Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Horus
Senior Member+
Posts: 30915
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

አቢይ አህመድ ብሄራዊ ጦሩን በማዘዝ አገር ካላረጋጋ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ወታደራዊ መንግስት ያውጃል

Post by Horus » 26 Jul 2020, 00:05

የዛሬውን የጦር አዛዥ መግለጫ ልብ ብሎ ለሰማው የሚለው ይህ ነው። የፖለቲካ ቡድኖች በተጣሉ እና ህዝብ እየቀሰቀሱ ስርዓት ባፈረሱ ቁጥር የኢትዮጵያ ጦር ሰራዊት እየፈረሰው አይበታተንም ። ልክ ዎያኔ እንዳደረገው ። መከላከውያው ሌላ ስራ የለውም። ኦነግ እና አቢይ ሲነታረኩ አገር ቢፈርስ ተመልሶ ለማኝ የሚሆን የሰራዊቱ አባል ነው ። ስለዚህ አለምንም ጥርጥር አቢይ ህግና ሰርዓት ማረጋገጥ ካልቻለ አለምንም ጥርጥር ወታደሩ መንግስት ይዞ ፓርቲዎችን ሁሉ እስር ቤት ይከትታል። ይህ ሳይንስ ነው። ወታደሩ ኮርፖሬት ጥቅም አለው ። የራሱ የሆነውን የህልውና መሰረቱ የሆነውን የሰራዊቱ ድርጅት ቀጣይነት ማረጋገጥ ግድ ይለዋል ። ለዚህ ነው አቢይ ምን ግዜም የመከላከያውን ሙሉ ድጋፍ ያለው ። ለዚህም ነው ከዚህ በኋላ መንግስት በአመጽ አፈርሳለሁ የሚል ሁሉ የወታደሩን ጥይት የሚቀምሰው ። እንደ ጃዋር እና ገርባ ያሉ የፖለቲካ መሃይሞች የማይገባቸው ይህን መሰሉን የፖለቲካ ሳይንስ ነው ። ከላይ የጠቀስኩት ሚሊታሪ ኮርፖሬቲዝም ከአራቱ አንዱ የኪዴታ ምክኛቶችና ሞዴሎች ነው፣ ባጭሩ !

Tiago
Member
Posts: 2053
Joined: 30 Jul 2018, 02:09

Re: አቢይ አህመድ ብሄራዊ ጦሩን በማዘዝ አገር ካላረጋጋ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ወታደራዊ መንግስት ያውጃል

Post by Tiago » 26 Jul 2020, 01:30

The role of military in the affairs of internal security matter is most important.
Military is the only institution in the country that defends the country from the internal
threats. The military institutions are responsible for the safety of state and watching the
country from different sides. in light of these ,if PM Abiy is not taking firm action against
TPLF ,OLF and Querro trouble makers ,the military should step in (not military coup).
I would like to see provisional military admin and the likes of Jawar to face martial
law.Ethiopia really needs strong men .personally I find the PM to be soft as well as an
impostor,that is why Ethiopia got itself in these mess in the first place
.

Horus
Senior Member+
Posts: 30915
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: አቢይ አህመድ ብሄራዊ ጦሩን በማዘዝ አገር ካላረጋጋ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ወታደራዊ መንግስት ያውጃል

Post by Horus » 26 Jul 2020, 02:15

Tiago,
አንተ እንደ ምትለው አንድ ሚሊታሪ ራሱ ገዢ ለመሆን የሚፈልግ ጄኔራል ወታደሩን አስተባብሮ ስልጣን ለመያዝ ኩዴታ ያደርጋል ። የሚሰጠው ምክኒያ ሁልጊዜ የፖልለቲካ መሪዎች ባልገዋል ወይም አልቻሉም የሚል ነው። ያ ሌላ አይነት የኪዴታ ምክ ን ያት ነው። እኔ ከላይ ያሳየሁት በጣም መሰረታዊ ነገር ነው። ምሳሌ፣ ነገ እነ ኦነግ የበላይ ሆነው መንግስት ቢይዙ አሁን ያለውን ጦር ልክ እንደ መለስ ይበትኑታል ። ያም ማለት አሁን ያለው ወታደር ፈርሶ ለማኝ ይሆናል ። ይህ እንዲሆን አሁን ያሉት ጄኒራሎች በፍጹም አይፈቅዱም። ወያኔም ሆነ ኦነግ የኢትዮጵያን ሰራዊት በጦር አሸንፈው ነው 4 ኪሎ ሊገቡ የሚችሉት ። ለዚህ ነው ከዚህ በኋላ ቄሮ በለው ሸኔ ኦነግ ጃዋር በለው ምናንም በአመጽ ስልጣን ሊወስድ ከፈለገ የሚጠብቀው ጥይት ነው ።

