-
- Member
- Posts: 4207
- Joined: 27 Sep 2017, 21:56
ኢሳያስ አፈወርቂ የኢትዮጵያ ፕሬዚዳንት ካረጋችሁኝ የኤርትራን መገንጠል ልተውው ብሏል? ወያኔ እና ሻብያ ከጥንቱኑ የሚያስማማቸው ነገር አልነበረም?
ይሄ በጣም ገራሚ ቃለመጠይቅ ነው ማለት ይቻላል:: በውስጡ ብዙ ነገሮች ይዟል::
1. በትግል ላይ እያሉ የኤርትራ እና የትግራይ ድንበር ይካለል ተብሎ ነበር::
ስብሐት “ እኛ ፓርቲ በመሆናችን ይህንን መወሰን አንችልም ብለን እምቢ ብለናል” ብሏል:::: የዛሬ የአጋመዎች ለኤርትራ ፍቅር ከየት መጥቶ ነው ስለ ኤርትራ የሚሰብኩት? እነሱ ከጥንቱ መለያየት ፈልገው ነበር:: እና?
2. ስብሐት ነጋ “እኛ የኤርትራን መገንጠል ነበር የምንፈልገው” ብሏል::
እኛ ኤርትራ አብራን እንድትቀጥል አልፈለግንም ብሏል: ምክንያቱ ደሞ የኤርትራ ሕዝብ ጥያቄ ስለሚያስጨንቀን ነው ብሏል:: የትግራይ መገንጠል ሳያስጨንቀው ስለ ኤርትራ መጨነቁ በጣም ይገርማል::
3. የኤርትራ ጥያቄ በወረበላ(ኢሳያስ ) አይቀለበስም ብሏል:
???
ለማለት የፈለገው የኤርትራ መገንጠል ባንድ ዱርዬ የስልጣን ጥም አይዳፈንም ነው ::
4. ስብሐት “የደርግ ወታደር ኢትዮጵያዊ አልነበረም ይልቅ ወያኔ በጣም የኢትዮጵያ ፍቅር ያቃጥለው ነበር” ብሎ አንከተከተን
????
https://www.youtube.com/watch?v=kB5v0FFcPac