Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum

Lakeshore
Member
Posts: 2627
Joined: 24 Jul 2018, 09:32

Re: ሃጫሉ ሁንዴሳን ማን ገደለው? እስቅኤል, ጀዋር , ህውአት

Post by Lakeshore » 01 Jul 2020, 09:42

ኣብይ ኣሀመድ ሚኒም ቢዘገይም በመጨረሻ ከብቶቹን ነድቶ ወደበረቷቸው ኣስገቢትዋል ይህ የሁን የሚባል ነው፥፥ አንዲሁም ፊጋውን ከብት ሃጫሉንም ሌሎቹ ከብቶች ረጋግጠው ገደሉት ፥፥ የ አግዚያብሄር መምጫው ኣይጣወቅም ፥፥

Ethiopia is land of proud, patient, and wise peoples. For those foreign agents who tried to destabilize Ethiopia will perish. The next move should be to destroy the agame in the [deleted] land. we can't allow some ignorant criminals hold the agame peoples hostage. Abyi with ethiopian people should march to agame land for once and forever. Otherwise, he will be responsible for every Ethiopian blood spilled including the figa kebt Hachalu.

If Abiy brings him to justice earlier he would be alive by now. Yesterday was another disappointing speech by Abiy, he is the head of the government. In situations like these peoples need clear leadership which he lacks. Peoples need assurance to uphold the law of the land. But instead, he pretends to look wise and plead. He has to do it there is no one to come and save him.

MatiT
Senior Member
Posts: 11549
Joined: 16 Feb 2013, 10:18

Re: ሃጫሉ ሁንዴሳን ማን ገደለው? እስቅኤል, ጀዋር , ህውአት

Post by MatiT » 01 Jul 2020, 10:42

:!: bbb:oops: ጀዋር ለምን #ዐቢይን አምርሮ ይጠላል?
ጀዋር የሚያውቀው፣ ተከታዮቹ ግን የማያውቁ #አራት ጉዳዮች!
..................................
በዚህ ሰዓት አዕምሮ ያለው ሰው ራሱን አንድ ጥያቄ መጠየቅ አለበት፡፡ ለመሆኑ ጀዋር ዐቢይን ለምን አምርሮ ይጠላል? ዐቢይ የኦሮሞን ጥቅም አሳልፎ ስለሚሰጥ ነው? በፍጹም አይደለም፡፡ ዐቢይ ጀዋርን ስለገፋው ነው? ይህም አይደለም፡፡ ዐቢይ ክፉ ሰው ስለሆነ ነው? በጭራሽ፡፡ የጀዋር የሥልጣን ጥም ከፍ ያለ ስለሆነ ነው፡፡

ጀዋር ዐቢይን አሳምሮ ያውቀዋል፡፡ ስለሚያውቀውም ይፈረዋል፡፡ የሥልጣን ጥሙ እንዳይረካ ሊያደርጉ ከሚችሉ ሰዎች ውስጥ ዋነኛው ዐቢይ ነው፡፡ ስለሆነም ባለው በሌለው ኃይሉ ይህን ሰው ማስወገድ ይፈልጋል፡፡ ምክንያቱም ዐቢይ በእርሱና በግቡ መካከል የተቀመጠ ትልቅ ተራራ ነውና፡፡ ለዚህ ደግሞ የኦሮሞን ብሔርተኝነት ካባ መከናነብ ቀላሉ ዘዴ ነው፡፡ ይህ ፍላጎቱ ከሕወሓት ወግኖ ዐቢይን እስከ መውጋት ይዘልቃል፡፡ በኦሮሞ ስም አሮሞን ለሚደግሉ ወገኖች ጥብቅና እስከመቆም ይዘልቃል፡፡ ዐቢይን ለማስወገድ ከሰይጣን ጋር ከመሰለፍ የሚያግደው ያለ አይመስልም፡፡

አንዱ የጀዋር ስትራቴጂ ዐቢይ በኦሮሞ ዘንድ በውሸት እንዲጠላ ማድረግ ነው፡፡ ይህ እንዲሆን ደግሞ የዐቢይ ማንነት ዋና መገለጫዎች ለህዝብ እንዳይታዩ መስራት አለበት፡፡ አስተውሉ! ጀዋር ይህን የሚያደርገው በኦሮሞ ትግል ውስጥ ላበረከተው አስተዋጽኦ ህዝቡ የሰጠውን የክብር ቦታ ያለ አግባብ በመጠቀም ነው፡፡ ጀዋር ስለ ዐቢይ እንዳይታወቅ የሚፈልግ አራት ዋና ዋና ጉዳዮች እነዚህ ናቸው፤

1. ዐቢይ ለኦሮሞ ፍትሐዊ ጥቅም እንደሚሰራ፣
2. ዐቢይ አገርን የሚያሻግር ሐሳብ እንዳለው፣
3. ዐቢይ ያሰበውን የማስፈጸም ችሎታ እንዳለው፣
4. ዐቢይ መልካም ስብዕና ያለው መሪ መሆኑን መደበቅ

