Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Ejersa
Member
Posts: 3976
Joined: 05 Nov 2019, 10:39

የኦሮማራ ጥምረትን በማፍረስ የሀገርን ህልውና አደጋ ላይ ለመጣል የሚደረግ ጥረት እንደማይሳካ ተገለጸ!

Post by Ejersa » 14 Aug 2020, 10:41

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የአርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳን ህልፈተ ህይወት ተከትሎ በተፈጠረው ቀውስ ለተጎዱና ለተፈናቀሉ ወገኖች ድጋፍ አደረገ። በርክክብ ሥነ ሥርዓቱ ላይ የአማራ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ ተመስገን ጥሩነህ እና የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳት አቶ ሽመልስ አቢዲሳ የጋራ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡

አቶ ተመስገን የተፈጠረው ክስተት መቼም ቢሆን መከሰት የሌለበት እና ሁሉም ኢትዮጵያዊ የማይደግፈው የነውጥ መንገድ ነው ያሉ ሲሆን የኦሮሞ እና የአማራ ወጣቶች ለውጡን እውን ለማድረግ በአንድነት እንደቆሙ ሁሉ ዛሬም በመተባበርና መደጋገፍ የብልጽግና ጉዟቸውን እንደሚቀጥሉ አስረድተዋል፡፡

የብልጽግና ፓርቲን ለማጥፋትም ሆነ የኢትዮጵያን ህዝብ አንድነት ለመጉዳት የሚሰሩ የነውጥ ኃይሎች እንደማይሳካላቸው የተናገሩት ፕሬዚዳንቱ የህግ የበላይነትን ለማስከበር በሚደረገው ጥረት ውስጥ በህግ ቁጥጥር ውስጥ ያሉ ሁሉ ህግ በሚፈቅደው መንገድ ብቻ ምርመራው እየተጣራ እርምጃ መውሰድ እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል፡፡ የአማራ ክልል በኦሮሚያ ክልል ለደረሰው ጉዳት 3 ሺ ኩንታል የምግብ ቁሳቁስ እና የገንዘብ ድጋፍ ማድረጉንም ለጋዜጠኞች ገልጸዋል፡፡

የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳም በአማራና በኦሮሞ ህዝቦች መካካል እሳት እየጫሩ የለውጡን ጉዞ ለማደናቀፍ የሚደረገው ጥረት አይሳካም፤ ትብብርና ድጋፋችን ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል፡፡ የአማራ ክልል የአርቲስት ሀጫሉን ኅልፈተ ህይወት ተከትሎ ለደረሰው አስከፊ ሀዘን ከኦሮሞ ህዝብ ጎን ስለነበረ እና ለተደረገው ድጋፍ ሁሉ በኦሮሞ ህዝብ ስም አድናቆታቸውንና ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡

ምንጭ፣ የአማራ ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት

kibramlak
Member
Posts: 2155
Joined: 26 Sep 2013, 09:27

Re: የኦሮማራ ጥምረትን በማፍረስ የሀገርን ህልውና አደጋ ላይ ለመጣል የሚደረግ ጥረት እንደማይሳካ ተገለጸ!

Post by kibramlak » 14 Aug 2020, 11:14

ምነው ሽመልስ የተናገራት እና ይህ ጽሁፍ ምን አገናኘው?

Post Reply