Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Horus
Senior Member+
Posts: 30903
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

እንቁጣጣሽ የሚለው ቃል እንዴት ተፈጠረ?

Post by Horus » 11 Sep 2020, 01:54

በቅድሚያ እንኳን ለዚህ ቅዱስ አዲስ ቀን አደረሳችሁ ! ከዚህ ከዛሬ ቀን የበለጠ እጅግ ታላቅ ዋጋ ያለው ነገር የለምና !!!

ግን እንቁጣጣሽ ማለት ያንቺ ጣጣ እንቁ ወይም ጌጥ ነው ማለት አይደለም ። ጥንታዊና ትክክለኛ ቃል እንኩታታሽ ነበር ። ለምን ብትሉ? ይህ ያዲስ አመት ቀን ልክ ዛሬም እንደ ምናደርገው ከሰው ሰው፣ ከቤት ቤት ስጦታ ያውም ያበባ፣ ያደይ አበባ የምንሰጣጥበት ቀን ነበር ። ዛሬም ቢሆን ልጆች ያደይ አበባ ባለበት ቦታ አበባ ቆርጠው ለናቶች፣ ለጎረቤት ይሰጣሉ ። ያደይ አበባ በሌለበት በወረቀት ላይ ያበባ ስዕል ስለን እየዞርን እንሰጣለን !!! ይህን ውብ የሆነ ያዲስ አመት ምልክት የሆነውን አበባ እንኩ እንኩ እየተባለ የሚከበር የእንኩታታ ቀን ነበር ። ይህም ማለት ያበባ ስጦታ መሰጫጫ ቀን ነበር ። ይህን የንኩታታሽ ቀን ነው ቃሉ ተበላሽቶ ከ በቀ ተለውጦ፣ ተ በጠ ተለውጦ እንኩታታሽ የነበረው እንቁጣጣሽ የሆነው ። ለዚህም ነው እንቁ የሚለው ቃል ትርጉም አልባ የሆነው ። አዲስ አመት ምንም ነገሩ ከእንቁ ጋር አይገናኝም ። አንድ ቀን ይህ የሚታረም ይመስለኛል !! መልካም አዲስ አመት !!!

Guest1
Member
Posts: 1926
Joined: 28 Dec 2006, 01:02

Re: እንቁጣጣሽ የሚለው ቃል እንዴት ተፈጠረ?

Post by Guest1 » 11 Sep 2020, 06:44

እንኩታታሽ ኮልታፋ ያስመስላል :lol: ስለዝህ ማበላሸት ሳይሆን እንቁጣጣሽ ማሳመር ሳይሆን ኣይቀርም። ክ ወደ ቅ፤ ት ወደ ጥ መቀየር የተለመደ ስለሆነም። እንዳልከው ከእንቁ ጋር አይገናኝም።
መልካም አዲስ አመት ያርግልን!!

simbe11
Member
Posts: 2087
Joined: 23 Feb 2013, 13:02
Location: Addis Ababa

Re: እንቁጣጣሽ የሚለው ቃል እንዴት ተፈጠረ?

Post by simbe11 » 11 Sep 2020, 22:16

የጉራጌው ዘረኛ
ሁሉን የኛ የኛ
ሆረስ,
ከፊንፊኔ ኬኛዎቹ ቄሮዎች የማትሻል ዘረኛ::
እንቁጣጣሽ : እንቁ ለጣትሽ (መታጨት : ጋብቻ : ሰርግ : ደስታ) ያመለክታል:: ጉራጊኛ ለማስመሰል አትፍጨርጨር

Horus
Senior Member+
Posts: 30903
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: እንቁጣጣሽ የሚለው ቃል እንዴት ተፈጠረ?