#ዐቢይ ለኦሮሞ ፍትሐዊ ጥቅም እንደሚሰራ ይደብቃል

ዐቢይ የኦሮሞ ህዝብ የሚገባውን ቦታና ጥቅም ማግኘት አለበት ብሎ ከልብ ያምናል ይሰራልም! ጀዋር ይህን አሳምሮ ያውቃል፡፡ ልዩነታቸው ግን ግልጽ ነው፡፡ ዐቢይ የኦሮሞን ህዝብ ጥቅም ከሌሎች የኢትዮጵያ ህዝቦች ነጥሎ አያይም፡፡ ሁሉም ህዝቦች የሚጋበቸውን ፍትሐዊ ትቅም ማግኘት አለባቸው ብሎ ያምናል፡፡ ፍትሐዊነት ሲሰፍን የኦሮሞ ህዝብ ይጠቀማል፡፡ ኦሮሞ ቁጥሩንና ትልቅነቱን የሚመጥን ጥቅም ማግኘት አለበት፡፡ ይህ እንዲሆን አንድ ጉዳይ መፈጸም አለበት፡፡ ህጎችና ፖሊሲዎችን ቀርጾ ሥራ ላይ ማዋል! ለጀዋር ግን የኦሮሞ ህዝብ ደሴት ነው፡፡ እንዴተ ሆኖ? እነ ጀዋር የኦሮሞን ህዝብን ቁስል ይነካካሉ፡፡ ቁስል መነካካት ግን ቁስሉን አያድንም፡፡ ጠዋት ማታ ህዝቡን ያስለቅሳሉ፡፡ ህዝብን ማስለቀስ ግን መፍትሔ አያመጣም፡፡ ቁስል ማድማትና ማስለቀስ እውቀት አይፈልግም፡፡ የህዝብ ትክክለኛ ጥያቄ የሚመለሰው በጥሞናና በጥልቀት ተጠንተው ሥራ ላይ በሚወሉ ፖሊሲዎችና ህጎች ነው፡፡ ይህ ደግሞ ጊዜ፣ እውቀት ብስለትና ጥበብ ይፈልጋል፡፡ ዐቢይ ይህን እያደረገ ነው፡፡ ጀዋር ግን ተከታዮቹ ይህን እንዲያውቁ አይፈልግም፡፡ በሬ ወለደ ተረት ይፈጥራል፡፡ ዐቢይ ነፍጠኛ ነው ይላል! እስቲ እንዴት ሆኖ? ተከታዮቹ ራሳችሁን ጠይቁ!

#ዐቢይ አገርን የሚያሻግር ሐሳብ እንዳለው ይደብቃል

ብዙ ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማኅበረሰባዊ ችግሮች አሉን፡፡ ዐቢይ እነዚህ ችግሮች ለመፍታት ምን ማድረግ እንዳለበት ያውቃል፡፡ ተጨባጭና ግልጽ የሆኑ እቅዶችም አሉት፡፡ ይህን ሐሳቡን ለማወቅ #መደመርን ማንበብ በቂ ነው፡፡ የጀዋር ተከታዮች ግን ጸሐፊውን ያለ ምክንያት ስለ ጠሉ፣ መጽሐፉን ለማንበብ ምክንያት ያጣሉ፡፡ የዐቢይ ሐሳብ ግን አገር ላይ ብቻ አያተኩርም፡፡ ከአገር አልፎ የአፍሪቃን ቀንድ ያስባል፡፡ አልፎም አፍሪቃን ያስባል፡፡ ጀዋር ከክልል አልፎ የሚሄድ ሐሳብ የለውም፡፡ ለክልልም የሚመጥን ሐሳብ የለውም፡፡ የኦሮሞን ህዝብ ታላቅነት የሚመጥን ሐሳብ የለውም! ለኦሮሞ ህዝብ ተጨባጭ እቅድ የለውም፡፡ ‹‹የኦሮሞ ጥያቄ አልተመለስም›› በሚል አስመሳይ ለቅሶ፣ ጠዋት ማታ ተከታዮቹን ያስለቅሳል፡፡ ከላይ እንደተጠቀሰው ለቅሶ የኦሮሞን ጥያቄ አይመልስም፡፡ የኦሮሞ ህዝብ ጥያቄ በፖሊሲና በህግ ያለመዛነፍ ይመለሳል፡፡ የሌሎች ብሔር ብሔረሰቦችም ጥቅም አብሮ ይከበራል፡፡ የኦሮሞን ህዝብ በትክክልና በርግጠኝነት የሚመልስ የዐቢይ አካሄድ ነው፡፡ ይህን ለማወቅ የሚያስፈልገው ለቅሶ ሳይሆን በአስተውሎት ማመዛዘን ብቻ ነው፡፡ ጀዋር ግን ተከታዮቹ ይህን እንዲያዉቁ አይፈልግም፡፡ ለምን? ተከታዮቹ ራሳችሁን ጠይቁ!

