Page 1 of 1

ሃጫሉ ለምን ተገደለ?

Posted: 29 Jun 2020, 20:43
by Amayah
ሰው ሁሉ ሃጫሉን ማን ገደለው እያለ ይጠይቃል ። ያ በምርመራ የሚረጋገጥ ነገር ነው ። ከወዲሁ ለማወቅ የሚቻለው ግን ሰውዬው ለምን ሞተ የሚለው ነው ። ደሞ ጠቃሚው ጥያቄ ያ ነው ።

Re: ሃጫሉ ለምን ተገደለ?

Posted: 29 Jun 2020, 21:10
by Amayah
ነገሩን ሁሉ ከፖለቲካ ኮንስፒራሲ አኳያ ካየነው ፣ ሃጫሉ በዎያኔ፣ በምኒልክ ደጋፊ ወይም ጎበና በሚላቸው ኦሮሞ ሊገደል ይችላል ። በተለይ መጨረሻ ላይ በንጉሱ ላይ የተናገረው ጋጥ ወጥ ዘለፋ ሁሉንም ያስቆጣ ነገር ነው።

ግን ሰውዬው ብዙ የግል ጸብ ውስጥ የሚገባ ሰው ነበር ። በኔ ግምት ገዳዩ ተይዞ ሲረጋገጥ የግል ጠብ የሚሆን ይመስለኛል። ለነገሩ ሃጫሉ ብዙ ጠላት ያፈራ ሰው ነው ። ለምን? ለምንድን ነው መካሪ ያልነበረው? ወላጆች አሉት ወይ? የኔ ጥያቄ ያ ነው?

Re: ሃጫሉ ለምን ተገደለ?

Posted: 29 Jun 2020, 21:22
by Amayah
አሁን ብዙ ሰዎች ይህ የሆነው ባቢይ ላይ የቄሮ ሰልፍ ለማስነሳት ነው የሚሉ አሉ፣ ተሳስተዋል ። ባሁን ሰአት ቄሮ ለሰልፍ ቢወጣ በኮሮና ተወርሮ ራሱ ስለሚያልቅ ይህን የሚያደርጉ አይመስለኝ ። ስለዚህ የገዳዩ አላማ አቢይን ለማበሳጨት የሚለው ዉሃ አይዝም ።

Re: ሃጫሉ ለምን ተገደለ?

Posted: 29 Jun 2020, 21:53
by Amayah
ቲፒኤላኢፍም ይህን ነገር አሁን ሊያደርገው አይችልም። አገሩ በኮሮና ጊዜያዊ አዋጅ ሰር ስላለች ብጥብጥ ሆነ ሰልፍ የሚደረግበት ወቅት አይደለም ። አንድ በከፍተኛ አካል የሚደረግ ግድያ ታይሚንግ ይፈልጋል ።

ይህ ሃጫሉና ሌላ አንድ ሰው ተጨቃጭቀው ምናልባትም በዘር ጉዳይ በዛ ሳቢያ ይመስለኛል ሰውዬው የተገደለው ።