Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
gagi
Member
Posts: 618
Joined: 16 Jun 2013, 16:34

Sham election and hush money

Post by gagi » 12 Sep 2020, 16:30

Amdom Gebreslasie (Opposition)

የትግራዋይነት ውሃ ልክ!

1) ኣንተ ለትግራዋይነት ገና ኣልበቃህም ለሌባ ሌባ ማለት ካቃተህ ለህወሓት ካድሬነት እንጂ ለተፎካካሪ ፓርቲ ለፖለቲከኛነት ኣልደረስክም። ህወሓት ኮሮጆ ዘርፋለች ለማለት እንዴት ይከብደሃል? ዕዙም !

2) መገንጠል እያላቹ የሌለ ትርክት የምትቀባጥሩ ሶስታቹ ድጋፍ ሰጪ ድርጅቶች (ሳወት፣ ውናት፣ ባይቶና) ሃሳባቹና የትግራይ ህዝብ ኣራንባና ቆቦ መሆኑ፤ ገንጣይ ኣስገንጣይ ሃሳባቹ እንዲህ በባዶ ሲሸኝ ዋጥ፣ ዝም የምትሉ ከሆነና ኣሸማቃቂ ሽንፈት ተከናንባቹ ሳለ ቃል የተገባላቹ ብር ለመቀበል ኣቁማዳቹ የምትለግቡ ከሆነ የትግራይን ህዝብ ኣትመስሉትም፣ ኣታውቁትም፣ ኣትወክሉትም።

3) በህዝቡ ፈቃድ በድምር 1 ወንበር የማይሞላ ድምፅ እያላቹ በህወሓት ፈቃድ 38 ወንበሮች የምትቀበሉ ከሆናቹና የፈለገው ድምፅ ብታሰሙ የህወሓት በቀቀንና ኣቃጣሪዎች እንጂ የህዝቡ ድምፅ ልትሆኑ ኣትችሉም። ምክንያቱ ህዝብ ኣልመረጣቹማ።

4) የትግራይ ህዝብ የሰጣቹ ድምፅ እንደ ይሁዳ ለህወሓት ብር የምትለውጡ ከሆነ ሰኣቱ ሲደርስ ልክ እንደ ይሁዳ ራሳቹ ታጠፋላቹ።

5) ለእውነት የእውነት የህዝብ ወኪሎች ከሆናቹ ግን የህወሓት የማደለያ ብር ወደ ጎን በመቱው ሓቁ ታወጡታላቹ።
ወዳጄ ትግራዋይነት ሓቀኝነት፣ ታማኝነት፣ ፅናትና ጀግንነት ነው። እነዚህ ፈተናዎች በብቃት የሚያልፈው ትግራዋይ ፓርቲ ዓረና ትግራይ ብቻ ነው።

የትግራዋይነት ውሃ ልክ ዓረና ነው! ብየ ስነግርህ በኩራት ነው።

ኣንድ ትግራዋይ እንደዚህ ዓይነት ማጭበርበርና ውርዴት ኣጋጥሞት እንዳለ "ዋጠው" ሲባል የሚሰጠው ምላሽ "ሞት ይሻላል" የሚል ነው።

ዓረና በዚህ የነተሎተሎ ምርጫ ያልተሳተፈው ከህወሓት(ትእምት) የሚለቀቅ ብር ጠልቶ ሳይሆን ለትግራይ ህዝብ ካለው ትልቅ ክብር ነው።

ስለ ለራሱ ድምፁ ማሰማት ያልቻለው ፓርቲ የህዝብ ድምፅ ይሆናል ተብሎ ኣይጠበቅም።

ሞት ይሻላል!