Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Horus
Senior Member
Posts: 16860
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

የፖለቲካ ሳይንስ፣ አቢይ አህመድ ጠ/ሚ መሆን የፈለገው ለምንድን ነው?

Post by Horus » 05 Sep 2020, 16:58


እኔ ሆረስ ነኝ ቃላት አልፈልጥም፤ ዝም ብዬ በስመነጋ አልቀባጥርም። ይህን ልጠይቃችሁ?

አንድ፣ አቢይ ለምን ጠቅላይ ሚኒስቴር ወይም ፕሬዚዳንት መሆን ፈለገ?

ሁለት ፣ አቢይ አህመድ ጠቅላይ ሚኒስቴር የሆነው እንዴት ነው? እንዴት ስልጣን ላይ ወጣ?

ሶስት፣ አቢይ አህመድ ስልጣን ላይ የሚቆየው እንዴት ነው?

አራት፣ ያቢይ አህመድ ቁልፍ ቡድን አባላት እነማን ናቸው? የተጽኖ ቡድን አባላትስ መራጭ አባላትስ?

አምስት፣ እነዚህ ያቢይ አገዛዝ (ሪጂም) አባላት ከየት ነው ሚመለመሉት? እንዴት እና በምን መለኪያ?

ስድስት፣ ስለዚህ አሁን ስልጣን ላይ ያለው አገዛዝ ባህሪ ምንድን ነው? በአሁን ወቅት የራሱ ሪጂም ካራክተር ይልዟል ወይ?

ሰባት ፣ ይህ አገዛዝ ለስንት ግዜ ይገዛል? ከዚያስ ከስልጣን የሚወርደው እንዴት ነው? ለምን ይወርዳል? ማነው የሚተካው? ለምን?

በነዚህ 7 ቁልፍ ጥያቄዎች ላይ በፖለቲከ ቲኦሪ ላይ የቆመ ሃሳብና መልስ የሌላቸው ስዎች 24/7 ስለፖለቲካ ሲያወሩና ሲጽፉ ሳይ በጣም እገረማለሁ!!

ለምሳሌ እስከ ዛሬ የታከለ ኡማ ገንዘብ፣ ቤትና መሬት ማከፋፈል ከአቢይ አገዛዝ (ረጂም ካራክተር) ጋር በቲኦሪ ደግፎ ያቀረበ አንድም ሰው የለም ። ኢዜማ ራሱ ያን አላረገም ።

ሁሉ ስለ ሌብነት ሲያወራ የድርጊቱ ትርጉም ምን እንደ ሆነ የገባው እንዳለ ያጠራጥራል ። ድርጊቶቹን በዝርዝር ማሳየቱ በጣም አስፈላጊ ጅማሮ ነው? አሁን እነዚህ መረጃዎች ከላይ ላሉትን 7 ጥያቄዎች መመለሻ ግብኣት እንዲሆኑ ሳይናሳዊ የፖለትካ ቲኦሪ ማወቅና መጠቀም የግድ ነው ።
Last edited by Horus on 06 Sep 2020, 14:45, edited 1 time in total.

DefendTheTruth
Member
Posts: 3551
Joined: 08 Mar 2014, 16:32

Re: የፖለቲካ ሳይንስ፣ አቢይ አህመድ ጠ/ሚ መሆን የፈለገው ለምንድን ነው?

Post by DefendTheTruth » 05 Sep 2020, 17:34

Horus wrote:
05 Sep 2020, 16:58

እኔ ሆረስ ነኝ ቃላት አልፈልጥም፤ ዝም ብዬ በስመነጋ አልቀባጥርም። ይህን ልጠይቃችሁ?

አንድ፣ አቢይ ለምን ጠቅላይ ሚኒስቴር ወይም ፕሬዚዳንት መሆን ፈለገ?

ሁለት ፣ አቢይ አህመድ ጠቅላይ ሚኒስቴር የሆነው እንዴት ነው? እንዴት ስልጣን ላይ ወጣ?

ሶስት፣ አቢይ አህመድ ስልጣን ላይ የሚቆየው እንዴት ነው?

አራት፣ ያቢይ አህመድ ቁልፍ ቡድን አባላት እነማን ናቸው? የተጽኖ ቡድን አባላትስ?

አምስት፣ እነዚህ ያቢይ አገዛዝ (ሪጂም) አባላት ከየት ነው ሚመለመሉት? እንዴት እና በምን መለኪያ?

ስድስት፣ ስለዚህ አሁን ስልጣን ላይ ያለው አገዛዝ ባህሪ ምንድን ነው? በአሁን ወቅት የራሱ ሪጂም ካራክተር ይልዟል ወይ?

ሰባት ፣ ይህ አገዛዝ ለስንት ግዜ ይገዛል? ከዚያስ ከስልጣን የሚወርደው እንዴት ነው? ለምን ይወርዳል? ማነው የሚተካው? ለምን?

በነዚህ 7 ቁልፍ ጥያቄዎች ላይ በፖለቲከ ቲኦሪ ላይ የቆመ ሃሳብና መልስ የሌላቸው ስዎች 24/7 ስለፖለቲካ ሲያወሩና ሲጽፉ ሳይ በጣም እገረማለሁ!!

