Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Aurorae
Member
Posts: 635
Joined: 10 Nov 2019, 02:21

Re: እኔ ማበዴ ነው... ልሳቅ ወይስ ላልቅስ?

Post by Aurorae » 30 Jul 2020, 12:39

Brother Meleket,

Impressive. You are a human database. :lol: :lol: Awesome. You really are an asset.

kerenite
Member
Posts: 4477
Joined: 16 Nov 2013, 13:15

Re: እኔ ማበዴ ነው... ልሳቅ ወይስ ላልቅስ?

Post by kerenite » 30 Jul 2020, 14:02

Meleket wrote:
30 Jul 2020, 11:41
ክቡር ወንድማችን Fed_Up

እውነት ሁሌም ብርቅ የሆነ የማይጠገብ ውበት ኣላት። ስለሆነም ኣንድ እውነትን የተላበሰ በመረጃና በማስረጃ የተደገፈ ጽሑፍ ውበቱ ለማንም ደምቆ የሚታይ ይሆናል። ለዛሬ ወንድማችን Fed_Up ያገራችንን የኤርትራ ግድቦች ታሪክ በጨረፍታ እንድንቃኝ “ዙራማ ሃገርካ” እንደሚባለው የሃገራችንን የተለያዩ ቀዬዎች እየተዘዋወርን ለማየትና ትዝታዎቻችንን ለማደስ እንድንችል ጎረቤቶቻችንም ስለ አገራችን ቀዬዎች እውነታን ያውቁ ዘንድ ኣስችለሃልና እናመሰግናለን።

በርግጥ ቀደምቶቻችን፡ዓዲቐይሕ ኣካባቢ ቆሓይቶ በተባለችው ታሪካዊት ቀዬ ውስጥ የሰሩት ቅድመ ኣኽሱሙ የሳፊራ ግድብ፡ አገራችን ኤርትራ ቢያንስ ቢያንስ ከ2ሺህ ዓመታት በላይ ግድብ የመስራት ልምድ እንደላት ሕያው ምስክር ነው። :mrgreen:

http://www.shabait.com/about-eritrea/er ... 21-qohaito
እንዳልከው ኤርትራ ውስጥ በመቶዎች የሚቆጠሩ ግድቦች (ዲጋ ወይ ራሕያ ብለን የምንጠራቸው እንደየ የሚይዙት የውሃ መጠን የተለያዩ የውሃ ቋቶች) እንደተሰሩ፡ በአማካይ በየአመቱ 4-5 ግድቦች (የውሃ ቋቶች) እንደተሰሩ ግልጽ ነው። በርግጥ የቱርኮችንና የግብጦቹን ባናውቅም፣ ጣልያኖች በማይ ስርዋ፣ በማይ ኣንበሳ፣ በዓዲ ንፋስ፣ በበለዛ፣ ቫለነኪ፣ በዓዲ ሸኻ፣ በዒላበርዕድ፣ በሽፍሽፊት ወዘተ መለስተኛ ግድቦችን ሰርተዋል። የጣልያን ሃብታሞች እነ ዳናዳይም በዒላበርዕድ፣ በጋህቴላይ፣ በጊንዳዕ ወዘተ ትንንሽ ግድቦች ገንብተዋል። ከዚህ በተጨማሪም የተለያዩ ማኅበራትና የግብረሰናይ ድርጅቶችም በኤርትራ በርካታ ቀዬዎች ውስጥ ትንንሽ ግድቦች (ዲጋና ራህያ) መስራታቸውን ማስታወስ ኣለመዘንጋትም የግድ ይላል። ለኣብነት፦