Post by Horus » 11 Sep 2020, 22:44

simbe11 wrote:
11 Sep 2020, 22:16
የጉራጌው ዘረኛ
ሁሉን የኛ የኛ
ሆረስ,
ከፊንፊኔ ኬኛዎቹ ቄሮዎች የማትሻል ዘረኛ::
እንቁጣጣሽ : እንቁ ለጣትሽ (መታጨት : ጋብቻ : ሰርግ : ደስታ) ያመለክታል:: ጉራጊኛ ለማስመሰል አትፍጨርጨር

አንተ ድንጋይ ራስ፤
አንካ፣ እንካ፣ እንኩታታ አማርኛ እንጂ ጉራጌኛ አይደለም ። አንተ ፍሬፈርስ ታዲያ አዲስ አመትና የሰርግ እንቁ ምን አገናኛቸው? ችግሩ አንተ 32 IQ ባዶ ቅክልህ ውስጥ አዝለህ ይህን ያ1ኛ ክፍል ሎጂክ ሊገባህ አይችልም ። እስቲ ዛሬ እንኳ ለለውጥ ዝም ብለህ አንድ ነገር ተማር !!!

ethiopian
Member+
Posts: 5335
Joined: 09 Oct 2011, 21:29

Re: እንቁጣጣሽ የሚለው ቃል እንዴት ተፈጠረ?

Post by ethiopian » 12 Sep 2020, 01:01

this exactly is what is wrong with Ethiopia ... fuuuckken retards like horus who thinks he got it all. From where i came from nobody cares bout this holiday unfortunately because you fucktards like Horse pushed them aside. We will build a new clean Ethiopia ....

Guest1
Member
Posts: 1926
Joined: 28 Dec 2006, 01:02

Re: እንቁጣጣሽ የሚለው ቃል እንዴት ተፈጠረ?

Post by Guest1 » 12 Sep 2020, 01:07

እንቁጣጣሽ : እንቁ ለጣትሽ (መታጨት : ጋብቻ : ሰርግ : ደስታ) ያመለክታል:: ጉራጊኛ ለማስመሰል አትፍጨርጨር

እንኩታታሽ ጉራግኛም ሊሆነ ይችላል። እንቁጣጣሽ ከተደረገ ኣመቺ የሆነ የድምጽ መቀየር ነው።።

Horus
Senior Member+
Posts: 30903
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: እንቁጣጣሽ የሚለው ቃል እንዴት ተፈጠረ?

Post by Horus » 12 Sep 2020, 01:15

Guest 1 = simbe11 = ethiopian (አሁን ሳይቸግርህ ድብቅ ስሞችህን ሁሉ አጋለጥክ ። ማኦ ሴቱግ ምን ይል ነበር መሰለህ? እባቡ ከተደበቀበት እንዲወጣ ሳሩን አነቃንቀው ይል ነበር ። አንቁታታሽ አማርኛ ነው ስል ማነትህን ሁሉ ነገርከን ።

Guest 1 is simbe11, simbe11 is ethiopian (with small e) ሁሉም ያንድ ወያኔ ካድሬ ስሞች ናቸው :lol: :lol:

ethiopian
Member+
Posts: 5335
Joined: 09 Oct 2011, 21:29

Re: እንቁጣጣሽ የሚለው ቃል እንዴት ተፈጠረ?

Post by ethiopian » 12 Sep 2020, 01:17

wow Horus is a genius Gurage KUNT ... BRAVO

Horus
Senior Member+
Posts: 30903
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: እንቁጣጣሽ የሚለው ቃል እንዴት ተፈጠረ?

Post by Horus » 12 Sep 2020, 01:29


Guest1
Member
Posts: 1926
Joined: 28 Dec 2006, 01:02

Re: እንቁጣጣሽ የሚለው ቃል እንዴት ተፈጠረ?

Post by Guest1 » 12 Sep 2020, 01:32

ethopian
this exactly is what is wrong with Ethiopia ... fuuuckken retards like horus who thinks he got it all.

From where i came from nobody cares bout this holiday unfortunately because you fucktards like Horse pushed them aside.