ለምሳሌ እስከ ዛሬ የታከለ ኡማ ገንዘብ፣ ቤትና መሬት ማከፋፈል ከአቢይ አገዛዝ (ረጂም ካራክተር) ጋር በቲኦሪ ደግፎ ያቀረበ አንድም ሰው የለም ። ኢዜማ ራሱ ያን አላረገም ።

ሁሉ ስለ ሌብነት ሲያወራ የድርጊቱ ትርጉም ምን እንደ ሆነ የገባው እንዳለ ያጠራጥራል ። ድርጊቶቹን በዝርዝር ማሳየቱ በጣም አስፈላጊ ጅማሮ ነው? አሁን እነዚህ መረጃዎች ከላይ ላሉትን 7 ጥያቄዎች መመለሻ ግብኣት እንዲሆኑ ሳይናሳዊ የፖለትካ ቲኦሪ ማወቅና መጠቀም የግድ ነው ።I remember an instance where someone called this guy "a worthless citizen" and he, the journalist, too seems to be trying to impress with a long list of X - Y- attached numbers. Else no new content in my view.
Face the truth, if you may wish to be part of the solution instead of remaining part of the problem.

Horus
Senior Member
Posts: 16860
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: የፖለቲካ ሳይንስ፣ አቢይ አህመድ ጠ/ሚ መሆን የፈለገው ለምንድን ነው?

Post by Horus » 05 Sep 2020, 17:54

Sun

ይህ የትንተና መምሪያ የተጻፈው ላንተ አይደለም። በእኔ ግሞት የነገሩን ጭብጥ ሊገባህ የሚችል አይደለም ። ይህ የተጻፈው ያቢይ አህመድን አገዛዝ ከመጀመሪያ እስከ ዛሬ ሂደቱን በዝርዝር ለሚያውቁትና ይህ ሪጂም ወዴት እየሄደ እንደ ሆነ ጥሩ ግምት ላላቸው እንደ ብርሃን የሚያሳያቸው ሳይንሳዊ ዘዴ ነው ። እነሱ ሲያዩት ይውቁታል።


ግድ የለህም ታገስ፣ አዲሶቹ የቀን ጅቦች እንዲ በቶትሎ ቶሎ ከግባቸው እንደ ማይደርሱ ታያለህ፣ ታገስ !

Guest1
Member
Posts: 1498
Joined: 28 Dec 2006, 01:02

Re: የፖለቲካ ሳይንስ፣ አቢይ አህመድ ጠ/ሚ መሆን የፈለገው ለምንድን ነው?

Post by Guest1 » 05 Sep 2020, 18:18

1. ንጉስ ትሆናለህ ስለተባለ።
2. የአሜሪካ ምርጫ ስለሆነ
3. በዘዴና በሴራ ክክክክክክ
4. ቁልፍ ቡድን ጌታቸው ረዳ ክክክክክክክክክክ
5. ከአዲስ አበባና ዲያስፖራ
6. ባህሪይ እንደ ሳሙና ክክክክክክክክክክክክክክ
7. ለአንድ ጊዜ፤ በምርጫ ወይም በፍጥጫ ክክክክክክክክክክክክ ለምን ይወርዳል? የጊዜ ገደብ 2 የምርጫ ዘመን ስለሆነ። ማን ይተካዋል? ኣልተረጋገጠም ሰው ጠፋ ክክክክክክክክክክክ።
የጥያቄዎቹ ብዛት ክ7 በላይ መሆናቸውና ሊያሳስብህ በማይገባው ብዙ ስለተቸገርክ ኣስቆኛል። ክክክክክክክክክክክክ

Wedi
Member
Posts: 1105
Joined: 29 Jan 2020, 21:44

Re: የፖለቲካ ሳይንስ፣ አቢይ አህመድ ጠ/ሚ መሆን የፈለገው ለምንድን ነው?

Post by Wedi » 05 Sep 2020, 19:12

Horus wrote:
05 Sep 2020, 16:58

እኔ ሆረስ ነኝ ቃላት አልፈልጥም፤ ዝም ብዬ በስመነጋ አልቀባጥርም። ይህን ልጠይቃችሁ?

አንድ፣ አቢይ ለምን ጠቅላይ ሚኒስቴር ወይም ፕሬዚዳንት መሆን ፈለገ? - ፈላጭ ቆራጭ ለመሆን

ሁለት ፣ አቢይ አህመድ ጠቅላይ ሚኒስቴር የሆነው እንዴት ነው? እንዴት ስልጣን ላይ ወጣ? - አጭበርብሮና Confused and convince አድርጎ

ሶስት፣ አቢይ አህመድ ስልጣን ላይ የሚቆየው እንዴት ነው? - ስልታን ይቀናቀኑኛል የሚላቸውን በማሰርና ከጥቅም ውጭ በማድረግ

አራት፣ ያቢይ አህመድ ቁልፍ ቡድን አባላት እነማን ናቸው? የተጽኖ ቡድን አባላትስ? - ምንም የለውም /አብሮት ያለው በገንዘብ የተገዛ ሆዳም ብቻ ነው

