Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Revelations
Senior Member+
Posts: 33724
Joined: 06 Jan 2007, 15:44

[የእለቱ ሰባራ ዜና] ትጥቅ ማውረዳቸው ባይታወቅም እሳቸው ከስልጣን መውረዳቸው ተሰምቷል

Post by Revelations » 27 Jul 2020, 10:01

ማነው ወራጅ:- ኦቦ ዳውድ ኢብሳ
ማነው አውራጅ:- ዝርዝር አለን ተረጋግተው ይጥብቁ!

Wedi
Member+
Posts: 7989
Joined: 29 Jan 2020, 21:44

Re: [የእለቱ ሰባራ ዜና] ትጥቅ ማውረዳቸው ባይታወቅም እሳቸው ከስልጣን መውረዳቸው ተሰምቷል

Post by Wedi » 27 Jul 2020, 10:10

ዳውድ ኢብሳ ጡረታ ወጣ ነው የምትለኝ?? :oops: :oops:

Revelations
Senior Member+
Posts: 33724
Joined: 06 Jan 2007, 15:44

Re: [የእለቱ ሰባራ ዜና] ትጥቅ ማውረዳቸው ባይታወቅም እሳቸው ከስልጣን መውረዳቸው ተሰምቷል

Post by Revelations » 27 Jul 2020, 10:30

Wedi wrote:
27 Jul 2020, 10:10
ዳውድ ኢብሳ ጡረታ ወጣ ነው የምትለኝ?? :oops: :oops:
ለደህንነታቸው ሲባል ስልካቸው በቴሌ በመቆለፉ የወደፊት እቅዳቸውን ልንጥይቃቸው አልቻልንም:: ግና እንደታጠቁ ጡረታ አለ ወይይይይይ?!

Wedi
Member+
Posts: 7989
Joined: 29 Jan 2020, 21:44

Re: [የእለቱ ሰባራ ዜና] ትጥቅ ማውረዳቸው ባይታወቅም እሳቸው ከስልጣን መውረዳቸው ተሰምቷል

Post by Wedi » 27 Jul 2020, 10:40

Revelations wrote:
27 Jul 2020, 10:30
ለደህንነታቸው ሲባል ስልካቸው በቴሌ በመቆለፉ የወደፊት እቅዳቸውን ልንጥይቃቸው አልቻልንም:: ግና እንደታጠቁ ጡረታ አለ ወይይይይይ?!
የዳውድ ኢብሳ ነገር እኮ በጣም የሚገርም ነው፡፡ በቃ "ማነው ትጥቅ አስፈች፣ ማነውስ ትጥቅ ፈች" አንዳሉ እንደዛቱ ከነ ሙሉ ትጥቃቸው ጥሩታ ወጡ ማለት ነው? :roll: :roll:

Revelations
Senior Member+
Posts: 33724
Joined: 06 Jan 2007, 15:44

Re: [የእለቱ ሰባራ ዜና] ትጥቅ ማውረዳቸው ባይታወቅም እሳቸው ከስልጣን መውረዳቸው ተሰምቷል

Post by Revelations » 27 Jul 2020, 10:46

የአስወራጆቹን ስም ይቆይና የአውራጆቹን ስም እናስቀድም

ኢብሳ ነገዎ (የአውራጆች መሪ)
ቶሌራ አዳባ
አቶምሳ ኩምሳ
ቀጀላ መርዳሳ
አራርሶ ቢቂላ (ስልጣን ተረካቢ)
ጃዊሳ ጋቢሳ
ሚኪያስ ኢርቆ
ዋቆ ኩኔ

Revelations
Senior Member+
Posts: 33724
Joined: 06 Jan 2007, 15:44

Re: [የእለቱ ሰባራ ዜና] ትጥቅ ማውረዳቸው ባይታወቅም እሳቸው ከስልጣን መውረዳቸው ተሰምቷል

Post by Revelations » 27 Jul 2020, 11:02

ንኡስ አስወራጆች (ከኦዲፍ - ODF)