ኣይዞህ እንደ ፈረንጆች ኑው ዪር እናከብራለን። ክክክክክክክክክክክክ
እንቁጣጣሽ ወይም አዲስ አመትን ሁሉም ያውቃል ኤርትራዊ ካልሆነ በስተቀር። እንዳልከው ግን ሁሉም አያከብረውም። ግን ማን ማንን ፑሽ ኣደረገ? የአረቦች አዲስ ኣመት ፑሽ ተደረገ? ከነበር ደግሞ በኦሮሞ ካሌንዳር ስንተኛው ሺ ይሆን ነበር? ኤርትራ እንቁጣጥዐሽ አይከበርም? እዝያ የፈረንጆች ወይስ የአረቦች ካሌንደር ነው የሚከበረው? ወይስ አዲስ አመት አታከብሩም? ክክክክ

አንተን ብሎ ethiopian

Guest1
Member
Posts: 1926
Joined: 28 Dec 2006, 01:02

Re: እንቁጣጣሽ የሚለው ቃል እንዴት ተፈጠረ?

Post by Guest1 » 12 Sep 2020, 01:47

ሆረስ
ይህ ገስት ነው። ያንተና የተወሰኑ ስዎችን ብቻ እዝህ ፎረም ኣነባለሁ። ሌላው ስማቸውን አይቼ አርእስቱን እንኳን አላነብም። 90% ለስድብ የሚመጣ ነው። ተግባባን?

ethiopian ተረጋጋ ምነው ተቃጠልክሳ!

Guest1
Member
Posts: 1926
Joined: 28 Dec 2006, 01:02

Re: እንቁጣጣሽ የሚለው ቃል እንዴት ተፈጠረ?

Post by Guest1 » 12 Sep 2020, 01:47

ሆረስ
ይህ ገስት ነው። ያንተና የተወሰኑ ስዎችን ብቻ እዝህ ፎረም ኣነባለሁ። ሌላው ስማቸውን አይቼ አርእስቱን እንኳን አላነብም። 90% ለስድብ የሚመጣ ነው። ተግባባን?

ethiopian ተረጋጋ ምነው ተቃጠልክሳ!

Horus
Senior Member+
Posts: 30903
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: እንቁጣጣሽ የሚለው ቃል እንዴት ተፈጠረ?

Post by Horus » 12 Sep 2020, 03:19

Guest1

አሁንማ እንዲያውም ኢትዮአሽ ሆንክብኝ ! ሰማ እኔ እዚህ ፎረም ውስጥ እጅግ በረጅሙ የተጠኑ ነገሮች ብቻ ነው ምጽፈው ። ግ ን ባለጌ ሲሳሰድ እኔ የመርካቶ ልጅ መሆኔን አትርሳ። ኣጥንት በሚሰብር ስብድ ነው ምመልሰው ። አንድም ቀን ያልሰደበኝ ሰው ነክቼ አላቅም ። ግ ን ለባለጌ አልመችም ምክኛቱም እኔ የናገረው በጣም ስለማወቀው ነገር ብቻ ነው። እኔ እዚህ ፎረም ላይ ከ 10 ሺ በላይ ፖስት አለኝ ፣ አንድም ነገር ኢትዮጵያን ካልነካ አልመልስም ፣ እኔን ከነካ ጉራጌን ከነካ መልስ ጠብቅ ! በቃ!! አላማውን የሚደብቅ ፈሪ ነው ወይ ሌባ ነው ።

አንተን የሰደብኩህ "ስለ እንቁጣጣሽ፡ "አትፍጨርጨር" የሚል ቆሻሻ የዎያኔ ቃል ስለተጠቀምክ ነው። እኔ ቋንቋ በሚመለከት አልፍጨረጨርም፤ ላስተምርህ ስለምችል ማለት ነው። እንቁጣጣሽ እንኩታታሽ እንዳልነበር እኔን በመስደብ ልታረጋግጥ አትችልም። እውቀት ካለህ አሳየን? የለህም ! ቢኖርህ ባሁን ግዜ መረጃህን አቅርበህ ነበር ። ይህ ነው የኢትዮጵያ ችግር .. የማያውቁ ሙሉ ቀን ሚለፈልፉበት !! ለምንድን ነው የኢትዮጵያዊ አይ ኩ 68 የሆነው? !!!

