Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Wedi
Member+
Posts: 7993
Joined: 29 Jan 2020, 21:44

የፕሮፈሰር መስፍን አስገራሚ ትንታኔ!! "ጉራጌ ተበታተነና ብዙ ስሞች ሰጥቶት የቀረው ዓጽሙ ብቻ ነው!!"

Post by Wedi » 11 Sep 2020, 10:49

የፕሮፈሰር መስፍን አስገራሚ ትንታኔ!! "ጉራጌ ተበታተነና ብዙ ስሞች ሰጥቶት የቀረው ዓጽሙ ብቻ ነው!!" :oops: :oops:

‹‹የኢትዮጵያ ሕዝቦች›› የሚሉት! የኢትዮጵያን ሕዝብ ከሰነጣጠቁት በኋላ ለስንጥቅጥቁም ሰም አውጥተዋል፤ ትግሬ ትግራዋይ ሆነ፤ መቀሌ መቐለ ሆነ፤ በዚህ ጉዳይ ላይ ሽንጡን ገትሮ ሲከራከር የነበረው የሪፖርተር ‹ጋዜጠኛ› ትዝ ይለኛል፤ ስለባቔላ አያውቅም!

ጋላ ማለት ነውር ሆነና ኦሮሞ ተባለ፤ ጉራጌ ተበታተነና ብዙ ስሞች ተሰጡት፤ እንዲያውም ጉራጌ የቀረው ዓጽሙ ብቻ ነው ለማለት ሳይቻል አይቀርም፤ ወላሞ ወላይታ ተባለ፤ እስላም ሙስሊም ተባለ፡፡
Please wait, video is loading...

Guest1
Member
Posts: 1926
Joined: 28 Dec 2006, 01:02

Re: የፕሮፈሰር መስፍን አስገራሚ ትንታኔ!! "ጉራጌ ተበታተነና ብዙ ስሞች ሰጥቶት የቀረው ዓጽሙ ብቻ ነው!!"

Post by Guest1 » 11 Sep 2020, 15:47

አባይና ዓባይ የተለያየ ነው ብለው የመዘገቡ ትግረኛና ግዕዝ ብቻ የኤርትራውም። በመደበኛ አማርኛ ዐ የለም። ዩ ትዩብ የፊደል ቆጠራ መመልከት ነው። እንደ ወሎና ክፍለሃገር ገጠሬው ለየት ያለ እ ቢኖረውም በጉሮሮ የሚፈጠር ዐ አይነት ስለመሆኑ የተጠና ማስረጃ የለም። ትግረኛን ትግረኛ ያደረገው ዐ እንደሆነ ሁሉ አማርኛን አማርኛ ያደረገው ዐ መጥፋቱ ነው። ፕሮፌሰሩ እራሳቸው ዐ አይጠቀሙም ምናልባት ወደ ትግረኛ ሲወስዳቸው ክክክክ

Horus
Senior Member+
Posts: 30911
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: የፕሮፈሰር መስፍን አስገራሚ ትንታኔ!! "ጉራጌ ተበታተነና ብዙ ስሞች ሰጥቶት የቀረው ዓጽሙ ብቻ ነው!!"

Post by Horus » 11 Sep 2020, 16:52

ቋንቋ የማሰቢያ መሳሪያ ነው። የመግባቢያ መሳሪያ ነው። ቋንቋ ለመፍጠር የሚያስፈልገው ድምጽ ነው እንጂ ምልክትና ፊደል ኋላ የሚመጣ ነው ። ቋንቋ በድምጽ ሰርቶ ለብዙ ዘመን በኋላ ነው ምልክት እና ፊደል የሚባሉት ቴክኖሎጂዎች የተፈለሰፉት ። ለምን ቢባል የተልያዩት ድምጾች ስም እየሰጡ፣ ምልክት እየሰጡ ለማወቅና ለማስታወስ፣ ለመመዝገብ። ስለዚህ ሰዎችን አንዱ ካንዱ የሚለይ ድምጽ ነው ። ድምጽ ባዮሎጂ ነው። ሁለት ወይም መቶ የተለያዩ ህዝቦች (የተለያዩ ድምጾች) በተመሳሳይ ምልክት ሊሰይሙ ይችላሉ ። ከ አንዱ ከ፣ ሌላው ቀ፣ ሌላ ኧ ለሚባሉት ድምጽች ይጠቀማል ።

