Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Horus
Senior Member+
Posts: 30929
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

ወጅ እና ወረብ፤ የምስራቅ ጉራጌ አገሮች

Post by Horus » 27 Jun 2020, 02:10

በየግዜው ስለመካከለኛ ዘመን ኢትዮጵያ፣ ስለግራኝ እና ተከትሎ ስለመጣው የኦሮሞ መስፋፋት ውይይት ሲደረግ የሚነሱ ብዙ ጥንታዊ ሕዝቦችና አገሮች አሉ ። ለምሳሌ በዝቋላል ዙሪያ ስለኖሩት የማያ ሕዝቦች አንዱ ናቸው ። በሰፊው የሚታወቁት የእንደ ገብጣን ባለአገር ጋፋቶች ሌላው ናቸው። የዝዋይ ዙሪያ የዛይ ጉራጌዎች አሉ ።

በተለይ ግን ወጅ እና ወርብ የሚባሉት ትላልቅ የምራቅ ጉራጌ አገሮች ዛሬም ሕዝቦቹ ያሉ ስለሆነ ድሮ የነባቸው ስፋትና አቀማመጥ ለማወቅ ሕዝቡን ማጥናት ብቻ ነው። የወጅ (ዋጅ) ጠቅላይ ግዛት ዛሬ እጅግ ያነሰ ቢሆንም የዘመናችን ስልጤ ጉራጌ ነው ። የወጅ ጎረቤትና የወረብ አረግ (ዉርባረግ) ጉራጌ አገር ወረብ ነው ። ያ ሰፊ ሕዝብ ከስምጥ ሸለቆው ልክ እንደ አዘርነት ጉራጌ በትንሹ በስልጤ አካባቢ ይኖራል ። የትልቁ ወረብ ጠ/ግዛት ስሙ ተይዞ ያለው በስልጤ ዋና ከተማ ወራቤ ነው ። ታሪክ ጻፊዎች ወረብ አሉት ድሮም ስሙ ወረቤ ነበር ።

የፈጠገር ጠ/ግዛትም ወደ ሃዲያ የነበረው አገር ሳይሆን በምስራቅ ሰሜን የነበረው እና ጋፋቶችም የነበሩበት ነው። ዋና ከተማው ባደቄ የዛሬ ናዝሬት ነበር ። ከፈጠገር ምዕራብ ማያዎች ነበሩ ።

አንድ ቀን ሁሉም በምርምር ይገኛል ።