አምስት፣ እነዚህ ያቢይ አገዛዝ (ሪጂም) አባላት ከየት ነው ሚመለመሉት? እንዴት እና በምን መለኪያ? -

ስድስት፣ ስለዚህ አሁን ስልጣን ላይ ያለው አገዛዝ ባህሪ ምንድን ነው? በአሁን ወቅት የራሱ ሪጂም ካራክተር ይልዟል ወይ? - አጭበርባሪና አወናባጅ

ሰባት ፣ ይህ አገዛዝ ለስንት ግዜ ይገዛል? ከዚያስ ከስልጣን የሚወርደው እንዴት ነው? ለምን ይወርዳል? ማነው የሚተካው? ለምን? - እድሜው አጭር ነው/ በሚቀጥለው ምርጫ ከስልጣን ይባረራል

በነዚህ 7 ቁልፍ ጥያቄዎች ላይ በፖለቲከ ቲኦሪ ላይ የቆመ ሃሳብና መልስ የሌላቸው ስዎች 24/7 ስለፖለቲካ ሲያወሩና ሲጽፉ ሳይ በጣም እገረማለሁ!! - አንተም ከእነሱ አንዱ ነህ
Horus
Senior Member
Posts: 16860
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: የፖለቲካ ሳይንስ፣ አቢይ አህመድ ጠ/ሚ መሆን የፈለገው ለምንድን ነው?

Post by Horus » 05 Sep 2020, 20:22

Wedi,
ለምን ቁጥር 5 ዘለልከው?

እስቲ መልሶችህን እንደ ገና ተመልከታቸው። ቁጥር አንድ ላይ አቢይ አህመድ ጠ/ሚ መሆን የፈለገው ዲክታቶር ለመሆን ነው አልክና ቁጥር ሰባት ላይ አቢይ በሚቀጥለው ምርጫ፣ ማለት በግንቦት 2013 ከስልጣን ይወርዳል አልክ። መቼ ነው አንድ ዲክታቶር በምርጫ የወረደው? አንድ በምርጫ የሚወርድ መሪ እንዴት ዲክታቶር ሊባል ይቻላል? መለስ ዲክታቶር ነበር፤ መቼ ነው በምርጫ ከስልጣን የወረደው?

እንደ ገና ሞክር !!

sun
Member+
Posts: 5403
Joined: 15 Sep 2013, 16:00

Re: የፖለቲካ ሳይንስ፣ አቢይ አህመድ ጠ/ሚ መሆን የፈለገው ለምንድን ነው?

Post by sun » 05 Sep 2020, 20:24

Horus wrote:
05 Sep 2020, 17:54
Sun

ይህ የትንተና መምሪያ የተጻፈው ላንተ አይደለም። በእኔ ግሞት የነገሩን ጭብጥ ሊገባህ የሚችል አይደለም ። ይህ የተጻፈው ያቢይ አህመድን አገዛዝ ከመጀመሪያ እስከ ዛሬ ሂደቱን በዝርዝር ለሚያውቁትና ይህ ሪጂም ወዴት እየሄደ እንደ ሆነ ጥሩ ግምት ላላቸው እንደ ብርሃን የሚያሳያቸው ሳይንሳዊ ዘዴ ነው ። እነሱ ሲያዩት ይውቁታል።


ግድ የለህም ታገስ፣ አዲሶቹ የቀን ጅቦች እንዲ በቶትሎ ቶሎ ከግባቸው እንደ ማይደርሱ ታያለህ፣ ታገስ !
Really? :P
Horus, the day and night groaning old hyena,

This means according to you I have to imitate you by sniffing and smoking too much like you and then after that get hallucinated and whistle non stop through the back and front holes? Keep the non stop sniffing and smoking and then get more energy to whistle more and more through all of your cursed holes. Okay? Okay!


Day and night Hyena Song

"I'm money broke and it's no joke can't core use the rope this time (Hey !!)
nuckel up buckel up the ride's getting rough but i will not loose my mind (Hey !!)
i asked'em if i could come in and the first thing they said was no (Hey !!)
if i can't come in thats mean that i can't come back that means i got nowhere to go
i'm a hyena fighting for lion share
sometimes the lions share ain't there

absent from political authority an animal i've become (Hey !!)
total disorder and confusion is the life style that i run (Hey!!)
permit me to do what i want and i will i'm a nomad to travel (Hey !!)
i'm a hyena fighting for lion's share
sometimes the lions share ain't really there

every time i turn around it's the same sad story
getting ganked and under ranked i wish i could end up as a word mincing commissary
i'm a bad missionary with a wicked message i often wickedly send
whom can i trust in a world of greed for a person of my breed
when i'm taught to take and take but don't have any thing to give

whom can i trust when i'm taught to take but don't have anything to give
I'm money broke and it's no joke and don't even care to use the rope this time (Hey!!)
nuckel up buckel up the ride's getting rough but i will not loose my mind (Hey !!)
permit me to do what i want and i have nowhere to travel (Hey !!)
concrete class stone and gravel

i'm a hyena fighting for the lion's share
sometimes the lions share ain't really there
sometimes the lions share ain't there.....sh!t!"
:P

Sam Ebalalehu
Member
Posts: 1521
Joined: 23 Jun 2018, 21:29

Re: የፖለቲካ ሳይንስ፣ አቢይ አህመድ ጠ/ሚ መሆን የፈለገው ለምንድን ነው?