Guest1
Member
Posts: 1926
Joined: 28 Dec 2006, 01:02

Re: እንቁጣጣሽ የሚለው ቃል እንዴት ተፈጠረ?

Post by Guest1 » 12 Sep 2020, 04:11

simbe11
Member
Re: እንቁጣጣሽ የሚለው ቃል እንዴት ተፈጠረ?
• Report this post
• Quote
Post Sat Sep 12, 2020 2:16 am
የጉራጌው ዘረኛ
ሁሉን የኛ የኛ
ሆረስ,
ከፊንፊኔ ኬኛዎቹ ቄሮዎች የማትሻል ዘረኛ::
እንቁጣጣሽ : እንቁ ለጣትሽ (መታጨት : ጋብቻ : ሰርግ : ደስታ) ያመለክታል:: ጉራጊኛ ለማስመሰል አትፍጨርጨር
Top

Simba የጻፈውን quote ማድረጌ ነበር።

Horus
Senior Member+
Posts: 30903
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: እንቁጣጣሽ የሚለው ቃል እንዴት ተፈጠረ?

Post by Horus » 12 Sep 2020, 05:29

ያቤሎ
እኔ እስከ ማውቀው ሲዳማዎች ጨምበለላ መች እንደ ሚወል የሚወስኑት በጨረቃ ዙረት ነው ። ጉራጌ በታሪኩ በኦሪት ዘመን ሁሉ የሚያምነው በጸሃይ፣ በብርሃን ብሎም በብርሃን አምላክ እዝኬር ነው። ጉራጌ የሰማይ አምላክ አምላኪ ነው በሙሉ ታሪኩ ። ሲመርቅም ከሰማይ ይውረድ ከምድር ይውጣ ብሎ ነው የሚጀምረው ልክ ዛሬ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ክዱስ እንደ ምንለው !!!

የሲዳማ አዲስ አመት ክረምት ሲገባ ሰኔ ላይ ነው ። የጉራጌ አዲስ አመት ክርማን (ክረምት፣ የመከር ወቅት) አልፎ ጸሃይ ሲወለድ ዛሬ አክራሚ ላይ ነው አዲስ አመት ማክበር የሚጀምረው ። ይህን በአል ለ15 አድርጎ በመስቀል ታላቁ ለብርሃን አምላክ ምጅር (ደመራ) ተቃጥሎ በአሉን ይዘጋል ። ማንም ጎሳ መስቀልን እንደ ጉራጌ ሚያከብር የለም ። መስቀል የብርሃን፣ የጸሃይ በአል ነው ። ይህን ከሲዳማ ጋር ፍጹም የተለየ ነው። የብርሃን አምላክ ከግብጽ እስከ ኦሪት ይዘን ያለነው እኛ ነን ።


Guest1
Member
Posts: 1926
Joined: 28 Dec 2006, 01:02

Re: እንቁጣጣሽ የሚለው ቃል እንዴት ተፈጠረ?

Post by Guest1 » 12 Sep 2020, 07:00

ጨሃምባላ፤ የፈለግከውን ስም ስጠው ከክረምት ወደ በጋ መሸጋገሪያን በደስታ መቀበል ነው። ሌላ ምክንያትስ ኣለ? ለባላባቱ ግብር የሚከፈልበት ጊዜ ነው? ኣምላካቸውን የሚያመሰግኑብት ጊዜ ከሆነ ሃይማኖታዊ ስለሚሆን ክርስትንና እስላምን ማጥላላት አያስፈልግም።

የፈረንጅና የአረብ ዘመን አቆጣጠር ከአየር ጸባይ መለወጥ ጋር ምንም ግንኙነት የለውም! አዲስ አመት በፈረንጅ አገር በረዶ ነው... የአረቦችም ሌላ። የኢትዮጵያ የዘመን አቆጣጠር ሃይማኖታዊ ነበር ለማለት ይሁን ከ8 አመት ብኋላ ደረሰን የሜለው አፈታሪክ ቢኖርም የጳጉሜ ጉዳይና ከአደይ አበባ፤ ከተፈጥሮ ከባህላዊው ዘመን መለወጫ ጋር እንዴት ሊገጥም እንደቻለ ከታሪክ መጽሃፍ መፈለግ ነው።

Ethoash
Senior Member+
Posts: 26144
Joined: 20 Apr 2013, 20:24

Re: እንቁጣጣሽ የሚለው ቃል እንዴት ተፈጠረ?

