Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Post Reply
tarik
Senior Member
Posts: 18343
Joined: 26 Feb 2016, 13:04

Photo Of: Atse Menelik Was Z 1st African Leader 2 Drive A Car @ Z Same Time Agame Yohanes Walked Bare-feet!!!WEEY GUUD!!

Post by tarik » 30 Jul 2020, 15:25

. BTW: THIS WAS IN 1907.
:lol:
Last edited by tarik on 30 Jul 2020, 16:30, edited 1 time in total.

Wedi
Member
Posts: 803
Joined: 29 Jan 2020, 21:44

Re: Photo Of: Atse Menelik Was Z 1st African Leader 2 Drive A Car @ Z Same Time Agame Yohanes Walked Bare-feet!!!WEEY GU

Post by Wedi » 30 Jul 2020, 15:37

ዳግማዊ አጼ ምኒልክና ኢትዮጵያን ዘመናዊ የማድረግ ሕልም !

ዘመናዊ የአስተዳደር ተቋም የካቢኔት ሹመትን የጀመሩት ምኒልክ ናቸው ። በዚያን ግዜ ድርጊታቸውን የሚነቅፉ ተቃዋሚዎች ቢበዙባቸውም ራሳቸው እንደ ተራው ሰው ወርደው ላይ ታች በማለት ወፍጮ እያስፈጩ ፣ መኪና እየነዱ ፣ በስልክ እያወሩና የመሳሰሉትን እያደረጉ ህዝባቸው እንዲለምድ ብዙ ደክመዋል ።

ዳግማዊ አጼ ምኒልክ ታጋሽ አስተዳደር አዋቂ ሕዝብን በብቃትና ዘመናዊ በሆነ መልኩ ለማስተዳደር የሚችሉ መሆናቸው ይነገራል ፤ በተጨማሪም እርቅ በማድረግ ፣ በመደራደርና ችግሮችን በመፍታት ያምናሉ ። ሁልጊዜም ተዋግተው ድል ካደረጓቸው ጋር እርቅ አድርገው ተስማምተው ከተለያዩ ሹማምንቶች ጋር በአንድነት ኖረዋል ። ዳግማዊ አጼ ምኒልክ የግል ንብረት በመሰብሰብ የሚያምኑ መሪ አልነበሩም ። በዘመናቸው ከቤተመንግሥት ውጭ በስማቸው የተመዘገበ ርስት ስለሌላቸው ለልጆቻቸው ያወረሱት ምንም ንብረት አልነበረም ። ዳግማዊ አፄ ምኒልክ ሲለፉና ሲደክሙ የነበረው ግን ኢትዮጵያ በባእድ ወራሪዎች እንዳትደፈርና ከውጭው ዓለም እኩል በዘመናዊነትና በቴክኖሎጂ እንድትጓዝ ነበር ።

ዳግማዊ አጼ ምኒልክ በንግስና ዘመናቸው ኢትዮጵያን ዘመናዊ ለማድረግ ከነበራቸው ሕልምና ከተገበሯቸው ብሔራዊ ተግባራት በጥቂቱ እነሆ : –

