Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Za-Ilmaknun
Member
Posts: 4080
Joined: 15 Jun 2018, 17:40

What other Regions could learn from Somali Region. Mustefe ..the true leader !

Post by Za-Ilmaknun » 05 Aug 2020, 18:04

Within a short two years Somali Region is transforming itself from a dusty poor place to one of a vibrantly growing Region. The Region once known for its egregious human right abuses and widespread illicit activities by TPLF generals, is now turning to be a Region where people are living in harmony and schools are built in the hundreds. What do the killer, the docile and looting Regions learn from this leader and his work? :mrgreen:


gagi
Member
Posts: 627
Joined: 16 Jun 2013, 16:34

Re: What other Regions could learn from Somali Region. Mustefe ..the true leader !

Post by gagi » 05 Aug 2020, 20:11

The traitor TPLF is allergic to harmony between and among peoples.

The ethno fascist TPLF is an antithesis to peace and peaceful coexistence.

TPLF is a criminal cartel. It is a force of evil comprised of people who are chronically suffering from the consequences of a sense of inferiority

The current fight by TPLF is not to regain its control over the central government of Ethiopia. The real intention of these barbarians with a mind of medieval times is to install puppet governments in Addis Ababa and Asmera.

The TPLF traitors should be defeated by all means if peace has to prevail in Ethiopia and the entire Horn!

Za-Ilmaknun
Member
Posts: 4080
Joined: 15 Jun 2018, 17:40

Re: What other Regions could learn from Somali Region. Mustefe ..the true leader !

Post by Za-Ilmaknun » 30 Oct 2020, 20:16

Hopefully Ethiopia will be blessed with such leaders like Mustefe who consider themselves as human beings first. It is anybody's guess what could have happened to Somali Region if the Abdi Illey kinds are still the leaders. PM Abiys should look for such leaders in every corner of the country to help him navigate thru the toxic political culture he inherited from the Nega Dynasty.


Za-Ilmaknun
Member
Posts: 4080
Joined: 15 Jun 2018, 17:40

Re: What other Regions could learn from Somali Region. Mustefe ..the true leader !

Post by Za-Ilmaknun » 04 Dec 2020, 15:03

"After it lost power at the center, the TPLF did everything possible to subvert the reform agenda of the Ethiopian prime minister. It organised an illegal election, sponsored violent groups to disrupt peace in different parts of the country, and finally ordered its forces to attack the Northern Command of the Ethiopian Army. This is why the federal government finds itself in a predicament at this moment."

"The ideology of the TPLF clique has long spread divisiveness and hostility to the detriment of the Tigrayan people and the people of Ethiopia at large. But a new generation of Ethiopians has decided to reject ethnic extremism and conflict and embrace progress and peace. A party like TPLF which lags behind times and does not learn from its mistakes is, at last, harvesting bitter fruits."

https://www.aljazeera.com/opinions/2020 ... -ideology/

Wedi
Member+
Posts: 7993
Joined: 29 Jan 2020, 21:44

Re: What other Regions could learn from Somali Region. Mustefe ..the true leader !

Post by Wedi » 04 Dec 2020, 15:11

Za-Ilmaknun, WOOOW, wonderful concidence!! I am now listening to Ethio 360. The Powerful Ermias is equating Mustefe to the great general Parker

Za-Ilmaknun
Member
Posts: 4080
Joined: 15 Jun 2018, 17:40

Re: What other Regions could learn from Somali Region. Mustefe ..the true leader !

Post by Za-Ilmaknun » 11 Dec 2020, 17:07

ሙስጠፌ እና አብዲልሃፊዝ Hardtalk
(ሙክታሮቪች)

መሰረቱን እንግሊዝ ሀገር ያደረገው ዩኒቨርሳል ቲቪ በሶማሌው ማህበረሰብ ሰፊ ተመልካች ያለው የመገናኛ ብዙሀን ነው። በርካታ ፕሮግራሞች ሲኖሩት ጋዜጠኛ አብዱልሃፊዝ መሀመድ የሚያዘጋጀው የቃለመጠየቅ ዝግጅት በሞጋችነቱ እና ስሱ ጉዳይን አንስቶ በማፋጠጥ አቀራረቡ ዝናን ያተረፈ፣ በርካታ ታዋቂ የፖለቲካ ተክለስብዕና ያላቸው እንግዶች የሚቀርቡበት "ሀርድ ቶክ" አይነት ሾው ነው።

