Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Abere
Senior Member
Posts: 11111
Joined: 18 Jul 2019, 20:52

የዐብይ አህመድ እርምጃ የሚያስራቸው ሁሉ አጫሉን ገዳይ ናቸው ካለ ፣ እርሱንም በግድያው ተጠርጣሪ አብሮ ያደርገዋል - የደንቆሮ ሥራ ነው።

Post by Abere » 03 Jul 2020, 13:06

የዐብይ አህመድ እርምጃ የሚያስራቸው ሁሉ አጫሉን ገዳይ ናቸው ካለ ፣ እርሱንም በግድያው ተጠርጣሪ አብሮ ያደርገዋል - የደንቆሮ ሥራ ነው። የዐብይ አህመድ ችግሩ እንዴ ጨጓራ ታጥቦ ሆዱ አይጠራም።የምድር እና የሰማይ ያህል የአቋም ልዩነት ያላቸውን ግለሰቦች እና ቡድኖች ሁላችሁም የአጫሉ ገዳይ ናችሁ ማለት ፌዝ ነው። ቢያንስ በቡድን ደረጃ ማን ገዳይ አንዴ ሆነ ሰው ያውቃል። ሾላ በዲፍኑ ንፁህ ነፍስ እና ግብር ከእርሱ በላይ ስለ ኢትዮጵያ የሚቆረቆሩትን ማሰር እና ማንገላታት እራሱን ፀረ-ኢትዮጵያዊ ያደርገዋል። ለእነ ጁሃር እና የጥንት የፓለቲካ ፍቅረኞች ወያኔዎችን ለማስደሰት ንፁሃንን አብሮ ማሰር አንድም ዕብደት ሁለትም ፍርሃት እና በእራስ አለመተማመን ነው።በእንዴነዚህ ዓይነት ሰዎች ስለምትመራ ነው ኢትዮጵያ ጥሩ መስመር ላይ የማትገኜው። ቀደምት አንድ በበታችነት ስሜት የሚሰቃይ መለስ የሚባል የህሌና ድዊ አሁን ደግሞ እንዴ ዥዋዥዌ ጥሩ እና መጥፎ እየቀያየረ የሚመራ አካሄድ ገደል የሚያስገባ ነው። ዐብይ አህመድ ንፁሃን በአስቸኳይ መፍታት አለብህ።

Maxi
Member+
Posts: 5951
Joined: 06 Mar 2014, 04:33

Re: የዐብይ አህመድ እርምጃ የሚያስራቸው ሁሉ አጫሉን ገዳይ ናቸው ካለ ፣ እርሱንም በግድያው ተጠርጣሪ አብሮ ያደርገዋል - የደንቆሮ ሥራ ነው።

Post by Maxi » 03 Jul 2020, 13:26

አብይ አህመድ ከፍተኛ እብደት ላይ ነው ያለው፡፡ ሰውየው ተስፋ የቆረጠ ይመስላል፡፡ ስለዲሞክራሲ እያወራ እንዴት የሚልቴሪ ዮኒፎን ለብሶ መግለጫ ይሰጣል?

መንግስቱ ሃይለማያምም ወደ መጨረሻው ዘመን እንዲህ ያደረገው ነብር፡፡

በጣም የሚያሳዝነው ነገር መንግስቱ ሃይለማርያም እንዲያ በኢትዮጵያ የማይደራደር በብዙ መቶ ሽህ ጦር ይዘም ከውድቀት አልዳነም፡፡ በአሁኑ ሰዓት ጦሩ በሙሉ በብሄር የተከፋፈለ ነው፡፡ ወያኔ እስከ አፍንጫው ታጥቆ ነዳች እየጨመረ አገሪቱን በማቀጣጠል ላይ ይገኛል፡፡ ታዲያ እንዲ ኢትዮጵያ ከፍተኛ ውጥረት ውስጥ ባለችበት በአሁኑ ሰዓት እንደነ እስክንድር ነጋ፣ ልደቱ አያሌውን፣ ኢንጅነር ይልቃን የመሳሰሉ ሰላማዊ ታጋዮች በኢትዮጵያ ሁለት መንግስት ነው ያለው ከሚለው ከጃዋር አጋር በሃጫሉ ግድያ አሳቦ ማሰር በጣም አሳፋሪ ነገር ነው፡፡

ምናልባትም አብይ አሁን እየሄደበት ያለው ነገር የኢትዮጵያን የመፈራረስ መጀመርያ እንዳይሆን ስጋት አለን፡፡

Post Reply