Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Horus
Senior Member+
Posts: 30915
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

ኢትዮጵያ ታላቅ አገር የምትሆነው እንዴት ነው?

Post by Horus » 10 Sep 2020, 21:48

ጠ/ሚ አቢይ አህመድ የ2013 አዲስ አመት ንግግር ሰጥተዋል ። የንግግሩ መፈክር "ወደ ልዕልና እንመጥቃለን ገና" ይባላል። ዛሬ (2020) ኢትዮጵያ 110 ሚልዮን ሕዝብ አላት፣ GDPዋ ወደ 60ኛ አካባቢ ነው።

አቢይ ዛሬ ባሳወቀው "ራዕይ 2030" ማለትም 2040 እንዳውሮፓ፣ ኢትዮጵያ 250 ሚሊዮን ሕዝብ ይኖራታል፤ ባፍሪካ ከሚኖሩት 2 ሃያል አገሮች አንዷ ትሆናለች፤ በአለም ላይ ከሚኖሩት 20 ከፍተኛ አገሮች (Big 20) አንዷ ትሆናለች የሚል ነው።

ልዕልና ማለት ልዑል የበላይ፣ ላይ ያለ፣ ከፍተኛ፣ የላቀ ማለት ነው። ከዚህ ጋር ተያይዞ የአባይ ፕሮጀችትና የዉሃ ሃብት እድገት፤ አረንጓዴ አገር፣ ኩታ ገጠም እርሻ፣ የኢንዱስትሪ ፓርኮች፣ አንድነት ፓርክ፣ የሸገር ዉበትና እንጦጦ ፓርክ ተጠቅሰዋል። የወንጪ፣ ጎርጎራና ኮይሻ ይዋባሉ ተብሏል።

ይህ ሁሉ በጣም ተደጋፊ ራዕይ ነው። ይህም ይሳካ ዘንድ የኢትዮጵያ ሕዝብ በመደመር እስትራተጂ ዙሪያ አንድ ሁኑ ተብሏል ።

ግን የዚህ እስትራተጂ ትልቅ ድክመትና እንዳይሳካ የሚያደርገው የኢትዮጵያ እድገት ከብልጽግና ፓርቲ ጋር ተቋልፎ ከወዲሁ የአንድ ፓርቲ አምባ ገነንነት ማወጁና ቀስ በቀስ ለሚያመረቅዝ፣ ለሚሰፋ አመጽ፣ ግጭትና ቀውስ ቀጠሮ መስጠቱ ነው። ኢትዮጵያ ቻይና አይደለችም። ኢትዮጵያ በጣም የተከፋፈለ፣ የተቋሰለ፣ ያልዳነ ቁስል፣ ገና ያልታከመ ቁስል ባለልበት አገር እንደ ኮሚኒስት ቻይና ያንድ አውራ ፓርቲ ዲክታቶርሺፕ ያውም የሰራተኛ መደብ ሳይሆን ያንድ ጎሳ ዲክታቶርሺፕ ባለበት አገር የ2030 ራዕይ የሚመራው የሚከወነው በብልጽግና ፓርቲ ነው መባሉ እጅግ ያሳዝናል።

አቢይ አህመድ አሁንም በኢትዮጵያ መንግስትና በአንድ የፖለቲካ ፓርቲ መካከል ያለውን ግዙፍ ልዩነት አለማወቁ ወይም ማወቅ አለመፈለጉ በጥቂት ግዜ ውስጥ አገሪቱ ወደ አምባገነን ሰርዓት ላይ ወድቃ ወደ ሕዝባዊ አንድነትና ትጋት ሳይሆን ወደ ሕዝባዊ አመጽ መግባቷ የግድ ነው ። ያ ሲሆን ደሞ ይህ ሁሉ ለቱሪስት መሳቢያ ሚደረገው አገር ማስዋብ ከንቱ ሆኖ ይቀራል ።

ኢትዮጵያ አንድ የጎሳ ቫንጋርድ ፓርቲ ዲክታቶርሺፕ የሚሸከም ጀርባም ሆነ ትከሻ የላትም ። ይህ ነው የዛሬ ያቢይ አዋጅ ግዙፍ ስህተት !!!