሉ ግንዳቸው ባብዛኛው ጥንታዊ ግብጽ ወይም ቀምጥ ነው ። በአንድ አምላክ ማመንን ያስተማሩ ግብጾች ናቸው፣ ፍላጎት ካለው ሄደህ እነ አከን አተንን አጥና

የኬር መስቀል !!!

simbe11
Member
Posts: 2087
Joined: 23 Feb 2013, 13:02
Location: Addis Ababa

Re: መስቀል ምን ማለት ነው?

Post by simbe11 » 24 Sep 2020, 15:50

ሆረስ,
በመስቀል የጉራጌ ክርስትያን እና እስላም በአንድ ያከብራሉ ይባላል:: እንደውም የእስላምና የክርስትያን ስጋ በአንድ ድስት ይቀቀላል ይባላል ( የክርስቲያን ስጋ ምልክት ታስሮበት):: ሁለቱ ነገሮች ምን ያህል እውነትነት አላቸው? ጥያቄ ነው!!!

ለማንኛውም ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለብረሃነ መስቀሉ በሰላም አደረሳችሁ!!

Horus
Senior Member+
Posts: 30914
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: መስቀል ምን ማለት ነው?

Post by Horus » 24 Sep 2020, 16:50

simbe11 wrote:
24 Sep 2020, 15:50
ሆረስ,
በመስቀል የጉራጌ ክርስትያን እና እስላም በአንድ ያከብራሉ ይባላል:: እንደውም የእስላምና የክርስትያን ስጋ በአንድ ድስት ይቀቀላል ይባላል ( የክርስቲያን ስጋ ምልክት ታስሮበት):: ሁለቱ ነገሮች ምን ያህል እውነትነት አላቸው? ጥያቄ ነው!!!

ለማንኛውም ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለብረሃነ መስቀሉ በሰላም አደረሳችሁ!!
ያ የተጋነነ ነው ። ትልቅ ሃይማኖታዊ ያልሆነ በዕል ከሆነ ለምሳሌ ሰርግ ሙስሊም ዘመድ ወይ ጎረቤት ቢስሚላሂ ብሎ ያርድና ለብቻ ይሰራላቸዋል ። ስጋ ካልሆነ ለምሳሌ አይብ ጎመን የመሳሰሉት ምንም ችግር የለውም ። በመስቀልና አረፋ የሚሆነው በሙስሊሙ በአል ክርስቲያ ጎረቤት በስራ ይረዳል እንጨት መፍለጥ እህል መወቀጥ ምናንም ። የክሪስቲያን በአልም ሲሆን እንዲሁ። ከዚያ ሌላ ስጋ ወይም ደም በሌለው ነገር እንደ ገንፎ፣ ጭኮ፣ አይብ፣ ጎመን ችግር የለውም ። አንተ ያልከው ዉሸት ነው ። እኔ ሙስሊም ዘመዶች አሉኝ ከድሬ ደዋ ሚመጡ ።

እኔ ማስታወሰው አባታችህን አንድ በግ አውጥቶ ይሰጣቸዋል ፣ ያርዱትና ምግብ ይዘጋጅላቸው ነበር ።

መልካም መስቀል !!

Horus
Senior Member+
Posts: 30914
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: መስቀል ምን ማለት ነው?

Post by Horus » 25 Sep 2020, 15:42

Post Reply