Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
tlel
Member
Posts: 1559
Joined: 28 Dec 2019, 14:24

Re: የኢትዮ360 እና ዳኛቸው አሰፋ አወቅኩሽ ናቅኩሽ

Post by tlel » 21 Jul 2020, 17:28

Guest1 wrote:
20 Jul 2020, 05:09
‘ያ ያልከው የወሎ ፖለቲካ ካልቸር ነው !!! ወያኔኮ በወሎ ሲያልፍ ተዘፍኖለት ነው ፤ ባምቦ ሲያልፍ ግን ተወግቶ ነው !!! ያ ነው የፖለቲካው ምድርና ሰማይ የሚለየው መስመር !!!’
የወሎ ፓለቲካ ‘እኛ ብዙ የመጠቁ ምሁራን ኣለን፤ ከሁሉም የበለጠ እኛ እናውቃለን’ ማለት ከሆነ፤ የድሮ የክፍለ ሃገር ፓለቲካ ጎጃሜ ጎንደሬ ወሎዪና ሸዋዬ የሚባለው ከሆነም በሁለቱም እስማማለሁ። ይህን ልክክስክስ ፓለቲካ ማለት ያዳግታል። ምሁራኑ የተከፋፈለው ክልሌነትና እኛ እናውቃለን ባይነትም ቢባል የተሻለ ነው። ኣንድ በጣም ታዋቂ የወሎ ፓለቲከኛ የወሎ ሪፐብሊክ እንመሰርታለን ብሎ ነበር እንደ ቀልድ።

በወሎ ወያኔን የተቀበሉት ምናልባት ጎንደርና ጎጃም ስለተቃወሙ (የባህር ዳር ተማሪዎች ተገለው ነበር) እና እንደኛ ተራማጅ ሃሳብ ያላቸው (ከእኛ ፓለቲካውን የበለጠ እናውቃለን ባይነት የመጣ) በማለት ሳይሆን ኣይቀርም። በኣምቦ የተዋጉት ከሆነ ምናልባት የመንግስቱ ሃ/ማርያም ደጋፊዎች (እነ መኢሶንና ማሌሪዶች መሸሸጊያ ስለነበር) በተጨማሪም የሰሜን ወረራ አድርገው ስላዩት ይሆናል። ወያኔ ድጋፍ ያገኘው ደርግ ስለተጠላ ብቻ ኣልነበረም። ሌላ ኣማራጭ ባለመኖሩም ጭምር ነው።
ወያኔን እልል ብሎ ወሎ ካስገባ ይኸው ዛሬ በሻብያ በ ሀዋሃት የተታለለው ጥቂት የወሎ ህዝብ እውነት ሻብያን ህዋሃት ነው ነፃ ያወጣቸው ማነነው የውሎ ድርቅን ያዘጋጀው ሃይለስላሤን ለማውረድ። ለምን ወሎ ተመረጠ የኢሳያስ ኣጎትና ኢሳያስ ወሎ ውስጥ ምን ያረጉ ነበር፣ ዛሬ ወሎ ያ የመሰለ ጀግና ምን ላይ ነው የት ደረሰ። ኣገሩና መሬቱ እየተሸጠ ነው ራያና ከሚሴ። ወሎን የግሉ ያደረገው እስካሁን ድረስ ኢሃፓዎች፣ ሻብያና ህዋሃት ነው። ይህን ጥልቅ ነገር ህዝብ እያዛመደ ኣያውቅም በጭቆና ውስጥ ስላለ የእለቱን ምግን ነው የሚፈልገው።

Guest1
Member
Posts: 1926
Joined: 28 Dec 2006, 01:02

Re: የኢትዮ360 እና ዳኛቸው አሰፋ አወቅኩሽ ናቅኩሽ

Post by Guest1 » 22 Jul 2020, 01:28

‘’ባለፈው የዳኛቸው ኢንተርቬው ሊል የሞከረው አቢይ በመወደድ ሊገዛቸው ስላልቻለ እነኦነግን ማለቱ ነው፣ አሁን ሃይል የመጠቀሚያ ወቅቱ ነው ማለቱ ነው ። ግን አንድም ሰው ይህን ማለቱን አያቅም ። ‘’
መልእክቱ ለኣርሶ ኣደሩ/ለገበሬው/ለስርቶ ኣደሩ ኣልነበረም። ለጠ/ሚኒስቴሩና ለመንግስታቸው እንጂ። ስለሆነም መልእክቱ መንግስትን ለሚፈታተኑ በጠቅላላ ነበር። ለምን ኦነግ ብቻውን እዝህ እንደገባ ግልጽ ኣይደለም። መልእክቱስ ለገበሬውና ለህዝቡ ግልጽ ኣልነበረም? ነበር። ገበሬው መንግስትን በደንብ ያውቃል።

