Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Eripoblikan
Member
Posts: 3206
Joined: 15 Sep 2019, 13:49

ይድረስ ለኢሳቱ ሲሳይ አጌና ከስብሃት አርአያ

Post by Eripoblikan » 03 Jul 2020, 03:26

በኣርቲስቱ ሓጫሎ ሞት በጣም ኣዝነናል። በመንግስተ ሰማያት ያኑሮው ለቤተሰቡ ደግሞ ጽናት ይስጣቸው። ሂወት ክቡር ነው፡ ማንኛው ሰው፡ በሚናገረው ጥሩ ይሁን መጥፎ ራሱ ነው ተጠያቂ የሚሆነው። ሰው፡ ኣስቀያሚ ስራ እና ኣጸያፌ ቃላት ሲወረውር ስናይ ወይምደግሞ ስንሰማ፡ ግለሰቡ መጥፎ ሰው ስለሆነ ብቻ ነው፡ እንጂ ካንድ ቢሄር ስለተወለደ ኣይደለም። ሰው ሞተ ተብሎ የሚጨፍር ፡ የኣእምሮ ስንክልና ያለበት ወይም ደግሞ በሰይጣን የታሰረ ሰው መሆን ኣለበት። እንደዚሁ ኣጸያፌ ተግባር የሚያደርግ ሰው ለመጀመርያ ጌዜ ነው የሰማሁት። መወገዝ ያለበት ሰው ወይም ደግሞ ሰዎች ናቸው።

በመቀጠል፡ እናንተ ሰዎች፡ ችግር ኣላቹ፡ ሲጀምር፡ የኤርትራ ወጣት ፡ በኢትዮጵያ ጉዳይ ገብቶ ሂወት የሚከፍል ሰው የለም። ተገቢም ኣይደለም። የኤርትራ ህዝብ ጠላት፡ እናንተው መንግስት ብላቹ የምትጠሩት፡የምታሺቃብጡት፡ ህዝብ የማይውክል ብጉልበቱ ስልጣን ላይ ቁጭ ብሎ ያለ ኣንባገነኑ ነው። 95% የኤርትራ ህዝብ የምንትገለው ያለነው፡ ለምን እንደሆነ ኣሳምራቹ ታቃላቹ።

ጥይት በማይደርስበት ቦታ ቁጭ ብላቹ፡ ጦርነት እንዲታወጅ ጊፌት እያደረጋቹ ናቹ፡ በናንተው ምክንያት ስንት የድሃ ልጅ የሞት እና ስንክልና እጣ እንድያነሳ እያደረጋቹት ነው።

ኤርትራ በውድ ልጆችዋ ደም ዋጋከፍላ ያለች ልእላዊት ሃገር መሆንዋን እያውቃቹ፡ በተደጋጋሚ፡ ባሕር፡ የባሕር ሃይል፡ ዓሰብ፡ ቀይባህር ወዘተረፈ እያላቹ፡ የኤርትራ ልእላዊነት ደፍራቹዋል። የኢሳያስ ሳይሆን፡ የሰፌው የኤርትራ ህዝብ ንብረት ነው። ስለ ሰላም እና ዲሞክራሲ ከመናገራቹ በፌት፡ ራሳቹ ከብሔርተኝነት ስሜት ነጻ ሁኑ። ስሜተኞች መሆን፡ ኣያዋጣም። እናንተው ኣዋቂዎች ወይምደግሞ የፖለቲካ ተንታኞች ኣርጋቹ እራሳቹን፡ የምትቆጥሩ ሰዎች ናቹ የዚህሉ ችግር ምክንያት።

የሚገርሞው እና ልታፍርበት የሚገባህን፡ እዛ ቁጭ ብለህ፡ የኢትዮጵያ መንግስት ከኤርትራ መንግስት ሆነውን ወያነን መውጋት ኣለባቸው ያልከው፡ የሚገርም ነው። የኔ ውንድም እና እህት ላንተው ፍላጎት ለማርካት፡ ሊዘምቱልህ ኣትሰብ፡ ለናንተው፡ ጦርነት እንደ እግርኮስ ጨወታ ነው።

በብዙሃኑ መገናኛ መስመር ወጥታቹ ከመናገራቹ በፌት ኣማኩሩ። ምክንያቱም በኤትዮጵያ ውስጥ ሂወት ሊቀጥፍ ይችላል።

ኤትዮጵያ ሰላም ሲሆን፡ ኤርትራም ሰላም ይሆናል፡ይሂው ነው፡ የፍትህ ፈላጊ የኤርትራ ህዝብ ሙኘት።

በኤትዮጵያ ጉዳይ ኣያገባንም፡ ጥሩ ከመመኘት በቀር፡ እናንተው እንደዚሁ።

sebdoyeley
Member+
Posts: 5507
Joined: 14 Feb 2020, 04:27

Re: ይድረስ ለኢሳቱ ሲሳይ አጌና ከስብሃት አርአያ

Post by sebdoyeley » 03 Jul 2020, 03:37

[quote=Eripoblikan post_id=1080349 time=1593761162 user_id።
[/quote]
agamepoblican=agame Mahlana, you may try but your agame clan is done, if it is true the death of the young Artist was orchestrated in agami$tan :lol: :lol: :lol: :lol:

Post Reply