Guest1
Member
Posts: 1926
Joined: 28 Dec 2006, 01:02

Re: አቢይ አህመድ ብሄራዊ ጦሩን በማዘዝ አገር ካላረጋጋ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ወታደራዊ መንግስት ያውጃል

Post by Guest1 » 26 Jul 2020, 02:25

ወታደሩ ስራ የለውም... ለማኝ ስለሚሆን... ? በህዝብ እንቅሰቃሴ መንግስት ሲቀየር ወታደሩ ከህዝብ ጋር በመወገኑ ስለሚሆን ወታደርነቱ አገር ጠባቂነቱን ይቀጥላል ። የህዝብ እንቅሰቃሴ በተበታተነበትና እርስ በርስ የሚጋጭበት ሁኔታ ሲፈጠር ማለትም መንግስት መግዛት ሲያቅተው ወታደሩ መንፈንቅለ መንግስት ሊያካሄድ ይችላል የተደራጀና የታጠቀ ሃይል ስለሆነ። በኣሁኑ ጊዜ ኢትዮጵያ ወታደሩ በቋንቋ የተለያየና ክልሎችም የታጠቁ ስለሆኑ በየክልሉ ወታደራዊ መንግስት ሊቋቋም እና አገር ሊፈራስስ ከዚያም የርስ በርስ ጦርነትም ሊያስከትል ይችላል። ህዝባዊ እንቅሰቃሴው በዘር የተከፋፈለ ስለሆነ ለንደዝህ አይነት አገር መፈራራስ አመቺ ሁኔታን ይፈጥራል ቢባል የበለጠ ትርጉም ይሰጣል።

ወታደሩ ኣንድ ከሆነስ? ጊዜያዊ ወታደራዊ መንግስት ይቋቋማል። በሃይል ስላም ማስከበር ይከተላል። ብሄራዊ ራእይ ከሌለው (ኣስታራቂ ካልሆነ) ኣገርን እንደ ኮርፖሬሺን (የገቢ ምንጭ) ብቻ ኣድርጎ ማስተዳደሩን ይቀጥላል። ለገቢው ተቀናቃን የሚመስለውን ሁሉ ያጠፋል። የወታደሩ ኣደረጃጀትና የበላይ አካሎች ሚና ወሳኝ ይሆናል። የወታደራዊ መንግስት መቋቋም የህዝብ ጥንካሬና ኣንድነት መሻከርን ያሳያል። ወታደሩ አገር አንድ ለማድረግ ሳይሆን ለመበታተን ከሆነ ደግሞ ካለፈው የባሰ ኣሳዛኝ ሁኔታ ውስጥ ገብተናል። የህዝብን ኣቅም የሚበታትን ስለሆነ ኣንዳችም ለህዝብ የሚፈይደው ነገር የለምና!

kibramlak
Member
Posts: 2155
Joined: 26 Sep 2013, 09:27

Re: አቢይ አህመድ ብሄራዊ ጦሩን በማዘዝ አገር ካላረጋጋ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ወታደራዊ መንግስት ያውጃል

Post by kibramlak » 26 Jul 2020, 02:26

እርግጥ ነው ሀገርን አስከብራለው ለሚል የጦር ሰራዊት ይህን አይነት የንፁሀንን ህይወት እየቀፀፈ ያለ ትርምስ ዝም ብሎ ማየት ከሞት የበለጠ ውርደት ነው፣፣ ምናልባትም ይህ ሀገር ወዳድ የሆነው ጦር የሚጠበቅበትን ግዳጅ ለመወጣት አንድ ቀን ቆርጦ ይነሳ ይሆናል፣፣ አረማመዱን አይቶ ስንቱን ይቀሙታል እንደሚባል፣ አብይ አረማመዱን ካልቀየረ የዚህችን ሀገር እና ህዝብ መከራ ማባባስ እንጅ የተለየ ነገር አይመጣም፣፣

Horus
Senior Member+
Posts: 30915
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: አቢይ አህመድ ብሄራዊ ጦሩን በማዘዝ አገር ካላረጋጋ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ወታደራዊ መንግስት ያውጃል