ኢቫንጀሊካን ቸርች በ(ዓዘፋ፣ ሽዕብ ሰለባ፣ ዓዲ ገርግሽ፣ ደቂ ገብሩ፣ ገለብ፣ ጽዓዘጋ፣ መርሓኖ፣ ዓዲ ሓውሻ፣ እምባደርሆ፣ ሽማንጉስ ታሕታይ፣ ጣዕረሽ፣ ሃዋጹ፣ ኮርባርያ ወዘተ)
ሉተራን ቸርች በ(እግሪ መኸል፣ ዳምባ፣ ኣፈልባ፣ ማይ ልብሱ፣ ደቁጽንዓ፣ ዛውል፣ ምለዛናይ፣ ዓዲ ኹቡሎ፣ ዝባን ዖና፣ ዓዲ ገላይ(ሊባን) ወዘተ)
ቃለህይወት ቤተክርስትያን በ(እንዳደቆ፣ ዓዲ ባህሮ፣ መስፍንቶ፣ ዓዲ ኣበይቶ፣ ቤት መካእ ወዘተ)፣
ካቶሊካዊት ቤተክርስትያን በ(ዓዲ ጽንዓይ፣ ዓዲ ከፈለት፣ ዓዲ ከልከልቲ፣ ተኾንዳዕ፣ ሽንድዋ፣ ደቂ ዘርኡ፣ ባምቢ፣ ዓመጺ፣ ሕምብርቲ፣ ወዘተ)
ኢራ የተባለው የኤርትራ የእርዳታ ድርጅት በ( ድርኮ፣ ጸሎት፣ ዓዲ ቐሺ፣ ሕምብርቲ፣ ዓደኾሎም ወዘተ)
የኃይለስላሴ ዘመን ግዜ ነው መሰል ደግሞ በፎሮና በማይ ነፍሒ። በደርጉ ዘመንም ሳይሆን ኣይቀርም በምግብ ለስራ ፕሮግራም ድንቋና ኣብነታዊዋ የዓዲ ላምዛ ግድብና እላይ የተጠቀሱት በርካታ ግድቦች ተገንብተዋል።

ኤርትራዉያን ግለሰቦችም በ(ዓዲ ቆንጺ፣ እምባደርሆ፣ ባምቡቖ)፣ ሕዝብም በራሱ ጥረት በ(ሓሊቦ፣ ጎርበዓቲ፣ ማዕረባ፣ ጻዕዳ ክርስትያን፣ ጻዕዳ እምባ፣ ወኪዱባ ወዘተ) ትንንሽ ግድቦቹን በየቀዬው ገድቧል።

ከነጻነት ወዲህም የኤርትራ መንግስትም በእርሻ ሚኒስትር በኩል ጥንት ሳሕል ላይ በትግሉ ዘመን ሮራ ባቕላ ላይ ማነጽ እንደጀመረው ዓይነት ትንንሽ ግድቦችን (የውሃ ቋቶችን) በመላው አገሪቱ ክፍሎች እንዳነጸ ይታወቃል። ከአመት ወደ አመት ልምዱም እየተካበተ ሲኼድ በሚሊዮኖች ሜትር ኪዩብ የሚቆጠር ውሃን መከዘን የሚችሉ እንደ ዲጋ ቶኮር፡ ሰሞሞ፣ ዲጋ ሓርነት፣ ዲጋ ዓዲ ሞንግንቲ፣ ዲጋ ኮዳዱ፣ ዲጋ ዓዲ ሓሙሽተ፣ ዲጋ ሃየሎ ወዘተን ግድቦችን አንጿል።

ከጦቢያው የትግራዩ ወያኔ ጋር እየተፋለመና ዓለምም ማዕቀብ ጥላበት በነበረ ወቅትም፡ የኤርትራ ህዝብና መንግስት በአስርና በመቶ ሚሊዮኖች ሜትር ኪዩብ የሚቆጠር ውሃን ለመከዘን የሚችሉ ግድቦችን በገርሰት፡ ፋንኮ፡ ገርገራ፡ ሰለድ፡ ዓዲ ሃሎ፡ ከርከበት፡ ጋሕተላይ፡ ታኪታ፡ ቃቅብዳ፡ ዑናፈርዖ፡ ግላስ፡ ብርኪቶ፡ ዳዕሮታይ ወዘተ ለማነጽ በቅቷል።

ባጠቃላይ እነዚህ ብዙ ገንዘብ የፈሰሰባቸው 20 ኣስመራን ሊያንጹ ይችላሉ የተባሉት መጠነኛ ይዘት ያላቸው ግድቦች ከነጻነት በፊትና በኋላም የተሰሩ ናቸው። በነዚህ ግድቦች አማካኝነት መሬቱ በበጋ ወራትም ለምቶ፡ ፍሬ አፍርቶ የኤርትራን ገበያ ሁሉ በምርት ሲጥለቀለቅ ማየት ደስ ያሰኛል ይናፍቃልም።