Post by Ethoash » 12 Sep 2020, 07:17

እንቁጣጣሽ የመጣው ከግዕዝ ቃል ነው። ፱፱% ቃላቶች ከግፅዝ እንደሚመጣ እወቅ። ለምሳሌ እንቁጣጣሽ አከባበሩ ከትግሬዎች የተቀዳ መሆኑን የሶስት ሺህ ዘመን አለን በሚል ትርክት አማሮች አረጋግጠዋል። ስለዚህ ወዴት ቀረብ ቀረብ።

ጉራጌዎች ቢሆኑንም ጉራ ከሚለው የትግሬ ክፍል ስለመጡ ነው እንደዚህ የስራ ስው የሆኑት ። የአሁኑን ግዜ ጉራጌ ማለቴ አይደለም ሆረር የመሳስሉት የታሪክ አተሎች ናቸው በስመ ጉራጌ አቶ ብር አምጡን ሲደግፍ የነበረ እብድ ነው ። አትፍረዱበት ። አንዳንዴ እብደቱ ቢነሳበት።

አቶ ሆረር አንዳንዴ ግንፍል ሲልበት የኔን የክብር ስም ኤክስፕርት የሚለውን ሊውስድ ይፈልጋል። እኔ የምላቸው ብዙ ነገሮች እውነት እየሆኑ ሲመጡ እሱም ከኔ ተከትሎ እኔ ተብያለሁ ለማለት ፈልጎ ተብቻለሁ ማለት ጀምሮ ነበር አንድ ስሞን።

እኔ በጥሩ ሁኔታ ቄሮ የሻሽመኔውን ንፅ ደም ሲያፈሱ ። አብይ አለቀለት ሻሽመኔን ዘግቶ ገዳዮቹን ካላደነ እና ለፍርድ በገሀድ ካልዳኘ ብዬ ነበር ያልኩት ደረስ።

ሌሎችም የቴክኖለጂ ምክሬን ለግሼ ነበር ማን ይስመኛል ግን ያልኩት ተራ በተራ እየሆነ መጥቶ ሲያይ ይህ ተባይ የኔን ገድል ውስዶ እኔ ነኝ ትቢት ተናጋሪ ማለት የጀመረው። በነገራችን ላይ ገድል ፣ ጅግና በነገራችን ላይ ጀግና ለወንድ ነው ለሴት ምንድነው በአማራ የሴት ጀግና ስለሌለ ስያሜው ላይ አልተጨነቁበትም ። ግን በትግርኛ ጀግና ለሴትም አለ።

ጉራጌ አንገቱን ቀና ያረገው መቶ አምሳ አመቱ ቢሆን ነው ጣሊያኖች ካገኙዋቸው በኋላ እንዴት ተደርጎ ነው እንቁጣጣሽን ለትግሬዎችና ለአማሮች የሚያስተዋውቁት። በኔ በኩል ምንም አይነት ልጃገረድ ተፈልጎ ስለማይገኝ አዲስ አበባ ውስጥ አማሮች በሕግ ይህንን በሀል ማክበር መከልከል አለባቸው። ምድረ ስራ ፈት በሙሉ {ምድረ} ግፅዝ ቃል ነው።