Post by Horus » 26 Jul 2020, 02:55

አው ልዩ ልዩ ክልሎች የራሳቸው የፖሊስ፣ ሚሊሺያ ና ልዩ ሃይል ገምብተዋል። እነዚህ ልዩ ሃይሎች ምን ያህል ማዕከላዊውን ሰራዊት እንደ ሚፎካከሩና የሃይል ሚዛናቸው ማለትም የውጊያ ብቃታቸው ምን እንደ ሚመስል አላቅም ። ግን ዛሬ ለፖለቲካው መረጋጋት የሰራዊቱን ድጋፍ የሚሻው ገዥ ፓርቲ ብልጽግና ነው። ከብልጽኛ የወጣው ዎያኔ አሁን ወታደሩ ውስጥ ድጋፍ ሊኖረው አይችልም ። ደሞዝ የሚከፍለው ፓርቲ 4 ኪሎ ያለው እንጂ መቀሌ ያለው ቡድን አይደለም ። ስለዚህ በኔ ግምት አቢይ ሰራዊቱ ድጋፍ አለው። ስለሆነም ኦነግ፣ ሽኔ፣ ወያኔ፣ እስላሚክ ጃዋር ሁሉም ተሸናፊ ናቸው፣ እስር ቤት ማቀቁም ተፈቱ ለውጥ የለውም ። ስልጣን ካቢይ የሚቀማ አንድም ቡድን የለም ።

justo
Member
Posts: 3178
Joined: 05 May 2013, 17:54

Re: አቢይ አህመድ ብሄራዊ ጦሩን በማዘዝ አገር ካላረጋጋ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ወታደራዊ መንግስት ያውጃል

Post by justo » 26 Jul 2020, 03:47

Horus wrote:
26 Jul 2020, 00:05
የዛሬውን የጦር አዛዥ መግለጫ ልብ ብሎ ለሰማው የሚለው ይህ ነው። የፖለቲካ ቡድኖች በተጣሉ እና ህዝብ እየቀሰቀሱ ስርዓት ባፈረሱ ቁጥር የኢትዮጵያ ጦር ሰራዊት እየፈረሰው አይበታተንም ። ልክ ዎያኔ እንዳደረገው ። መከላከውያው ሌላ ስራ የለውም። ኦነግ እና አቢይ ሲነታረኩ አገር ቢፈርስ ተመልሶ ለማኝ የሚሆን የሰራዊቱ አባል ነው ። ስለዚህ አለምንም ጥርጥር አቢይ ህግና ሰርዓት ማረጋገጥ ካልቻለ አለምንም ጥርጥር ወታደሩ መንግስት ይዞ ፓርቲዎችን ሁሉ እስር ቤት ይከትታል። ይህ ሳይንስ ነው። ወታደሩ ኮርፖሬት ጥቅም አለው ። የራሱ የሆነውን የህልውና መሰረቱ የሆነውን የሰራዊቱ ድርጅት ቀጣይነት ማረጋገጥ ግድ ይለዋል ። ለዚህ ነው አቢይ ምን ግዜም የመከላከያውን ሙሉ ድጋፍ ያለው ። ለዚህም ነው ከዚህ በኋላ መንግስት በአመጽ አፈርሳለሁ የሚል ሁሉ የወታደሩን ጥይት የሚቀምሰው ። እንደ ጃዋር እና ገርባ ያሉ የፖለቲካ መሃይሞች የማይገባቸው ይህን መሰሉን የፖለቲካ ሳይንስ ነው ። ከላይ የጠቀስኩት ሚሊታሪ ኮርፖሬቲዝም ከአራቱ አንዱ የኪዴታ ምክኛቶችና ሞዴሎች ነው፣ ባጭሩ !
Why don't you give the guy a breathing space, isn't that what lidetu, jawar and debretsion said, that Abiy is not legit after September 30, and Iskinder said that Abiy is not legit in Addis Abeba. Now you're saying if this or that, Abiy is not legitimate.

Give the guy a breathing space for heaven's sake, stop with this incremental demand nonsense that does not appreciate what has already been achieved. Berhanu and Ezema seem to understand that, Ermias Legesse trying to secure a role for himself keeps shifting the goal post, it looks immature and childish.