ፕሬዝዳንት ሙስጠፌ ኦማር ከዚህ ሞጋች ጋዜጠኛ ፕሮግራም ላይ እንደሚቀርብ ከተነገረ ጀምሮ በርካቶች በጉጉት ጠብቀውታል። እንደተገመተው የሞቀ፣ ዱላ ቀረሽ፣ በስሜት የተሞላ እና ኋላም በመከባበር የተቋጨ ቆይታ አድርገዋል።

ከዚህ ቀደም እዚህ ምንደር ያጋራሁትን ላላነበቡት መድገሙ መረጥቀኩ። ብታነቡት እንደምታተርፉበት ቅንጣት ያህል አልጠራጠርም።

ወደ ጥያቄ እና መልሱ በቀጥታ ልግባ።

ጋዜጠኛው:

ክቡር ፕሬዝዳንት አቶ ሙስጠፋ ኦማር፣ ለቃለመጠየቅ ፍቃደኛ ስለሆኑ ከልብ አመሰግናለሁ። በርካቶች በተለይ በስልጣን ላይ ያሉ ሰዎች በፕሮግራሜ ላይ ስጋብዛቸው እሺ አይሉኝም። እርስዎ ፍቃደኛ በመሆንዎ ለድፍረትዎና የራስመተማመንዎ ሳላመሰግን አላልፍም።

ወደ መጀመሪያ ጥያቄዬ ልግባ እና ክልሉን እርስዎ ከመምራቶ በፊት የነበረበትን አጠቃላይ ሁኔታ እስቲ ለተመልካቾቻችን ጠቅለል ያለ ምስል ይስጡልን።

ሙስጠፋ:

በአላህ ስም እጅግ ሩህሩህ እጅግ አዛኝ በሆነው እጀምራለሁ መልሴን። እኔም በዚህ በርካታ የተከበሩ ሰዎች ሲቀርቡበት በነበረው ዝግጅትህ ላይ እንደቀርብ ስለተጋበዝኩ አመሰግናለሁ። ፍቃደኛ የሆንኩትም በአንተ ሚዛናዊ እና ሞያዊ ስነምግባር አድናቆት ስላለኝ እና ዩኒቨርሳል ቲቪ የክልላችንን ጉዳይ በዋነኝነት ሲዘግብ ስለነበረ፣ አሁን ያለውን የሽግግርና የለውጥ ሁኔታ ለህዝባችን መረጃ ለመስጠት የእናንተን ፕሮግራም ምርጫዬ ስላደረግኩ ነው።

ወደ ጥያቄህ ስመጣ፣

ክልሉን እኔ ከመረከቤ በፊት የነበረበት ሁኔታ እጅግ ለመናገር በሚከብድ ደረጃ የሶማሌ ህዝብ የተዋረደበት፣ እንደማህበረሰብ ቅስሙ የተሰበረበት፣ የሰውልጅ መሆኑ የተካደበትና ከፍተኛ እንግልት የደረሰበት፣ ከአውሬ ጋር የታሰረበት፣ አካላዊና መንፈሳዊ ማሰቃየቶች የተፈፀመበት፣ ያለፍርድ ሰዎች በአሳቃቂ ሁኔታ የተገደሉበት፣ ሴቶች የተደፈሩበት እንዲሁ በጅምላ ሰዎች በአንድ መቃብር እየተረሸኑ የሚቀበሩበት ክልል ነበረ።

ለአዕምሮ የሚከብዱ ወንጀሎች ተፈፅሟል።

ይህም የአለም ሰብአዊ መብት ተማጋች ድርጅቶችን ሪፖርት፣ የተቀረፁ ምስሎችን ጭምር በማየት ማረጋገጥ ማንም ሰው የሚችለው ነው።

ክልሉን ስንረከብ እንደ መንግስታዊ ተቋም የሚሰሩ የመንግስት መስሪያቤቶች አጠቃላይ የሉም። መዋቅራቸው ፈርሶአል። አጠቃላይ የክልሉ ቢሮክራሲን ሊያቀላጥፉ የሚችሉ መንግስታዊ ድርጅቶች ወድመዋል። በጣም በሚያሳዝን ደረጃ የነበረ ክልልን እና መንፈሱ የተሰበረ ህዝብን ነው ስንመጣ ያገኘነው። እንዲሁ በቀላሉ ተዘርዝሮ የሚያልቅ አይደለም። በእጅጉ የሚያሳዝን የሚያስቆጣ እና የሚያስቆጭ ሁኔታን ነው ያገኘነው።

ጋዜጠኛ:
እርግጥ ነው የገለፁት ሁሉ እውነት ስለመሆኑ፣ ክልሉን በቅርበት ስለምከታተል ልክ ነዎት። ለውጥ መጥትዎ፣ እርስዎ ወደ ስልጣን ከመጡ በኋላ ያሳኳቸው ቁልፍ ተግባራትን እባክዎ ሊዘረዝሩልኝ ይችላሉ?