ቃላትና ቋንቋ ማሰቢያ መሳሪያዎች (ቱልስ) ናቸው ። ማንኪያ የመብሊያ መሳሪያ እንደሆነ ማለት ነው ። እነዚህም ቃላት የነገሮች ማመልክቻ ምልክቶች የሚሰሩት ከምሳሌና (ምስል) እና ሜታፎር (የሃሳብ ማሳፈሪያ) ነው። ዛፍ የአንድ እጽ ስም ነው ። ራሱ ዛፍ የሚለው ድምጽ ለምን ለዚያ እጽ መጠሪያ ሆነ የሚለውን ለማወቅ ፊሎሎጂ ማወቅ ያስፈልጋል። ከዚያ ባለፈ የዘር ዛፍ ካልን ምሳሌና ሜታፎር ውስጥ እንገባለን ። በየትም ሕዝብ ውስት ምሳሌና ሜታፎር አለ፣ እነሱም የሚመነጩት ቁሳዊ፣ አካልዊ፣ ከበባዊ ከሆነ እንቅስቃሴና ማህበራዊ ልምዶች ነው ። ጽንሰ ነገር ወይም ክንሴፕት የምንልቸው ነገሮች ሁሉ ሜታፎሮች ናቸው፣ አንዱን ነገር ብሌላ ነገር በማስመሰል አንድን ትርጉም ወደ ሌላ ነገር በማሳፈር፣ በማሻገር ነው ሃሳባችንን በቋንቋ የምንገልጸው ።

ስለዚህ የሰዎች ልሳንና ላንቃ መንጋጋ የተለያየ ስለሆነ ድምጻቸው ይለያያል ። በዘር በጣም ሚቀራረቡ ሰዎች ተመሳሳይ ድምጽ አላቸው ። ከዚያ ባለፈ የቋንቋ ሰዋስው፣ የቋንቋ ትርጉም፣ የቋንቋ አግባብና ዘይቢዎች (ምሳሌ ቅኔ፣ ሰምና ወርቅ፣ አግብዎ፣ አሽሙር) ሁሉም አርቲፋክቶች ናቸው ።

እና ቁም ነገሩ አ፣ ዐ፣ ሃ፣ ሓ የሚወክሉት የተለያየ ድምጽ መኖር አለመኖር ላይ ነው እንጂ አንድ ቋንቋ ሚነገሩ ተመሳሳይ ድምጽ ያላቸው ወንድማምቾች የተለያየ ፊደል መጠቀም ይችላሉ ፊደላቱ በዚያ ቋንቋ ተናጋሪ እስከ ተለመዱ ድረስ ። ፊደል ምልክት ነው ፣ የሰው ዘር መለያ አይደለም ። ፍጹም ጎደርኛ ሚናገር ፈረንጅ አለ ። ፍጹም ጃፓንኝ ሚነገር አበሻ አለ።

EPRDF
Member
Posts: 2162
Joined: 26 Jan 2010, 12:58

Re: የፕሮፈሰር መስፍን አስገራሚ ትንታኔ!! "ጉራጌ ተበታተነና ብዙ ስሞች ሰጥቶት የቀረው ዓጽሙ ብቻ ነው!!"

Post by EPRDF » 11 Sep 2020, 19:02

Wedi wrote:
11 Sep 2020, 10:49
የፕሮፈሰር መስፍን አስገራሚ ትንታኔ!! "ጉራጌ ተበታተነና ብዙ ስሞች ሰጥቶት የቀረው ዓጽሙ ብቻ ነው!!" :oops: :oops:

‹‹የኢትዮጵያ ሕዝቦች›› የሚሉት! የኢትዮጵያን ሕዝብ ከሰነጣጠቁት በኋላ ለስንጥቅጥቁም ሰም አውጥተዋል፤ ትግሬ ትግራዋይ ሆነ፤ መቀሌ መቐለ ሆነ፤ በዚህ ጉዳይ ላይ ሽንጡን ገትሮ ሲከራከር የነበረው የሪፖርተር ‹ጋዜጠኛ› ትዝ ይለኛል፤ ስለባቔላ አያውቅም!

ጋላ ማለት ነውር ሆነና ኦሮሞ ተባለ፤ ጉራጌ ተበታተነና ብዙ ስሞች ተሰጡት፤ እንዲያውም ጉራጌ የቀረው ዓጽሙ ብቻ ነው ለማለት ሳይቻል አይቀርም፤ ወላሞ ወላይታ ተባለ፤ እስላም ሙስሊም ተባለ፡፡
ክርስቶስ የኢየሱስ ስምነው፣ ክርስትያን ደግሞ የእምነቱ ተከታይ ነው።
ጅዩዲዝም ሃይማኖቱ ሲሆን፣ ጂው ደግሞ የእምነቱ ተከታይ ነው።
ልክ እንደዛው፣ ኢስላም ሃይማኖቱ ሲሆን ሙስሊም የእምነቱ ተከታይ ነው።
ምንም የተቀየረ ነግር የለም ፕሮፌሰሩ የርጅና ትንታኔ ውስጥ ነው።

Post Reply