Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Horus
Senior Member+
Posts: 30831
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: የፖለቲካ ሳይንስ፣ አቢይ አህመድ ጠ/ሚ መሆን የፈለገው ለምንድን ነው?

Post by Horus » 09 Sep 2020, 17:44

አቢይ አህመድ መቼም አንዳንድ ግዜ ማንም ሳያስገድደው የሚሰራው ስህተት ያስገርማል ። ስለ ትግሬ ምርጫ ሲተች ትክከኛ ዋል ተጠቅሟል፣ እሱም የጨረቃ ምርጫ ነው።

ከዚያ በላይ የደረገው ያፍ ወለምታ ማለትም የእድርና እቁብ ምርጫዎችን ዝቅ ዝቅ በማደግ ያደረገው ዝም ብሎ አፍ እላፊ ነው። እድርና እቁብ እጅግ መሰረታዊ የሆኑ ክቡር ሶሺያል ካፒታሎች፣ ከማንም የካድሬ ምርጫ ተቢዬ የፖለቲካ ነጋዴዎች ድራማ በላይ የሆነ እውነተኛው የተራው ሕዝብ መደራጃ ካልቸርን እንደ ባለጌ ልጅ መስደብ ላንድ የገር መሪ የማይመጥን አፍ እላፊ ነው ። አቢይ አመቺ ግዜ ሲያገኝ ሕዝቡን ይቅር ማለት አለበት ።

Dawi
Member
Posts: 4311
Joined: 30 Aug 2016, 03:47

Re: የፖለቲካ ሳይንስ፣ አቢይ አህመድ ጠ/ሚ መሆን የፈለገው ለምንድን ነው?

Post by Dawi » 10 Sep 2020, 00:14

Horus wrote:
09 Sep 2020, 17:44

Horus,

ሰውን ሰው ያደረገው ማነው?........ እቁብ ነው። :P

እድርና እቁብ "አገራዊ" የምርጫ ቦርድ የላቸውም፣ በየሰፈሩ በተፈለገ ጊዜ ምርጫ አርጎ ማቋቋም ይቻላል፤ የትግራይ ምርጫ የሰፈር ነው የጨረቃም ነው፣ የምርጫ ቦርድ አያውቀውም፤ ማለቱ ይመስለኛል።

Horus
Senior Member+
Posts: 30831
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: የፖለቲካ ሳይንስ፣ አቢይ አህመድ ጠ/ሚ መሆን የፈለገው ለምንድን ነው?

Post by Horus » 10 Sep 2020, 00:33

Dawi wrote:
10 Sep 2020, 00:14

እቁብና እድር የዎይኔ ቆሻሻ ምርጫ ትብዬ ድራማ ከምፈትርኩ ቀድሞ ለዘመናት የህዝቡ ኢንስቲቱሽን ሆነ ያልን ክቡር ካልቸር ለምንድን የዎያኔ ቆሻሻ ንትርክ ጋር ቀድሞውኑ ሚያያይዘው? ወይስ እሱም የኢ ሃዴግ ልጅ ስለሆነ? ዳዊ እድር/ እቁብ በምንም ሎጂክ ከኢሃደግ ጋር ማያያዝ የለበትም።

Dawi
Member
Posts: 4311
Joined: 30 Aug 2016, 03:47

Re: የፖለቲካ ሳይንስ፣ አቢይ አህመድ ጠ/ሚ መሆን የፈለገው ለምንድን ነው?