Post by Sam Ebalalehu » 05 Sep 2020, 20:38

It is a good catch above, Horus. But I disagree with your assumption that Ethiopians and political activists and cadres judge Abiy rationally. Ethiopians, in general, do. Political activists and cadres judge him contingent upon their political affiliation. To TPLF, Jawar and company and others who believe identity politics to be supreme he is a monster, way more than a dictator. To politicians and activists who despise identity politics he is an ok politician. They know where his heart is, but he has to navigate consciously not to step on the bombs the identity politics champions buried for the last thirty years.

Horus
Senior Member
Posts: 16860
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: የፖለቲካ ሳይንስ፣ አቢይ አህመድ ጠ/ሚ መሆን የፈለገው ለምንድን ነው?

Post by Horus » 05 Sep 2020, 20:39

sun = Defend The Truth መሆንክን ስለ አመንክ አመሰግናለሁ ።

Horus
Senior Member
Posts: 16860
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: የፖለቲካ ሳይንስ፣ አቢይ አህመድ ጠ/ሚ መሆን የፈለገው ለምንድን ነው?

Post by Horus » 05 Sep 2020, 21:08

ሳም እባላለሁ፡

እኔ ምንም አሰምሽን (ቅድመ ውሳኔ) የለኝም ። የፖለቲካ አክቲቪስቶችና ካድሬዎች እንዴት እንደ ሚመለከቱት አላቅም። እኔ የዘረዘርኩት አቢይና አገዛዙን ሳይንሳዊ በሆነ መንገድ መተንተን የሚፈልግ ሰውም ቢያንስ መጠየቅ ያለበትን እና ዘዴዎችን ነው የጠቆምኩት ።

የኢትዮጵያ ፖለቲካ መረታዊ መሰንጠቂያ መስመር በዘውግ እና ዜጋ ፖለቲካ ላይ መሆኑ እጅግ ትክክል ነው ። ያገሪቱ ቁጥር አንድ የፖለቲካና ሶሺያ ቅርቃር እሱ ነው ።

ስለዚህ የኔ አንዱ ጥያቄ ያቢይ አህመድ አገዛዝ የዘውግ አገዛዝ ነው ወይስ የዜጋ?

ይልቅስ አንተ በግልጽ የመልስከው ነገር አለ፣ ትክክል ሆንክም አልሆንክ ። የዜጋ ፖለቲካው ረድፍ የአቢይ ልብ የት እንዳለ ያውቃሉ ብለሃል ። ይህ ምን ማለት ነው? አቢይ የዜጋ ፖለቲካ አማኝ ከሆነ ያን ድምዳሜ የሚያረጋግጠው ኢምፒሪካል አብነት ምንድብን ነው?

ከላይ ላሉት 7+ ጥያቄዎቼ የዜጋ መልስ አላቸው ወይ?

አቢይ ሞንስተር (ጭራቅ) ነው የሚለው የነጃዋር አቋምና አቢይ ኦኬ ነው የሚለው የዜጋዎቹ አቋም ሁለቱም ሳይንሳዊ ጽንሶች አይደሉም ። አቢይ ዲክታቶር ወይ ዴሞክራት ነው። አቢይ የዘውግ ቡድን ጥቅም ተሟጋች ወይ የዜጋ ጥቅም ተሟጋች ነው ። የሁለቱም ቅይጥ ነው የሚሉ ደሞ ያንን ማሳየት አለባቸው ።

ግ ን ይህ ሁሉ አቢይ አህመድ ለምን ጠ/ሚ መሆን ፈለገ የሚለውን የምቲቭ ጥያቄ አይመልስም ።

Horus
Senior Member
Posts: 16860
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: የፖለቲካ ሳይንስ፣ አቢይ አህመድ ጠ/ሚ መሆን የፈለገው ለምንድን ነው?

Post by Horus » 05 Sep 2020, 22:21

ይህን የመጪው ምርጫ ውድድር ስሙ ። አቤቤ በቀጥታ ከኢዜማ ጋር ክርክር ስታደርግ ስሙ ። ይህ ሁሉ በጣም ጥሩ ነው !!