Horus
Senior Member+
Posts: 30915
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: አቢይ አህመድ ብሄራዊ ጦሩን በማዘዝ አገር ካላረጋጋ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ወታደራዊ መንግስት ያውጃል

Post by Horus » 26 Jul 2020, 04:01

ጀስቶ
ምንድን ነው ምታወራው? እዚህ ያስቀመጥኩት በፖለቲካ ሳይንስ ላይ የተመሰረተ ሃቅ ነው። ደሞ ከስር ያሉትን ማብራሪይዎቼን አንብብ። እኔ አቢይን ለመወጠር አይደለም ይህን ያልኩት ። እኔ ያልኩት አቢይ ጦሩን ተጠቅሞ ዘርኞችን ካልደመሰሰ እና አገርና መንግስት ካልጠበቀ ወታደሩ ኩዴታ አድርጎ የወታደር መንግስት ያቆማል አልኩኝ። ይህ ትንተና ገብቶህ ከሆነ እና አይ እንዲዚ ያለ ሴናሪዮ የለም ካልክ ንገረን ! ሚሊታሪ በፖለቲካ ውስጥ እንዴት ጣልቃ እንደ ሚገባ ቲሲስ ጽፌበታለሁ ፣ ተረት አይደለም የምጽፈው ? የኢትዮጵያ ፖለቲካ ወስጥ ያሉት ተጫዋቾች ሁልም ይታወቃሉ ፣ የሁሉም ፖለቲካዊ ባህሪ የሚታይ ነው ።

justo
Member
Posts: 3178
Joined: 05 May 2013, 17:54

Re: አቢይ አህመድ ብሄራዊ ጦሩን በማዘዝ አገር ካላረጋጋ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ወታደራዊ መንግስት ያውጃል

Post by justo » 26 Jul 2020, 05:35

Horus wrote:
26 Jul 2020, 04:01
ጀስቶ
ምንድን ነው ምታወራው? እዚህ ያስቀመጥኩት በፖለቲካ ሳይንስ ላይ የተመሰረተ ሃቅ ነው። ደሞ ከስር ያሉትን ማብራሪይዎቼን አንብብ። እኔ አቢይን ለመወጠር አይደለም ይህን ያልኩት ። እኔ ያልኩት አቢይ ጦሩን ተጠቅሞ ዘርኞችን ካልደመሰሰ እና አገርና መንግስት ካልጠበቀ ወታደሩ ኩዴታ አድርጎ የወታደር መንግስት ያቆማል አልኩኝ። ይህ ትንተና ገብቶህ ከሆነ እና አይ እንዲዚ ያለ ሴናሪዮ የለም ካልክ ንገረን ! ሚሊታሪ በፖለቲካ ውስጥ እንዴት ጣልቃ እንደ ሚገባ ቲሲስ ጽፌበታለሁ ፣ ተረት አይደለም የምጽፈው ? የኢትዮጵያ ፖለቲካ ወስጥ ያሉት ተጫዋቾች ሁልም ይታወቃሉ ፣ የሁሉም ፖለቲካዊ ባህሪ የሚታይ ነው ።
True, your scenario is factual, but it creates perceptions of a weak government, and in the marketplace of politics perceptions easily turn to reality, that is why woyane wants to pollute the landscape with scenarios and perceptions and people of good will like you need to refrain from that

Horus
Senior Member+
Posts: 30915
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: አቢይ አህመድ ብሄራዊ ጦሩን በማዘዝ አገር ካላረጋጋ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ወታደራዊ መንግስት ያውጃል

Post by Horus » 26 Jul 2020, 15:25

ጁስቶ
ህልም ፈርተን ሳንተኛ አናድርም ። ፐርሰፕሽን ሰዎች ላይ ተጽዕኖ ሰለሚያደር ሳይንስ አይነገር አትበል ። ሰውን ለትክክለኛ ወሳኔና ተግባር የሚያበቃው ጥሩ እውቀት ማለትም ሳይንስ ነው። በኔ ግምት አቢይ የሰራዊቱ ድጋፍ ምናልባትም ሙሉ ድግፍ ያለው ይመስለኛል። ይህ የሚሆነው በሁለት ምክንያቶች ነው ፤ አንድም ሰራዊቱ በኢትዮጵያዊነት ኢቶስ ስለተገነባ፣ ሌላም ሰራዊቱ ድርጅታዊ ጥቅሙን ስለሚጠብቅ (ይህ ነው ኮርፖሬት ኢንትረስት የሚባለው) ነው ። ይህ ማለት ግን አቢይ የሰራዊቱን ሙሉ ጉልበት መጠቀም ይፈልጋል ማለት አይደለም ። ለዚህ ነው ባ10 ኪ/ሜ የወታደር ካምፕ እያለ ሙሉ ሻሸመኔ በኦነግ ሽብርተኛ የወደመው ። ወፊትም ይህ እንዳይሆን አቢይ ማድረግ ያለበንት ነው ለማሳየት የሞከርኩት ።

justo
Member
Posts: 3178
Joined: 05 May 2013, 17:54

Re: አቢይ አህመድ ብሄራዊ ጦሩን በማዘዝ አገር ካላረጋጋ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ወታደራዊ መንግስት ያውጃል