☞ ስልክ ውጭ በተሰራ በ12 አመቱ አዚህ አስመጡ በ 1882
☞ ፖስታ ቤት በመክፈት በ 1896
☞ የሕትመት መሣሪያ ማስመጣት በ 1898
☞ የጥይት ፋብሪካ ማቋቋም በ 1899
☞ የማዕድን ፍለጋ ፕሮጀክት በ 1894
☞ የትራንስፖርትና የመገናኛ አውታሮችን ማቋቋም ( የባቡር መሥመር ዝርጋታ ከጅቡቲ – አዲስ አበባ) በ 1893
☞ ዘመናዊ ገንዘቦችን አስቀርጾ ማውጣትና ባንኮችን መክፈት በ 1898
☞ ገንዘብ መቅረጫ ማሽን አስመጥተው ሥራ ላይ ማዋል
☞ የክትባት መድሐኒት
☞ የኤሌትሪክ መብራት በመዘርጋት በ 1889
☞ የመንገድ የድልድይና የሕንፃ ሥራዎች ግንባታ በ 1896
☞ የሸክላ ፋብሪካ ማቋቋም
☞ ቶሎ የሚደርስ ልዩ የዛፍ ዘር አስመጥቶ መትከል በ 1886
☞ ዘመናዊ የከብት ማዳቀል እርባታ ሥራን ማስጀመር
☞ የሕክምና ተቋም ዘመናዊውን መድሃኒት አቀነባብሮ መጠቀም በ 1889
☞ ሆስፒታል በመጀመር በ 1890
☞ መድሃኒት መሸጫ ሱቅ ( pharmacy ) በመክፈት በ 1904
☞ የጽሕፈት መኪና በማስመጣት በ 1887
☞ ሲኒማ በመክፈት በ 1889
☞ የሙዚቃ ትምህርት ቤት በመክፈት በ 1887
☞ የመጠጥ ውሃ ቧንቧ ዝርጋታንና የጉድጓድ ውሃዎች ማደራጀት በ 1886
☞ የመጀመርያውን ጋዜጣ ” አእምሮ እና ጎህ ” በማሳተም በ1900
☞ የታርጋ ቁጥሯ D3130 የሆነች አውቶሞቢል በማስመጣትና ራሳቸው በመንዳት በ 1900
☞ ዘመናዊ ሆቴል ማቋቋም በ 1898
☞ የዲኘሎማቲክ ግንኙነትን በአቻነት ደረጃ አጠናክሮ መቀጠል
☞ የንግድ ግንኙነት ( ከውጭ አገሮች ጋር )
☞ የወሰን ክልል ስምምነት መፈረም
☞ በቂ ሕክምና ባልተገኘበት አጋጣሚ ማንም ሠው ታሞ ሲዳከም 48 ሠአት ሳይሆነው ሞተ ተብሎ በችኮላ እንደይገነዝ የሚያደርግ ደንብ አውጥቶ በሥራ ላይ ማዋል
☞ ባርነትን ማውገዝ እና በሕግ መከልከል
☞ በእየሩሳሌም ገዳም የኢትዮጵያ ይዞታ የነበረውን አርመን ፅርዓውያንና ግብፃውያን ስለአጣበቡት ከቱርክ ንጉሥ ከሡልጣን አብዱል ሂሚድሃን ጋር መልእክቶችን ተላልከው የአባቶችን ይዞታ ማስከበርና ማስፋፋት
☞ ለአዲስ አበባ ከተማ የመጀመሪያውን የሠፈራ ማስተር ፕላንና የቦታ አስተዳደር ደንብ ማውጣት
☞ የድንጋይ ከሠል ማዕድንን ማግኘትና ወዘተ ….ከብዙ ጥቂቶቹ ናቸው ።

ምኒልክ ተወልዶ ባያነሳ ጋሻ
ግብሩ እንቁላል ነበር ይህን ግዜ አበሻ
በሰራው ወጨፎ ባመጣው እርሳስ
ተፈጠመ ጣልያን አበሻ እንዳይደርስ
ምኒልክ ተጉዞ የምትጠይቁኝ
ፊትም አላለፈ ኋላም አይገኝ ።
ታላቅ ክብር ለእምዬ ምኒልክ ይሁን !

ዋቢ መጽሐፍት : – ” አጤ ምኒልከ ” በጳውሎስ ኞኞና ከነጋድራስ ገብረሕይወት ባይከዳኝ ስራዎች


gagi
Member
Posts: 266
Joined: 16 Jun 2013, 16:34

Re: Photo Of: Atse Menelik Was Z 1st African Leader 2 Drive A Car @ Z Same Time Agame Yohanes Walked Bare-feet!!!WEEY GU

Post by gagi » 30 Jul 2020, 16:14

ትክክል እኒህ ናቸው ታላቁ ምኒልክ::

በዓለም ታሪክ የተቀዳጁት ትልቅ ስፍራ ንቅንቅ የማይለው እምዬ ምኒልክ

ምድረ ባንዳ የፈለገውን ቢቀባጥር ቢወራጭ የእምዬ ተግባርና ክብር ስንዝር ያህል አይቀንስም

Za-Ilmaknun
Member
Posts: 1876
Joined: 15 Jun 2018, 17:40

Re: Photo Of: Atse Menelik Was Z 1st African Leader 2 Drive A Car @ Z Same Time Agame Yohanes Walked Bare-feet!!!WEEY GU

Post by Za-Ilmaknun » 30 Jul 2020, 18:05

King Minilik was one of a kind. He had done more for the country than all previous regimes combined. Great respect!!

Post Reply