አሁንም ለወርቃማዎቹ ሕዝቦች በሙሉ እንኩዋን በደስታና በስላም ምርጫቹሁን ለማካሄድ በቃቹሁ። አባይ ምክሬን ስምቶ ዝም ብሎ አለፋቸው ።እነሱም አረጉ ስማይ እና ምድሩ አልተደባላለቀም ። አማራ ሲያፋሽጉ የነበረው በሙሉ እውነት ሳይሆን ቀረ። አብይ እየለመደ የመጣ ይመስለኛል አማሮችን መስማት ካቆመ ። ኦሮሞችን መፍራት ካቆመ ጥሩ መሪ ይወጠዋል። አሮሞዎቹ ለምን አገራቸውን አያነዱትም ዝም ማለቱ ይሻላል። ምን አገባን ሻሽመኔ የእብዶች አገር ያላቸውን አንዲት ትልቅ ሪዞርት ካቃጠሉ ። ለምን ጉራጌ ሀገር ሪዞርቱ አይስራም ። ለምን ደቡብ አገር ላይ ኢንቨስትመንቱን የሚፈልጉ ክልሎች ተጠይቀው ኢንቨስትመቱ አይስጣቸውም ኦሮሞን ወይም ሻሽመኔን ቅርቅር ማረግ ሲገባን ቡዳ አማራ ስለትግሬዎች አርፈው ስለተቀመጡ አፋቸውን ይከፍታሉ።

አጫሉን የገደሉት በትግርኛ ሲያወሩ ነበር። በምን ሂሳብ ነው እኔ ከዳይ ከሆንኩ በትግርኛ እያወራሁ የመጣሁበትን የማጋልጠው። በዚህ ላይ አጫሉ ሲገደል ምን አባቱ ነበር አባይ የሚስራው ፈደራል ሻሽመኔ ልኮ የቃጠሎ አደጋ ከመድረሱ በፊት የአስቸኩዋይ ግዜ አዋጅ አውጆ ሰውን ፅጥ ለጥ አርጎ መግዛት ሲችል ። ዝም በማለቱ ያ ሁሉ ንብረት ያ ሁሉ ሰው አለቀ። እኔ ከስው ሕይወት ንብረትን አስቀድማለሁ።

ትግሬዎች ያራዳዎቹ ልጆች ታስታውሳላቹ ኦሮሞቹ ወይም ቄሮዎቹ ልደታቸውን ወይም ባህላቸውን ሲያከብሩ ወንዝ ዳርቻ ። ትግሬዎቹ ወታደሮች እስክአፍንጫቸው ታጥቀው ተደብቀው ይጠባበቁ ነበር። አንዲት ቀይ መስመር ቢያልፉ እኔን አያርገኝ ሊያረጉዋቸው። ግን እነዚህ ቡሽቲ ቄሮዎች ትግሬዎች የታጠቁ አልመስላቸውም ፊት ለፊታቸው ያልታጠቁ ፖሊሶች ሲለምኑዋቸው ። አልዳኝ አሉ አሻፈረኝ አሉ ከዚያማ አንዱ ወርቃማ ውጥቶ ፌክ ሹጉት ቢተኩስ ምድረ ቄሮ ገደል ገባ ። የቀረውም በአንድ ቀን ሩጠው ኬንያ ገቡ በመቅፅበት ፍጥነት ። ይህንን አስራር አብቾ ተምሮ ነገሮች ከመሆናቸው በፊት አስቀድሞ መጠንቀቅ አለበት እጅ ከፍንጅ መያዝ የለበትም ። ለዚህም የትግሬዎች አምላክ ረድቶት ፪፯ አምት እነዚህ አህዬች ምራ ብዬ መርቄሐለሁ።

Horus
Senior Member+
Posts: 30903
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: እንቁጣጣሽ የሚለው ቃል እንዴት ተፈጠረ?