Post by justo » 26 Jul 2020, 16:18

Horus wrote:
26 Jul 2020, 15:25
ጁስቶ
ህልም ፈርተን ሳንተኛ አናድርም ። ፐርሰፕሽን ሰዎች ላይ ተጽዕኖ ሰለሚያደር ሳይንስ አይነገር አትበል ። ሰውን ለትክክለኛ ወሳኔና ተግባር የሚያበቃው ጥሩ እውቀት ማለትም ሳይንስ ነው። በኔ ግምት አቢይ የሰራዊቱ ድጋፍ ምናልባትም ሙሉ ድግፍ ያለው ይመስለኛል። ይህ የሚሆነው በሁለት ምክንያቶች ነው ፤ አንድም ሰራዊቱ በኢትዮጵያዊነት ኢቶስ ስለተገነባ፣ ሌላም ሰራዊቱ ድርጅታዊ ጥቅሙን ስለሚጠብቅ (ይህ ነው ኮርፖሬት ኢንትረስት የሚባለው) ነው ። ይህ ማለት ግን አቢይ የሰራዊቱን ሙሉ ጉልበት መጠቀም ይፈልጋል ማለት አይደለም ። ለዚህ ነው ባ10 ኪ/ሜ የወታደር ካምፕ እያለ ሙሉ ሻሸመኔ በኦነግ ሽብርተኛ የወደመው ። ወፊትም ይህ እንዳይሆን አቢይ ማድረግ ያለበንት ነው ለማሳየት የሞከርኩት ።
oh, I understand, I don't know why I got the wrong impression

Guest1
Member
Posts: 1926
Joined: 28 Dec 2006, 01:02

Re: አቢይ አህመድ ብሄራዊ ጦሩን በማዘዝ አገር ካላረጋጋ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ወታደራዊ መንግስት ያውጃል

Post by Guest1 » 26 Jul 2020, 16:45

አቢይ የራሱን ጠንካራና ዘመናዊ ሰራዊት ገንብቷል በዝች በሁለት አመት ውስጥ። ክልሎችም እንደዝሁ ሰራዊት ኣላቸው ጠንካራም እንደ ትግራይ ለምሳሌ ኣሉ። ኣየር ሃይሉም የአቢይ ደጋፊ ሆኖ ከተቀረጸ ከሁሉም ክልሎች የበለጠ ጉልበተኛ ያደርገዋል። ይህም ሆኖ ኣሸናፊ ሆኖ የሚወጣው የአቢይ ብቻ ሳይሆን የትግራይም ነው። የአማራ ክልልንም ማሳነስ ኣይቻልም ምክንያቱም የክልል ልዩ ሃይልና ፓሊስ የህዝብ ድጋፋና እንብተኛነት ካስከተለ አቢይ ምንም ማድረግ ኣይችልም። መጨረሻው በክልል ተከፋፍሎ ራሱን የቻለ ፌደሬሽን ወይም አገር መገንባት ይሆናል። እስካሁን የተረጋገጠ ነገር ባይኖርም ምናልባት ይህ እንዲፈጠር ይፈለጋልም ይሆናል። አቢይ እያባበለና እያግባባ መቀጠል የፈለገው ወደ ጦርነት ሳይገባ በሰላማዊ መንገድ የተፈለገውን ግብ መምታት ስለማያዳግትና ጦርነት የኣለም ኣቀፍ ጣልቃ ገብነት ሊያስከትል ሰለምችል ሳይሆን ኣይቀርም።

እዝህ ገራሚው በአንድ በኩል ወታደራዊ መፈንቅለ መንግስት የማይቀር ነው እየተባለ ሰራዊቱ የአቢይ ደጋፊ ነው ማለት ቀልድ ነው ቁም ነገር?