ሙስጠፋ:

በርካታ ተግባሮችን እና ስኬቶችን በተጨባጭ አስመዝግበናል። ዝርዝሩ ብዙ ነው። ምናልባት ኋላ በሚነሱ ጥያቄዎች ዘርዘር አድርጌ እመለስበታለሁ።

በአጠቃላይ ግን ለማስቀመጥ:

የክልሉ ህዝብን አጠቃላይ ክብር ነው ወደ ቀድሞ ቦታው፣ ወደ የተከበረ እና የሚገባው የነበረ ስፍራ የመለስነው። የወጣቶች ምናብና መንፈስን ነው አድሰን በሀገራቸው ተስፋ እንዲኖራቸው የራስ መተማመን እንዲኖራቸው፣ ማለም እንዲችሉ የተገፈፉትን ሰብአዊ ክብር መልሰን ለሀገር ልማት እንዲተጉ ሞራላቸውን ከፍ አድርገን ምርታማ እንዲሆኑ አስችለናል።

የሶማሌን ህዝብ ክብር በኢትዮጵያ ከፍ እንዲል፣ ሀገራችን ሰላሟ የተጠበቀ እንዲሆን፣ የሶማሌ ህዝብ ሰላም ወዳድ ህዝብ መሆኑን የቀጠናውን ሰላም በማስከበረ ምሳሌ እንዲሆን አድርገናል። በርግጥም የሶማሌ ህዝብ ሀይማኖተኛ፣ ሰው አክባሪ፣ ሰላም ወዳድ፣ ሀገር ወዳድ እንደሆነ እንዲያረጋግጥ እድሉን አመቻችተንለት ለኢትዮጵያም፣ ለምስራቅ አፍሪካም መልካም እሴቱን አሳይተናል። ስርዓት ሲስተካከል ህዝብ የዘመናት የሰላም ጥማቱን በተግባር አሳይቷል። ይህ እኛ በሀላፊነት በቅንነት በሰራነው የተቀናጀ ስራ የመጣ ውጤት ነው።

+—

የሴቶቻችንን ክብር አስጠብቀናል። ከሁሉ በላይ በነፃነት መኖርን፣ ያለፍራቻ ወጥቶ መግባትን በክልሉ አስፍነናል።
እስከ ሶስተኛ ዲግሪ ድረስ የተማሩ የክልሉ የተማሩ ሰዎች፣ በመማራቸው እና በማወቃቸው መከበር ሲገባቸው የሚሸማቀቁበትን ስርዓት ለውጠን እውቀታቸውን ለማህበረሰባቸው እንዲያውሉ አስችለናል። ወደ ህዝብ አገልግሎት ስንጠራቸውም በችሎታ እና በችሎታ ብቻ መስፈርት ባደረግነው መሰረት አካታች የሆነ የሲቪል ሰርቪስ ስራን ተግባራዊ አድርገናል።

ከፈቀድክልኝ ትንሽ የማክለው ደግሞ

ከዚህ ቀደም በአብዲሌ የዘረፋ ቡድን የተዘረፉ መሬቶች እና ያለህግ የተዘረፉ ንብረቶችን አስመልሰናል ለህዝብ። የህዝቡን ንብረት መዝረፍ የሚባል ነገር ተወግዷል። በጥቅም ትስስር እና በሞኖፖሊ የመንግስትን ስልጣን በመጠቀም ይደረግ የነበረውን የኢኮኖሚ የበላይነት ለአንድ ወገን ማመቻቸትን አስቀርተናል።

በተለይም የሰራነው ቁልፍ ተግባር፣ የሶማሌን ህዝብ ጥያቄ ወደ መሀል ሀገር ወስደን ከሀገሩ ሀብት በፍትሃዊነት የሚገባውን እንዲጠይቅ ወክለነው የሚያኮራ ስራ ሰርተናል። የሶማሌ ህዝብ መሰረታዊ ጥያቄን ወደ መሀል ሀገሪቱ አጠቃላይ ፖለቲካ አምጥተን በመሞገት ከተፈጥሮ ሀብቱ የሚጠቀምበትን መንገድ በእስትራቴጂ እና በእውቀት ታግዘን በኩራት አቅርበናል። በዚህም የኢትዮጵያውያንን ክብር እና ፍቅር አረጋግጠናል። የሶማሌ ህዝብ የሚገባውን ክብር እንዲያገኝ፣ የፖለቲካው የዳር ተመልካች ሳይሆን የመሀል ተጫዋች እና በሚወሰኑ ውሳኔዎች ድምፅ ሆነነዋል።