እነዚህ ግድቦች በየተሰሩበት ስፍራ የመሬቱን የከርሰምድር ውሃ ክምችት በማደለብ እንዲሁም ለእንስሳትና ለእርሻ የሚያገለግል ውሃ በመከዘን እጅግ ትልቅ ሚና ኣላቸው። ዲጋ ወይ ግድብ ማነጽ ብቻ ሳይሆን ወደ ግድቡ የሚገቡ ተፋሰሶችን መፈወስና በችግኝ መሙላት አፈራችን እንዳይሸረሸር በእጅጉ ይጠቅማል። ሰረጀቃ ኣካባቢ እንዲሁም ሽከቲ ኣካባቢ ጥሩ ስራዎች ተሰርተዋል፤ ቢሆንም ግን በቂ ኣይደለም ብዙ ችግኝ ሊተከል ይገባዋል። ህዝብ ባጠቃላይ የህግ ታራሚዎችንም ጭምር፡ እንዲህ አይነት ስራዎችን በነጻ ፈቃዳቸው መስራት እንዲችሉ ሁኔታዎች ቢመቻቹ፤ ብዙ ችግኞች ለተከለም ልዩ ኣመለካከት ቢደረግ መልካም አካሄድና ምርታማነትን የሚያበረታታ አካሄድ ሳይሆንም ኣይቀርም። ለኣመታት በክረምታዊ የተማሪዎች ዘመቻ የተከናወነው አኩሪ የችግኝ ተከላ ሂደትም ሊደነቅና ሊመሰገን ሊበረታታም ይገባዋል።

የውሃ ኣቅርቦትን በተመለከተ ዕድሜ በታጋይ ኪዳነ ይመራ ለነበረው የጥናትና የትግባሬ ክፍል ነፍስወከፍ የኤርትራ ቀዬ ንጹሕ የውሃ አቅርቦት ተቋድሳለች ለማለት ይቻላል። ይህንን በመተግበር ዘንድም ሳቂታው የስራ ሰው ኣቶ ክብረኣብ የሚመራው የውሃ ጉድጓዶች ቆፋሪ ኩባንያ ያደረገው አስተዋጽኦ በኤርትራ ህዝብ ታሪክ ዘንድ የራሱን አኩሪ ምዕራፍ ይዟል። ይህ ሲባል ግን እንደ ከረን የመሳሰሉ አንዳንድ የኤርትራ ትልልቅ ከተሞች የውሃ ኣቅርቦታቸው እጅግ የተዋጣለት ነው ለማለት ያዳግታል።

ቢሆንም ወንድማችን እንዳልከው ኤርትራ ውስጥ ብዙም ራብና ጥም የለም ከተባለ፣ ህዝቡ ያለችውን ቁራሽ ተካፍሎ አምላኩን አመስግኖ የሚኖር ፈሪሃ እግዚአብሄር ያለው ህዝብ በመሆኑ ነው፡ ያለችው ትንሿም ብትሆን በረከት ኣላት። ይህ ሲባል ግን በስራ እጦትና በተለያዩ ምክንያቶች ተቸግሮና ተርቦ የሚኖር የለም ለማለት ኣይቻልም፤ ሕዝባችን ያለነገር “ኣብ ከብዲ ጽጉብ ጥሙይ የሎን” ማለትም “በጠገበ ሰው ከርስ፡ ርሃብተኛ የለም” አይልም። እንደሚታወቀው አለም ያወቀውና ጠሃይ የሞቀው የስደተኛ ጉዳይ አለብን፡ ህዝባችን የሚሰደደው በቦለቲካ ኣይደለም በኢኮኖሚ ምክንያት ነው ሲባልም እንሰማለን። ለምን በኢኮኖሚ ምክንያትስ ይሰደዳል? ተብሎ ከተጠየቀ ምን መልስ ነው የሚሰጥ? ስራ በተለዪም የህንጻ ስራዎች ክፍት ስላልሆኑም አይደል?