Horus
Senior Member+
Posts: 30915
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: አቢይ አህመድ ብሄራዊ ጦሩን በማዘዝ አገር ካላረጋጋ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ወታደራዊ መንግስት ያውጃል

Post by Horus » 26 Jul 2020, 17:10

መፈንቅለ መንግስት የማይቀር ነው ያለ ሰው የለም፣ ካለም ተሳስቷል። ሰራዊቱ ያቢይ ደጋፊ ነው ማለትና ወታደሩ ስልጣን ሊወስድ ይችላል ማለት አይቃረኑም ። ሶስት ነገሮችን መለየት ግድ ነው ።

አንድ፣ በየክልሉ የተከማቸው እልፍ ሺ ለብ ለብ ክምችት ከብሄራዊ ሰራዊት ማወዳደር ቀልድ ነው ። በመሳሪያም ሆነ መዋጋት ብቃት ቀናን ለሊት ናቸው ።

ሁለት ፣ አንዳቸውም የክልል ልዩ ሃይሎች አብረው ማዕከላዊ ሰርዊቱን ለዋጉ አይችሉም። ልዩ ሃይሎች ቢበዛ የክልልና ክልል እርስ በርስ ጦርነት ማድረግ ቢችሉ ነው ፣ በቃ

ሶስት ብሄራዊ ሰራዊቱ አቢይን ደፈም አልደገፈ ወደ መንግስት ፖለቲካ ስልጣን የሚመጣው ያገር መፍረስ፣ የመንግስት መፍረስ አደጋ ሲኖር ብቻ ነው። የጦር አዛዡ ያለው ይንን ነው። እኔ ደሞ የምለው አገር ማፍረስ የሚፈልጉ ካል አቢይ ሰራዊቱን ማዘዝ ግድ ይለዋል ነው ። እስከ ዛሬም ይህ ሁሉ ወድመት የመጣው ሰራዊቱ ህዝብ እንዲጠብቅ አለማድረጉ ነው።

Guest1
Member
Posts: 1926
Joined: 28 Dec 2006, 01:02

Re: አቢይ አህመድ ብሄራዊ ጦሩን በማዘዝ አገር ካላረጋጋ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ወታደራዊ መንግስት ያውጃል

Post by Guest1 » 26 Jul 2020, 17:47

የመንግስት ፓለቲካ ስልጣን ማለት መንግስት መመስረት ማለት ስለሆነ ጦሩ የኣቢይ ደጋፊም ኣይመስልም። እንደ ማስፈራራትም ነው።
ሶስት ብሄራዊ ሰራዊቱ አቢይን ደፈም አልደገፈ ወደ መንግስት ፖለቲካ ስልጣን የሚመጣው ያገር መፍረስ፣ የመንግስት መፍረስ አደጋ ሲኖር ብቻ ነው። የጦር አዛዡ ያለው ይንን ነው።
ወታደሩ ስልጣን ከያዘ ወይም መንግስት ከሆነ ወረደ ኣልደገፈውም። ምናልባትም የቁም እስረኛ ያደርጉታል። ወታደሩ የአገር ውስጥ ግዳጁን እንደ ታዘዘው የሚፈጽም ከሆነ (ማለት አገር የመፍረስ አደጋ ውስጥ እንዳትገባ) የአቢይ/መንግስት ደጋፊ ነው። ከመፈራረስ ያድናል።
ምንም ተባለ መፈንቅለ መንግስት ኣይኖርም ማለት ኣይደለም። ወታደሩን የያዘ መፈንቅለ መንግስት ሊያካሄድ ይችላል። ኣቢይ በወታደሩም ሆነ በየክልሉ ድጋፍ ከሌለው አዳጋ ውስጥ ነው። የተከፋፈለ ጦር ከሆነም ክልላዊ አገሮች ይፈጠራሉ። ወይንም በስምምነት ወደ ኮንፌደሬሽን እንሸጋገራለን። ሁለቱም ለማንም የማይጠቅሙ ናቸው። ስለዝህ መፍትሄው ወታደሩን ኣንድ ማድረግ ወይም ህዝቡን ኣንድ ማድረግ ኣይደለም?

tlel
Member
Posts: 1559
Joined: 28 Dec 2019, 14:24

Re: አቢይ አህመድ ብሄራዊ ጦሩን በማዘዝ አገር ካላረጋጋ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ወታደራዊ መንግስት ያውጃል

Post by tlel » 27 Jul 2020, 00:25

Look there if you see all the connected dot, the government is being used to set up Islamic government through Oromoia. Look at all in power including Aby, for now the government is saying Ethiopia because it needs support to eliminate Tplf but from behind, islamic government is being built look at who are the leaders in Oromia and even Amara they are attached to Islamic names and their groups are killing non muslim people in Oromia and the radical groups in West beating Ethiopian flags. could be for preparing the youth after Tplf. So, yes, if Ethiopians force to make the government Ethiopia it is possible, but within the government, it is hard to find out who is who. Why are only muslims are selected in leadership? Look the general himself and the oppositon of Aby as Jawar. This war within themselves is all drama there is agenda. in the mean time they are cleansing traditional Ethiopians who live in peace among themselves it doesn't matter if they are muslims or chiristians. This has been designed long time.
Last edited by tlel on 27 Jul 2020, 00:36, edited 1 time in total.