+—

በመሰረተ ልማት ደረጃም በርካታ ተግባሮች ጀምረናል። የተጠናቀቁ እና በጅምር ላይ ያሉ በርካታ ናቸው። የክልላችን ህዝብ ዋነኛ ችግር መንገድ እንደሆነ ግልፅ ነው። በህጋዊ መንገድ ስርአታቸውን ጠብቀው ሰባት ረጃጅም ደረጃ አንድ አስፋልት ተጀምረዋል። እንግዲህ እነዚህ ፕሮጄክቶች ሲጠናቀቁ የምንመሰገንበት እንደሚሆን አምናለሁ። አየህ፣ መሰረተ ልማት ጊዜን ይወስዳል። ፍሬው ለመታየት ጥቂት አመታት ሊወስድ ይችላል። ለፖለቲካ ትርፍ አያገለግልም። ለሀገር ለወገን የሚሰራ ነው።

ወደ ሰላሳ ከተሞች የሀያአራት ሰዓት መብራት አስገብተናል። የጤና ሴክተሩንም ለማሻሻል ከዚህ ቀደም ከፌዴራል የሚላክልንን ብቻ የምንጠብቀው አሁን 150 አምቡላንሶችን በራሳችን ወጪ ገዝተን ለራቅ ራቅ ላሉ ወረዳዎች አስረክበናል።

ወደ 450 ት/ቤቶችን አስሩ ከፍተኛ ደረጃ ትምህርቤት፣ ሶስት ቴክኒክ ኮሌጅ ሰርተናል።
ወረዳን ከወረዳ የሚያገናኝ መንገድ፣ የከተሞች የውስጥ መንገዶችን አሰርተናል።

አዲስ ሆስፒሎች እና እየታደሱ ያሉ ሆስፒታሎች፣ የደንብ ባንኮች፣ የፓርላማ ህንፃ እና የዞነን አስተዳደሮችን ህንፃዎች በአመት ከስምንት ወር ቆይታችን ውስጥ እያሰራን ነው። እውነት ለመናገር በአስር የመጨረሻ ወራት ከፍተኛ ስራዎችን አከናውነናል። ፖለቲካውን ካረጋጋን በኋላ ሰላም ካሰፈንን በኋላ የሰራነው ብዙ ነው።

ዝርዝሩ ብዙ ነው። የክልሉን የፀጥታ ሀይልን መልሰን በማደራጀት ተኣምር ሰርተናል። ከሁሉ በላይ ለልማት አመቺ የሆነውን ሰላም በክልሉ እውን ማድረጋችን ትልቁ ስኬታችን ነው።

ጋዜጠኛ:

በዘረዘሩልኝ ስኬቶች ላይ የማነሳቸው ጥያቄዎች አሉኝ። ከዚያ በፊት፣ ከጠቅላይ ሚኒስቴር ዶክተር አብይ አህመድ ጋር ያላችሁ ግኑኝነት እንዴት ነው?

ሙስጠፋ:

ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር መልካም ግኑኝነት ነው ያለን። በሀገሪቱ ህገመንግስት በተቀመጠው የፌዴራል እና የክልል የአሰራር እና የግኑኝነት ስርዓትና ደንብ ነፃነታችን ተጠብቆልን ነው የምንሰራው። አሁን ደግሞ በአንድ ፓርቲ፣ ብልፅግና፣ ስር በፓርቲ ደረጃ ስለምንሰራ መልካም የሆነ ገንቢ የሆነ ግኑኝነት ነው ያለን።

ጋዜጠኛ:

ካነሱት አይቀር ይህ የብልፅግና ፓርቲ ነገር፣ በርካቶች ጥያቄ ያነሱበታል። የሶማሌ ህዝብን መብት ያስጨፈልቃል እያሉ አስተያየት የሚሰጡ አሉ። ክብር ፕሬዝዳንት፣ ብልፅግና ስትባሉ፣ የተባለው ብልፅግና እውነትም ብልፅግና ስለመሆኑ በምን አረጋግጠው አመኑ? በፓርቲዎ ውስጥም ከፍተኛ የሆነ የፖለቲካ ሽኩቻ እና እስር ተካሂዷል፣ ከምዕራብ ሶማሌ ህዝብ ፓርቲ ጋርም ግጭት ውስጥ ገብታቹሀል።