Post by Dawi » 10 Sep 2020, 01:11

Horus wrote:
10 Sep 2020, 00:33
Dawi wrote:
10 Sep 2020, 00:14
Horus wrote:
09 Sep 2020, 17:44
አቢይ አህመድ መቼም አንዳንድ ግዜ ማንም ሳያስገድደው የሚሰራው ስህተት ያስገርማል ። ስለ ትግሬ ምርጫ ሲተች ትክከኛ ዋል ተጠቅሟል፣ እሱም የጨረቃ ምርጫ ነው።

ከዚያ በላይ የደረገው ያፍ ወለምታ ማለትም የእድርና እቁብ ምርጫዎችን ዝቅ ዝቅ በማደግ ያደረገው ዝም ብሎ አፍ እላፊ ነው። እድርና እቁብ እጅግ መሰረታዊ የሆኑ ክቡር ሶሺያል ካፒታሎች፣ ከማንም የካድሬ ምርጫ ተቢዬ የፖለቲካ ነጋዴዎች ድራማ በላይ የሆነ እውነተኛው የተራው ሕዝብ መደራጃ ካልቸርን እንደ ባለጌ ልጅ መስደብ ላንድ የገር መሪ የማይመጥን አፍ እላፊ ነው ። አቢይ አመቺ ግዜ ሲያገኝ ሕዝቡን ይቅር ማለት አለበት ።
Horus,

ሰውን ሰው ያደረገው ማነው?........ እቁብ ነው። :P

እድርና እቁብ "አገራዊ" የምርጫ ቦርድ የላቸውም፣ በየሰፈሩ በተፈለገ ጊዜ ምርጫ አርጎ ማቋቋም ይቻላል፤ የትግራይ ምርጫ የሰፈር ነው የጨረቃም ነው፣ የምርጫ ቦርድ አያውቀውም፤ ማለቱ ይመስለኛል።
እቁብና እድር የዎይኔ ቆሻሻ ምርጫ ትብዬ ድራማ ከምፈትርኩ ቀድሞ ለዘመናት የህዝቡ ኢንስቲቱሽን ሆነ ያልን ክቡር ካልቸር ለምንድን የዎያኔ ቆሻሻ ንትርክ ጋር ቀድሞውኑ ሚያያይዘው? ወይስ እሱም የኢ ሃዴግ ልጅ ስለሆነ? ዳዊ እድር/ እቁብ በምንም ሎጂክ ከኢሃደግ ጋር ማያያዝ የለበትም።
Horus,

Realizing Abiy is a master of analogies, he compared the similarities of the respectful "እቁብና እድር" cultural election with the "electoral" process that is taking place in Tigray at the wrong time.

Granted it's illegal "ጎጥ" "election", an exercise in futility however, it can also be taken as some "democratic exercise" as the p2 official of Tigray pointed out; as a matter of fact, p2 can draw a lesson or 2 from Tigray "election"? the "damage". if any, with the pandemic looming over our heads; can help in preparation for the coming national election. "ቆሻሻ"as a process? It is not.

So, I don't think Abiy's analogy should be taken in a negative way. He is not a type of guy that belittles such cultural assets of his country.

Horus
Senior Member+
Posts: 30831
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: የፖለቲካ ሳይንስ፣ አቢይ አህመድ ጠ/ሚ መሆን የፈለገው ለምንድን ነው?