አዳነች አቤቤ የምትለውን ሁሉ እነ አባዱላ ሲሰሩት የነበረው፣ ታከለ በአቢይ እውቅና የሰራው ፣ አሁን የሌብነቱ ልክ ለመንግስት ስልጣን አደጋ ሲሆን ነው አቤቤ ድፍንፍን እያረገች ምታልፈ ። ታከለ ለሕግ መቅረብ ሲኖርበት አቢይ ሌላ ሹመት ነው የሰጠው ።

ያዲስ አበባ ችግር የሜጋ ፕሮጀክቶ እጦት አይደለም ። ያዲስ አበባ ችግር የፍትህ እጦት ፣ የዲክታቶር አገዛዝ ችግር ነው ።

አቢይ አሁንም በ7 ሚልዮን ሕዝብ ላይ ነው ሚቀልደው ። አቤቤ ሌላ አዲስ ዲክታቶር ነቸ ። ይህን ሁሉ ወንጀል ስትዘረዝር አንድ ሰው ጠቅሳ ተጠያቂ አላደረገችም ።


Horus
Senior Member
Posts: 16860
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: የፖለቲካ ሳይንስ፣ አቢይ አህመድ ጠ/ሚ መሆን የፈለገው ለምንድን ነው?

Post by Horus » 06 Sep 2020, 00:22

ከዚህ ቀጥዬ የላይኞቹን 7 ጥያቄዎች አንድ ባንድ ባጭር ባጭሩ እመልሳለሁ ።

አንድ፣ አቢይ ለምን ጠቅላይ ሚኒስቴር ወይም ፕሬዚዳንት መሆን ፈለገ?

አንድ ሰው የህይወቱን ተልዕኮ ከቤተሰብ (ማህበራዊ ግፊት)፣ ከሃይማኖቱ፣ ከደረሰበት ጥቃት (ትራማ) እና ከህልውናዊ ፍላጎቱ ያገኛል ። አቢይ አህመድ የነገርን አላማውን ያገኘው ከእናቱ (ማለትም ከቤተሰብ) ግፊት እንደሆነ ነው።

ግን ዞሮ ዞሮ ጠ/ሚ መሆን የራሱ ውስጣዊ ፍላጎት መሆን አለበት ። የፖለቲካ መሪ መሆን ከሁሉም በላይ ከሃይል (ስልጣን) ፍላጎት ይመነጫል። ሕዝብ ነጻ ማውጣት ፣ አገር መገንባት፣ ለውጥ መፍጠር ወዘተ የሚባሉት ፓብሊክ ውጤቶች የያዝነውን ስልጣን ምን ላይ እንደ ምናውለው ይሳያል እንጂ ያንድ ሰው ፖለቲካዊ ሞቲቫቲኦን (ገፊ ምክኛቶች) የሚከተሉት ናቸው ። እነሱም የማንኛውም ፖለቲካ መሪ ፍላጎቶች አራት ናቸው፤ (1) ስልጣን (2) ሃብት (3) ዝና እና (4) ክብር ናቸው።

ማንኛውን ትልቅ ሆነ ትንሽ ፖለቲከኛ ባህሪ ምን እንደ ሆነ ሚነግረን ገፊ ምክንያት ወይ ስልጣን ነው ፣ ወይ ሃብት (ገንዘብ) ነው፣ ወይ የዝና የመታውቅ ፍላጎት ነው፣ ወይም የክብር የስታተስ ፣ የበላይ ሆኖ መታየት ፣ ክብር የማግኘት ፍላጎት ነው።

ከዚያ ባለፈ ወደ ፊት እንደ ማሳየው አንድ መሪ ሕዝብ ወይም ሰዎች የሚፈልጉት ነገር የሚያደርገው ወይ ሰዎች እንዲመርጡት፣ እንዲወዱት፣ እንዲደግፉት ወይም እንዲከተሉት ነው። ለምሳሌ ታከለ ለምን ገንዘብ፣ ቤትና መሬት ለደጋፊዎቹ ለምን እንዳከፋፈለ በሌላ ጥያቄ እመለስበታለሁ። ይህ ባጭሩ የቁጥር አንድ መልስ ነው ።
Last edited by Horus on 06 Sep 2020, 15:58, edited 1 time in total.

Guest1
Member
Posts: 1498
Joined: 28 Dec 2006, 01:02

Re: የፖለቲካ ሳይንስ፣ አቢይ አህመድ ጠ/ሚ መሆን የፈለገው ለምንድን ነው?

Post by Guest1 » 06 Sep 2020, 02:06

አቤቤ ... ይህን ሁሉ ወንጀል ስትዘረዝር አንድ ሰው ጠቅሳ ተጠያቂ አላደረገችም ።
ኣሳማኝ ነጥብ።

Horus
Senior Member
Posts: 16860
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: የፖለቲካ ሳይንስ፣ አቢይ አህመድ ጠ/ሚ መሆን የፈለገው ለምንድን ነው?

Post by Horus » 06 Sep 2020, 02:30

ሁለት ፣ አቢይ አህመድ ጠቅላይ ሚኒስቴር የሆነው እንዴት ነው? እንዴት ስልጣን ላይ ወጣ?