የማክያቬሊ መጽሃፍ በፍልስፍና የተሞላ ነው። አገር ማስተዳደርና ግብረገብን ለመጀመሪያ ጊዜ የነጣጠለ ሰው ነው ይባላል። አገር መምራት የሞራል ጥያቄ ሳይሆን የሚያወጣውን፤ በስልጣን የሚያቆየውን መስራት ነው ወዘተ... ስለዝህም ጭካኔን ያወደሰ ነው እየተባለም ይወገዛል።

የፍልስፍና ኣስተማሪ ፓለቲካ አያውቅም ማለት በጣም ያዳግታል። እንዲያውም ፍልስፍና የተማረ ከሁሉም በላይ የተሻለ ስለ ፓለቲካም ሆነ ስለሳይንስ የበለጠ ግንዛቤ ይኖረዋል እንደ ምርጫው። ፍልስፍና የሳይንሶች የበላይ ሳይንስ ኣልነበረም? ከፍልስፍና ኣልነበረም ሌሎች ሳይንሶች የተወለዱት?

ሰውዬው ለምን የውጭ አገር ጸሃፊዎችን ይጠቅሳል? ኢኮኖሚው ስለዝህም ፓለቲካውም ከውጪው አለም ጋር የተገናኘ ስለሆነ። አለበዝያ ወይ እውቀትን አለመሻትና መፍራት ነው ወይም ኢትዮጵያን እንደ ደሴት መቆጠር ይሆናል። ዘመናዊ ት/ቤትም ባላስፈለገ!!!

Horus
Senior Member+
Posts: 30933
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: የኢትዮ360 እና ዳኛቸው አሰፋ አወቅኩሽ ናቅኩሽ

Post by Horus » 22 Jul 2020, 02:14

Guest1
ካክብሮት ጋር፣ አንተም በድሮ ት/ቤት ውስጥ ነው ያለሀው ፣ አንተም በፈረሰው የግሪክች ስህተት ውስጥ ነው ያለሀው። የኔ ወንድም አሁን ያልከው ሁሉ ስናድግ የተማርነው ተረት ነው። ሳይንስ ምን ላይ እንደ ሆነ ማወቅ ፍላጎት ካለው ይህን ተከታተል ። የነሬኔ ዴካርት አለም ተዘሯል፣ ምናብ ስለ ነበር !!! ሰላም!!


Horus
Senior Member+
Posts: 30933
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: የኢትዮ360 እና ዳኛቸው አሰፋ አወቅኩሽ ናቅኩሽ

Post by Horus » 22 Jul 2020, 03:43

THE SANDERS HALL, HARVARD UNIVERSITY - WHAT IS THE RIGHT THING TO DO? WHAT YOU SAY QEROS ????


Guest1
Member
Posts: 1926
Joined: 28 Dec 2006, 01:02

Re: የኢትዮ360 እና ዳኛቸው አሰፋ አወቅኩሽ ናቅኩሽ

Post by Guest1 » 22 Jul 2020, 10:35

ኢሳያስም ሆነ ሌላው የህብረተስብ ክፍል በኢትዮጵያዊነት የፈለገው ቦታ መኖር ይችል ነበርና ወሎ መኖሩ ምን ያስገርማል? የሻቢያን ታሪክ ለማወቅ ከተፈለገ በጣም ግሩም የሆነውን የሹመት ሲዳኝን መጽሃፍ ማንበብ ነው። ሻቢያ ከውሎ ይበልጥ ኤርትራ የሰሩት ጀብዱና ጭካኔ የከፋና የከረፋ ነው። ጥቁር ነጥብ፤ ምንጊዜም የማይረሳ!!

