Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Wedi
Member+
Posts: 7959
Joined: 29 Jan 2020, 21:44

ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም አብይ አህመድ "ህሌና የለለው" በማለት ሸንቆጥ አደርጉት!!

Post by Wedi » 02 Sep 2020, 17:04

ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም አብይ አህመድ "ህሌና የለለው" በማለት ሸንቆጥ አደርጉት!!
:P :P
Prof. Mesfin Woldemariam

ኅሊና የት ገባ!
መስፍን ወልደ ማርያም
ነሐሴ 2012

ኢዜማ አምጦ የወለደው መግለጫ አ ሸባሪ ነው፤ የሚደንቀው አንድም የአገዛዙ ባለሥልጣን፣ ጠቅላይ ሚኒሰትሩንም ጨምሮ፣ የጸጸት ወይም የሐዘን መልስ አላሰማም፤ እኔ የቀድሞው ከንቲባ በፈቃዱ ሹመቱን የሚያስረክብ መስሎኝ ነበረ፤ ይህ እንዳይሆን ደግሞ የተቀናጀ በሚመስል ዘዴ በሌላ ሚኒስቴር በሚኒስትርነት ተሾመ! ይህ አንዱ የአገዛዙ ዓይነ-ደረቅነት ነው፤ ዓይነ-ደረቅነቱን ሲያደርቀው የቀድሞው ከንቲባ በሚያሳፍረው ነገር እንደሚኮራ ነገረን! ምን ትሆናለችሁ እያለን ነው!

ጠቅላይ ሚኒስትሩም ሆነ የዱሮው ከንቲባ ጉዳዩ በገለልተኛ ቡድን እንዲጣራ በማለት ሀሳብ አላቀረቡም፤ ምናልባት ከኛ በላይ ማን አለ ብለው ይሆናል፤ በሌላ የሕግ ሚዛንና የሕዝብ ድምጽ በሚታወቅበት አገር የቀድሞው ከንቲባ ወይ ራሱን ያሰናብታል፣ ወይ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ያሰናብተዋል፤ የኛ ጠቅላይ ሚኒስትር የምድሩን ጉዳይ ሁሉ እናንተ እንደፈለጋችሁ ብሎ እሱ በሰማይ ላይ ትላልቅ ፎቅ እየሠራልን ነው!
አልጨረስሁም!


Please wait, video is loading...

Guest1
Member
Posts: 1926
Joined: 28 Dec 2006, 01:02

Re: ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም አብይ አህመድ "ህሌና የለለው" በማለት ሸንቆጥ አደርጉት!!

Post by Guest1 » 02 Sep 2020, 17:33

ምናልባት ከኛ በላይ ማን አለ ብለው ይሆናል
ብቻችውም ኣይደሉም ድጋፊም የበላይም ኣላቸው። ፒፒዎች። በአገሪቱ ሰላም ለመፍጠር የተደረገም ነው።
አዳነች አቤቤ ጠንካራ ሴት ደስ ትለኛለች ብለውም ነበር። ኣሁን ደግሞ ተመልስው ሊወቅሷት? ፕሮፌሰሩ ሚስጢሩን ኣልደረሱበትም ወይም ኣውቀው ያጯጩሃሉ።

experts
Member
Posts: 249
Joined: 26 Apr 2019, 10:55

Re: ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም አብይ አህመድ "ህሌና የለለው" በማለት ሸንቆጥ አደርጉት!!

Post by experts » 02 Sep 2020, 18:57

ፕሮፌስሩ መቃዠት ጀምረዋል። አንድ ስሞን ያሞግሳሉ ወድያው ይወቅሳሉ። ለነገሩ እሳቸውና እውነት ሆድና ጀርባ ናቸው። ታሪካቸው ከኃይለስላሴ ዘመን ጀምሮ በክህደትና ማጭበርበቅ የተካኑ ናቸው አሁን ምንም ቢሉ አይገርመኝም። በተለይ የሚቀልባቸው ብርሃኑ ነጋ ስለሆነ ሁሌም እሱ ያዘመመበትን አይተው ያዘማሉ። ኑሮ ለሆድ ማለት እንዲህ ነው።

sun
Member+
Posts: 9312
Joined: 15 Sep 2013, 16:00

Re: ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም አብይ አህመድ "ህሌና የለለው" በማለት ሸንቆጥ አደርጉት!!

Post by sun » 02 Sep 2020, 20:45

[quote=experts post_id=1100287 time=1599087424 user_id=50856]
ፕሮፌስሩ መቃዠት ጀምረዋል።አንድ ስሞን ያሞግሳሉ ወድያው ይወቅሳሉ። ለነገሩ እሳቸውና እውነት ሆድና ጀርባ ናቸው። ታሪካቸው ከኃይለስላሴ ዘመን ጀምሮ በክህደትና ማጭበርበቅ የተካኑ ናቸው አሁን ምንም ቢሉ አይገርመኝም። በተለይ የሚቀልባቸው ብርሃኑ ነጋ ስለሆነ ሁሌም እሱ ያዘመመበትን አይተው ያዘማሉ። ኑሮ ለሆድ ማለት እንዲህ ነው።[/quote]

WELL SAID INDEED! :P

TGAA
Member+
Posts: 5598
Joined: 07 Apr 2019, 20:34

Re: ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም አብይ አህመድ "ህሌና የለለው" በማለት ሸንቆጥ አደርጉት!!

Post by TGAA » 02 Sep 2020, 21:20

Tribal goons always have disdain for truth. They know the truth doesn't reward with plunder as deceit dose. So anyone who calls " the new tribal overlords " are necked are supposedly "ridiculed". Outright daytime loot is justice delivered, killing is done for good of the people, a kangaroo court is, they say, the best justice delivery system the world has ever known. One really would have made the best cartoon characters out of these charlatans, but the unfortunate reality is that these belly slaves prolong the suffering of the Ethiopian people.

Fed_Up
Senior Member+
Posts: 20403
Joined: 15 Apr 2009, 10:50

Re: ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም አብይ አህመድ "ህሌና የለለው" በማለት ሸንቆጥ አደርጉት!!

Post by Fed_Up » 02 Sep 2020, 21:56

The question should be are those all substandard condominiums are given away to any foreign entities or Ethiopians? If it is given away to Ethiopians then there is nothing wrong doing in the administration side. Especially I congratulate if it is true those benefited are the peasants once they used to own the land.

What is wrong with you, Ethiopians? Don’t you love your country and people? With such mentality, Ethiopia will cease to exist sooner. You will find yourself and family living in fragmented, war ridden, poorest of all poor....multiple clans ran regions. You should see the big picture than playing by the iq63 clans. You can do better than this.

Post Reply