Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Hameddibewoyane
Member
Posts: 3890
Joined: 25 Sep 2019, 02:42

አንዳርጋቸው ፅጌ የኢሳት ዋና ስራ አስኪያጅ ሆኑ!!!

Post by Hameddibewoyane » 27 Jun 2020, 12:33

የቀድሞው የግንቦት ሰባት ከፍተኛ አመራር የነበሩት አንዳርጋቸው ፅጌ የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥን (ኢሳት) ዋና ስራ አስኪያጅ በመሆን ስራ ጀምረዋል። የአዲስ ማለዳ ምንጮች እንደተናገሩት ጣቢያው ከመጪው ሐምሌ 1/2012 ጀምሮ በአዳዲስ የአሰራር ስርዓት እና አዳዲስ ዝግጅቶች ወደ ህዝብ እንደሚቀርብ እና ጣቢያውንም የህዝብ ሚዲያ ለማድረግ ዝግጅት መጨረሱ ታውቋል።

ኢሳት በአዳዲስ ዝግጅቶች እና አቀራረቦች ለሕዝብ ለመድረስም ተጨማሪ እና ብቃት ባላቸው የሰው ኃይል ለመደራጀት ሰዎችን መቅጠሩንም ምንጮች ለአዲስ ማለዳ ጨምረው አስታውቀዋል።
ጣቢያው ከዓመታት በፊት በተደጋጋሚ በትግል ላይ የነበረውን የግንቦት ሰባትን እንቅስቃሴ እና የበረሀ ውሎ በመዘገብ ለሕዝብ ሲያደርስ መቆየቱ የሚታወስ ነው።
(አዲስ ማለዳ)

መልካም የስራ ዘመን አንዳርጋቸው ፅጌ
ኢትዮጵያዊነት ከዘር በላይ ነው!!!