Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Abere
Senior Member
Posts: 11129
Joined: 18 Jul 2019, 20:52

ኢትዮጵያዊያን የምንናገርውን ቀድመን እንመርምር - ዓሣ ስንጠይቅ እባብ እንዳይሰጠን።

Post by Abere » 27 Jun 2020, 10:23

በ ቀ.ኃ.ሥ. ዘመን ዝናብ እና ጥጋብ ሲሰለቸው ህዝብ "ይኸ ያረጀ ሰማይ እና ያረጀ ንጉሥ ይልነበር"። ከዚያም ደርግን እግዜር ጄባ አለ። በደርግ ዘመን ደግሞ "ይኸ የባርያ መንግሥት ተባለ"። እግዜርም በተራው ወያኔ የምትባል ከእረኝነት ወደ ቤተ-መንግሥት አስገባት። በእርሷ ህዝብ አምርሮ አለቀሰ - እከክ ሆና ህዝብን በላችው። ህዝብ እንዴ ልማዱ - ወያኔን" የቡቲቶ-ቅማላም ዘመን" በማለት ወደ ሰማይ ጠየቀ። አሁን የቡቲቶ-ቅምል ድሪቶ እየተቃጠለ እየጨሰ ነው።እግዜር ቀጣዮን ባለተረኛ ምን ዓይነቱን ይሰጠን ይሆን።