Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Abere
Senior Member
Posts: 11044
Joined: 18 Jul 2019, 20:52

ፍየል ወዲህ፣ቅምዝምዝ ወዳ - ዐፄ ምንሊክን ያልተሳደበ ኦነግ እና ወያኔ በፍፁም የለም።ታዲያ የአጫሉ እኮ የማንኪያ ይህል ነበረች።

Post by Abere » 30 Jun 2020, 10:20

ፍየል ወዲህ፣ቅምዝምዝ ወዳ - ዐፄ ምንሊክን ያልተሳደበ ኦነግ እና ወያኔ በፍፁም የለም።ታዲያ የአጫሉ እኮ የማንኪያ ይህል ነበረች። የዚህን አንድ ፍሬ ልጅ ህይወት የ ጦስ ዶሮ ያደረገ ኦነግ እና ወያኔ ዐረመኔ እራሱ ሊገልፀው አይችልም። አጫሉ ተናገረው የተባለው 50 ዓመት ወያኔ እና ኦነግ ሲሳደብ ከነበረው ጋር ሲነፃፀር አባይን በጭልፋ የመቆንጠር ያህል ነው። ማንም ከእመ-ጤፍ የሚቆጥረው አልነበረም- ተደጋግሞ ተደጋግሞ ለጆሮ የሰለቸ እና የተለመደ ነገር ነው። እምዬ ምኒልክ ያቢንጫጫ ያቦንጫጫ ጀብዱ ታሪካቸው አይቀየር። በእውነት እምዬ በህይወት ቢኖሩ በዚህ አንድ ፍሬ ልጅ ሞት እጅግ ልባቸው ይሰበር ነበር። ደግሞስ ሰው ከዕድሜው ይማራል። ይህ ልጅ የመኖር ዕድል ቢያገኝ፣ ያለምንም ጥርጥር ይፀፀት ነበረ። ለታሪክም ክብር ይሰጥ ነበር። ምን ይሆናል የቀበሮ ባህታዊ ወያኔ ቀድሞ በላው - ለንስሃ ሞት እንዳይበቃ ዕድሜ ነፈገው። ከዚህ ፍረም ላይ እንኳን ኦሮሞ መስለው ግን ኦሮሞ ላይ እሳት የሚጥሉት ወያኔዎች ናቸው። አንድ ኦሮሞ ከዚህ ፎረም ላይ አላየሁም - በሙሉ ወያኔ ነው። ወያኔን ከኦሮሞ ጀርባ ላይ ማውረድ የዜግነት ብቻ ሳይሆን የሰብዓዊ እና ሞራላዊ ግደታ ነው።