የወሎ ምሁራኖች ከክልላዊነት በመነጨ ሳይሆን ኣይቀርም አማራና ኦሮሞ ነን እያሉ (ህዝቡ ፍቃደኛ ሳይሆን ኣጥብቆ አማራ ነን እያለም) መለፍለፋቸው ችግር ሳይፈጥርባቸው ኣልቀረም። አማራ ነኝ ከማለት ኢትዮጵያዊ ነኝ ማለት የጀመሩም ነበሩ። መብታቸው ቢሆንም ክሁለት ብሄር የወጣው ሁሉ ኢትዮጵያዊ ነኝ ካለ እነዝህ ድብልቆች (ነገር ቆስቋሶች)፤ ወደ ነፈሰው ለመንፈስ ወይም ተቀባይነት እንዲኖራቸውም፤ የህልውና ጉዳይ አድርገውትም ወይም ኢትዮጵያዊነትም ለማንገስም ይሆናል ፕሮፓጋንዳው ወይም አጉል ኣወቅኩ ባይነት። በኣብዛኛው ግን የክልላዊ ኣስተሳሰብ ተጭኗቸው። ይህ ታሪክን መመርመር ይሻል።

ኢሃፓና መኢሶን ኢሰፓ ሁሉም ኣንድ ናቸው። ነጻ ኣውጪ የነበሩትም ጭምር ከተማሪ ንቅናቄ የመጡና በጣም ያልተራራቀ አመለካከት ያልነበራቸው ሁሉም ሶሻሊስታዊ ነን ባዮች። በተግባር ግን ጎጠኞች፤ ክልለኞች፤ ዘራፌዎች እንከናም ናቸው።

ወደ ዲሞክራሲያዊ ጎዳና መግባት ያልተቻለው ለምንድነው? በነዝሁ ምክንያት 1. ከተማሪ ንቅናቄ ጀምሮ የታየው ኢዲሞክራሲያዊነት፤ 2. ዲስፋንክሽናል ቢሄቭየር የተባለው፤ ግለሰብና ዘር ማንዘሩን ማዋረድ፤ 3. የንኡስ ከበርቴ ጭንቀታምነትና ወላዋይነት 4. በቂ የተማረ ክፍል ኣለመኖር 5. የግለሰብ ነጻነት ኣለማክበር ስለዝህም በቡድን በዘርና በሃይማኖት ወዘተ....መመራት 6. የአለም ፓለቲካና ኢኮኖሚም መቀየርም ይህን ኣባብሶታል። መፍትሄው ከራስ መጀመር ዲሞክራሲያዊ መሆን፤ ስድብና ጥላሸት መቀባትን ማውገዥ፤ ትምህርት እንዲስፋፋ የመናገርና የመጻፍ መብት እንዲከበር መጣር .... ህግ ማስከበር።

Abere
Senior Member
Posts: 11135
Joined: 18 Jul 2019, 20:52

Re: የኢትዮ360 እና ዳኛቸው አሰፋ አወቅኩሽ ናቅኩሽ

Post by Abere » 22 Jul 2020, 11:01

@Guest1:

የሚከተለውን አባባልህን ማስተካከል ወይም ማረቅ አለብህ። በበኩሌ የተሳሳተ የግልህ ግንዛቤ ይመስለኛል። ስለ ዶር ዳኛቸው ከሆነ የእራሱን የፓለቲካ ርዕዮት ወይም አቋም መተቸት ይገባህል እንጅ የተሳሳተ ታሪካዊ ትንታኔ ለመስጠት ትልቅ ስህተት ይመስለኛል።

"የወሎ ምሁራኖች ከክልላዊነት በመነጨ ሳይሆን ኣይቀርም አማራና ኦሮሞ ነን እያሉ (ህዝቡ ፍቃደኛ ሳይሆን ኣጥብቆ አማራ ነን እያለም) መለፍለፋቸው ችግር ሳይፈጥርባቸው ኣልቀረም።" Guest1