እኔ ብዙ ጭጋግ ውስጥ የተወዣበረ ዝባዝንኬ አላበዛም።

አንድ ሰው ስልጣን ላይ ያለውን መሪ ገድሎ ቦታውን ሊይዝ ይችላል። ክዴታይባላል። ስልጣን ዙሪያ ባሉ ቁልፍ ሰዎች መካከል ሻጥር ተካሂዶ አንዱ ስልጣን ላይ ይወጣል። አንድ ልዑል ንጉስ የሚሆነው እንደዚያ ነው ። አንድ ዲክታቶር በዉሸት ምርጫ ወንበር ይይዛል ። የኮሚኒስትና ማ ዕከላዊ ፓርቲ የሚሰራው እንዲያ ነው። ወይ በአመጽ፣ ወይ ባብዮት በመሳሪያ አፈሙዝ ስልጣን ይያዛል። ወይ አንድ ሰው ህዝብ መርጦት ባገሬው ምርጫ ሕግ መሰረት ወንበር ይይዛል።

አቢይ አህመድ ጠ/ሚ የሆነው ጥቂት የኢህአዴግ ፓርቲ ወሳኞች (ቁልፎች) አዋሳ ላይ በሰጡት ድምጽ ነው ። ለ27 አመት የኢትዮጵያ ሕዝብ ያደረጉት ትግል ተዉት ። ብዙ ፓርቲና የታጠቁ ቡድኖች ያደረጉት ትግል ተዉጥ ቄሮ ፋኖ ኤጀቶ ዘርማ አርዴ ሌላ ሌላ ያደረጉት መንገድ መዛት ሌላም ሌላም ተዉት ። ያ ሁሉ ዎያኔ ለምን ወደቀ? የሚለውን ጥያቄ ይመልሳል እንጂ በተላይ አቢይ ለምን ጠ/ሚ ሆነ የሚለውን አይመልስልም ። ተስማማን?

አቢይ ዙፋን ላይ የወጣው በጣም ጥቂት እፍኝ ማይሞሉ ሰዎች በሰጡት ድምጽ ነው። የዚያን እለት የሲዳማው ሽጉጤ፣ ደመቀ፣ ደብሬ ወይም ሌላ ሰው እርስቴ ሊነግስ ይችል ነበር ።
የአቢይ አህመድ ጠቅላይነት መሰረት ያ ቡድን ነው ። ይህ የፖለቲካ ሳይንስ ይባላል። ሌላው ሶሺያ ሳይንስ ነው።

ልብ በሉ ዎያኔ ለምን ወረደ? ሃይለማሪያ ለምን ለቀቀ የሚሉት ነገሮችና ያ እንዲሆን ያደረጉት ምክኛቶች ለምን አቢይ በተለይ ጠ/ሚ ሆነ ለሚለው መልስ አይሆኑም ። ስለሆነም አቢይን ጠ/ሚ ያደረጉት ሰዎች 300 እንኳ አይሆኑም ።

ጥያቄ 3 ይቀጥላል
Last edited by Horus on 06 Sep 2020, 15:59, edited 1 time in total.

Guest1
Member
Posts: 1498
Joined: 28 Dec 2006, 01:02

Re: የፖለቲካ ሳይንስ፣ አቢይ አህመድ ጠ/ሚ መሆን የፈለገው ለምንድን ነው?

Post by Guest1 » 06 Sep 2020, 02:46

(1) ስልጣን (2) ሃብት (3) ዝና እና (4) ክብር ናቸው።
ህዝብ ለማገልገል፤ ለማንቃት፤ ህዝብ ነጻ ለማውጣት አገር ለማሳደግ፤ አንዳቸውም ለምን ኣልተጠቀሱም? ኔጋቲቭ ላይ ብቻ ለምን?
ጊዜ መሪን ይፈጥራል የሚባለውስ?
አገሪቱ ጊዜው የሚጠይቀውን መሪ አገኘች ቢባልስ?
ታሪክን ወደፊት ሳይሆን ወደኋላ የቀለበሰ መሪ ሊባል ይችላል? ጉድ!!

Horus
Senior Member
Posts: 16860
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: የፖለቲካ ሳይንስ፣ አቢይ አህመድ ጠ/ሚ መሆን የፈለገው ለምንድን ነው?

Post by Horus » 06 Sep 2020, 03:24

Gኡእስት1
ከሳይንስ የወጣ ስሜትና ያልተባለ ነገር እኔ ሆረስ ላይ አይሰራም ። አንድ መሪ ለምን ስለ ፓብሊክ ፕሮጀችት፣ አገር እድገት፣ ብልጽኛ ወዘተ ስለሚያወራና ስለሚተገብር ታገስ እነግርሃለሁ ። አንድ ሰው ያገር መሪ ሲሆን ያገር ሃብትና ያገር ታክስ ሰብሳቢ ነው ፣ ይህ ሁሉ ለምን እንደ ሚደረግ ሳታስብ ግለሰብ ባለስልታንን መል አክ ማደረግ ስነሳ ያልኩ ነገር ነው ። ፖለቲካ ምን እንደ ሆነ ሳያውቁ የፖለቲካ ተከታይ መሆን ማለት ነው። አቢይ በግሉ ተነስቶ የሚፈይደው፣ የሚያሳድገው አንዳች ነገር የለም ። አርቱን ተከታተል ፣ አትቸኩል ። እኔ አቢይን አልጠላውም ፣ ግ ን አቢይ የፖለቲካ እንሰሳ እንደ ሆነ ሁሉ ማወቅ አለበት !