Selam/
Senior Member
Posts: 11847
Joined: 04 Aug 2018, 13:15

Re: አቢይ አህመድ ብሄራዊ ጦሩን በማዘዝ አገር ካላረጋጋ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ወታደራዊ መንግስት ያውጃል

Post by Selam/ » 27 Jul 2020, 00:35

Kichamam Woyane - You still live in cold-war era. Get lost. KIFU!
yaballo wrote:
26 Jul 2020, 01:24
Really? .. in the "corporate rules" of Abiy's army, is there any mention of the fact where ALL Ethiopian regimes have been booted-out of power by a more determined peasant armies representing a tribe or two? ..

That is: poor Ethiopia's brief experiment with 'a democratic change' is truly over & another rounds of destructive civil wars await poor Ethiopia.

DON'T WORRY .. NO ONE EXPECTS MEMBERS OF YOUR FUGA TRIBE TO VOLUNTEER IN ANY OF THE WARS.
:roll:

VIDEO: Rebels control Addis Ababa 1991

Horus
Senior Member+
Posts: 30915
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: አቢይ አህመድ ብሄራዊ ጦሩን በማዘዝ አገር ካላረጋጋ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ወታደራዊ መንግስት ያውጃል

Post by Horus » 27 Jul 2020, 01:56

የዎያኔ ወረራ ዘመን ! እነሆ ለዚህ በቃን ! ግዜ የሁሉን አስተካካይ !!!

eden
Member+
Posts: 9268
Joined: 15 Jan 2009, 14:09

Post by eden » 20 Jul 2023, 20:15

Horus wrote:
26 Jul 2020, 00:05
አቢይ ምን ግዜም የመከላከያውን ሙሉ ድጋፍ ያለው ። ለዚህም ነው ከዚህ በኋላ መንግስት በአመጽ አፈርሳለሁ የሚል ሁሉ የወታደሩን ጥይት የሚቀምሰው ።
Horus wrote:
26 Jul 2020, 02:15
አሁን ያለውን ጦር ልክ እንደ መለስ ይበትኑታል ። ያም ማለት አሁን ያለው ወታደር ፈርሶ ለማኝ ይሆናል ። ይህ እንዲሆን አሁን ያሉት ጄኒራሎች በፍጹም አይፈቅዱም።
Horus wrote:
26 Jul 2020, 02:55
በኔ ግምት አቢይ ሰራዊቱ ድጋፍ አለው። ስልጣን ካቢይ የሚቀማ አንድም ቡድን የለም ።
Horus wrote:
26 Jul 2020, 17:10
በየክልሉ የተከማቸው እልፍ ሺ ለብ ለብ ክምችት ከብሄራዊ ሰራዊት ማወዳደር ቀልድ ነው ። በመሳሪያም ሆነ መዋጋት ብቃት ቀናን ለሊት ናቸው ።

አንዳቸውም የክልል ልዩ ሃይሎች አብረው ማዕከላዊ ሰርዊቱን ለዋጉ አይችሉም። ልዩ ሃይሎች ቢበዛ የክልልና ክልል እርስ በርስ ጦርነት ማድረግ ቢችሉ ነው ፣ በቃ

አገር ማፍረስ የሚፈልጉ ካል አቢይ ሰራዊቱን ማዘዝ ግድ ይለዋል ነው።

wey gud

Horus
Senior Member+
Posts: 30915
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re:

Post by Horus » 20 Jul 2023, 21:58

eden wrote:
20 Jul 2023, 20:15
Horus wrote:
26 Jul 2020, 00:05
አቢይ ምን ግዜም የመከላከያውን ሙሉ ድጋፍ ያለው ። ለዚህም ነው ከዚህ በኋላ መንግስት በአመጽ አፈርሳለሁ የሚል ሁሉ የወታደሩን ጥይት የሚቀምሰው ።
Horus wrote:
26 Jul 2020, 02:15
አሁን ያለውን ጦር ልክ እንደ መለስ ይበትኑታል ። ያም ማለት አሁን ያለው ወታደር ፈርሶ ለማኝ ይሆናል ። ይህ እንዲሆን አሁን ያሉት ጄኒራሎች በፍጹም አይፈቅዱም።
Horus wrote:
26 Jul 2020, 02:55
በኔ ግምት አቢይ ሰራዊቱ ድጋፍ አለው። ስልጣን ካቢይ የሚቀማ አንድም ቡድን የለም ።
Horus wrote:
26 Jul 2020, 17:10
በየክልሉ የተከማቸው እልፍ ሺ ለብ ለብ ክምችት ከብሄራዊ ሰራዊት ማወዳደር ቀልድ ነው ። በመሳሪያም ሆነ መዋጋት ብቃት ቀናን ለሊት ናቸው ።