Post by Horus » 10 Sep 2020, 02:05

Dawi,

በዚህ ነገር ላይ ይህ የመጨርሽ ሃሳቤ ነው። በአቢይ ላይ አሉታዊ አዎንታዊ ምናምን አይደለም ። የትግሬ ምርጫ ሚልዮን ሕዝብ የሚካፈልበት የፖለቲካ ልድገመው የፖለቲካ ምርጫ፣ የፖለቲካ ጉዳይ ነው ። እቁብ ምርጫ የሚባል ነገር የለውም፣ ሶስት ሰዎች ብር ሰብስበው እጣ ታሰወጣሉ፣ እድርም እንዲሁ ፣ ግን እነዚህ ኢንስቲሽኖች ክቡር ናቸው። አቢይ ስለራሱ ፖለቲካ ሲቀባጥር በህዝቡ ሲቪል ህይወትና በሱ የፖለቲካ ዴማጎጊ መሃል መለየት አለበት ። አዋቂ ከሆነ የክልል ፖለቲካ ምርጫና የሰፈር ቀብር እድር የተለያዩ ካታጎሪ መሆናቸውን መገንዘብ ነበረበት ፣ ያን ስለማያቅ ነው የተሳሳተው ። ለምሳሌ አልትራ እስትራክቸር ምንድን ነው? ኢንትራእስትራክቸር ምንድን ነው ? ይህን የመሳሰሉ ባዶ ቃላት መወርወር ፍሬዝ ሞንገሪንግ ይባላል። እንዲተወው ምከሩት ! አይጠቅመውም ። ደሞ መሪ ሲሳሳት ተሳስተሃል የሚል ዜጋ ነው ምንፈልገው ። አንተም ብትሆን ይህን ያንን ማለቱ ይሆናል እያልክ ክሪቲካል ፋኩልቲህን አታስጨንቀው ። ስህተት ስታይ ስህተቱን በስሙ ጥራው ፣ ያ ነው አቢይን የሚተቅመው ።

መልካም እንቁጣጣሽ !!!

Horus
Senior Member+
Posts: 30831
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: የፖለቲካ ሳይንስ፣ አቢይ አህመድ ጠ/ሚ መሆን የፈለገው ለምንድን ነው?

Post by Horus » 10 Sep 2020, 03:05

አንድ ሕዝብ መሪውን በደንብና በጥልቀት ማወቅ ስላለበት እህው በእኔ እይታ ስለ ጠ/ሚ አቢይ ገፊ ፍላጎቶች ...

በስይኮሎጂ የሰው ልጅን ባህሪ የሚገፉት ሞተሮች ሞቲቬሽን ይባላል። ሞቲቬሽን አራት (4) አይነት ናቸው።

አንደኛው ሄዶኒስም ወይም ደስታና ስቃይ ነው ። አንድ ነገር የምናደርገው ደስታ ስለሚሰጥና ሳቃይን ስለሚያስወግድ ነው። የደስታ ምንጭ ሃያልነት፣ ጉልበት፣ ጥንካሬ፣ የአካል፣ ያይምሮ፣ የመንፈስ ጥንካሬ ሁሉ የደስታ፣ የፍስሃ ምንጮች ናቸው። መሪ በስልጣን ፍላጎት ይመራል። ስልጣን ወይም ሃይል የደስታ ምንጭ ነው።

ሁለተኛ ፕሩደንስ ወይም ጥቅምና ጉዳት ነው ። አንድን ነገር የምናደርገው ጥቅም ስለሚሰጥና ጉዳትን ስለሚያስወግድ ነው ። ይህ የሚያገለግል፣ ዋጋ ያለው፣ የሚያሳድግ፣ የሚደግፍ፣ ይህወትን የሚያረዝም ማለት ነው። አንድ አገልግሎት የሚሰጥ ነገር ጠቃሚ ነገር ይባላ። መሪ በገንዘብ ፍላጎት ይገፋል።

ሶስተኛው ኤቲክስ ወይም ጥሩና መጥፎ (ፍትህና ግፍ) ነው ። አንድን ነገር የምናደርገው ትክክል ስለሆነና መጥፎነትን ስለሚያስወግድ ነው። ይህ ጥራት ያለው፣ ንጹህ፣ ትክክል፣ ስርዓት ያለው ኦርደር ያለው ያልተቃወሰ ማለት ነው። አንድ መሪ በዝና ፍላጎት ይገፋል። መልካምነት የዝና ምንጭ ነው።

አራተኛው ኤስተቲክስ ወይም ዉበትና አስቀያሚነት ነው። አንድን ነገር የምናደርገው ዉበት ስለሚሰጥና አስቀያሚነትን ስለሚያስወግድ ነው። ይህ ተራ ያልሆነ፣ ልዩ ነገር፣ በብዛት የሌለ ከብዙሃኑ የተለየ ማለት ነው። አንድ መሪ በክብር ፍላጎት ይገፋል ። ለምሳሌ የጎሳ መሪ ገፊ ፍላጎት ክብር ነው ። ለዚህ ነው የዲግኒቲ ፖለቲካ የሚባለው።

