Page 1 of 1

የኢትዮጵያ ፖለቲካዊ እድገት፣ የፖለቲካ ፓርቲዎችና የሕዝብ ተጽዕኖ

Posted: 15 Sep 2020, 21:56
by Horus
ለሚቀጥለው የፓርቲዎች ውይይት የቀረበው ባለ አራት ነጥብ አጀንዳ

ንድ፤ ሕገ መንግስትና ሕገ ማንግስታዊነት

ሁለት፤ ታላቁ የኢትዮጵያ አገራዊ ተቃርኖ ምንድን ነው? (ጎሰኝነትና ኢትዮጵያዊነት?፤ ባለክልል ፤ ክልል አልባ?)

ሶስት፤ የፖለቲካ ፓርቲዎች አደረጃጀት (በዜግነት መሰረት ወይስ በዘውጌነት?)

አራት፤ ከፓርቲዎች አረጃጀት አኳያ ትክክለኛ ምርጫ እንዴት ማካሄድ ይቻላል?


እነዚህ ድንቅ ጥያቄዎች ናቸው !! የአንድ አገር ፖለቲካዊ እድገት ማለት እንደዚህ ነው ። አገር በኢኮኖሚ ብቻ አይደለም የሚያድገው !!!


Re: የኢትዮጵያ ፖለቲካዊ እድገት፣ የፖለቲካ ፓርቲዎችና የሕዝብ ተጽዕኖ

Posted: 16 Sep 2020, 21:01
by Horus
አሁን የኢትዮጵያ ሕዝብ የፖለቲካ እውቀትና ብስለት የት እንደ ደረሰ የሚታይበት ወቅት ላይ ደርሰናል ። ምን ማለቴ ነው?

የመንግስትን ቀን ተቀን ስራ በአይነ ቁራኛ የሚጠብቁት ረድፎች አንደኛ ሚዲያ፣ ሁልተኛ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ ሶስተኛ የሲቪል ማህበሮችና አራተኛው ሕዝቡ ለምሳሌ ግለሰብ ምሁራን ወዘተ ናቸው ። እስካሁን ከሚዲያ ሌላ የቀሩት ቁራዎች ብዙም አይሰሙም ።

እንደ ሚታወቀው የመንግስት ፖሊሲ የሚቀርጹና መንግስትን የሚመሩ የፖለቲካ ፓርቲዎች ናቸው ። የፖለቲካ ፓርቲዎች ያገርና የመንግስት ጥቅም ብቻ ሳይሆን የያንዳንዱ መደብ፣ የሕዝብ አካል፣ ቡድን ፣ ረድፍ ትቅም በፖሊሲያቸው በማካተት መንግስት የመምራትና በመንግስት ላይ ተጽኖ ፈጣሪዎች ናቸው።

ነገር ግን የፖለቲካ ፓርቲዎችን ስራ በአይነ ቁራኛ የሚጠብቅ፣ የሚደግፍ፣ የሚተች ማነው? ያ ከላይ ያሉት የሚዲያው፣ የሲቪል ማህበራትና ሰፊው ሕዝብ (ምሁር፣ ነጋዴ፣ ደበሬ፣ ወዘተ) ናቸው ስለሆነም ...

ለምሳሌ ለሚቀጥለው የፓርቲዎች ውይይት 4 ትላልቅ ያጀንዳ ርዕሶች ተመድበዋል ፤ እንሱም ...

ሕገ መንግስትና ሕገ ማንግስታዊነት
ታላቁ የኢትዮጵያ አገራዊ ተቃርኖ ምንድን ነው?
የፖለቲካ ፓርቲዎች አደረጃጀት
ከፓርቲዎች አረጃጀት አኳያ ትክክለኛ ምርጫ እንዴት ማካሄድ ይቻላል?

ናቸው ። ይህ ሆኖ ሳለ ...
እስካሁን ድረስ የሚዲያው ሆነ፣ የሲቪሉ ረድፍ፣ ወይም የሕዝቡ አካላት እነዚህን 4 አጀንዳዎች በሚመለከት ፓርቲዎች የሚያቀርቡት ሃሳብ የለም ። ፓርቲዎች ላይ ገምቢም ሆነ ሂሳዊ ተጽኖ ሲያደርጉ አይታይም ።

ይህ ሁሉ የሚያሳየው ህብረተሰባችን ሌት ተቀን ፖለቲካ መሰል ነገሮች ቢነታረክም አንድ የፖለቲካ ኮሚኒቲ ፣ ማቹር የፖለቲካ ኮሚኒቲ ማድረግ የሚገባውን ማድረግ እንዳልጀመረ ነው ።


Re: የኢትዮጵያ ፖለቲካዊ እድገት፣ የፖለቲካ ፓርቲዎችና የሕዝብ ተጽዕኖ

Posted: 17 Sep 2020, 03:53
by Horus
እዚህ ቪዲዮ ውስጥ የአንድ ፖለቲካ ፓርቲ ሚና ምን እንደ ሆነ የኢዜማን ረፖርት ስሙ !!!


Re: የኢትዮጵያ ፖለቲካዊ እድገት፣ የፖለቲካ ፓርቲዎችና የሕዝብ ተጽዕኖ

Posted: 17 Sep 2020, 10:51
by Horus