ወንድሜ ኢዜማ የጋዜጣ መግለጫ የተከለከለው ለምንድን ነው ። ያቢይ ስም እንዳይጠፋ ፣ ስሙ፣ ዝናው (ገጽታው) ከሌባው ታከለ ጋር እንዳይያያዝ ነው፣ ግ ን ታከለን ካምቦ ያመጣው አቢይ ነው። ዛሬም አበቤን አምጥቶ አዲሳባ ያስቀመጣት ሴት ስለሆነች ወንዶች እንዳይሰድቧት ምናምን ነው። አቤቤ ግ ን ከኢዜማ የላቀ ሌበንት ነው ያወጣው። ታዲያ አቢይ ለምንድን ነው አው ኢዜማ ወይም እስክንድር ትክክል ነበሩ ያላለው ። ዉሸታም የስልጣን ነጋዴ ዲክታቶር የምሆን ምኞት ወስጥ ያለ ሰው ስለሆነ ነው ። ይህ ሁሉ ወደፊት ይረጋገጣል። አቢይ ክልሲክቻል ማኒፑሌተር ተጫዋች ነው።

እውነትኛ ንጹ ቢሆን በታከለ ስራ በጣም ተናዶ እሱን ለፍርድ ያቀርብ ነበር ። አንተ አይምሮህ በስሜት ስለተሸፈነ እውነትን ማየት አትችልም ፣ ይህ ነው እውነቱ !!!

Horus
Senior Member
Posts: 16860
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: የፖለቲካ ሳይንስ፣ አቢይ አህመድ ጠ/ሚ መሆን የፈለገው ለምንድን ነው?

Post by Horus » 06 Sep 2020, 04:53

ሶስት፣ አቢይ አህመድ ስልጣን ላይ የሚቆየው እንዴት ነው?

ከዚህ በፊት እንዳልኩት አንድ ሰው የመንግስት ስልጣን መያዝ ከፈለገ መጀምሪያ ስልጣን ላይ ያለውን ሰው ያወርዳል ። በምን ዘዴ? ታቁታልችሁ!

ከዚያም የመንግስት አውታሮችን ተራ በትራ ይቆጣጠራል ፤ ህንጻዎቹን ይዞ የድሮ አለቆችን አስወግዶ የሱን ሰዎች ያቀምጣል ። መጀመሪያ ከቤተ መንግስት ዘብ ይጀምራል ፣ ቀጥሎ ስለላንን፣ የወታደር አለቆችን ፣ ፖሊስ ፣ እያለ በመሳሪያ ሊያወርዱት የሚችሉትን ሁሉ ከጥቅም ውጭ ያደርጋል ። ቀጥሎ የገንዘብ ማከማቻ ቦታዎችን ባንክ ምናምን ይቆጣጠራል ። ቀጥሎ የዝና (የዜና) መሳሪያዎችን እያለ የመንግስት ህዋሳትን ይይዛል።

ይህ ሁሉ እኛ አቢይ ከመስቀል አደባባይ ጀምሮ በተሞከረበት ግድያ፣ ግልበጣ ሌላም ሌላም ብዙ ስላየን ብዙ ማለት አልሻም ።

ቀጥሎ አንድ መሪ የሚያደርገው የገንዘብ፣ ሃብት፣ ታክስ፣ ግብር፣ ባንክ ፣ ሌላም ሌላም የገንዘብ ምንጭ መቆጣጠር አለበት ። አቢይም ይህን ነው ያረገው። ይህን ማድረግ የሚያስፈልገው ቁልፍ ደጋፊዎቹ፣ የስልጣኑ ቁክፍ ዘበኞች፤ መከፈል ስላለብቸው ነው።

ቀጥሎ አንድ መሪ 3 አይነት ፣ ባለ 3 ረድፍ የደጋፊዎች ረድፍ እንዲኖረው ግድ ነው ። አንዱ ወደ ስልጣን እንዲወጣ ድምጽ የሰጡትና የመሪውን ህይወት ሚጠብቁት ከጸጥታ እስከ ከፍተኛ የወታደር አለቆች ፣ የስለላና የዘብ ፣ የፓርቲ አለቆች ፣ የመሪውን ዝና ሕዝብ ግንኙነት፣ ወዘተ ሚንከባከቡት ቁልፍ ረድፍ የሚባሉትን ይመለምላል፤ ከስሩ ያእጋል።

ቀጥሎ ተጽኖ ፈጣሪ ሚባሉት ሚዲያ፣ አርቲስቶች፣ ነጋዴ፣ ምሁር ወዘተ ይመለምላል። የነዚህ ተጽኖ ረድፍ ስራ ታች ያለውን ሕዝብ ማሳመን፣ ማታለል፣ ማደንዘዝ ነው። እነዚህ ከምሁራዊ አማካዊዎች ጀምሮ እስከ አርቲስቶች፣ እስከ ነጋዴ ብር ለጋሾች፣ እስከ ሃይማኖት መሪዎች ያካትታል ።