አንድ ሰው በክብር ወይም በጎሳ ፖለቲካ ሲጠመድ ምን ማድረጉ ነው ። ከፍ ያለ እስታተስ እፈልጋለሁ፣ ከዚህ የላቀ ዋጋ ይሰጠኝ፣ ተንቄያለሁና ልከበር፣ ሪስፔክት ልደረግ ማለቱ ነው። ባንድ ቃል ዝቅተኝነት ስለሚሰማኝ ከፍተኝነት እንዲሰጠኝ እፈልጋለሁ ማለቱ ነው። የፍልስፍና ስሩ ወደ ዉበት የሚሄደው ዝቅተኝነት አስቀያሚ ስለሆነ እና ከፍተኘት ከዉበት ጋር ስለሚያያዝ ነው።

የአቢይ ቁልፍ ገፊ ፍላጎቶች ሃይልና ክብር ናቸው። በመሰረቱ ይያያዛሉ። የበታች መሆን ሃይል ከማጣት ከስልጣን አልባነት የሚነሳ ነው። ውብ ነገር ከፍተኛ ዋጋ አለው፣ ስለሆነ በጣም ተፈላጊና ክቡር ነው። ሃይልና ስልጣን ያለው ሰው የበላይ ነው ። ጥሮ ተጣጥሮ የበላይ መሆን ይባላል። ምክንያቱም የበላይ ሰው የፈለገውን ስለሚያደግ ሃይል ወይም ስልጣን አለው ማለት ነው።

በአንድ ቃል ያንድ መሪ የስልጣን (ህይል) ፍላጎትና የክብር (የበላይነት) ፍላጎት ያንድ ሳንቲም ጎፈርና ዘውድ ናቸው።
አቢይ አህመድ ማነው?

አቢይ አህመድ ማለት ይህ ነው። ይህ ሁሉ ከተማ የማስዋብ ጥድፊያው ሳይኮሎጂያዊ ስሩ እሱ ነው። ከአራቱ የአቢይ መሪነት ገፊ ምክኛቶች ቁልፍ የሆኑት ሁለቱ ስልጣንና ክብር እንደ ሆኑ ይታላል። ። ማለትም አቢይን የሚገፋው ሞቲቬሽንን ሃብት ወይም ኤቲክስ አይደለም ። ድሃ ስለነበረ የሰው ተልዕኮ ሃብት ማካበት ነው ብሎ አያምንም ። አንድ ነገር ከሃይማኖት ወይም ፍልስፍና ተነስቶ ትክክል ወይም መልካም አይደለም ከሚል በሞራል መርህ የሚገፋ ሰው አይደለም ። እሱ ማኪያቬሊ፣ ሮበርት ግሪንን የሚከተል ፍጹም ፕራግማቲክ፣ አስፈላጊ የሆነውን ሃይል፣ ስልጣን እና አስፈላጊ የሆነውን ክብር፣ የበላይነት፣ ተፈላጊነት በማንኛውም ዘዴ እንደ ሁኒታው በመለዋወጥ ለማግኘት የሚሰራ ሰው ነው።

ኤርሚያስ ለገሰ በትክክል ስላየው መርህ የሌለው ሲትዌሽናል ተለዋዋጭ ሰው መሪ ነው ያልው ትክክል ነው ። ግን ለምን አቢይ ይህን መሰል ፕራግማቲክ ሰው እንደ ሆነ ስሩን አላገኘውም ። አቢይ ወታደር ነበር፣ ሰላይ ነበር ፣ ከልጅነቱ አንጎሉን ያነጸው በማክቬሊያዊ ታክቲካል ፍጹም ፕራክቲካል ፍጹም ፕርግማቲክ በሆነ ፍልስፍልና እና እስትራተጂ ስለሆነ ነው።