ሙስጠፋ:
አንድ በአንድ ዘርዘር አድርጌ እንድመልስልህ ጥያቄዎችህን በቅደም ተከተል አስቀምጥልኝ።

ጋዜጠኛው:
እሺ ከብልፅግና ፓርቲ እንጀምር

(ሙግቱ ተጀመረ! በክፍል ሁለት እመለስበታለሁ። #ሼር ያድርጉ)

ክፍል ሁለት ከፍተኛ ሙግት የታየበት ነው። እመለሳለሁ።

Za-Ilmaknun
Member
Posts: 4080
Joined: 15 Jun 2018, 17:40

Re: What other Regions could learn from Somali Region. Mustefe ..the true leader !

Post by Za-Ilmaknun » 18 Dec 2020, 19:53

የትህነግ ቡድን የሕልውናው መሰረት በብሔረሰቦች መካከል ክፍፍልና ግጭት መፍጠር እንደነበር የሱማሌ ክልል ምክትል ርእሰ መሥተዳድር ሙስጠፌ መሐመድ ገለፁ፡፡

የትህነግ ቡድን በተለያዩ ክልሎች ግጭት እንዲነሳ ሲያደርግ እንደነበር ርእሰ መሥተዳድሩ ተናግረዋል፡፡

ቡድኑ በተለይ በአማራና ኦሮሞ መካከል ልዩነት እንዲኖር በዋናነት ሲሰራ እንደነበርም አቶ ሙስጠፌ ገልፀዋል፡፡

በሱማሌና በኦሮሞ ብሔረሰቦች መካከል ተፈጥሮ የነበረው ግጭትም የዚህ የትህነግ ተግባር አካል እንጂ ብሔረሰቦቹ ለዘመናት አብረው በሰላም የኖሩ ናቸው ብለዋል ምክትል ርእሰ መሥተዳድሩ፡፡

ቡድኑ በሌሎች ክልሎች ግጭት እንዲባባስ የተለያዩ ድጋፎችን በማድረግና ትግራይ ክልል ውስጥ ግጭትን እንዲኖር የሚያደርግ አካል ባለመኖሩ ትግራይ ሰላማዊ ሆኖ እንዲታይ በማድረግ የ27 ዓመት የስልጣን ዘመኑ በሃገሪቱ ከመጣው ሪፎርም የተሻለ መሆኑን ለማሳየት ጥረት ሲያደርግ ነበር ብለዋል አቶ ሙስጠፌ፡፡

የትህነግ ቡድን ለ27 በዓመታት በኢትዮጵያ ህዝቦች ላይ የፈጸመው ወንጀል ይቅርና በቅርቡ በማይካድራ የፈጸመው ወንጀል ብቻ እንደ ዓለም አቀፍ ሽብርተኛ እንዲፈረጅ ያደርገዋል ማለታቸውን ኢብኮ ዘግቧል፡፡

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በፌስቡክ https://bit.ly/2UwIpCw
ዩቱዩብ https://bit.ly/2HYJBLZ
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m

TGAA
Member+
Posts: 5625
Joined: 07 Apr 2019, 20:34

Re: What other Regions could learn from Somali Region. Mustefe ..the true leader !

Post by TGAA » 18 Dec 2020, 20:12

There is a lot the sick children of Ethiopia Oromia and Beshangul can learn from enlightened leadership like that of Mustefe.


Za-Ilmaknun
Member
Posts: 4080
Joined: 15 Jun 2018, 17:40

Re: What other Regions could learn from Somali Region. Mustefe ..the true leader !

Post by Za-Ilmaknun » 18 Feb 2021, 20:48

Not only leadership but human kindness is exemplified by Mustefe.


TGAA
Member+
Posts: 5625
Joined: 07 Apr 2019, 20:34

Re: What other Regions could learn from Somali Region. Mustefe ..the true leader !

Post by TGAA » 18 Feb 2021, 21:52

He is the future. Whatever dinar Egypt is throwing your way -- your snail brain can't do anything the solidification of Ethiopian nationalism. The more it is tested by fire its iron nature calcifies. And one by one it takes down its enemies -- you weak jelly can't do anything about it. Ethiopian are alphas -- what is left is your chatty girly talk-- keep on mumbling.

Post Reply