Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Hameddibewoyane
Member
Posts: 3890
Joined: 25 Sep 2019, 02:42

ሰበር ዜና:ህወሓት የፈንቅል ንቅናቄ አባላትን አፍኖ ወደ በረሃ ወስዶ ከገደለ በኋላ በኮሮና ሞቱ ብሎ ማሳበብ ጀምሯል‼️

Post by Hameddibewoyane » 15 Aug 2020, 12:22

በትግራይ ከየአቅጣጫው እየመጣ ያለውን የወጣቶች ንቅናቄ ለማፈን #የስብሃት ነጋ ቤተሰብ በተለያየ መንገድ እየጣረ ይገኛል። በሁሉም የትግራይ ዋና ዋና ከተሞች ተቋውሞ የሚያደርጉትን ወጣቶች ብቻ ሳይሆን በዝምታ ተቀምጦ ያለውን ትግራዋይንም እየገደሉ መሆኑ ተሰምቷል። ህወሓት የተለየ የፖለቲካ አቋም ያላቸውን ወጣቶች ሳያንሰ የኮሮና ቫይረስን ሰበብ በማድረግ ህብረተሰቡ ስለተገደሉት ወጣቶች ማንኛውንም ጥያቄ እንዳያነሳ፣ ቀባሪ ቤተሰብም ሆነ ወዳጅ ዘመድ ልጆቻችንስ ብለው እንዳይጠይቁ እያደረገ ስለመሆኑ ከአከባቢው የደረሰን ማስረጃ ያስረዳል።

ይህ የጭካኞች ስብስብ ራሱ ገድሎ ማሳበብን እንደሆነ ላለፉት 45 አመታት ሲያደርገው የነበረና ከማንም በላይ የተካነበት ጉዳይ መሆኑ ይታወቃል። በዚህ ረገድ የህወሓት ዋነኛ ዒላማ የሆነው የፈንቅል ንቅናቄ አባላት ሲሆኑ ወጣቶቹን እየያዙ "ማንን እንደምትፈነቅሉ እናያለን" በማለት ወደ በረሃ በመውሰድ እንደሚገድሏቸው ታውቋል። የወጣቶቹ ቤተሰቦች እና በአካባቢያቸው የሚኖሩትን ማህበረሰብ በሰፈሩ "ኮሮና ተገኝቷል" በማለት እርስ በእርስ እንዳይነጋገርና እርሙንም እንኳን እንዳያወጣ በማገድ እንደሚገኙ ታውቋል።

ይህ የሚያመለክተው ህወሓት የሚባለው ጨካኝና ጨቋኝ ቡድን መጨረሻው እየተቃረበ መሆኑን ነው። በመሆኑም ፍፁም በጭካኔ የተሞላ ተግባር በመፈፀም እስትንፋሱን ለማስቀጠል በማጣጣር ላይ ይገኛል። የስብሃት ነጋ ቤተሰብ ህልውናውን ለማትረፍ ያለው አማራጭ መግደልና መግደል ብቻ ነው። የለውጥ ጥያቄ ያነሱትን ወጣቶች ወደ በረሃ በመውሰድና በመግደል ደብዛቸውን ያጠፋል። በዚህም የትግራይ ህዝብ በፍርሃት ቆፈን ተለጉሞ የስብሃት ነጋ ቤተሰብ ባሪያና አገልጋይ ሆኖ እንዲቀጥል ጥረት በማድረግ ላይ ይገኛል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ፤ የስብሃት ነጋ፣ የአባይ ፀሃዬ እና የስዩም መስፍን ዘመዶች እና ቤተሰቦች ወደ አዲስ አበባ አበልጆቻቸው ጋር ስልክ በመደወል በትግራይ ነገሮች በፍጥነት እየተቀያየሩ ስለሆነ በቅርቡ ብልጽግና ተቀላቅለናል በማለት ወደ አዲስ አበባ ለመመለስ እንደሚፈልጉ መናገራቸው ተሰምቷል።