እርግጥ አንድ ዲክታቶር ስልጣን ላይ ለመሰንበት የሚፈልገው የሴኩሪቲና ወታደር ድጋፍ ብቻ ቢሆንም የሲቪል ቁልፍ ረድፍና የተጽኖ ረድፍ ድጋፍ አስፈላጊ ነው። የስልጣን መሰረት፣ የህዝብ መሰረት ወዘተ ሚባለው ያ ነው።

ስለሆነም ፖለቲካ ሳይንስ ማያውቁ አቢይ ስልጣን ላይ ለመሰንበት የኦነግ ድጋፍ፣ የህዝብ ድጋፍ፣ የኦሮሞ ያማራ የደቡብ ድጋፍ ይፈልጋል የሚሉ ሁሉ ፖለቲካ አያቁም። አቢይ የነሱ ድጋፍ ሚፈልገው ዴሞክራት መሆን ከፈለገ ብቻ ነው። ዲክታቶር ሆኖ መግዛት ከፈለገ ገንዘብ፣ ቤት፣ መሬት፣ መኪና፣ ደሞዝ፣ ስልጣን በደንብ ሚሰጣችው የቁልፍና የተጽኖ ረድፎችን መልምሎ እነሱን በማስደሰት እንዲጠብቁት አድርጎ ሊገዛ ይችላል ።

ታከለ ኡማ ይህን ሁሉ ገንዘብ፣ ቤት፣ መሬት፣ መኪያ የሸለመው እነዚህ ቁልፍ እና ተጽኖ ደጋፊ መመልመልና ለማማለል ነበር ። ወደፊትም የሚሆነው ያ ነው ። ያበቤም ሚሽን ያ ነው ።

ይቀጥላል
Last edited by Horus on 06 Sep 2020, 16:00, edited 1 time in total.

Guest1
Member
Posts: 1498
Joined: 28 Dec 2006, 01:02

Re: የፖለቲካ ሳይንስ፣ አቢይ አህመድ ጠ/ሚ መሆን የፈለገው ለምንድን ነው?

Post by Guest1 » 06 Sep 2020, 08:47

እውነተኛ ታሪክ
ኣንድ ቀን መንግስቱ ግቢው ውስጥ ሲዘዋዋር እዚያው ያሳሰረውን ጓደኛውን ከእሰር ቤቱ ደጃፍ ቁጭ ብሎ አገኘው። ጓደኛው ደፋር ሰው ነበርና በንዴት “አንተም መሪ ሆነክ’’ አለው።
መንግስቱም ‘ኣንተ ልትሆን ነበር?' ብሎ መለሰለት ይባላል ክክክክክክ
ለመሪነት ኣትበቃም ተባባሉ። መንግስቱ መሪ መሆን የቻለው ብቃት ስለነበረው ኣይደለም?

Sam Ebalalehu
Member
Posts: 1521
Joined: 23 Jun 2018, 21:29

Re: የፖለቲካ ሳይንስ፣ አቢይ አህመድ ጠ/ሚ መሆን የፈለገው ለምንድን ነው?

Post by Sam Ebalalehu » 06 Sep 2020, 09:02

An Ethiopian leader could cease to control the military if he turns out to be a dictator. If a dictator he happens to become, the military starts to fracture along ethnic lines.
When TPLF runs the show, it was for that reason almost all leadership position were held by TPLF “generals.” Now, the military leadership is more or less shared.
Abiy has no the chance to be a dictator. If the Amharas and the southerners pull out their support to his administration, there will no be an Abiy led administration let alone a dictator one. This noise making is about nothing.

Guest1
Member
Posts: 1498
Joined: 28 Dec 2006, 01:02

Re: የፖለቲካ ሳይንስ፣ አቢይ አህመድ ጠ/ሚ መሆን የፈለገው ለምንድን ነው?

Post by Guest1 » 06 Sep 2020, 12:05

Abiy has no the chance to be a dictator. If the Amharas and the southerners pull out their support to his administration, there will no be an Abiy led administration let alone a dictator one. This noise making is about nothing.
ያሻውን መፈጸም ከቻለ፤ በሃይል መቅጣትም ከቻለ ዲክቴተር ካልተባለ ምን ልባል?
ዲክቴተር ስንት ወታደር ያስፈልገዋል? ክክክክክክክክክክክክክ እንቅጠር። የአቢይ ወታደር ስንት ሺ ይደርሳል? 100 000? የኢሳያስ ወታደሮችስ? የአሜሪካንና የአረብ አገር ወታደሮችስ አይረዱትም?

አማራና ደቡብ ቢያፈነግጥ ምን ሊፈጠር? አገር ልትፈርስ? አገር መግዛት ሊያቀተው? ምንም ነገር ኣይመጣም። ሁለቱ ከተስማሙ አዲስ አበባን መያዝ ይችላሉ ምንም ጥርጥር የለውም። ኢሳያስ ወታደሩን ኣይልክም የኣለም ህግ ኣይፈቅድለትም። የኦሮሞያ ጊዜያዊ ትርምስ ይፈጠራል። ከመተላለቅ ብለው ወደ ዲሞክራሲያዊ ሽግግር የግድ ሁሉም ይገባል።

Post Reply