Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Meleket
Member
Posts: 3057
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

አምቦ - ከወዲያኛው መንደር የመጣው "ተስቦ"

Post by Meleket » 01 Jul 2020, 08:21

Meleket wrote:
01 Jul 2020, 08:11
ክብር፡ ተስፋ በቆረጡ በጽልመት ኃይሎች ለጋ ሕይወቱን ለተቀጠፈው፡ ለህግ ልዕልናና ለኦሮሞ ህዝብ መብት ሲታገል ለተሰዋው ለአርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳ!!! መጽናናቱን ለመላው ሰላም ወዳድ የኢትዮጵያ ህዝብና በትህትናና በፍቅር ሀገር ለመምራት ለሚታትረው ለሰላማዊው ወጣት ጠቅላይ ኣብዪ ተመኘን!!!
Meleket wrote:
04 Mar 2018, 03:03
“አምቦ፣
አንቺ የደም ገንቦ”፣
ከወዲያኛው መንደር የመጣው ተስቦ
ፍልቅልቅ ቀየሽን በጭካኔ ከቦ፣
ስንት ንጹሓንን ማገደ ጠራርቦ።

ለሰሚ ሚገርመው በጣም የሚያስደስተው፣
ያ ሁሉ ወገንሽ እጁን ያጣመረው፣
ያ ሁሉ ወገንሽ ደምሽ ያቆራኘው፣
ነግ በኔ በማለት ችግርሽን ሊጋራው፣
ያን ክፉ ተስቦ ድራሹን ሊያጠፋው፣
እነሆ ጀምሯል ትግሉ ተፏፉሟል፣
ማን ምን እንደሆነ ሜዳው ላይ ይታያል።

ሚሊዮኑ ወገንሽ ነግ በኔ ካላለ፣
ፈውስ መፈለግ ላይ አንቺን ካልመሰለ፣
በጽዳት ዘመቻ ካንቺ ጋር ካልዋለ፣
ተስቦው ቀስ በቀስ ሁሉን ያጋድመዋል እየፈነገለ።

ስለዚ ወገኔ እየተስተዋለ፣
ለመብትህ መቆም ነው አሁን ግዜ ሳለ።