አቢይ በጣም በጣም ፕራክቲካል ሰው ነው። ስለሆነም በየቀኑ ማግኘት ያለበትን የስልጣን (የሃይል) መጠን እና የክብር፣ ሪስፔክት በላይነት መጠን ለማግኘት፣ ባንድ ቃል ስልጣን፣ ቦታ እና በነገሮች የበላይነት ቦታ ለመቆጣጠር ፍጹም ፕራግማቲች፣ ፍጹም ፕራክቲካል የሚሆን ሰው ነው፣ የሚለዋወጥ ሰው ነው። ይህን ስንት ሰው ያውቃል?
ይህ ተክለሰብነት አደገኛ መሪ ያደርገዋል ወይ? እዚህ ከቀረቡት ነጂ ፍላጎቶች ተነስተን አቢይ አሀመድ ዲክታቶር የሚሆን ሰው ነው ወይ? ዲክታቶር የሚሆን መሪ ምን አይነት ሰው ነው?

አቢይ ስልጣንና ክብር ዲክታቶር እንዲሆን ሳይገደድ ካገኘ በፍላጎት ተነስቶ ዲክታቶር አይሆንም። ግን ከነዚህ ሁለት ፍላጎትች ሚገታው ከመጣ ዲክታቶር ይሆናል ። ዲክታቶርነት ራሱም ፕራግማቲክ እርምጃ ነው። ካስፈለገ ይሆናል፣ ካላስፈለገ አይሆንም።

አቢይ መወደድ በጣም ይፈልጋል ፣ መፈራት እንጂ መናቅ አይወድም ። ስለዚህ ዲክታቶር የሚሆነው ተገዶ ብቻ ነው። ለመወደድ ብዙ ነገር እያደረገ ነው። አበባ ያድላል፣ ሰው ይመስላል፣ ተራ ሰው ይሆናል፣ ይደባለቃል፣ ግን እንዲህ ያለ ሰው ሁሉን አድርጎ ካልተወደድ ዲክታቶር ይሆናል። በመርህ ምንም ዘዴ የሚከተለው ስለሌለ ።

Horus
Senior Member+
Posts: 30831
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: የፖለቲካ ሳይንስ፣ አቢይ አህመድ ጠ/ሚ መሆን የፈለገው ለምንድን ነው?

Post by Horus » 10 Sep 2020, 03:55

ይህን ተከታተሉ አቢይ በዚህ ከቀጠለ ምርጫ መደርጉንም ያጠራጥራል ...

አቢይን እንደ ፍጹም አዋቂ አምናችሁ አቢይን ያለ ነቀፋ ለምትከተሉ ካድሪዎች ይህን ስሙ !!

Horus
Senior Member+
Posts: 30831
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: የፖለቲካ ሳይንስ፣ አቢይ አህመድ ጠ/ሚ መሆን የፈለገው ለምንድን ነው?