አንዳቸውም የክልል ልዩ ሃይሎች አብረው ማዕከላዊ ሰርዊቱን ለዋጉ አይችሉም። ልዩ ሃይሎች ቢበዛ የክልልና ክልል እርስ በርስ ጦርነት ማድረግ ቢችሉ ነው ፣ በቃ

አገር ማፍረስ የሚፈልጉ ካል አቢይ ሰራዊቱን ማዘዝ ግድ ይለዋል ነው።
wey gud
ምንም ጉድ የለም!

ይህ የተባለው የዛሬ 3 አመት አቢይ ኢትዮጵያዊ ነኝ ፣ ኢትዮጵያዊ ሰራዊት አንጻለሁ በሚልበት ወቅት ነው ።

የኩዴታ ቲኦሪና ሞዴል አይለወጥም ፤ ወታደሩ ኮርፖሬት ወይም እንደ ድርጅት የመኖር ጥቅምና ፍላጎት አለው ። ሚሊታሪ የሚፈርሰው አገር በሌላ ጦር ሲፈርስ ነው ልክ እንደ ወያኔ የዛሬ 30 አመት ወይም ጣሊያን ኢትዮጵያን ሲወርር ።

ዛሬ አቢይን ከስልጣን ለማውረድ የሚፈልግ ኃይል እንጂ ሰራዊቱን ለማፍረስ የሚዋጋ ሌላ ጦር የለም ። ትህነግ ሞክሮ ተሸንፏል ።

አሁን ለሰራዊቱ መከፋፈል ዋና ምክንያት የአቢይ ኢትዮጵያዊ አለመሆንና የኢትዮጵያ ሕዝቦች መንግስት ለመለወጥ መነሳታቸው ነው ። አቢይ አህመድ የኢትዮጵያን መከላከያ ባማራ ላይ፣ በጒጂ ላይ፣ በጉራጌ ላይ፣ ወይም በሱማሌ ላይ የራሳቸውን ሕዝብ እንዲወጉ ካዘዘ ጦሩ በጎሳ ተከፋፍሎ ይፈርሳል ወይም ሰራዊቱ ውስጥ ያሉ አገርም፣ ሰራዊትም በፍረስ የለበትም የሚሉ ጄኒራሎች ካሉና ከተደራጁ አቢይን ከስልጣን ያስወግዳሉ በሰላም ሆነ በኩዴታ ።

ይህን ፖሲቢሊቲ የሚወስነው በኦሮሞ እና ሌሎችች ጄኔራሎች መሃል ያለው የሃይል ሚዛን እና ሰራዊቱ ውስጥ ያላቸው ተሰሚነት ነው። አንድ አገር በመደብና ጎሳ ፖለቲካ ሲከፋፈል የሚከተለው የኩዴታ አይነት ሶአይታል (societal military intervention in politics) ይባላል ።

ስለዚህ በኦሮሞ ፖለቲካ በላይነት በተነሳው አመጽ ሚሊታሪው በጎሳ ተከፋፍሎ ሊፈርስ ይችላል፣ ወይም ይህ እንዳይሆን የሚፈልገው የሰራዊቱ ክፍል አቢይን ከስልጣን አስወግዶ ወታደራዊ አስተዳደር ሊያውጅ ይችላል ። የዚህ ውጤት ወሳኙ የህዝቡ ትግል ሚዛን ነው ።

አማራ አሁን በያዘው ቀጥሎ ያማራ ሽግግር መንግስት አቁሞ ወታደራዊ ኃይሉን ካደራጀ በመላ ኢትዮጵያ በግድ የሚመጣውን የሽግግር ሂደት ሚዛን ይደፋል መሃል አገርና ደቡብ ካማራ ጋር ስለተቀናጁ !

ስለዚህ የዛሬ 3 አመትና ዛሬ ኢትዮጵያ የተለያዩ እንሰሶች ናቸው ።

Post Reply