Post by Horus » 13 Sep 2020, 01:26

guest1

የሲዳማ ነገር ገለባበጥከው ፣ ሲዳማ አዲስ አመት የሚያከብረ በጋ (በልግ) አልቆ ክረምት ሲገባ ሰኔ ላይ ነው እንጂ ከረምት አልቆ በጋ (ጸደይ) ሲገባል አይደለም ። ሲዳማ ሲመርቅ እርጥብ ሁን ነው የሚለው፣ ማለትም ለዉሃ ነው እንጂ ለብርሃን አይደለም የሚጸለየው ። ብርሃን የሕይወት ሁሉ ምንጭ መሆኑ መርምረው በጻሃይ ያመለኩት ጥንታዊ ግብጾች ናቸው። ሺ ግዜ ዉሃ ቢኖር ብርሃን ከሌለ፣ ሙቀት ከሌለ ሕይወት ሚባለ ነገር የለም ። ሲዳማ ይህን ምስጢር አያቅም፣ አዲስ አመት ሚቆጥረው ዝናብ ሲጀምር ነው።

ኢቶአሽ
እኔ ከዛሬ እስከ መስቀል የፍንደቃል የኬር በዓል ላይ ነኝና መቀባጠሩን ቀንስ ፣ ገና ብዙ ምናስተምራችሁ ነገር ስላለ ታገስ። ላሁኑ በዚህ ተዝናና !!!


Horus
Senior Member+
Posts: 30903
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: እንቁጣጣሽ የሚለው ቃል እንዴት ተፈጠረ?

Post by Horus » 13 Sep 2020, 05:41

አውቃለሁ በዚህ አባባሌ በጣም እንደ ምታዝን፡

አንድ፤ ኦሮሞ ምንም የራሱ የሆነ ቀን መቁጠሪያ የለውም ። ከዚያ ባለፈ በጋላ የተዋጡ ሕዝቦች በቅደመ ኦሮሞ የነበራቸው ባህል ነው ያለው።

ሲዳማ ዘመን የሚቆጥረው በዝናብ መጀመሪያ (ሰኔ) እንጂ በክረምት ማብቂያ መስከረም አደለም። ኦሮሞ በሁለቱም የለበትም ። የቦረና ኦሮሞ የሲዳማ ባህል ያመልካል ። የሸዋ ኦሮሞ የሸዋ ባህል ያመልካል ።

ኢሬቻ መስቀል ማለት ነው። በሸዋ እንጂ የሌላ ኦሮም እምነት አይደለም ። ደሞ ኢሬቻ ወንዝ ወርደው ምንም ማያውቁ መንጋ ያከብሩታል ። የዉሃ እምነት ከሆነ ልክ እንደ ሲዳማ የመገኖ አምላክ ሆኖ ክረምት ሲገባ ነው ሚከበረው እንጂ ክረምት አልፎ የብርሃን የእውቀት ዘመን ሲገባ ወንዝ ወርዶ ዉሃ ሚያመልክ ኢሊትሬት ማህበረሰብ ማለት ነው።

ስለዚህ ኦቦ ይቤሎ ራስህን ብዙ አታጋልጥ ። አንተ ያለህ ኢትዮጵያን የመጥላት በሽታ ነው እንጂ ያንተ ዘር ጸሃይንም፣ ጨረቃንም ፣ አላመለኩም ። ኋልም የብርሃን አምላክ የተባለውን እግዚአብሄርን ወይም የጨረቃ አምላክ የተባለውን አላህን አላመለኩም። ሌላው ቀርቶ የነሲዳማን መገኖ፣ የነ ጃኜኦን ዬሮን አላመለኩም።

ችግሩ ያለው ይህ ኦሮም ይህ እምነት ያ እምነት አመለከ አይደልም ። የኦሮሞ ደንቆሮ ተነስቶ ክርስትናን፣ እስልምናን መሳደብ ሲሞክር ነው።

Wedi
Member+
Posts: 7993
Joined: 29 Jan 2020, 21:44

Re: እንቁጣጣሽ የሚለው ቃል እንዴት ተፈጠረ?