Post by Horus » 10 Sep 2020, 16:32

የጠ/ሚ አቢይ ቃለ መጠይቅ ክፍል 2 ውስጥ አንዳንድ አስገራሚም አሳሳቢም ነገሮችን አግኝቻለሁ ።

ለምሳሌ ስለ ኮሮና ቀውስ ሲመልስ "አንቲፍራጃይል" የሚል ቃል ይጠቀማል ። ይህ እጅግ በጣም ነው ያስገረመኝም ያስደሰተኝም። 'አንቲፍራጂሊቲ' የሚባለው ጽንስና ቲኦሪ የፈጠረው ናሲም ጣሌብ የሚባለው የሊባኖስ ምሁር ነው። የጽንሱ ቁም ነገር አንድ ነገር ቀውስ ሲያጋትጥመው ምን ይሆናል? የሚል ነው ። አንዱ ነገር የሰበራል፣ አንዱ ተሰብሮ እንደ ገና ያገግማል፣ አንዱ ቀውሱን ይቋቋማል ። አንቲፍራጃይል የሆነው ነገር ግን ቀውሱን ወይም አደጋውን ወይም ጥቃቱን እንደ ግብአት በመጠቀም እንዲያውም እራሱን ያሻሽልበታል የሚል ነው ። እኔ እዚህ ፎረም ላይ ይህን አስመክቼ የኮሮና ወረራ እንዴት ላዳዲስ ቴክኖሎጂዎች ፍልሰፋ ምክኛት እንደ ሚሆኑ ጽፌ ነበር። አቢይ አህመድ ልክ በዚህ መልኩ አንቲፍራጃይል የሚለውን ቃል ጠቅሶ በኮሮና ዙሪያ ስለተደረጉ ፈጠራዎች ሲናገር ስሠማ እጅግ ነው ደስ ያለኝ። ማለትም መጻፉ ኢትዮጵያ መድረሱን ያሳያል ። ቢሄቬየራል ኢኮኖሚክስ የሚባለው ቲኦሪም ባገራችን መግባቱ ያሳያል!! ኤቦ ብያለሁ ። (መጻፉ፤ Nassim Nicholas Taleb, Antifragile: things that gain from disorder, 2012)

ሌላው አቢይ ለመጀመሪያ ግዜ በዝርዝር እንዴት ጠ/ሚ ለመሆን ከልጅነቱ እስከ አሁን እንደ ተዘጋጀ ነግሮናል ። ተወልደ የሚባለው ሰላይ በሰጠው ኢንተርቬው የአቢይ Enneagram personality type 3 (achiever) እንደ ሆነ ራሱ አቢይ አረጋገጠልን። ጉግል አድርጋችሁ ተመልከቱት ። ይህም በብዙ መልኩ ጥሩ ነው። ህዝቡ የምሪውን ትክለ ሰውነት ማወቁ ። እርግት የሴኩሪቲ፣ የዲፕሎማሲ እና የስለላ ችግር በፈጥርም። አንድ መሪ ምን እንደ ሚያስብ ፣እንዴት እንደ ሚያስብ ጠላት ማወቅ ስለሌለበት ማለት ነው።

እኔን ያሳሰበኝ አቢይ ስለ ብልጽግና ፓርቲ ብቸኛ ብቁነት እና አሸናፊነት የተናገረው ነው። ያም ማለት ለሎች ፓርቲዎች ተስፋ ቆርጠው እንዲሞቱ ከፍተኛ የስይኮልጂካል ጦርነት ወይም ግድያ ነው ያደረገባቸው ። ፌት አኮምፕላዬ ማለት ነው ። ያበቃ የሞተ ነገር የምርጫው ውጤትና ሚቀጥለው 10 አመት ማ እንደ ሚገዛ ። ይህ እጅግ አነጋጋሪ ነገር ነው ።

Last edited by Horus on 10 Sep 2020, 20:10, edited 1 time in total.

Horus
Senior Member+
Posts: 30831
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: የፖለቲካ ሳይንስ፣ አቢይ አህመድ ጠ/ሚ መሆን የፈለገው ለምንድን ነው?

Post by Horus » 10 Sep 2020, 17:03

ጠ/ሚ ምን አይነት ሰው ነው? (ኢኒያግራም 3፡ ስኬታማ)

ይህን ስትሰሙ የፒኮኩ ነገር አስታውሱ !!

Horus
Senior Member+
Posts: 30831
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: የፖለቲካ ሳይንስ፣ አቢይ አህመድ ጠ/ሚ መሆን የፈለገው ለምንድን ነው?

Post by Horus » 10 Sep 2020, 17:36

አንቲፍራጃይል ማለት ምን ማለት ነው?

