Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
TGAA
Member+
Posts: 5623
Joined: 07 Apr 2019, 20:34

ማን ነው ለአማራ ህዝብ ጭፍጨፋ ተጠያቂው ፤ የአማራ ብልጽግና ፓርቲ ( አደፓ)

Post by TGAA » 15 Sep 2020, 20:53

በምንም መስፍርት ቢታይ የአማራ ህዝብን በተለየ ሁኔታ ተጠቂ የሚያደርገው ምክንያት ባልኖረ ነበር የወገብ አጥንት ያለው ተወካይ ቢኖረው ኖሮ፡ የአማራ ክልልን ወክያለሁ የሚለው አደፓ (አማራ ብልጽግና ) ትልቅ ድክመት በሚወክለው ህዝብ መጠን በፌደራል ውክልና እንዲኖረውና ተመጣጣኝ ተጽእኖ በፌደራል መንግስት ላይ እንዲያሳድር ከማድረግ ይልቅ እድሜ ልኩን የምጽኦት ጠ ባቂ ከመሆን መዝለል አልቻለም ፡ አንዴ ሀይማኖት ተቋሙ ሲጠቃ፤ አንዴ ሁሉም ብሄር ትላንት የበቀለድ ባንዲራ እንዲያውለበለብ ሲፈቀድ ፤ እርሱ ግን በየመገዱ ላይ ሲከለክል ፤ በየወራቱ ነፍጠኛ እየተባለ ሲሰደድ ፤ ሲገደል ፤ አንዴ በኦሮምያ ከዚያ ደግሞ በቤንሻንጉል ፤ ድምጹን እንኳን ከፍ አድርጎ አትግደሉን የማይል በድን ድርጅት ቢኖር አዴፓ ነው፡ ለምንድነው እንደዚህ ድኩም የሆነው የድርሻውን ቦታ ስለማይጠይቅ ብቻ ነው ፤ በወያኔ ግዜን የነበረውን እንተውና አሁን ያለውን እንይ ፤ ከውጭ ጉዳይ በስተቀር መከላከያ፤ ህዝብ ደህንነት ፤ ብሄራዊ ባንክ ፤ አዲስ አበባ ከንቲባ፤ ሁሉም የተያዘው በኦሮሞ ኢትዮጵያዊያን ነው ፤ ይህ ምንም ባልሆነ ነበር አማራ ሲጠቃ እኩል የሚመክት ፤እኩል የሚያካፍል ፤ እኩል የሚዳኝ ስርአት ቢኖር ኖሮ፤ ነገር ግን በለማ የሚመራው መከላከያው ትእዛዝ ስላልደረሰኝ ብሎ አማራ ሲጨፈጨፍ ቁጭ ብሎ ያያል ፤ አብይ የአማራ ልዩ ሀይል ሲሰለጥን ይከነክነዋል ፤ የኦሮሞ አስተዳደር ግን በየሳምንቱ ያሰመልቃል (4 ዙር ) በአስተሳሰቡ ኢትዮጵያዊ ፤በድርጊቱ ኢትዮጵያዊ የሆነ ሁለ ገብ ፤ ለሁሉም ኢትዮጵያዊ እኩል የሆነ ፤ በንፍትህና በርትህ የሚያስተዳደር የኢትዮጵያ መንግስት እስከሚመጣ ድረስ የአማራ ብልጽግና፤ አብን ፤ ህብረ ብሄራዊ ድርጅቶች በሙሉ ለአማራ ድምጽ መሆነ ነበረባቸው ፡ ፡ እየሆኑ ግን አይደለም ፡፡ አቶ ሺመልስ ወልድያ ላይ 2 ተማሪ ተገደለ ብሎ መግለጫ ያወጣል ፤ አዴፓ ግን 300 ሰው ታርዶበት ትክክል አይደለም እንኳን ብሎ እንኳን አያወግዝም ፤ በፊት ለፊት የሚደረግ ወንጀል ዘር ማጥፋት ፤ ፊት ለፊት ነው መወገዝ ያለበ ፤ ከተዘጋ በር በስተጀርባ አይደለም ፡፡ የአማራ ብልጽግና ለክ እንደሌላው ኢትዮጵያዊያን በሞላ ተመጣጣኝ ስልጣንና ተጸእኖ በፊደራል መንግስቱ ላይ ማሳደር መቻል አለበት ፤ ይህ ነው አሁን የአማራውን ሰቆቃ እንዲዋጥ እያደረገው ያለው ፡፡