በእርግጥ ለሰው ልጅ አስፈላጊ የሚባሉት ነገሮች ምግብ ውሃና መጠለያ ዋነኞቹ መሆናቸውን ብዙ ሲነገርላቸው ይሰማል። በሃገራችን ምግብና ውሃ በበቂ ሁኔታ ኣለ፡ ረሃብም ተወግዷል የምንል ከሆነ፡ ታድያ መጠለያዎቻችን ቤቶቻችን ህንጻዎቻችንም ከነበሩበት ደረጃ የተሻለ ውበት እንዲኖራቸው ቢደረጉ፡ እየፈራረሱ ያሉትም ቢጠገኑ፡ ርእሰ ከተማችን አሥመራም ይበልጥ ብትዋብ ሌሎች ከተሞቻችንም እንዲሁ ቢዋቡ መልካም ነው ብሎ በጨዋ መንገድ መጠየቅ መልካም ሳይሆን አይቀርም! “8.6 ሚሊየን” ሕዝብን ገጽታህን እየገነባህም እኮ ማስተዳደር ይቻላል። ብዙም ሳንርቅ የጎረቤታችን የጦቢያው ወጣቱ ጠቅላዪ ኣብዪ እንኳ ባቅማቸው መቶ ምናምን ሚሊየን ህዝብ አንደላቀው እንኳ ባይሆን ገጽታቸውን ለመገንባት እየተጉ በመልካም መንፈስ ለማስተዳደር እየጣሩም ኣይደል? በንጹሕ ኤርትራዉያን የተዘረፈ ሃብት የመሠረት ድንጋይ የተደረገለትን የህዳሴው ግድባቸውን እየገነቡ ጎንለጎንም ባህርዳርንም ሓዋሳንም አዱ ገነትንም ዴብረብርሃንንም ወዘተንም እያስዋቡም ኣይደል? እኛም ጎንለጎን ማድረግ የምንችላቸውን ነገሮች ብናደርግ መልካም ነው። ይህም ማለት የህግ ልዕልናን ለመተግበር ከጎረቤቶቻችን መንግሥታት ጋር እየሰራን ህወሓትንና እሱን የመሳሰሉ ኣወናባጆችንም ኣደብ እያስገዛን ግድቦቻችንንም እየሰራን በሚገባም እየተጠቀምንባቸውና መሬታችንንም እያለማንባቸው ከተሞቻችንንም ሆነ ገጠሮቻችንንም እያስዋብን ኤርትራዉያን በነጻነትና በትብብር መንፈስ ለመጓዝ ምን ያንሰናል? ምንም! :mrgreen:

ሰላም ሰላም ከተማ አሥመራ፣
ምስ ለንደን ምን ፓሪስ ከነወዳድራ።
:mrgreen:
You know what brother Meleket?

You are a walking encyclopedia albeit nowadays it has become obsolete due to google.

Keep it up. You are a real teacher and we are learning a lot.

Ethoash
Senior Member+
Posts: 26144
Joined: 20 Apr 2013, 20:24

Re: እኔ ማበዴ ነው... ልሳቅ ወይስ ላልቅስ?

Post by Ethoash » 02 Aug 2020, 01:31

almaze wrote:
26 Jul 2020, 02:04
Haddas Eritrea! አዲሲቱዋ ኤርትራ :lol: :lol: :lol:





my heart bleed for Eritrean

this is my expert opinion.... this house build using Asbestos .... once Asbestos was wonder material it is fire resistance, break resistance. and temp. resistance so it is prefect material to build houses .. but in 1986 Canadian find out Asbestos cause cancer... Asbestos was fine until exposed and fiber like material breath in by human only cause a problem hence the above picture show the Asbestos is exposed there is no other way to remove the Asbestos and hope for better there are 3 type Asbestos if it is 3rd level then air tie cover implemented and many costly material used to remove the Asbestos... Asbestos so dangerous even before you remove it the insurance company people come to check u have air tie closed area so no body breath in the Asbestos... this is what the Canadian do for their citizen but they sell Asbestos to Mexico, India and many other countries...


here r two video tell the story of Asbestos


second part pls goggle it yourself

Post Reply