Horus
Senior Member+
Posts: 30831
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: የፖለቲካ ሳይንስ፣ አቢይ አህመድ ጠ/ሚ መሆን የፈለገው ለምንድን ነው?

Post by Horus » 11 Sep 2020, 10:34

እኔ እዚህ ላይ የፖለቲካ ፓርቲ ቲኦሪ ለማቅረብ አይደለም ። ግን ይህን ፍጹም አሳሳቢ ነገር ለመድገም ነው።

አቢይ በንግግሩ፣ ለንግግሩ ብዙ ምሳሌ፣ ብዙ ሜታፎር ይጠቀማል ። ትላንት ካንድ የሾላ ፍሬ አንድ የሾላ ዛፍ እንዴት እንደ ሚበቅል፤ ካንድ የድንጋይ ተራራ እንዴ የላሊበላ መቅደስ እንደ ሚጠረብ ነግሮናል ። በ10፣ 20፣ 30 አመት አንዲት ሃያል ኢትዮጵያ በብልጽና ተገነባለች ያለው ግን ዉሸት ብቻ ሳይሆን ሳያብ የተናገረው ነው ። ለምን በሉ?

አንደኛ አትዮጵያን ሃላል አገር የሚያደርጉ ህዝቧ ሁሉ ናቸው። የሚመራቸው ፓርቲም ከሁሉም ህዝብ የመጡና ሚወክሉ ናቸው። ፒፒ መላ ህዝብ አይወክልም።
ሁለት ራሱ አቢይ ፒፒ አሁን ላይ በሌቦች የተሞላ ነው ብሎን ነበር። ያም ማለት ከመጥፎ ዘር የበቀለ ዛፍ መጥፎ ነው ። ዝግባባ ሾላ አይሆንም ። ፒፒ ለብቻው ገገዛ የሌቦች ብቻ ሳይሆን የወሮ በላዎች ስብስብ ነው የሚሆነው።
ሶስተኛ በማንኛው ሳይንስና ታሪክ ያንድ ባርቲ ዲክታቶርነት እንደ ኢትዮጵያ ያለን ዝጉርጉር አገር ወደ 30 አመት አዲስ ጦርነት ነው ሚደፍቃት እንጂ ሃያል አገር አያደርጋትም።

አብይ ከዚህ የ ፒፒ አምባገነን ህልሙ መላቀቅ አለበት ። ኢትዮጵያ ቢያንስ 3 እስከ አራት ተፈራርቀው ተቀናጅተው የሚመሯት አገር መሆን ያለባት እንጂ ያንድ ፓርቲ ባሪያ አገር ታሪካዊ ሃፍረት እንጂ ክቡር አገር አይሆንም።

Horus
Senior Member+
Posts: 30831
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: የፖለቲካ ሳይንስ፣ አቢይ አህመድ ጠ/ሚ መሆን የፈለገው ለምንድን ነው?

Post by Horus » 11 Sep 2020, 12:22

ታላቅ አገር የገነቡ ነጻና ታታሪ ፈጣሪ ሰዎች ግልሰቦች ናቸው እንጂ ያንድ ፓርትይ ባሪያ የሆኑ መንጋዎች አይደሉም !!

Guest1
Member
Posts: 1926
Joined: 28 Dec 2006, 01:02

Re: የፖለቲካ ሳይንስ፣ አቢይ አህመድ ጠ/ሚ መሆን የፈለገው ለምንድን ነው?

Post by Guest1 » 11 Sep 2020, 12:45

ታላቅ አገር የገነቡ ነጻና ታታሪ ፈጣሪ ሰዎች ግልሰቦች ናቸው
በመሰረቱ ዲሞክራሲ የሚባለው የግለሰብ ነጻነት ነው።
7ተኛው ንጉስ እንደተመኘው ከሆነ የ7 ቁጥር እድል ደርሶታል። 20ና 30 አመት ማለት ይችላል።

Horus
Senior Member+
Posts: 30831
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: የፖለቲካ ሳይንስ፣ አቢይ አህመድ ጠ/ሚ መሆን የፈለገው ለምንድን ነው?