ኦቦ ሌንጮ ለታ (የቀድሞ ኦኔግ መሪ)
ኦቦ ሌንጮ ባቲ (የቀድሞ ኦኔግ መሪ)
ኦቦ በያን አሶባ (የቀድሞ ኦኔግ መሪ)

Wedi
Member+
Posts: 7989
Joined: 29 Jan 2020, 21:44

Re: [የእለቱ ሰባራ ዜና] ትጥቅ ማውረዳቸው ባይታወቅም እሳቸው ከስልጣን መውረዳቸው ተሰምቷል

Post by Wedi » 27 Jul 2020, 11:06

Revelations wrote:
27 Jul 2020, 11:02

ኦቦ ሌንጮ ባቲ (የቀድሞ ኦኔግ መሪ)

ሌንጮ ባቲ በውጭ ጉዳይ በኩል የአብይ አሀመድ ከፍተኛ አማካሪ ሆኖ እየሰራ ያለ ሰው እኮ ነው፡፡ አንድ ሰው በአንድ ግዜ የሁለት ፓርቲ አገልጋይ ሊሆን ይቻላል? Conflict of interest? :oops:

Abere
Senior Member
Posts: 11071
Joined: 18 Jul 2019, 20:52

Re: [የእለቱ ሰባራ ዜና] ትጥቅ ማውረዳቸው ባይታወቅም እሳቸው ከስልጣን መውረዳቸው ተሰምቷል

Post by Abere » 27 Jul 2020, 11:15

አሁን አቶ ዳውድ ዒብሣ በህግ ያለመከሰስ መብቱ ተገፏል ወይስ አልተገፈፈም? ከነ ጦር መሣሪያው ጡረታ እንዴ ወጣ በህግ ያለመጠየቅ መብቱም አብሮት ጡረታ ወጥቷል ማለት ነው? መልከ ጥፉን በስም ይደግፉ ይባላል ዐብይ ሀቀኛ ከሆነ ለምን ኦነግ የሚባል ትርጉም ዐልባ የጥፋት ድርጅት አይዘጋም። የዓሣ ግማቱ ከጭንቅላቱ - ከታች አስከ ላይ ድረስ ያለው ትርጉም ዐልባው ኦነግ ነው። ዳውድ ዒብሳ ብቻውን አይደለም።

Revelations
Senior Member+
Posts: 33724
Joined: 06 Jan 2007, 15:44

Re: [የእለቱ ሰባራ ዜና] ትጥቅ ማውረዳቸው ባይታወቅም እሳቸው ከስልጣን መውረዳቸው ተሰምቷል

Post by Revelations » 27 Jul 2020, 11:28

ዋና አስወራጆች

ጠቅላይ ኮሎነል አቢይ አህመድ
ኦቦ መከላከያ ለማ መገርሳ
ኦቦ አባዱላ ገመዳ

Wedi
Member+
Posts: 7989
Joined: 29 Jan 2020, 21:44

Re: [የእለቱ ሰባራ ዜና] ትጥቅ ማውረዳቸው ባይታወቅም እሳቸው ከስልጣን መውረዳቸው ተሰምቷል

Post by Wedi » 27 Jul 2020, 11:33

Revelations ዋናው ጥያቄ አሁን እነዚህ አስወራጆች ኦነግ ሸኔን እና ኮማንደር ጃል ማሮን ምንድን ነው የሚያደርጉት? :roll: :roll:

Revelations
Senior Member+
Posts: 33724
Joined: 06 Jan 2007, 15:44

Re: [የእለቱ ሰባራ ዜና] ትጥቅ ማውረዳቸው ባይታወቅም እሳቸው ከስልጣን መውረዳቸው ተሰምቷል

Post by Revelations » 27 Jul 2020, 14:30

Abere wrote:
27 Jul 2020, 11:15
አሁን አቶ ዳውድ ዒብሣ በህግ ያለመከሰስ መብቱ ተገፏል ወይስ አልተገፈፈም? ከነ ጦር መሣሪያው ጡረታ እንዴ ወጣ በህግ ያለመጠየቅ መብቱም አብሮት ጡረታ ወጥቷል ማለት ነው? መልከ ጥፉን በስም ይደግፉ ይባላል ዐብይ ሀቀኛ ከሆነ ለምን ኦነግ የሚባል ትርጉም ዐልባ የጥፋት ድርጅት አይዘጋም። የዓሣ ግማቱ ከጭንቅላቱ - ከታች አስከ ላይ ድረስ ያለው ትርጉም ዐልባው ኦነግ ነው። ዳውድ ዒብሳ ብቻውን አይደለም።
My friend, that kind of policy only apply in western democracies. In Ethiopia, whoever is in power arrests whomever they want. And Obo Daud Ibssa wasn't going for democracy either. The all fit together just fine. ለማንኛውም ግን ኦቦ ዳውድ እቤታቸው ተቀምጥው ደህንነታቸው በወታደር እየተጠበቀ ነው:: ጃል መሮ እስኪመጣን የጥበቃውን ስራ እስኪረከብ ድረስ::

Revelations
Senior Member+
Posts: 33724
Joined: 06 Jan 2007, 15:44

Re: [የእለቱ ሰባራ ዜና] ትጥቅ ማውረዳቸው ባይታወቅም እሳቸው ከስልጣን መውረዳቸው ተሰምቷል

Post by Revelations » 27 Jul 2020, 14:46

Wedi wrote:
27 Jul 2020, 11:33
Revelations ዋናው ጥያቄ አሁን እነዚህ አስወራጆች ኦነግ ሸኔን እና ኮማንደር ጃል ማሮን ምንድን ነው የሚያደርጉት? :roll: :roll:
There is no OLF-Shene. There's only OLF and it now has a new leader. Will Jal Maroo fall inline accept the new leadership or not? That's the question.

Revelations
Senior Member+
Posts: 33724
Joined: 06 Jan 2007, 15:44

Re: [የእለቱ ሰባራ ዜና] ትጥቅ ማውረዳቸው ባይታወቅም እሳቸው ከስልጣን መውረዳቸው ተሰምቷል

Post by Revelations » 27 Jul 2020, 18:12

Please wait, video is loading...

Revelations
Senior Member+
Posts: 33724
Joined: 06 Jan 2007, 15:44

Re: [የእለቱ ሰባራ ዜና] ትጥቅ ማውረዳቸው ባይታወቅም እሳቸው ከስልጣን መውረዳቸው ተሰምቷል

Post by Revelations » 28 Jul 2020, 07:02

ነገር ግን የግንባሩ ሊቀ መንበር በከተማው ውስጥ እያሉ፣ በሚመሩት ድርጅት ስብሰባ ላይ ሳይገኙ ውይይቱን ስለማድረጋቸውና አቶ ዳውድ ስለስብሰባው የሚያውቁት ነገር ስለመኖሩ ከቢቢሲ ለተጠየቁት ጥያቄ አቶ አራርሶ መልስ ሰጥተዋል።

“አቶ ዳውድ የተለየ ጉዳይ ስለገጠማቸው እየተንቀሳቀሱ የዕለተ ከዕለት ሥራቸውን ማከናወን አልቻሉም። ስለዚህም ስብሰባችን ላይ መገኘት አልቻሉም” ብለው፤ ይሁን እንጂ ስለ ጉዳዩ ከአቶ ዳውድ ጋር ተነጋግረውበት እንደነበር ገልጸዋል።

ጨምረውም፤ ስብሰባው እንዲካሄድ የሊቀ መንበሩን ይሁንታ እንዳገኙ በመጥቀስ “ውይይታችንን ሳንጨርስ ኔትዎርክ ተቋርጦ ነበር። ነገር ግን የድርጅቱ ከፍተኛ አመራር [ጉሚ ሰባ] ተሰብስቦ እንዲመክር ተስማምተን ነበር” ብለዋል።