ወሎ የሚታወቀው በግልፅ ሙሉ ኢትዮጵያዊነት ተምሳሌተ ናሙና - እስላም ክርስቲያኑ በዓለም ላይ በተለየ ተግባቦ የሚኖርበት ክፍለ ሀገር ነው። ወሎዬ በወንዝ እና በተራራ እዬለዬ ጎጠኝነት ሲሰብክ አልሰማንም። በተጨማሪም እኔ ወሎ የመገንጠል እና የክልል ጥያቄ ያራምድ ነበር ሲባል ይኸ አዲስ ነገር ከአንተ አፍ የሰማሁ ይመስለኛል። ሌላው ይኸም ለእኔ አዲስ በመጀመሪያ ይኸ የጎሣ ጉዳይ የእገሌ ነኝ የእገሌ ነኝ ወያኔ ከመጣ ከጥቂት ዓመታት ወድህ የተሰበከ ህዝብ ያደናገረ እንጅ አንድ ክፍለ ሀገር የሚወቀስበት አይደለም። ያም ሁኖ በአገር ህዝብ ከመጣበት ወዲህ እኔ ወሎዬ አማራነኝ ሲል እንጅ ሌላ ነገር ሰመቼ አላውቅም - ይኸ በከሚሴ ወረዳ ብቻ ያለ እስጠ አገባ ንትርክ ነው። ስለ አማራ ከተነሳ በድፍን አሁን አማራ ከሚባሉት ክልል በብዛትም ይሁን በስነ-ልቦና ከወሎ በላይ አማራ የለም። ከእኛ በላይ ፉጨት አፍ ማሞጥሞጥ ነው - ይላል የአገሬ ሰው። በመቀጠል የወሎ ህዝብ ችግር የነበረው የሸዋ ነግሥታት ግፍ ነበር። በተለይም የሰው በላው ኃይለሥላሴ መንግስት መውደቅ ስለንበረበት እና የወሎ ህዝብ በተለዬ መልኩ በጥፍራም ፊውዳሎች እና በኃይለሥላሴ ጥላቻ ለዘመናት ተርግጧል። እና ዘውዳዊ ሥርዓቱ መውደቅ ትክክል ነው - የዴሴ የተማሪዎች የትግል ቀንድልነት የሚመሰገን ነው። የትግሉን ድል የተረከበው አገራዊ ትውልድ መወቀስ ያለብት ለምን የተረጋጋ እና የተሻለ ሥርዓት አልፈጠረም ብቻ ነው። በቂም ብቻ ተነሳስቶ ኋላቀር ስርዓት ለጣለ ህዝብ ዘለፋ መስጠት ምናልባት ከቦጥቧጩ ወዝ መጣጭ የፊውዳል ውላጅ ዝርያ የመነጨ ሃሳብ ነው።

Guest1
Member
Posts: 1926
Joined: 28 Dec 2006, 01:02

Re: የኢትዮ360 እና ዳኛቸው አሰፋ አወቅኩሽ ናቅኩሽ

Post by Guest1 » 22 Jul 2020, 13:30

‘’እኔ ወሎዬ አማራነኝ ሲል እንጅ ሌላ ነገር ሰመቼ አላውቅም’’ - እየዋሸህ መሰለኝ። ልክ ነህ ህዝቡ አማራ ነን ይላል (ስነልቦናው)። እያወራን ያለነው ግን ኦሮሞም አማራም ነን የሚለው የምሁራኑ አጉል መራቀቅን ነው። በምክንያትም ነው። ከኣያት ስም ጀምረህ ወደ ኋላ መቁጠር ነው ታገኘዋለህ። በዝህ አንከራከር!

ቀሚሴዎች ድሮ ኣርጎባ ተብለው ይጠሩ ነበር። እነሱም በኦሮሞ አፋቸው የሃራርጌ መሆናቸውን በደንብ ያስታውቃል። የቤት ኣሰራራቸውም እንደዝሁ የሃራርጌ ነው። የቦረናዎቹ ከቦረና የመጣነን ነን ሲሉ በማስረጃ ቦራን የሚል ቃል ከየት ተገኛ ይላሉ። ለምን ኣዲስ እንደሆነብህ እንጃ!

የክ/ሃገሬነት ወይም ዛሬ ክልሌነት የምንለው በደንብ አረጋግጠሃል። ..... ሰው በላይ የሃይለ ስላሴ መንግስት :lol: ኣሳቅከኝ። እቴጌ መነን የዬት አገር ሰው ነበሩ? የማን ልጅ? ... የድሮ የክ/ሃገሬነት ኣሁንም እንዳለ ነው። የተማሪዎች እንቅስቃሴ ከዳር እስከዳር አገሪቷን ያጠለቀለቀ ነበር! ደግሞ የፊዩዳል ርዥራዥ? :x

Post Reply