#ዐቢይ ያሰበውን የማስፈጸም ችሎታ እንዳለው ይደብቃል

ዐቢይ የተግባር ሰው እንደ ሆነ እስካሁን የሰራቸው ነገሮች ምስክር ናቸው፡፡ በሁለት ዓመት ውስጥ እጅግ ብዙ ነገሮችን ለውጧል፡፡ ይህ ሰውዬ አላበዛም እንዴ እስከሚባል ድረስ ብዙ ነገሮችን ቀይሯል፡፡ ተዓምር ነው በማለት የዜና አውታሮች የለውጡን ፍጥነት ዘግበዋል፡፡ ሰውዬው አያወራም እንጂ የሰራቸውን ቢናገር እውነትም ተዓምር ናቸው፡፡ ጀዋር ይህ እንዲታወስ አይፈልግም፡፡ ህዝቡ ይህን ሁሉ ረስቶ ‹‹ምን ለውጥ አለ›› በሚል ትዝታ እንዲቆዝም ይፈልጋል፡፡ ዐቢይ ግን በቃል የሚናገራቸውን በተግባር ሰርቶ የሚያሳይ መሪ ነው፡፡ ይህን ዓይንና ጆሮ ያለው ኢትዮጵያዊ ያውቀዋል፡፡ መዘርዘር ካስፈለገ ከበቂ በላይ መረጃ አለ! በእርግጥ ኢትዮጵያ ውስጥ እጅግ ብዙ መለወጥ ያለባቸው ነገሮች አሉ፡፡ ይህ ሰውዬ በሁለት ዓመት ይህን ተዓምር ከሰራ፣ ተጨማሪ አምስት ዓመት ቢሰጠው ምን ያህል ይሰራ ይሆን? የጀዋር ተከታዮች ራሳችሁን ጠይቁ!

#ዐቢይ መልካም ስብዕና ያለው መሪ መሆኑን ይደብቃል

ዐቢይ ይቅርታን የሚያስቀድም መሪ ነው፡፡ ፍቅርን በተግባር የሚኖር ሰው ነው፡፡ ትዕግስተኛ መሪ ነው፡፡ ደግሞም ሙስናን የሚጠየፍ፣ ለድሃው የቆመ፣ ፍትሕ የሚያስደስተው መሪ ነው፡፡ የአገሩና የህዝቡ ክብር እንዳይቀንስ የሚመኝ መሪ ነው፡፡ ጀዋር ዐቢይን በሌብነትና እና በምግባረ ብልሹነት መክሰስ እንደማይችል ያውቃል፡፡ ዐቢይ የመልካም ስብእና ባለቤት መሆኑ ጀዋርና ሳያበሳጭ አይቀርም፡፡ ምክንያቱ ግልጽ ነው፡፡ አንደኛ እርሱ በጭራሽ ከዐቢይ ጋር የሚስተካከል የግል ስብዕና ሊኖረው እንደማይችል ይገነዘባል፡፡ ዐቢይ ትዳሩን የሚያከብር፣ አገሩን የሚወድ የሁሉንም መልካምነት የሚመኝ ሰው ነው፡፡ ጀዋር በነዚህ መስፈርተ ከተመዘነ ታች መውረዱ ነው፡፡ ህዝብ ሃቀኛ፣ አገሩን የሚወድና የህዝቡን ክብር ከሚፈልግ መሪ በላይ ምን ይፈልጋል? በዐቢይ አካሄድ ኢትዮጵያ ውስጥ ፍትሐዊነት፣ ተጠያቂነትና የህግ የበላይነት መስፈኑ አይቀርም፡፡ ይህ ደግሞ እንደ ጀዋር ላሉ የሥልጣንና የሐብት አቋራጭ መንገድ ፈላጊዎች አይመችም፡፡ ስለዚህ ዐቢይን ማጥቂያ መንገድ በነጭ ውሸት ‹‹የኦሮሞን ህዝብ ጥቅም ሽጠሃል›› ብሎ መክሰስ ነው፡፡ ሌላ መንገድ የለውማ! እውነትና ንጋት ግን እያደረ ይጠራል! የጀዋር ደጋፊዎች ራሳችሁን ጠይቁ!

የአገርን እጣፈንታ የሚወስነው የመሪው ጥበብና ችሎታ ብቻ አይደለም፡፡ የህዝቡም አስተውሎትና አርቆ አሳቢነት አስፈላጊ ነው፡፡ የጀዋር ደጋፊዎች ኅሊናችሁን መርምሩ፣ የልባችሁን እውነተኛ ድምጽ አዳምጡ! ከዚያ ትክክለኛ መስሎ የሚታያችሁን ውሳኔ ወስኑ፡፡

ቸር ሰንብቱ!

Post Reply