Post by Wedi » 13 Sep 2020, 06:59

:P :oops:

ዕንቁጣጣሽ

ዘመነ ማቴዎስም፣ ዘመነ ማርቆስም፣ ዘመነ ሉቃስም ሆነ ዘመነ ዮሐንስ፤ በአራቱም ዘመናት አስቀድሞ ርእሰ ዓውደ ዓመት ቅዱስ ዮሐንስ(መጥምቁ) ይዘከራል፡፡ ዮሐንስ የስሙ ትርጉም «ጸጋ እግዚአብሔር» ማለት ነው፡፡ ዘመናት ዘመናትን እየወለዱ፣ ሰዓታት ደቂቃን ቅጽበትን /ሰኮንድን/ ሳይቀር እየሰፈሩ/እየቆጠሩ/ ዕለታት ሳምንታትን፣ ሳምንታት ወራትን፣ ወራት ዓመታትን አሁን ላለንበት ዘመን ደርሰናል፡፡ ዓውደ ዓመት በግእዝ ሲሆን በአማርኛ የዘመን መለወጫ/ ቅዱስ ዮሐንስ፣ ዕንቁጣጣሽ እየተባለም ይጠራል፡፡

የ"ዕንቁጣጣሽ" አመጣጥ

ዓመታት ተፈጽመው አዲስ ዓመት ስንጀምር ቅዱስ ዮሐንስ፣ ዓውደ ዓመት፣ አዲስ ዓመት ፣ ዕንቁጣጣሽ እየተባለ ይጠራል፡፡ ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን እንደሚያስረዱት ዕንቁጣጣሽ የሚለው ስያሜው አመጣጥ ወይም ጥንተ ታሪክ በመጀመሪያ ኖኅ ለሦስቱ ልጆቹ አህጉራትን በዕጣ ሲያካፍላቸው አፍሪቃ ለካም ደረሰችው፡፡ በአፍሪቃ ምድርም ሲገባ በመጀመሪያ ያረፈው በኢትዮጵያ ነበር፡፡ ሀገሪቱም በአደይ አበባ አሸብርቃ ነበር፡፡ ወሩ ወርኃ መስከረም በመሆኑ ደስ ብሎት «ዕንቁ ዕጣ ወጣሽልኝ» ይህችን ወቅት እንቁጣጣሽ ብሏታል፡፡

ሁለተኛው የሀገራችን ንግሥት ንግሥተ ሳባ የንጉሥ ሰሎሞንን ዜና ጥበብ እየሰማች ስታደንቅ ትኖር ነበር፡፡ በጆሮዋ የሰማችውን በዓይኗ ዓይታ ለመረዳት ስለፈለገች በግመሎች ላይ ሽቶና እጅግ ብዙ ወርቅ እንዲሁም በኢትዮጵያ የሚገኝ በኢየሩሳሌም የማይገኝ ልዩ ልዩ ገጸ በረከት አስጭና ከብዙ ሠራዊት ጋር ወደ ኢየሩሳሌም ገባች፡፡ ከንጉሡ ሰሎሞንም ጋር ተገናኝታ የያዘችውን ገጸ በረከት ከሰጠችው በኋላ ብዙ ነገሮችን ጠየቀችው፡፡ እርሱም አንድ ነገር ላይ ሰውሮ ሁሉንም ገለጸላት፡፡ ቤተ መንግሥቱንም፣ በቤተ መንግሥቱ የሚገኙ እጅግ በጣም የከበሩ ዕቃዎችን ሁሉ አስጎበኛት፡፡ ሲያበቃ «ዕንቁ ለጣትሽ ጌጥ ይሁንልሽ» ሲል እጅግ በጣም የከበረ ዕንቁ አበረከተላት/ሰጣት/፡፡ ወሩም ወረኃ መስከረም ነበር፡፡ ከዚህ በመነሣት እንቁጣጣሽ የሚለው መጥቷል፡፡ አሁን ከሚፈጸመው ሥነ ሥርዓት ደርሶ በመፈጸም ላይ ይገኛል፡፡ የሚከበረውም መስከረም አንድ ቀን ነው፡፡

አንድም «ዕንቁ ዕፅ አወጣሸ» ብሎ የአበባውን መፈንዳትን ያስረዳናል፡፡

Post Reply