Post by Horus » 11 Sep 2020, 13:37

Guest1 wrote:
11 Sep 2020, 12:45
ታላቅ አገር የገነቡ ነጻና ታታሪ ፈጣሪ ሰዎች ግልሰቦች ናቸው
በመሰረቱ ዲሞክራሲ የሚባለው የግለሰብ ነጻነት ነው።
7ተኛው ንጉስ እንደተመኘው ከሆነ የ7 ቁጥር እድል ደርሶታል። 20ና 30 አመት ማለት ይችላል።
ትክክል ነው፤ ለዚህ ነው የፒፒ ፓርቲ ወደ ብልጽግና ማማ ያወጣናል የሚለው አሳፋሪ ባዶ የኮሚኒስት የሰለቸን ፕሮፓጋንዳ መሆኑን ማሳወቅ ግዴታችን ነው። እኔ በዚህ አባባል ውስጥ የማየው ካመት ሁለት አመት በኋላ ጭፍን አምባገነንነት ነው። ከወዲሁ ይቁም።

Horus
Senior Member+
Posts: 30831
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: የፖለቲካ ሳይንስ፣ አቢይ አህመድ ጠ/ሚ መሆን የፈለገው ለምንድን ነው?

Post by Horus » 11 Sep 2020, 17:52

እስቲ ከላይ ያለውን ያቢይ አህመድ አመታዊ ግምገማና የአውድማ አመታዊ ግምገማን አፎካክራችሁ አዳምጡት !
2013 የስጋትና ተስፋ አመት

አንዳንድ ከተነሱ ድንቅ ሃሳቦች መሃል

የብፕልጽግና ፓርቲ መሰረታዊ የርዕዮተ አለም ችግር ያለው በመሰረቱ የአቢይ አህመድ ግላዊ (ፐርሶናል) አጀንዳ ማራመጃ ድርጅት ነው የሚለው አባል ብዙ እውነትነት አለው ።

አቢይ አህመድ የራሱ ውስጣዊ ፍላጎት እንጂ የማህበረ ሰቡ ጥልቅ ችግርና ፍላጎት ወይም ጥያቄ በውል የተገነዘበ መሪ አይደለም የሚለው እንዲሁ እውነትነት አለው ።

አቢይ አህመድ ግልጽነት የለውም፣ አንድ የሚደብቀው የራሱ መንገድ የራሱ አጀንዳ የራሱ ፍላጎት አለው የሚለው እንዲሁ እንውነትነት አለው ፣ ይህም ቀስ በቀስ የታማኝ ነት ችግር ያስከትላል ።

የዚህ አመት ችግሮች ሁሉ ተንከባለው ወደ 2013 ተሻግረዋል የሚለውም እንዲሁ

Horus
Senior Member+
Posts: 30831
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: የፖለቲካ ሳይንስ፣ አቢይ አህመድ ጠ/ሚ መሆን የፈለገው ለምንድን ነው?

Post by Horus » 14 Sep 2020, 02:14

የማንኛውም የፖለቲካ መሪ መሰረታዊ ፍላጎት ስልጣን፣ ገንዘብ፣ ዝና እና ክብር ነው ። ይህ ደሞ መንግስት ላይ ያለ ብቻ ሳይሆን የፖለቲካ ድርጅቶችንም ያካትታል

Horus
Senior Member+
Posts: 30831
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: የፖለቲካ ሳይንስ፣ አቢይ አህመድ ጠ/ሚ መሆን የፈለገው ለምንድን ነው?

Post by Horus » 30 Nov 2022, 01:47

እስቲ ይቺን የሴፕቴበር 5 2020 ውይይት እንደ ገና ቃኙት!

Post Reply