ዋናው ሊቀ መንበር ባለመገኘታቸው በምክትሉ የሚመራ አይነት ሰብሰባ መካሄዱን በመግለጽ፤ በዚህም ሊቀ መንበሩን ጨምሮ “ምንም አይነት ሹም ሽር አልተካሄደም” ሲሉ አስረግጠው ተናግረዋል።

አቶ አራርሶ ቢቂላ ይህንን ይበሉ እንጂ የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ቢሮ ኃላፊ የሆኑት ገዳ ኦልጅራ (ዶ/ር) ግን የተካሄደውን ስብሰባ በተመለከተ የተለየ ሃሳብ እንዳላቸው ለቢቢሲ ተናግረዋል።

"ትናንት በአቶ አራርሶ ቢቂላ የተመራው ሰብሰባ የድርጅቱ እውቅና የለውም” በማለት ስብሰባው በግንባሩም ሆነ በሊቀ መንበሩ የማይታወቅ መሆኑን ለቢቢሲ ገልጸዋል።

አቶ አራርሶ፤ ከአቶ ዳውድ ስብሰባ ለማካሄድ ፍቃድ እንደተሰጣቸው ተናግረው ስብሰባ ሲጠሩ፤ ገዳ (ዶ/ር) ወደ አቶ ዳውድ እንደደወሉና፤ አቶ ዳውድ ስለ ስብሰባው መረጃ እንዳልደረሳቸው እንደገለጹላቸው ተናግረዋል።

ያለ ድርጅቱ ሊቀ መንበር እውቅና ስብሰባ ማካሄድ ተገቢ አይደለም ብለው ለስብሰባ የሄዱ ሰዎችን እንደከለከሉ ገልጸው፤ “ሲከለከሉ የታጠቁ የመንግሥት አካላትን ይዘው መጥተው፣ በጉልበት ገብተው ነው ስብሰባቸውን ያካሄዱት። ስብሰባው ሕጋዊ አልነበረም” ብለዋል።

ገዳ (ዶ/ር) አያይዘውም ስብሰባው ላይ የተነሱ አጀንዳዎችን እንደማያውቁ ተናግረዋል።

በስብሰባው ሹም ሽር ተካሂዶ፤ በአቶ ዳውድ ምትክ አቶ አራርሶ ሊቀ መንበር ሆነዋል የሚል ወሬ እንደተናፈሰ ጠቅሰን፤ እውነት ስለመሆኑ ሲጠየቁም እሳቸውም ተጨባጭ መረጃ እንዳልደረሳቸው አስረግጠው፤ “ከወሬ ያለፈ አይመስለኝም። ለዚያ የሚያበቃ ስብሰባ አይደለም” ብለው ምላሽ ሰጥተዋል።

ቢቢሲ ካናገራቸው የኦሮሞ ነጻነት ግንባር አመራር አባላት በተጨማሪ ለተለያዩ መገናኛ ብዙሃን ስለተፈጠረው ነገር የሚሰጡት ማብራሪያ እርስ በርሱ የሚቃረን ሲሆን ግለሰቦች ከሚሰጡት ምላሽ ውጪ እስካሁን ከግንባሩ ተሰጠ መግለጫ የለም።

ሊቀመንበሩ ከአቶ ዳውድ ኢብሳ ከመኖሪያቸው መውጣት እንዳልቻሉ እንዲሁም የስልክ ግንኙነት ስለሌላቸው በድርጅቱ ውስጥ እተካሄደ ስላለው ነገር ቁርጥ ያለ ነገር ለመስማት አልተቻለም።

Revelations
Senior Member+
Posts: 33724
Joined: 06 Jan 2007, 15:44

Re: [የእለቱ ሰባራ ዜና] ትጥቅ ማውረዳቸው ባይታወቅም እሳቸው ከስልጣን መውረዳቸው ተሰምቷል

Post by Revelations » 28 Jul 2020, 16:19

Please wait, video is loading...

Post Reply